fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

رفتن به کانال در Telegram

❤️ ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ይላሉ **ጸጋ ያለምስጋና አያድግም ይላሉ** እግዚአብሔር ሆይ ስለሆነልኝ፣ ክፉውንም ከእኔና ከቤተሰቦቼ ስላራክልኝ 👏 አመሰግንሃለሁ ❤️ 👇👇👇 http://www.youtube.com/@haileG2239

نمایش بیشتر
2 296
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-1130 روز
آرشیو پست ها
ሰላም እንዴት ናችሁ ውዶች! የመቁረቢያ ልብስ ለጠየቃችሁኝ ቤተሰቦቼ በዚህ መልክ የተዘጋጄ ስላለ እንድላክላችሁ የምትፈልጉ ቤተሰቦቼ በውስጥ መስምር አናግሩኝ!
+2
ሰላም እንዴት ናችሁ ውዶች! የመቁረቢያ ልብስ ለጠየቃችሁኝ ቤተሰቦቼ በዚህ መልክ የተዘጋጄ ስላለ እንድላክላችሁ የምትፈልጉ ቤተሰቦቼ በውስጥ መስምር አናግሩኝ!

ሰይጣን በጭራሽ መስማት የማይፈልገው አጅግ አደገኛው ቃል!! ጸሎት ላለማድረግ የሚቀርቡ እጅግ አሳዛኝ ምክንያቶች!! መቁጠሪያና የክፉ መናፍስት ውጊያ!! https://youtu.be/Uas5XUE0ejg

