fa
Feedback
HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

رفتن به کانال در Telegram

❤️ ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ይላሉ **ጸጋ ያለምስጋና አያድግም ይላሉ** እግዚአብሔር ሆይ ስለሆነልኝ፣ ክፉውንም ከእኔና ከቤተሰቦቼ ስላራክልኝ 👏 አመሰግንሃለሁ ❤️ 👇👇👇 http://www.youtube.com/@haileG2239

نمایش بیشتر
2 280
مشترکین
-124 ساعت
+107 روز
+3530 روز
آرشیو پست ها
🚩እንደ ጠላት ሐሳብ ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ሐሳብ፣ እንደ ጠላት ክፋት ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ቸርነት አገልግሎቱ በተቀደሰ ቦታ ተሰጥቷል! አገልግሎቱ ይቀጥላል! እግዚአብሔር ስሙ በእውነት የ
+9
🚩እንደ ጠላት ሐሳብ ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ሐሳብ፣ እንደ ጠላት ክፋት ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ቸርነት አገልግሎቱ በተቀደሰ ቦታ ተሰጥቷል! አገልግሎቱ ይቀጥላል! እግዚአብሔር ስሙ በእውነት የተመሰገነ ይሁን። ለአባታችን እግዚአብሔር ረጅም ዕድሜን ያድልልን። ለሚቃወሙ ለምተቹ ለምሳደቡ እግዚአብሔር አምላክ አሁንም ልቦና ይስጣቸው። በጣም የሚሳዝን ጊዜና ዘመን ላይ እንገኛለን። 🔥🔥🔥 #Subscribe #Like #Share    👇👇👇👇 www.youtube.com/@haileG2239 www.youtube.com/@pagumentube

ጉድ! ማህፀን በመተት የሚሰልቡና የሚያሰልቡ በፀጋ የመጸለይ ጥበብ እንጸልያለን ግን ሁለም ውድቀት || በሴት ጓደኛዎ የተጎዳች #ethiopia 😭🔥🚩🔥 https://youtu.be/QlNOEfN3YhE

በመፈወሳችን በመዳናችን ለምን ተናደዱ? ፍቅረ ዓለም የዲያብሎስ ማሰሪያ ነው አጋንንት በአጋንንት አይወጣም || የዲያብሎስን ሥራ ተቃወሙ #eotc 😭💥 https://youtu.be/joWbsuFZKA0

◈ አንድ ቀለም ቀቢ ባለሙያ አስቀድሞ የሚቀባውን ግድግዳ በደንብ አድርጎ ሊጠርገውና ሊወለውለው፣ መፍረስና መፈነቃቀል ያለበት ጭቃ ካለም ሊያፈርሰውና ሊፈነቃቅለው ይገባል፡፡ ምክንያቱም እንዲያ ካላደረገ አዲስ የሚቀባው ቀለም ብዙም ሳይቆይ ግድግዳው ላይ በቆየው አሮጌ ቀለም ምክንያት ይወድቅበታልና፡፡ ◈ ልክ እንደዚሁ አንድ ክርስቲያንም በእርሱነቱ ላይ ያለውን አሮጌ ቀለም (ማንነት) ሳይወለውልና ፍቆ ሳይጥል ዘላቂነት ያለውን ቀለም መቀባት (አዲስ ሕይወትን መጀመር) ያቅተዋል፡፡ አሮጌ ማንነቱ አዲስ ሰውነቱን ያበላሽበታል፡፡ እንኳንስ በሁለንተናው ያለውን ይቅርና በአንዲት የሰውነት ሕዋሱ ላይ አንዲት ያረጀች ማንነት ካስቀረም በዚያች ምክንያት አካለ ጎደሎ ይሆናል፡፡ ያውም በነፍሱ፡፡ እንግዲያውስ እኛም በጦም በሁለንተናችን እንጠቀምና እንለወጥ ዘንድ አስቀድመን በየትኛውም ሕዋሳቶቻችን ላይ ያሉትን አሮጌ ቀለሞች በንስሐ ሞዶሻ ፈረካክሰን ልንጥላቸው ይገባናል፡፡ ◈ አስተውሉ! ምንም ዓይነት አሮጌ ቀለም በየትኛውም የሰውነት ክፍላችን ላይ ልናስቀር አይገባም፤ በዓይን የሚቀር ያረጀ ቀለም(ምኞት)፤ በእጅ የሚቀር ያረጀ ቀለም (ስርቆት)፤ በእግር የሚቀር ያረጀ ቀለም (ወደ ኃጢአት መንደር የሚሄድ ማንነት)፤ ሁለንተናችን ተቀብቶ ማለትም ታድሶ እንዳይታይ ዕንቅፋት ይሆኗል፡፡ ተቀብተን አሮጌ እንድንሆን ያደርገናል፡፡ ይኸውም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዲስ ቁራጭ ባረጀ ልብስ የሚጥፍ የለም እንዳለው ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የማቴዎስ ወንጌልን ሲተረጉም በ30ኛው ድርሳኑ የተናገረው #Subscribe #Like #Share    👇👇👇👇 www.youtube.com/@haileG2239 www.youtube.com/@pagumentube

