cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ደbre Sellaም Keጨnie Medhanialem Secondary School

KECHENIE School

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
1 223
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ማስታወቂያ ለ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያና ዩኒቨርሲቲ መግቢያና ፈተና ተፈታኞች በሙሉ:- ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 2014/15 የዩኒቨርሲቲ መግቢያና የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ወደ ተመደቡበት ካምፖስ ጉዞ ሲያደርጉ #መያዝ #የተፈቀደላቸው፣#መያዝ #የተከለከሉ እና #የጊዜ #ሠሌዳ እንደሚከተለው ያለው ሲሆን ተማሪዎች ከወዲሁ ራሣችሁን እንድታዘጋጁ ይሁን። ❶#መያዝ #የተፈቀደላቸው ✡️አንሶላ፣ ✡️ትራስ ጨርቅ፣ ✡️የማታ ልብስ፣ ✡️ደረቅ ምግብ፣ ✡️ልብስ፣ቦርሳ፣ ✡️የመፈተኛ ካርድ፣እርሳስ፣ላጲስ፣የማስታወሻ ደብተር፣ባዶ ወረቀት፤መጽሐፍ ❷፣#መያዝ #የተከለከሉ ☸️ማንኛውም ድምፅ የሚቀዳ፤ቪዲዮ የሚቀዳ ወይም ፎቶግራፍ የሚያነሳ፤ ☸️ካሜራ ☸️ማንኛውም ከቴሌ መስመርም ይሁን ከቴሌ ውጭ መልዕክት በድጂታል ቴክኖሎጂ መቀበያ ወይም ማስተላለፊያ ውጤቶች(ታብሌት፣ኮሚፕዩተር፣ላብቶፕ፣ ስልክ፣አይፓድ፥ሃርድ ዲስክ፣ፍላሽ) ❸ #የጊዜ #ሠሌዳ ✡️ማህበራዊ ሳይንስ $social science dep't ➤26_28/1/2015 ዩኒቨርስቲ መግቢያ ➤29/01/2015 ኦሬንተሽን ➤30/01/2015_02/02/2015 ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ ይሆናል። ✡️የተፈጥሮ ሳይንስ Natural Science dep't ➤05_06/2/2015 ዩኒቨርስቲ መግቢያ ➤07/02/2015 ኦሬንተሽን ➤08/02/2015_11/02/2015 ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ ይሆናል። አስፈታኝ ት/ቤቶች ተማሪዎች መረጃው እንዲደርሳቸው አድርጉ።
نمایش همه...
የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ድረስ በሁለት ዙር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። ለዚህም ተማሪዎች እራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪ አቅርቧል። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሽፋ ለኦቢኤን በሰጡት ቃል ፤ በአጠቃላይ በሁለት ዙር በሚሰጠው ፈተና ከ984,000 በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ገልፀዋል።ፈተናውን ከሚወስዱት ውስጥ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር 622,739 መሆኑን አመልክተዋል። የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ብዛት ያላቸው በመሆኑ በመጀመሪያው ዙር ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 3 /2015 አስቀድሞ ፈተናው እንደሚሰጣቸው አቶ ረዲ ተናግረዋል። የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር ደግሞ 361,279 ሲሆን በሁለተኛው ዙር ከጥቅምት 8 እስከ 11/2015 ፈተናውን እንደሚወስዱ አስረድተዋል። ከዚህ ቀደም የነበሩ የፈተና ችግሮችን ለመፍታት ፈተናው በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል ፤ ፈታኞቹ ደግሞ የዩኒቨርሲቲ መምህራን መሆናቸውን አሳውቀዋል። በተጨማሪም ፤ ፈተናው ከዚህ ቀደም ከነበረው ከ4 ኮድ ከፍ ማለቱን ገልፀዋል። ፈተናው ተዘጋጅቶ እየታተመ ሲሆን ፈተናው እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ ተፈታኞች እራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸውም አሳስበዋል። T.me/ethio_mereja @ethio_mereja
نمایش همه...