አንድ ምሥጢር ሹክ ልበላችሁ? ብዙ ጊዜ "ለምን 'ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ' ትላላችሁ?" የሚሉ ሰዎች ትሰሙ ይኾናል። እኔ በበኩሌ፡ "ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ" የምልበትን፡ አንዱን ትልቁን ምክንያቴን ልንገራችሁ፦ => የኢትዮጵያን መንፈሳዊ ታሪክ የሚያስተውልና መንፈሳዊ ጥበቧን የሚመረምር ሰው፡ በተለይ በድንግል ማርያም በኩል ያለውን፡ በመንፈሳዊ ሕይወቱ ለማደግ በጣም ቀላል ስለሚኾንለት ነው። ስለ እስራኤልም ብትመረምሩ፡ የኾነ ቦታ ደርሳችሁ ትቆማላችሁ፤ ስለግብፅም ብትመረምሩ፡ የኾነ ቦታ ያጎድሉባችኋል፤ ስለሶርያም ብትመረምሩ፡ የኾነ ቦታ ደርሳ ከኾነ ነገር ጋር ትደባለቅባችኋለች። ስለሮምም፣ ስለግሪክም፣ ስለፋርስም፣ ስለእንግሊዝም ብታስቡ፡ ኹሉም ጎዶሎ ይበዛዋል። ስለኢትዮጵያና ስለድንግል ማርያም ሀገርነት ስታስቡ ግን፡ ኹሉ ነገር ተጠቃልሎ ደጃችሁ ይመጣል። => እና፡ ኢትዮጵያ፡ ለመንፈሳዊ ሕይወቴ ጠቃሚ ኾና ስላገኘኋት ተሳብኩባት፥ "አስቀድማችሁ መንግሥቱንና ጽድቁን ፈልጉ" የሚለው መመሪያም ተግባራዊ ኾነና፡ ለአካዳሚክ ሕይወቴም፡ ይኽቺ ደኃ አገር በጣም ጠቃሚ ኾና አገኘኋት። በአጭሩ፡ እግዚአብሔርን በመፈለግ ጉዞ ውስጥ፡ የትምህርት ዕድል ሰጥታ ከሰፊ እንጀራዋ ለማቋደስ እጇን ዘርግታ፥ ወጪዬን ሸፍና በሰፊው ከተቀበለችኝ አሜሪካ ይልቅ፡ ይኽቺ ውጥንቅጥ አዙሪት ውስጥ ያለችው ኢትዮጵያ በብዙ እጥፍ ጠቀመችኝ። => እንጂ ከኢትዮጵያ ጋር ከሚያገናኙኝ ይልቅ፡ የሚበዙት፡ የማያገናኙኝ ዕድሎች ነበሩ። "ተምረሽ ፈረንጅ አገር ኺጂ፥ እዚህ ምንም የለም" በሚል ማኅበረሰብ መካከል ነው ያደግነው። ከተቻለ በአካልም፥ በመንፈስም፤ ከአገሪቱ እንድንላቀቅ የሚመክረን ነው የሚበዛው። በኢትዮጵያ ላይ የተሻለ እንጀራ የሚወጣልን ራሱ፡ አገሪቱን እንደማናውቃትና እንደማንፈልጋት