እንኳን አደረሳችሁ (16) "ሰላም ለኪ እመቤቴ ኪዳነ ምህረት ሆይ እንደ ቃል ኪዳንሽ ምስጋናሽ የሚነገርበት ቤተ ክርስቲያን በስምሽ ያሳነጸዉን መታሰቢያሽን ያደረገዉን በስምሽ የፀለየዉን ከበረከትሽ ታ
እንኳን አደረሳችሁ (16) "ሰላም ለኪ እመቤቴ ኪዳነ ምህረት ሆይ እንደ ቃል ኪዳንሽ ምስጋናሽ የሚነገርበት ቤተ ክርስቲያን በስምሽ ያሳነጸዉን መታሰቢያሽን ያደረገዉን በስምሽ የፀለየዉን ከበረከትሽ ታሳትፊዉ ይቅር ባይ ከሚሆን ልጅሽ ይቅርታን ታሰጭኝ ዘንድ ሰላም እያልኩ ከፊትሽ ወድቄ በቃል ኪዳንሽ እማፀንሻለሁ።" መልክዐ ኪዳነ ምህረት #Subscribe #Like #Share 👇👇👇👇 www.youtube.com/@haileG2239 www.youtube.com/@pagumentube

በሰላቢ መተት ሀብት ንብረቷ የወደመባት እህት የእምነት ኃይል ጎደለን አጋንንት ሁለም በድብቅ ያጠቁናል || መናፍስትና የእምነት ኃይላችን #ንቁ 🚩🔥💥 https://youtu.be/e0x6VUkSvPY?si=PC9hwqo7kzs69u0C

