HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ
رفتن به کانال در Telegram
❤️ ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ይላሉ **ጸጋ ያለምስጋና አያድግም ይላሉ** እግዚአብሔር ሆይ ስለሆነልኝ፣ ክፉውንም ከእኔና ከቤተሰቦቼ ስላራክልኝ 👏 አመሰግንሃለሁ ❤️ 👇👇👇 http://www.youtube.com/@haileG2239
نمایش بیشتر2 265
مشترکین
+124 ساعت
+57 روز
+2230 روز
آرشیو پست ها
የመቁጠሪያ ጥቅም እስካሁን ካልገባችሁ ይኼንን ትምህርት ከልባችሁ አዳምጡና ፍረዱ!! ባሕታዊ ገብረመስቀል እፎይን መቃወም ለምን ፈለጉ!? https://youtu.be/HCGpAgQropw
ይህንን እውነት ከተረዳችሁ፡ ከዛሬ ጀምሮ የጸሎት ሕይወታችሁ ይቀየራል!! ተንበርክኮ መጸለይ ከመናፍስት ውጊያ አንጻር ያለው ጥቅም!! https://youtu.be/yB8ppibYdwU?si=NL30Qep2bMxnX5DC
የውይይት አሳብ፡ "ዲጂታል ዝንጋኤ"
=> አስተውሉ! በስልካችን ላይ ለሰዓታት መቆየት፣ ፌስቡክና ቲክቶክ ላይ መዘዋወር አይሰለቸንም። ነገር ግን ለ፲፭ ደቂቃ ጸሎት ስንቆም አእምሯችን ይበተናል፣ ይጨንቀናል፣ ይደክመናልም። ሰይጣን ስልካችንን እንደ ጦር መሣሪያ እየተጠቀመበት ይሆን? ስልካችን የጸሎት ሕይወታችንን እንዴት ሰረቀው? በቴክኖሎጂ መካከል ሆነን እንዴት አእምሯችንን ሰብስበን ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘት እንችላለን? ለጸሎት የምንሰጠው ጊዜና ለስልክ የምንሰጠው ጊዜ ያለውን ልዩነት እንዴት እናጥብበው? ይኼስ ብዙ እየጎዳን አይመስላችሁም?
የውይይት አሳብ፡ "ሥርዓታዊነት ወይስ መንፈሳዊነት?"
=> ብዙዎቻችን ማዕተብ እናስራለን፣ አርብና ረቡዕን እንጾማለን፣ ቤተክርስቲያን እንሄዳለን። ነገር ግን ከቤተክርስቲያን ደጅ ስንወጣ ንግግራችን፣ ጠባያችንና ከሰዎች ጋር ያለን ግንኙነት ከማያምነው ሰው አይለይም። "ቅዳሴ አስቀድሶ ወጥቶ መጣላት ወይም መሳደብ" ምንን ያሳያል? እምነታችን ለምን ጠባያችንን ሊለውጠው አልቻለም? በሥርዓት (Formalism) ላይ ብቻ ተጠምደን የልብ ለውጥን ዘንግተን ይሆን? ለዚህ መፍትሔው ምንድነው ትላላችሁ? ሁላችሁም የተሰማችሁንና የገባችሁን ጻፉ ሌሎቻችሁም በዛው አሳብ ስጡበት።
የመምህር ተስፋዬን ገጠመኝ ሰምታችሁ ተግባራዊ የማታደርጉ አሁኑኑ ይኼንን አዳምጡ!! ዘንዶ የሚገበርበት ሆቴል በአዲስ አበበና ድብቅ ምስጥሮቹ!! #ጸበል #ጸሎት https://youtu.be/FEJJ6mHwOFY
ጥያቄ 6፡ በመንፈሳዊ ውጊያ ውስጥ "ከንቱ ውዳሴ" ከሌሎች ሥጋዊ ኃጢአቶች ይልቅ አደገኛ የሚሆነው ለምንድነው?
ሀ) ሰዎች ስለሚያውቁብን
ለ) መልካም ሥራዎችን ሁሉ ሰርቆ ዋጋ ቢስ ስለሚያደርጋቸው
ሐ) ድካም ስለሌለው
መ) ምግብ ስለማያስፈልገው
ጥያቄ 5፡ ሰይጣን ለምን ንስሐ መግባት (ይቅርታ ማግኘት) እንደማይችል ቅዱሳን አባቶች የሚሰጡት ምክንያት ምንድነው?
ሀ) እግዚአብሔር ስለማይወደው
ለ) ሰይጣን ያለ ማንም አታላይ በራሱ ትዕቢት ስለወደቀና ባሕርዩ ወደ ክፋት ስለረጋ
ሐ) የንስሐ ጊዜው ስላለፈ
መ) መልሱ አልተጠቀሰም
ጥያቄ 4፡ "ምስጢረ ሥጋዌ" (Incarnation) ላይ መለኮትና ትስብእት በተዋሐዱ ጊዜ የመለኮት ባሕርይ በትስብእት ባሕርይ ተዋጠ (ተበላ) የሚለው የተሳሳተ ትምህርት የማን ነው?
ሀ) የንስጥሮስ
ለ) የአቡሊናርዮስ
ሐ) የአውጣኪ (Eutyches)
መ) የሉተር
ጥያቄ 3፡ በነገረ መለኮት ትምህርት "ኃጢአተ አዳም" (Original Sin) ለልጅ ልጆቹ የሚተላለፈው እንዴት ነው?