ኾነን፡ ለሌሎች ስናደላ እንደኾነ፡ ኹላችንም የምናውቀው ነው። ሥልጣን ለመያዝማ አገሪቱን መጥላት አለብን። ይኼ የሿሚ አገራት ትልቁ መሥፈርት ነው። ታድያ፡ ስለኢትዮጵያ በማወቅና በመመርመር ውስጥ፡ በአሁኑ ጊዜ፡ ወጣቱ ላይ የተጋረጠው ከባዱ አደጋ ምን መሰላችሁ? => "የአባቶቻችን ጥበብ" እየተባለ፡ የነኢሉሚናቲ (የኖስቲኮች) እውቀትም በእጸፋርስ እገዛ ተከሽኖ እየቀረበ መኾኑ ነው። ብዙ ወጣቶችንም ጠልፏል። "ኢትዮጵያዊ" እውቀት ተደርጎም ተወስዷል። ክርስትናና የኖስቲኮች ፍልስፍና፡ በአደገኛ ሁኔታ ተቀላቅለው፡ አንድ ላይ ተጠብሰው በሰሃን እየቀረቡላችሁ ነው። ብዙዎች "የነቁ" የሚመስላቸው ወጣቶች፡ ይኽኛውን መሥመር እየመረጡ ሳያቸው እፈራለሁ። ሉሲፈርም የራሱን እውቀቶች፡ "የጠፉ ኢትዮጵያዊ እውቀቶች" በሚል ስም፡ ለትውልዱ እያስተዋወቀ ነው። አስፈሪ መመሳሰሎች አሉ። የእግዚአብሔር የሚመስሏችሁ፡ ከእግዚአብሔር ያልኾኑ ብዙ "ኢትዮጵያዊ" መሳይ እውቀቶች አሉ። እግዚአብሔር ይኹናችሁ! => መለያው፡ መስገድ፣ መጸለይ፣ መጾም፣ ጸበል መጠመቅ፣ ንስሓ መግባት፣ እና መቁረብ ነው። አብሮም፡ ቅዱሳት መጻሕፍትን በአትኩሮት ማንበብ ነው። እግዚአብሔር ከእኛ ምን እንደሚፈልግ፥ ምን እንደከለከለ፥ ምን እንደሚጠላ፥ ምን እንደሚወድ ማወቅ ግድ ይለናል። በተጨማሪም፡ ገድል የተጻፈላቸውን ቅዱሳን፥ እና ክርስቲያን ነገሥታትን እወቋቸው። አስተሳሰባቸውን አጥኑት፤ መንፈሳዊ ባሕላቸውን መርምሩት፤ ከዳዊትና ከሰሎሞን ተያይዞ የመጣውን ነፍሳዊ ስብዕናቸውን ተላበሱት። ከዚያም፡ መንፈሳዊ ሕይወታችሁም፡ በትክክለኛው መሥመር ሲያድግ ይታወቃችኋል። በመንፈስ እነርሱም ይቀርቧችኋል። በመንፈስ ቅዱስ ኃይል፡ ነፍሳችሁ የረሳችውን ትክክለኛውን ሰማያዊ ጥበብ ያሠርጹባችኋል። እንጂማ፡ ኢትዮጵያ ሌላ ምን አላት ብላችሁ ነው? ያውም በዚህ ዘመን? ዘይት ራሱ ስንት ብር ገብቷል! ለማንኛውም፡ ከመሥመሩ አያናውጣችሁ!