ስለመንፈስ ከመንቃታችን በፊት ምን አጋጠመን ክፍል 1 ......? https://youtu.be/EFYmMAPjBfs

«ልጄ ሆይ አመስግን!» ◈ ••• በአለም ላይ በሚሊዬን የሚቆጠሩ ሰዎች የዕለት ጉርሳቸውን አጥተው ተርበው ያቃስታሉ፤ አንተን ግን እግዚአብሔር በቸርነቱ አጥግቦ እያኖረህ ነው እና አምላክህን አመስግነው። ብዙዎች በእዚህች ሰዓት እንደ መፃጉ በደዌ ተመተው በአልጋቸው ላይ ሆነው ምህረትን ከእግዚአብሔር ይለማመናሉ፤ አንተ ግን እንደ በደልህ ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ፍቅር በጤንነት ትመላለሳለህ እና አምላክህን አመስግን። ◈ ብዙዎች ይህችን ጀንበር ላያዩ አንቀላፍተዋል፤ አንተ ግን በምህረት ጥላ ውስጥ ሆነክ ይኼው አዲስ የቸርነት ቀናትን እየኖርካቸው ነው እና አምላክህን አመስግን። በደዌ አልጋ ላይ ተኝተህ ብትኖርም አመስግን፤ አልጋህን ተሸከምህ ተረማመድ የሚል አምላክ በቀኑ ወደ አንተ ይመጣልና አለኝ የምትለውን አጥተህ፤ የምትመካባቸውን ተነፍገህ እግዚአብሔር እንደበደለህ በሚነግሩ ክፉዎች መሐል ሆነህ ሀዘን ቢሰማህም "እርሱ ሰጡ እርሱ ነሳ" ብለህ እንደ ትዕግስተኛው ኢዬብ ትዕግስትን ተላብሰህ አመስግን። ◈ እንደ ይሁዳ መጠራትህ ለክህደት ሳይሆን ለመፅናት ከሆኑ ሐዋርያቱ ጉባኤ ትሆን ዘንድ ከቤተክርስቲያን እናትነት ተወልድህ ቆመሐል እና እግዚአብሔርን አመስግን። እንደ ዳዊት ማንም ቢታዘብህ አንተ ግን የምትማልከውን አምላክ አስበህ ስለተደረገልህ ነገር ሁሉ እንደ እንቦቅቅላ በኃይል አመስግን። ልጄ ሆይ እርሱ ምስጋና የባህሪው ነው፤ ቅዱሳን መላእክት በሰማይ፤ ቅዱሳን ልጆችሁ በምድር ለስሙ ምስጋና አዘጋጅተው ዘውትር ያመሰግኑታል፤ አንተም በምስጋና ከእነርሱ ጋር ተባበር። #Subscribe #Like #Share    👇👇👇👇 www.youtube.com/@haileG2239 www.youtube.com/@pagumentube

◈ ስብከት ወይም መንፈሳዊ ንባብ የእግዚአብሔርን ድምፅ የሚተላለፊበት መንገድ ሊሆን ይችላል፤ አንድ የወንጌል ጥቅስ ስታነብ ወይም ሲነበብ ስትሰማ እግዚአብሔር ለአንተ እና ለአንተ ብቻ በግልህ እንደተ
◈ ስብከት ወይም መንፈሳዊ ንባብ የእግዚአብሔርን ድምፅ የሚተላለፊበት መንገድ ሊሆን ይችላል፤ አንድ የወንጌል ጥቅስ ስታነብ ወይም ሲነበብ ስትሰማ እግዚአብሔር ለአንተ እና ለአንተ ብቻ በግልህ እንደተናገረው ሆኖ ይሰማሃል፤ ይህ ጥቅስ ለአንተ የሆነ ትርጉምና ጥቅም እንዳለው ሆኖ ይሰማሃል፤ ይሁን እንጂ ይኼኛው ጥቅስ በተለየ ሁኔታ በአሳብህ በልብህ በስሜቶችህና በእምነትህ ውስጥ ተጽዕኖ ያሳድርብሃል በውስጡ የእግዚአብሔርን ድምፅ ትሰማለህ፤ ስብከት ስትሰማም ተመሳሳይ ሁኔታ ሊከሰት ይችላል፤ የምትሰማው ስብከት ለአንተ የተነገረ ሆኖ ይሰማሃል፤ በዚህ ጊዜ "ዛሬ ድምጹን ብትሰሙት በማስመረር እንደ ሆነ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ" የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አስታውሱ ቃሉ ምንም ዓይነት አሻራ ሳይጥል እንዲያልፍህ አትተውት። (ዕብ 3፥15) አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ #Subscribe #Like #Share    👇👇👇👇 www.youtube.com/@haileG2239 www.youtube.com/@pagumentube

እውነተኛ ጸሎትና አደራረጉ || እውቀት ፍጻሜ የለውም! || ትህትናን እንዴት እንለማመድ? || ጸሎትና የአጋንንት ውጊያ || ጸሎት ማድረግ አልቻልኩም 🚩💥🔥 https://youtu.be/4ZtAiniNkXo

መምህር ተስፋዬ ከሰንበት ተማሪዎች ጋር ተፋጠጡ || ልጆቼ እንዳይሞቱ ብዬ ነው! || የጬሌና የባዕድ አምልኮ በቤታችን || 3ቱ እርሾዎችን እናስወግድ! 🚩🔥💥🙏 https://youtu.be/7jMRf9M3Nuw

