912
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
ለውድ ወላጆች
ከመስከረም 13/2019 ጀምሮ ተማሪ የምንሰጠው በመታወቂያ መሆኑን እያሳወቅን መታወቂያ ሲጠፋ ቀድመው ካላሳወቁ ት/ም ቤቱ ተጠያቂ እንደማይሆን በትህትና እናሳውቃለን::
ለዉድ ወላጆች
ከሰኞ መስከረም 11/2019 ጀምሮ ትምህርት ሙሉ ቀን እስከ 9:45 ሰዓት መሆኑን በትህትና እናስታውቃለን።
ቀን፦ 03/1/2019 ዓ.ም.
ለሚሞዛ ዩዝ እካዳሚ ወላጆችና ተማሪዎች በሙሉ፦
ጉዳዩ፦ ስለ2019 ዓ.ም. የትምህርት አጀማመርና ከተማሪዎች የሚጠበቁ ባህርያትና ሥነ ምግባራትን ስለማሳወቅ፤
ውድ የት/ቤታችን ወላጆችና ተማሪዎች በሙሉ በመጀመሪያ እንኳን ለ2019 ዓ.ም. የት/ዘመን በሠላምና በጤና አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን።
ውድ ወላጆች እንደሚታወቀው ሰኞ፥ መስከረም 04 ቀን 2019 ዓ.ም. አዲሱ የት/ዘመን ይጀመራል። በዕለቱ ተማሪዎች የክፍል ድልድላቸውንና መማሪያ ክፍላቸውን የሚያውቁበት ቀን ሲሆን የመጀመሪያ ሳምንት ግማሽ ቀን መሆኑን እናሳውቃለን::
በመሆኑም የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ከትምህርት ውጤታቸው ባሻገር የት/ቤታቸውን የሚሞዛ ዩዝ አካዳሚን ባሕልና ክብርን የሚያስጠብቁና በስነ ስርዓት የታነጹ እንዲሆኑ የሚከተሉት ስነ ባህሪያት እንዲኖራቸው ይጠበቃል።
1. አለባበስ እና ንፅህናን በተመለከተ፦ ተማሪዎች በሁሉም የትምህርት ቀናት የተሟላ እና ትክክለኛ የትምህርት ቤት የደንብ ልብስ መልበስ አለባቸው፤ ሌሎች ልብሶችን መደረብ ፈፅሞ አይቻልም፤ አጫጭር፣ ጠባብ የሆኑና ከጎን ክፍት የሆኑ ቀሚሶች አይፈቀዱም። የእጅ ንፅህናና ጥፍርን በአጭሩ መቆረጥና ቀለም አለመጠቀም፣ ትክክለኛ ጫማን ማድረግ (ነጠላ ጫማ፥ ክፍት ጫማና ከፍታ ያለው የፋሽን ጫማ አድርጎ መምጣት ፈፅሞ የተከለከለ ነው)፡፡
2. የፀጉር አሠራርና አያያዝን በተመለከተ፦ ሁሉም ወንድ ተማሪዎች ፀጉራቸውን በትክክል መቆረጥ (ከ1-2 ቁጥር ብቻ) እና በንፅህና መጠበቅ ይኖርባቸዋል። ያለአግባብ ያደገና ሥርዓት የሌለው አቆራረጥ ፈፅሞ የተከለከለ ነው። ሴት ተማሪዎች መደበኛ የፀጉር አሰራርን (እንደ ሹሩባ፣ ቁጥርጥር...) መሰል አሰራር ብቻ ይፈቀድላቸዋል፤ ነገር ግን ከማንኛውም ዓይነት ተገቢ ያልሆነ የፀጉር አሠራር ወይም ጌጣጌጦች አድርገው ወደ ት/ቤት እንዲገቡ አይፈቀድላቸውም።
3. ሰዓት አክባሪነትንና አጠቃቀምን በተመለከተ ተማሪዎች በሰዓቱ ማለትም ከጠዋቱ 1:00-2:00 ድረስ ወደ ት/ቤት በመድረስ ለቀኑ መዘጋጀት ይኖርባቸዋል። ከጠዋቱ 2፡00 በኃላ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪ አርፋጅ ተብሎ ይመዘገባል። ያለምንም በቂ ምክንያት ከትምህርት ገበታ መቅረት ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡ ከቀሩ ግን ህጋዊ የህክምና ማስረጃ የማቅረብ ግደታ አለባቸው።
4. የት/ቤት ቁሳቁሶችና አያያዝን በተመለከተ ሁሉም ተማሪዎች ለት/ቤት በተፈቀደ ቦርሳ ውስጥ የየዕለቱን ደብተሮች፣ መጸሐፍትና እና ቁሳቁሶች ምሳ እቃ በጥንቃቄ መያዝ አለባቸው። በመማሪያ ክፍል ውስጥ በተመደበለት/ላት ወንበር ላይ ብቻ መቀመጥ፤ የክፍል ውስጥ እቃዎችን (መማሪያ ቁሶች፣ ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች) ያለመምህራን ፈቃድ አለማንቀሳቀስና በአግባቡና በንጽህና መያዝ ይጠበቅባቸዋል።