ውድ የመድሽ አስተማሪዎችና ተማሪዎች ፤ ይህንን የትምህርት ቤታችን ቻናል ሁሉንም የቴሌግራም ተጠቃሚ ተማሪዎቻችን እንዲያውቁትና እንዲቀላቀሉ ሼር ማድረጋችን እና ይህንን @medshschool ሊንክ ተጥቀመው እንዲገቡ መንገራችን አንዘንጋ።👍👍👍👍👍 በትምህርት ቤቱ የሚተላለፉልን መልእክትና ጠቃሚ መረጃ እንዲሁም የትምህርት አጋዥ የሆኑትን የተለያዩ መረጃዎችን የሚለቀቅበት መሆኑንም እናሳውቃለን።
نمایش همه...
ማሳሰቢያ፦ በክፍለ ከተማችን በመንግስት ት/ቤቶች በቋሚነት በመስራት ላይ ለምትገኙ መ/ራን፦ 1ኛ. ከጀማሪ እሥከ መምህርነት ደረጃ ብቻ በሚለው ማስታወቂያ ተቀጥራችሁ ከዚያ በላይ ያለው አገልግሎታችሁ ያልተያዘላችሁ መ/ራን መረጃችሁን በመያዝ፤ እና 2ኛ. በተለያዪ የትምህርት አይነቶች በግላችሁ በመንግሥት ኮሌጅ (ዩኒቨርሲቲ) ተምራችሁ ያልተያዘላችሁ መ/ራን የት/ት ማስረጃችሁን ዋና እና ኮፒውን በመያዝ፤ አስከ 21/7/14 ረቡዕ 6:30 ድረስ ብቻ ክ/ከተማ ት/ፅ/ቤት በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ እናሳስባለን።
نمایش همه...
የቴ/ሙ/ስ/ ተቋማት መግቢያ ነጥብ ይፋ ተደረገ። በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ በ2014 ዓ.ም የሰልጣኞች ቅበላ መቁረጫ ነጥብን ይፋ አድርጓል፡፡ በዚሁ መሰረት በመጀመሪያ ዙርና 2ኛ ዙር የ2013 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ማጠቃለያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ከላይ በምስሉ በተቀመጠው መስፈርት መሰረት የቴ/ሙ/ስ/ ተቋማት ተቀብለው እንደሚያሰለጥኑ ተገልጿል። በትምህርት ሚኒስቴር የመቁረጫ ነጥብ መሠረት ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ አምጥተው ነገር ግን በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ገብተው ለመሰልጠን ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች በደረጃ 5 ወይም 4 መሰልጠን እንደሚችሉ ተገልጿል። አካል ጉዳተኞች በሚያመቻቸው እና በመረጡት ሙያና የስልጠና ደረጃ ገብተው እንዲሰለጥኑ ተፈቅዷል። የመቁረጫ ነጥቡ ለ2014 ዓ.ም የስልጠና ቅበላ ብቻ የሚያገለግል ነው ተብሏል። Note: የቴ/ሙ/ስ/ ተቋማት ተጠሪነታቸው ከትምህርት ሚኒስቴር ወደ ሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ተዛውሯል። @tikvahuniversity
نمایش همه...
ቀን 08/07/2014 ዓ.ም ማስታወቂያ በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ ባስመዘገባችሁት ውጤት መሠረት በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ማግኘት የሚያስችላችሁ ታማሪዎች ከዚህ ቅደም የተቋም እና የመስክ ምርጫ ማካሄዳችሁ ይታወቃል። ስለሆነም ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ምደባ የሚያደርግ መሆኑን አውቃችሁ የሚከተሉትን ማስተካከያዎች እንድታደርጉ እንጠይቃለን:: 1ኛ. የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የተማሪዎች አማካይ ውጤት አፈፃፀም፣ ወዘተ ከግንዛቤ በማስገባት የዩኒቨርሲቲ ምርጫችሁን እስከ መጋቢት 13/2014 ዓ.ም ድረስ በ http://Portal.neaea.gov.et ገብታችሁ እንድታስተካክሉ እየገለጽን ከምደባ በኋላ የሚቀርብ ምንም አይነት የምደባ ለውጥ የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን። 2ኛ. በጤና እና ልዩ ልዩ ጉዳዮች ምደባ በልዩ ሁኔታ እንዲታይላችሁ የምታመለክቱ ተማሪዎች መረጃችሁን እስከ መጋቢት 11/2014 ዓ.ም ድረስ በ https://student.ethernet.edu.et/ በኩል እንድትልኩ እያሳሰብን በአካል የሚቀርብ ምንም ዓይነት ማስረጃ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን። ትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ! You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ... Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/ Website: - aaceb.gov.et
نمایش همه...