አሸነፈችኝ! አልቻልኩም ትቆርባለች ትጸልያለች በመቁጠሪያ ታነደኛለች!! ዕድል ይከፍታል ተብሎ የወሰደችው ዕጽ ያደረጋትን ተመልከቱ!! የባልና ምስት የጋራ ጸሎት https://youtu.be/Me9CuPxbFkw

ሰይጣንን ግደልልን አጥፋልን የምል ትውልድ እንዴት ፈጠርን!? ጭፈራ ቤት ከመሄዳችሁ በፍት ይሄንን በደንብ አስተውሉ!! እጅግ በጣም የምንፈተነው ለምንድነው!! https://youtu.be/_pjDFQdNP3Y

#ከSwizerland ላዘዙኝ ቤተሰቦቼ ለጸሎት ቤትና ለመንፈሳዊ ህይወታቸው የሚያስፈልጋቸውን በጠየቁን መሰረት በዚህ መልኩ አስተካክለን በDHL በኩል ልከንላቸዋል። እግዚአብሔር ይመስገን። = የአቡነ
+2
#ከSwizerland ላዘዙኝ ቤተሰቦቼ ለጸሎት ቤትና ለመንፈሳዊ ህይወታቸው የሚያስፈልጋቸውን በጠየቁን መሰረት በዚህ መልኩ አስተካክለን በDHL በኩል ልከንላቸዋል። እግዚአብሔር ይመስገን። = የአቡነ ሐብተ ማሪያም ገድል 1 = የህልም አለም መጽሐፍ 1 = የነፍስ ውጋት መጽሐፍ 1 = መቁጠሪያ 5 = የአቡነ ሐብተማሪያም ስዕል 1 = ቅባዕ ቅዱስ 2 = የናርዶስ ሽቶ 5 = እጣን 1 ኪሎ = ዘቢብ 1 ኪሎ * ውድ ቤተሰቦቼ በዚህ መንገድ እንድላክላችሁ የምትፈልጉ ሁላችሁም በውስጥ መስመር አናግሩኝ በዚህ ስልክ መጻፍ ትችላላችሁ 0903162292 ወይም https://t.me/haile_gebriel_tube_bot

=> ሊቁ አባ ጊዮርጊስ እንዲህ ይላሉ፡- «ነፍስ የንስሐን መታጠቢያ ካልታጠበች፣ የኃጢአት ቆሻሻ ተጣብቆባት ትኖራለች። ትሕትና ደግሞ ወደ እግዚአብሔር የሚያወጣ መሰላል ነው፤ ትዕቢት ግን ሰውን ወደ ሲኦል የሚጥል ድንጋይ ነው።» ኃጢአትን በውስጥ መያዝ ነፍስን ያሳምማል። ንስሐ ግባ፣ ራስህን ዝቅ አድርግ፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ጸጋ የሚገኘው በትሑታን ልብ ላይ ነው። አባ ጊዮርጊስ ሥጋን እንደ ፈረስ፣ ነፍስን እንደ ጋላቢ ይመስሉታል። «ፈረስ (ሥጋ) ግልቢያውን እንጂ መንገዱን አያውቅም፤ ስለዚህ ጋላቢው (ነፍስ) በእግዚአብሔር ህግ መመራት አለበት። ሥጋዊ ፍላጎትህን በጾም ካልገራኸው፣ ነፍስህን ወደ ጥፋት ይወስድሃል።» ሥጋዊ ፍላጎቶችህን (ምኞት፣ ቁጣ፣ ስግብግብነት) በጾም እና በጸሎት ተቆጣጠራቸው። ነፍስህን ለሥጋህ አታስገዛ። አባ ጊዮርጊስ በጸሎት ጊዜ ስለምናደርገው ትኩረት እንዲህ ያስተምራሉ፡- «አንደበትህ የሚናገረውን ልብህ ካላሰበው፣ ጸሎትህ እንደ መዳብ ድምፅ ባዶ ነው። እግዚአብሔር ከቃላት ይልቅ የልብን መሻት ያያል።» በሚጸልዩበት ጊዜ በቃላት መሽሞንሞን ብቻ ሳይሆን፣ ልብን ከእግዚአብሔር ጋር በማዋሐድ፣ በአክብሮትና በጥሞና መጸለይ ይገባል። ሊቁ በተቸማሪ እንዲህ ይላሉ፡- «ይህች ዓለም እንደ ጥላ ናት፤ ያልፋልም፤ ዘላለማዊ ቤት ግን እግዚአብሔር ያዘጋጀልን ነው። ሞትን መፍራት የለብህም፣ ነገር ግን ለሞት ማዘጋጀት አለብህ።» ለዚህ ምድራዊ ሕይወት ብቻ የምትደክም አትሁን። ከሞት በኋላ ለምትኖርባት ዘላለማዊ ሕይወት ቅድሚያ በመስጠት መልካም ሥራህን በምድር ላይ አከማች። «አርጋኖን» በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ አባ ጊዮርጊስ እንዲህ ይላሉ፡- «ፍቅር እግዚአብሔርን የሚያገኙበት መንገድ ነው። እግዚአብሔርን መውደድ ማለት ደግሞ የፈጠረውን ፍጥረት ሁሉ መውደድ ነው። ጎረቤትህን የማይወድ እግዚአብሔርን ሊወድ አይችልም።» የክርስቲያን ሕይወት መለኪያ ሰዎችን መውደድ ነው። በእግዚአብሔር ፍቅር ውስጥ የምንኖር ከሆነ፣ ፍርሃትና ጥላቻ ከውስጣችን ይወጣል። በረከታቸው ይደርብን!