5. ሌሎች ከተማሪዎች የሚጠበቁ ስነ ምግባራትን በተመለከተ፦
👉 መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች ሲናገሩ በጥንቃቄና በጥሞና የማዳመጥ፤
👉ጥያቄ ለመጠየቅ፣ ሃሣብ ለመስጠትና ከክፍል ለመውጣት እጅ አንስቶ ፍቃድ የመጠየቅ፤
👉በውይይትና በንግግር ጊዜ በትህትና የመናገር፣ በጨዋነት ወይም በአክብሮት የመወያየት፣
👉የቁርስና የምሳ ሰዓትን አክብሮ የመመገብ፣ እንደማስቲካ፣ ከረሜላ፣ ቸኮሌት ወይም ጣፋጭ መጠጦችን ወደ ት/ቤት ይዞ አለመምጣት፤
👉በት/ቤቱ ቤተ መጸሐፍት፣ ላቦራቶሪዎችና በመጀመሪያ ህክምና እርዳታ ለመገልገል የየክፍሉን መመሪያዎች የማክበር፣ በሃላፊነትና ለትምህርታዊ ዓላማዎች ብቻ የመጠቀም፣ ወዘተርፈ ኃላፊነቶችና ግደታዎችን መወጣት ይጠበቅባቸዋል።
በአጠቃላይ ሁሉም የትምህርት ቤታችን ተማሪዎች እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን መመሪያዎችና ደንቦች እንዲሁም የት/ቤቱን ህግና ደንቦችና እንዲሁም በትምህርት ቢሮ. የተጠቃለሉ መብቶችና ግደታዎችን ሊያከብሯቸው እና ሊተገብሯቸው የሚገቡ ገዥ መመሪያዎች ናቸው። እነዚህን ህግና ደንቦችን ወይም መመሪያዎችን ተላልፎ የተገኘ ማንኛውም ተማሪ በትምህርት ቤቱ ህግና ደንብና በትምህርት ቢሮ የተማሪዎች መመሪያ መሠረት የዲሲፕሊን እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ለማሳወቅና ለማሳሰብ እንወዳለን።
የትምህርት ቤቱ አሰተዳደር
እንኳን ለ2019 የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ
🌼🌻🌼🌻🌼
ዉድ ወላጆች
ትምህርት የሚጀምረው ሰኞ መስከረም 4 ቀን 2019 መሆኑን እያሳወቅን የመጀመሪያው ሳምንት ግማሽ ቀን እስከ 6 ሰአት መሆኑን ከወዲሁ እናስታውቃለን።
🌼🌻🌼🌻🌼🌻
ለዉድ ወላጆች
የተማሪዎችን ምዝገባ በግዜ ላጠናቀቃችሁ ምስጋናችንን እያቀረብን ያላስመዘገባችሁ ወላጆች ከሀምሌ 15 በፊት ምዝገባችሁን እንድታጠናቅቁ እናስታዉቃለን።
ማሳሰቢያ:- ከሀምሌ 16 በኃላ ቦታ ቢሞላ ትምህርት ቤቱ ሀላፊነት የማይወስድ መሆኑን ከወዲሁ እናሳዉቃለን
ውድ ወላጆችና አሳዳጊዎች
እንኳን ደስ አላችሁ!
በ2018 የት/ዘመን የተፈተኑ የ6ኛ ክፍል
ተማሪዎቻችን 100% አልፈዋል
ውድ ወላጆችና አሳዳጊዎች
እንኳን ደስ አላችሁ!
በ2018 የት/ዘመን የተፈተኑ የ8ኛ ክፍል
ተማሪዎቻችን 100% አልፈዋል
ለውድ ወላጅ/አሳዳጊ
የ2018 ተመራቂ ተማሪዎች ጋዋን የሚሰጠው ከማክሰኞ ሰኔ 23 ቀን 2018 እስከ ሐሙስ ሰኔ 25 ቀን 2018 ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ መሆኑን እያሳወቅን ከላይ ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ውጭ ምንም አይነት ጋዋን የማይሰጥ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
ዉድና የተከበራችሁ
የ6ተኛ ክፍል አስፈታኝ
ወላጆች
ሰኞ ሰኔ 8 ቀን 2018 የ6ተኛ ክፍል ልጆቻችን ፈተና የሚጀምሩበት ቀን ስለሆነ ጠዋት 1 ሰዓት በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ እንዲገኙ እንዲሁም ለፈተና የሚያስፈልጉ መሳሪያዎችን አሟልተው በሰአቱ እንዲገኙ እናሳስባለን።
ዉድ ወላጆች
ከሰኞ ግንቦት 24 እስከ ረቡእ ግንቦት 26 ትምህርት ቤት ዝግ መሆኑን በትህትና እናሳዉቃለን።