ዶክተር እንዴት በመንፈስ ይያዛል? || በትልቅነት ውስጥ ያለ አዙሪት || የዮሐንስ ወንጌልን እንደ ታቦት || ያደፈጡ መንፈሶች ጉዳት || ታቦት ቢሰረቅ 🚩💥🔥 https://www.youtube.com/watch?v=QiDtjgjqZgw

«በኩረ መዘምራን ኪነ ጥበብ ወ/ቂርቆስ አባታችን» ለቅድስት ቤተክርስቲያን ብዙ አበርክቶዎችን ያደረጉ፤ በመዝሙራቸው ብዙዎችን ያጽናኑ፣ የብዙዎችንም ልቡና ወደ ንስሐ የመሩ፤ ከ50 ዓመታት በላይ ቤተ
«በኩረ መዘምራን ኪነ ጥበብ ወ/ቂርቆስ አባታችን» ለቅድስት ቤተክርስቲያን ብዙ አበርክቶዎችን ያደረጉ፤ በመዝሙራቸው ብዙዎችን ያጽናኑ፣ የብዙዎችንም ልቡና ወደ ንስሐ የመሩ፤ ከ50 ዓመታት በላይ ቤተ ክርስቲያንን ያገለገሉ። በዝማሬያቸው መሐል የሚመክሩ፣ የሚያጽናኑ አባታችን ቀድሞ ያማቸው በነበረው የጀርባ ሕማም ታመዋልና ለሕክምና ይኾናቸው ዘንድ እባክዎትን የበኩልዎትን ያድርርጉ ዘንድ ግዴታ እንዳለብዎት በመረዳት ከታች በተቀመጠው የእርሳቸው አካውንት ያስገቡ። በእርግጥ እርሳቸውን ተለምነን አልነበረም ማሳከም የነበረብን፡ የሚያስፈልጋቸውን ነገር ኹሉ አሟልተን ልንንከባከባቸው ይገባ ነበር። ግን ያው ብዙዎቻችን እውነተኛ አገልጋዮችን በአግባቡ ባለመከታተላችን በብዙ ችግር ውስጥ ኾነው ያገለግላሉ። አርአያ የሚኾኑንን ባናሳዝናቸውና በረከት ብናገኝባቸው መልካም ነው። እንግዲህ የባንክ አካውንታቸው ይኸው እንረባረብ! CBE 1000481007287 KINETIBEB W/KIRKOS W/MESKEL CMC Michael Branch

በመተት ልጅ የመውለድ ዕድላቸው የተወሰዱ ሰዎች || ምልክቶቹ ምንድናቸው? || መ'ቀደስ ለምን አቃተን? ኦርቶዶክሳዊ መዳን እንዴት ነው? #ethiopia 🚩🙏🔥 https://youtu.be/ifY4kYE4Q1A