ይሄንን ምልክት ካያችሁ የአለባበስ መተት ተደርጎባችኋልና እባካችሁን ንቁ!! የካህን ልጅ ነኝ የቀስ ልጅ ነኝ የምለውን ተውትና አሁኑኑ ይሄንን አድርጉ!! https://youtu.be/i8gwjWs2v2o

=> ጌታችን ለሰው ልጅ የሰጠው ሥጋና ደም «የሕይወት እንጀራ» ነው። በዮሐንስ ወንጌል 6፡51 ላይ «ከዚህ እንጀራ የሚበላ ሁሉ ለዘላለም ይኖራል፤ እኔም የምሰጠው ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው ሥጋዬ ነው» ይላል። የሰው ልጅ ትልቁ ረሃብ የሆድ ረሃብ ብቻ አይደለም፤ የነፍስ ረሃብ (ከእግዚአብሔር መለየት) ነው። መድኃኔዓለም ይህንን መልስ የሰጠው፣ የዓለማችን መከራና ረሃብ የመነጨው ከሰው ልጅ የመጀመሪያ ውድቀት (ከኃጢአት) ስለሆነ፣ ዋናው መፍትሔው ወደ እርሱ በመመለስ «የዘላለም ሕይወትን» ማግኘት ነው። => ሥጋውና ደሙ የሚሰጠው የረሃብን ችግር በድንገት ለመፍታት ሳይሆን፣ «አዲስ ሰው» ለመፍጠር ነው። የአእምሮ እና የልቦና መታደስ፡ በቅዱስ ቁርባን የሚቀደስ ሰው፣ ልቡ ይለሰልሳል፤ መተባበርን፣ መረዳዳትንና ፍቅርን ይማራል። የድህነት ዋነኛ መንስኤ ከሆኑት ስስት፣ ግፍ እና አለመተሳሰብ ይጸዳል። የማህበረሰብ ለውጥ፡ ክርስትና የጎረቤትን መራብ እንደራስ መራብ የሚቆጥርበት ሃይማኖት ነው። ስለዚህ አንድ ማህበረሰብ ሥጋውንና ደሙን በቅንነት ሲቀበል፣ በውስጡ «የፍቅር ማህበረሰብ» ይፈጠራል። የታረዘውን የሚያለብስ፣ የተራበውን የሚያበላ የሚፈጠረው ከዚህ መንፈሳዊ መሰረት ነው። => አንድ ሰው ሲራብ «ኑ ቁረቡ» ሲባል ግራ ሊያጋባ ይችላል። ነገር ግን ኦርቶዶክሳዊ ትርጓሜው እንዲህ ነው፡- መታመን፡ ሰው ችግሩን በራሱ ጉልበት ብቻ ለመፍታት ሲሞክር ይደክማል፤ ይበልጥ ይጨነቃል። ወደ እግዚአብሔር ሲቀርብ ግን እምነቱ ይጸናል፣ ከጭንቀት ነጻ ሆኖ በስራው ላይ ትኩረት እንዲያደርግ የአእምሮ ሰላም ያገኛል። የበረከት መክፈቻ፡ ሥጋውና ደሙ «አምላክነትን» (መለኮታዊ ጸጋን) ከሰው ጋር የሚያገናኝ ድልድይ ነው። ይህ ጸጋ በውስጡ ያለውን ሰው፣ እግዚአብሔር እንዲባርከውና በረከቱ እንዲበዛለት ያደርገዋል። => ጌታችን እንዲህ ያለው «ለሰው ልጅ ከምሰጠው ሁሉ የሚበልጠው ራሴን፣ ሥጋዬንና ደሜን ሰጥቼዋለሁ፤ ከዚህ በላይ ምን ልስጠው?» ማለቱ ነው። ማለት የፈለገው፡ እኔን የያዘ ሰው ዓለምን ሁሉ ይይዛል ማለት ነው። ያለንበትን ሁኔታ፡ ችግሩ ያለው «እግዚአብሔር ሰጪነቱን በመዘንጋት» ወይም «እኛም በጎረቤታችን በመዘንጋት» ነው። ሥጋውንና ደሙን የምንቀበል ክርስቲያኖች፣ በእውነት ከእርሱ ሆነን ብንኖር ኖሮ፣ በመካከላችን ምንም ዓይነት ረሃብና ድህነት ባልኖረ ነበር። => ባጭሩ፡ ሥጋውና ደሙ ለሆድ ሳይሆን ለነፍስ መፍትሔ ነው። የነፍስ ረሃብ ሲሞላ፣ የስጋ ረሃብን ለመፍታት የሚያስችል መለኮታዊ ጥበብ፣ ፍቅርና ትብብር በእኛ ውስጥ ይፈጠራል። እግዚአብሔር የሰጠንን ታላቅ ስጦታ (ሥጋውንና ደሙን) በመቀበል፣ እርስ በእርስ በመረዳዳት የረሃብን ችግር ማሸነፍ እንደሚገባን ነው።