ሀ) የአዳም የኃጢአት በደል/ጥፋተኝነት (Guilt) በቀጥታ ለልጆቹ ይተላለፋል
ለ) የአዳም የኃጢአት ውጤት የሆነው "ሞትና የባሕርይ መታደፍ" (Mortality) ይተላለፋል
ሐ) ኃጢአት የሚተላለፈው በደም ብቻ ነው
መ) ኃጢአት በፍጹም አይተላለፍም
ጥያቄ 2፡ በጸሎት ጊዜ ወደ ምሥራቅ ዞረን የምንጸልየው ለምንድነው?
ሀ) ፀሐይ ከምሥራቅ ስለምትወጣ
ለ) የጌታችን ዳግም ምጽዓት (መምጣት) ከምሥራቅ ስለሚሆንና ገነትም በምሥራቅ ስለነበረች
ሐ) ምሥራቅ የብርሃን ምልክት ስለሆነ ብቻ
መ) መልሱ ሀ እና ሐ ናቸው
ጥያቄ 1፡ እውነተኛ ንስሐ ተሟልቷል የሚባለው በየትኞቹ ሦስት ደረጃዎች ሲያልፍ ነው?
ሀ) ማዘን፣ ጸሎት ማድረግና ለድሆች መስጠት
ለ) ኃጢአትን ማመን (ማዘን)፣ ለካህን መናዘዝና ቀኖናን መፈጸም
ሐ) ቤተክርስቲያን መሄድ፣ ማስቀደስና መቁረብ
መ) ኃጢአትን መተው ብቻ
=> ሰላም ውድ ቤተሰቦቼ እንዴት ናችሁ ሁሉ መልካም ነው። በያላችሁበት ሰላሜ እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን። ዩቱብ ላይቭ ስንት ሰዓት ብገባላችሁ መልካም ነው ትላላችሁ? ህልምና ፍችዎቻቸው በሚለው ርዕስ ክፍል 6 እንቀጥላለን። ሰዓቱን ግን ሁላችሁን ግለጹልኝ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ነው ታዲያ የምትጽፉልኝ። መልካም ቀን። በዛውም የዩቱብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያላረጋችሁ አሁኑኑ በማድረግ ቤተሰብ ሁኑ። https://youtube.com/@haileG2239
ውድ ቤተሰቦቼ ጥያቄዎቹን እንዴት አያችሁ? በዚህ እንቀጥል ዘወትር ከሰዓት በኋላ የጥያቄና መልስ ጊዜ እንዲሁ ደግሞ መወያያ አሳቦችን ላቅርብላችሁ? ምን ትላላችሁ?
ጥያቄ 10፡ እንደ ክርስቲያን የመጨረሻው ድል የሚገኘው በምንድነው?
ሀ) በራስ ብልህነትና ጥንካሬ
ለ) ብዙ አጋንንትን በማስወጣት
ሐ) በእግዚአብሔር ጸጋና እስከ መጨረሻው በመጽናት
መ) በጾም ብዛት ብቻ
ጥያቄ 9፡ "ንቁ መሆን" ማለት ምን ማለት ነው?
ሀ) ሳይተኙ ማደር
ለ) ወደ ልብ የሚገቡ ሃሳቦችን ዘወትር መከታተልና መመርመር
ሐ) ብዙ መጽሐፍ ማንበብ
መ) ጫጫታ ባለበት ቦታ አለመገኘት
ጥያቄ 8፡ ሰይጣን በሰው ልብ ውስጥ "ቂምና በቀልን" የሚዘራው ለምንድነው?
ሀ) ሰውየው ጠንካራ እንዲሆን
ለ) የሰውየው ጸሎት በእግዚአብሔር ዘንድ እንዳይሰማ
ሐ) ሰዎች እንዲፈሩት ለማድረግ
መ) መልሱ አልተጠቀሰም
ጥያቄ 7፡ "ራስን መውቀስ" በመንፈሳዊ ተጋድሎ ውስጥ ያለው ጥቅም ምንድነው?
ሀ) ራስን ለሥነ-ልቦና ቀውስ መዳረግ
ለ) ሰይጣን በእኛ ላይ የሚከፍተውን የትዕቢት በር መዝጋት
ሐ) በሰዎች ፊት ትሑት ለመምሰል
መ) ተስፋ ለመቁረጥ
ጥያቄ 6፡ በጸሎት ጊዜ አእምሯችን ወደ ሌላ ቦታ ሲበተን ልናደርገው የሚገባው ትክክለኛ ውጊያ ምንድነው?
ሀ) ጸሎቱን አቁሞ ሌላ ጊዜ መጸለይ
ለ) በተበተነበት ቦታ ሁሉ ሃሳባችንን እየሰበሰብን ወደ ጸሎቱ መመለስ
ሐ) ሃሳቤ ለምን ተበተነ ብሎ ራስን መስጨነቅ
መ) በዝግታ መጸለይ
ጥያቄ 5፡ በመናፍስት ውጊያ ውስጥ "ጾም" ያለው ትልቁ ሚና ምንድነው?
ሀ) ሰይጣን ስለማይበላ እሱን ለመምሰል
ለ) ሥጋን ለነፍስ በማስገዛት መንፈሳዊ ኃይልን ለማግኘት
ሐ) ምግብ ለመቆጠብ
መ) ከሰዎች ለመለየት
اکنون در دسترس! پژوهش تلگرام ۲۰۲۵ — مهمترین بینشهای سال 