🚩አብዛኛው ሕብረተሰብ የእግዚአብሔርን የማዳን ነገር ዋጋ ሳይሰጡና በበጎነት ሳይመለከቱ፤ የራሳቸውን ምክንያት በመደርደር፤ ሰው ላይ የሚታየውን ችግር ፋይዳ ቢስ አድርገው፤ ባዶነታቸውን ሳይመለከቱ እንደ ነፍሳቸው ምኞት ይናገራሉ፡፡ “እንዲሁም ክፋትን ይጎነጉናሉ” ብዙው ሰው ረጅሙን ዕድሜ ያሳለፈው በምስጋና፣ በፀሎትና በአምልኮት ሳይሆን፤ በጥላቻ፣ በመለያየት፣ በመሰሪነትና አንዱን አንዱ ጥሎ በማለፍ ስለሆነ፤ በቤተ እግዚአብሔር ውስጥ ሆኖ ኃጢአያትን በመለማመድ፤ ደፋር፣ ኩሩ፣ ቀማኛና ነጣቂ በመሆን፤ ክፋትና ጥፋትን ለማቆየት እየሠራ ይገኛል፡፡ 🚩እኛም ታዲያ የምናስበው፣ የምናቅደውና አመለካከታችን ከክፋት ጋር የተያያዘ በመሆኑ፤ የብዙውን ትውልድ ዕድል አጥፍተን፤ ብዙ ከሃዲዎችን ማፍራታችን አንዱ የግፍ ሥራችን ምልክት ነው፡፡ በጎና ቅን ሆነን በመንፈስ ቅዱስ ተዋጅተን ወደ ሰው የምንሄድበት ሕሊና ስላጣን፤ ነገር እየጎነጎንን መሰሪ እቅድ ኑሯችን ውሰጥ ተክለን፤ ከጀርባችን ብዙ ክፋቶችን አዝለን እንኖራለን፡፡ 🚩ከእነሱ ሁሉ የተሻለው እንደ አሜኬላ ነው ያለው የነብዩ ቃል፤ አሜኬላ ተደብቆ የሚወጋ ከታች ስትረግጠው ከላይ የሚቧጥጥ፣ ጫማ አልፎ የሚያቆስል፣ የሚያደማ፣ የማያስሮጥ፣ ቁስል የሚሆን፣ እግርን የሚቆጠቁጥ፣ የሚያም፣ የሚያስጨንቅ፣ አረማመድን የሚገታ፣ የወደፊት ተስፋን የሚያመክን እና ቁልቁል የሚያሽከረክር ነው፡፡ ዛሬም የተሻለ የተባለው ሰው ሁሉ ልክ እንደ እሾህ የሚዋጋ ሆኖ በሥልጣን፣ በማዕረግ፣ በከፍታ ለሌላው ሰው እንደ አሜኬላ ሆኗል፡፡ ስለዚህ ከሁሉ ቅን የሆነውም፤ እንደ ኩርንችት ነው፡፡ ኩርንችት ደግሞ እንደ ደበኛ አድፋጭ፣ ተንኮለኛ፣ ምቀኛና ነገረኛ ምሳሌ በመሆን፤ በተፈጥሮ ሂደትም በምትረግጥበት ስፍራ ላይ እግርህንና ኮቴህን ተደብቆ የሚወጋ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህን ኩርንችትና አሜኬላ በሁሉም አቅጣጫ በኑሮችን ውስጥ የተለመደ አድርገን፤ በክፋትና በግፍ አሠራር የሌሎችን ሕይወት በግልጽና በስውር ስንጎዳ ይታያል፡፡ 🚩እኛም የኃያሉ አምላካችን የእግዚአብሔር ጥበቃና ምሕረት አብሮን እስካለ ድረስ፤ እንደተያዝን አንቀርም፡፡ ከታሰርንበት እንፈታለን፤ ከወደቅንበትም እንነሣለን! #Subscribe #Like #Share    👇👇👇👇 www.youtube.com/@haileG2239 www.youtube.com/@pagumentube

አጋንንት የተጠመቁ ሰዎችን አብዝቶ ይፈትናል የእኔን ጨርሻለሁ አንተ ተናገር መልስ ያጣው ኑሯችን || የባከነ ኑሮና ትውልድ #ethiopia 🚩💥🔥🙏 https://youtu.be/dgq6KmE7dSU

የአምልኮት ስግደትና የአጋንንት ውጊያ ጸሎትን እንዴት እንለማመድ? ከስንፍና ባርነት ነጻ እንውጣ || በማለዳ ለዛር ለውቃቢ ሰገድን #ethiopia 🚩 https://youtu.be/3m4EoxOKn1w?si=tP9A5L4Juh8zcEM5

ለምን ትድናላችሁ፣ ለምን ትፈወሳላችሁ ይሉናል በአየር ላይ የምንሳፈፉ ደብተራዎች ቅጠልና መስቀል የምይዙ ደብተራዎች || ጸሎት ማቆም #ethiopia 🙏💥🚩 https://youtu.be/SoEeV1KotTk

አጋንንት ውስጣችን በአራት መንገድ ይገባሉ ታቦት እንዴት ይሰረቃል? ምንዝር ጌጥና አጋንንታዊ አሠራሩ || ሃይማኖተኛ መሆንና አማኝ መሆን ልዩነቱ 🚩🔥 https://youtu.be/v1iFadaE_m0