ከላይ ለጻፍኩት ጥያቄ፡ በHailegebreal ወንድማችን ጥሩ ምላሽ ተጽፏል አንብቡት፦ የጌታችንና መድኃኔዓለም ክርስቶስ "ሥጋዬንና ደሜን ሰጥቼዋለሁ እኮ!" የሚለው መልስ በመጀመሪያ እይታ ለሥጋዊ ረሃብና ድህነት የተሰጠ የማይገናኝ መልስ ሊመስል ይችላል። ነገር ግን በጥልቀት ሲመረመር የችግሩን ሥረ-መሠረት (Root Cause) የነካ፣ ድህነትንና ረሃብን ከሥራቸው የሚነቅል ጥልቅ መንፈሳዊና ቁሳዊ ምስጢር ያዘለ ነው፦ 1. የችግሮች ሁሉ መነሻና የድህነት ሥረ-መሠረት ኃጢአት በመሆኑ፡ በዓለማችን ላይ ያለው ድህነት፣ ረሃብ፣ ጦርነትና ኢፍትሐዊነት የመጣው እግዚአብሔር ፍጥረታትን መመገብ አቅቶት ሳይሆን የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር በመራቁና በኃጢአት በመውደቁ ነው። ኃጢአት ደግሞ ስግብግብነትን፣ ፍቅር ማጣትንና የሰውን ድርሻ መቅማትን ያመጣል። መድኃኔዓለም "ሥጋዬንና ደሜን ሰጥቼዋለሁ" ሲል የሰው ልጅ ወደ እውነተኛው የሕይወት ምንጭ ተመልሶ ከኃጢአት ሲነጻ፣ ድህነትንና መከራን ያመጣው የኃጢአት እርግማን እንደሚወገድ ሲያሳየን ነው። 2. የቅዱስ ቁርባን የፅድቅ ተስፋና የተፈጥሮ ሕግን የመቀየር አቅም፡ ጌታችን በወንጌል "አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል" (ማቴ. 6:33) እንዳለው፣ ዋናውን የሕይወት መሠረት የሆነውን ቅዱስ ቁርባን የተቀበለና ከጌታ ጋር የተቀላቀለ ሰው ስጋዊው (ቁሳዊው) ነገር ትርፍ ሆኖ ይጨመርለታል። መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊትም "ጎበዛዝት ደኸዩ ተራቡም፤ እግዚአብሔርን የሚሹት ግን ከበጎ ነገር ሁሉ አይጎድሉም" (መዝ. 34:10) እንዲሁም "ጻድቅ ሲጣል ዘሩም እህል ሲለምን አላየሁም" (መዝ. 37:25) በማለት እንደመሰከረው፣ ጽድቅን የሚከተል ሕዝብ የእግዚአብሔር በረከት ይኖራል። => ከዚህም በላይ ቅዱስ ቁርባን አካላዊና ሥጋዊ ረሃብን የመወጣት ተአምራዊ ኃይል አለው። በቤተክርስቲያን ታሪክና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተረጋገጡ እውነታዎች እንደሚያሳዩት፣ ዓመታትን ሙሉ የቁሳዊ ምግብ ረሃብ ሳይሰማቸው በቅዱስ ቁርባን ብቻ (ብቸኛ ምግባቸው በማድረግ) የታላቁን አምላክ ምህረትና ኃይል እየመሰከሩ የኖሩ ቅዱሳንና አማኞች አሉ። ይህም እግዚአብሔር በባዶም፣ በውኃም ሆነ በቅዱስ ቁርባን ብቻ ሰውን ማኖር የሚችል ሁሉን ቻይ መሆኑን ያረጋግጣል። 3. ፍቅርና ወንድማማችነትን ማበጀት (የማኅበራዊ ድህነት መፍትሔ)፡ ሥጋውና ደሙ የመለኮት ፍቅር መገለጫ ነው። የክርስቶስን ሥጋና ደም የሚቀበል ሰው እውነተኛ የፍቅርና የርኅራኄ መንፈስ ያድሩበታል። አንድ ማኅበረሰብ ንስሐ ገብቶ ሥጋውንና ደሙን ሲቀበል እውነተኛ ፍቅር፣ መተሳሰብ፣ ረሃብተኛውን መመገብና የሌለውን መደገፍ ይለምዳል። ስለሆነም የሥጋውና ደሙ መገኘት ለአንድ ሕዝብ መንፈሳዊ ጥግ ብቻ ሳይሆን፣ እርስ በርስ በመረዳዳት ድህነትንና ረሃብን የሚያጠፋ ማኅበራዊ መፍትሔም ነው። => ስለዚህ ለራበውና ለደኸየው ሰው "ሃይማኖት ተምረህ፣ ንስሐ ገብተህ ቁረብ" ማለት ከምግብ መከልከል ሳይሆን፣ የመፍትሔዎች ሁሉ መፍትሔ ወደሆነው፣ በረከትንና ሕይወትን ወደሚያድለው የሕይወት ምንጭ መምራት ነው። ቁሳዊ ምግብ ለጊዜው ያጠግባል፤ ሥጋውና ደሙ ግን የዘላለምን ሕይወት ከመስጠቱም በላይ የዚህን ዓለም ረሃብና ድህነት በእግዚአብሔር በረከትና ተአምር ያጠፋል ፣ በቁሳዊውም ሆነ በመንፈሳዊው ሕይወት ሙላትን የሚሰጥ መለኮታዊ መፍትሔ ነው። እናንተስ ምን ትላላችሁ? አሳባችሁን አስቀምጡ!!

=> አንድ የሕዝቡ ችግር፣ ድህነትና ረሃብ ያሳዘናቸው ሰው፡ ወደ መድኃኔዓለም እንዲህ ብለው ጸለዩ፦ "ጌታ ሆይ፤ ለሰው ቀርቶ ለእንስሳት የምታዝንና ፍጥረትን ኹሉ የምትመግብ ኾነህ ሳለ፡ ሕዝብህ ሲራብ አይገድህምን?" መድኃኔዓለም ምን ብሎ መለሰላቸው መሰላችሁ? "ሥጋዬንና ደሜን ሰጥቼዋለሁ እኮ?!" አላቸው። የተሰጣቸው መልስ፡ ኹል ጊዜ ሳስበው፡ በጣም ይገርመኛል። ወገኖቼ! ለሥጋዊ ድህነታችንና ረሃባችን፡ ሥጋውና ደሙ መፍትሔ የሚኾነን እንዴት ነው? እስኪ የተረዳችሁትን ጻፉ?

+++ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ ውድ ቤተሰቦቼ +++

መምህር ተስፋዬ ለሰሎሞን ዘመቀት የማያዳግም ምላሽ ሰጠ ይደመጥ!! ሰሎሞን ዘመቀት መናገር ያልፈለገው ድብቁ ጉዳይ!! እጅግ መጠንቀቅ ያለባችሁ ነገር!! https://youtu.be/pgNVSKPKew4

እጅግ አነጋጋሪው የጴንጤ መዝሙር ስለ እመቤታችን! ይሄንን በጭራሽ ለጓደኛ ለቤተሰብ እንዳትናገሩ አደራ ተጠንቀቁ! አጋንንት በሽታ ሲሆኑ ይሄንን ጉድ ተመልከቱ! https://youtu.be/Q8Mj4eV43yY

** ወገኖቼ! ዘመኑ የክርስቲያኖች መፈተኛ ነው። በነዚህ አምስት ነጥቦች ላይ ተመስርታችሁ ሕይወታችሁን መርምሩ። => በሃይማኖታችሁ ጽኑ። => በንጽሕና ኑሩ። => ዓለምን ናቁ። => በዝምታ ተመላለሱ። => በፍቅር አሸንፉ። እግዚአብሔር አምላክ ይህንን ትውልድ በሥርዓተ ቤተክርስቲያን አጽንቶ ለዘላለም ሕይወት ያብቃን! አሜን በሉ ሁላችሁም!

=> ዓለም እያሳሳተች፣ ጌጥ እየማረከች፣ ትዕቢት ልብን እየሞላች ነው። ክርስቲያን የዚህ ዓለም ቱሪስት እንጂ ነዋሪ እንዳልሆነ መዘንጋት የለብንም። ዓለሙን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ በዓለም ያለው ሁሉ የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት የኑሮም ትዕቢት ነው። (፩ኛ ዮሐንስ ፪፥፲፭-፲፮)። ዓለም ውብ የሆነች እስር ቤት ናት። እዚያ ውስጥ የምትኖሩ አትሁኑ፣ ወደ ሰማያዊው ቤትዎ ተጓዙ። (ታላቁ ቅዱስ አንጦንዮስ)። => የሰይጣን ትልቁ ውጊያ ሰውን በጩኸትና በወሬ መበታተን ነው። ጸሎት ግን በልብ ውስጥ የሚደረግ ምስጢራዊ ንግግር ነው። በጩኸት መካከል ሳይሆን በዝምታ መሐል ነው እግዚአብሔር የሚናገረው። አንተ ግን ስትጸልይ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ። (ማቴዎስ ፮፥፮)። ዝምታ የነገረ መለኮት ቋንቋ ነው። ልብህን ከዓለም ወሬ ካልዘጋህ፣ የፈጣሪህን ድምፅ በጭራሽ አትሰማም። (ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ)። => የክርስቲያን ምልክቱ መስቀል (ፍቅር) ነው። ወንድሙን የሚጠላ፣ የሚቀናና የሚሰድብ ሰው የክርስቶስን ስም ቢጠራ እንኳን እግዚአብሔር አይቀበለውም። ክርስትና ማለት በፍቅር መኖር ነው። ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ ለሚረግሙአችሁ መልካም አድርጉ። (ማቴዎስ ፭፥፵፬)። ወንድሙን የሚያስቀይም ሰው የክርስቶስን አካል እየሰበረ ነው፤ የሰበረው ደግሞ በጌታ ፊት ይቆማል። (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)። መልካም ቀን ለሁላችን ይሁን!

ልጁን ለአጋንንት የገበረው እጅግ አደገኛው አባትና አሳዛኙ ክስተት!! ዲያቆኑ የአባቱን አጋንንታዊ መጽሐፍ ለምን አቃጠለ!! ጋዜጠኛውን በመተት አሳበዱት!! https://youtu.be/M4VasHKuj18

በፍልሰታ፡ ስለድግምታም ሴት ደፋሪዎች ስነግራችሁ የነበረው፡ ትዝ አላችሁ ወይ? እናንተም ብዙ ታሪክ አካፍላችሁኛል። እንደ ሮዛ ያሉ ብዙ ሴቶች አሉ። እንደ "አባ አረጋዊ" ያሉም ብዙ "አገልጋይ ነን"
በፍልሰታ፡ ስለድግምታም ሴት ደፋሪዎች ስነግራችሁ የነበረው፡ ትዝ አላችሁ ወይ? እናንተም ብዙ ታሪክ አካፍላችሁኛል። እንደ ሮዛ ያሉ ብዙ ሴቶች አሉ። እንደ "አባ አረጋዊ" ያሉም ብዙ "አገልጋይ ነን" ባዮች አሉ። በመተትም፣ በገንዘብም፣ በማስፈራራትም፣ በተስፋ መቁረጥም፣ በጉልበትም ሴቶቹን ዝም እያስባሉ መጠቀሚያ ያደርጓቸዋል። "ቆንጆ ቆንጆ ሴቶችን እያፈዘዝክ የምትተኛበት ድጋም ልሥራልህ" የኖረ የደብተራዎች ቢዝነስ ኾኗል። ሴቶቹ በክፉ መናፍስት አደንዛዥነት መጠቀሚያ ይኾናሉ። ኀፍረት ወይም የጥቅም ትሥሥር ይጫናቸውና ዝም ይላሉ። ነፍስ ያለው የሴቶች ጉዳይን በሕግ የሚከታተል የቤተክርስቲያን አካል ቢኖር፡ ካሉት አገልጋዮች ከ50% በላይ ከክህነት የሚያሽር ተግባር ላይ ያሉ ይመስለኛል። አምልኮ ባዕድና የአመንዝራነት መንፈስ አንድ ነው። በአፉ ብቻ እግዚአብሔርን እያመለከ፡ በልቡ ሰይጣንንና ገንዘብን የሚያመልክ ሰው፡ የማይቆጣጠረውና ከሴት ሴት የሚያክለፈልፈው የዝሙት ጦር ይለቅበታል። ይኽ ደግሞ፡ በቀላሉ፡ ከማን ወገን እንደኾነ ያሳብቅበታል። እርሱን የሚያውቁት ደግሞ፡ የኼደባቸው ሴቶች ናቸው። ነገር ግን፡ ሴቶቹ ወደፊት ወጥተው የኾነውን ነገር እንዳይናገሩና አንዳቸው ለአንዳቸው እንዳይቆሙ፡ "feminism" በሚል ማስፈራሪያ፡ ጥቃት ፈጻሚዎች፡ ቀድመው መንገዱን አጥረውታል። ለሴቶቹ የሚቆም የለም። ነገሩ ብልሽትሽት ብሏል። እናንተ ገና "Feminism እና መዘዙ" ላይ ናችሁ። ነገር ግን፡ ጠለቅ ያለ የሴቶች ጾታዊ ጥቃት እውቀት ያላት ሴት ብትኖር፡ በተለይ በሕግ አካላት እየታገዘች፡ እንዲህ ያሉ ባልታዛሮችን ልክ ታስገባቸው ነበር! ጽዮናውያን! ግድ የላችሁም፤ የራሳችሁ "version of feminism" ያስፈልጋችኋል። ወንዶቹ፡ የደብተራ መተት ተማምነው አፍልተዋል! "በቃችሁ" በሏቸው!