fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

رفتن به کانال در Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

کانال Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 15 791 مشترک است و جایگاه 5 384 را در دسته دین و مذهبی و رتبه 2 253 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 15 791 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 14 اکتبر, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 236 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 0 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 9.49% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 9.51% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 1 498 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 1 501 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 13 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 15 اکتبر, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته دین و مذهبی تبدیل کرده‌اند.

15 791
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+1837 روز
+23630 روز
آرشیو پست ها
ታክሲ፤ ከፒያሳ ሸዋ ዳቦ (ሜክሲኮ) (ጦር ኀይሎች) → አለም ባንክ፡፡ ፳፱. ኮልፌ ደብረ ፀሐይ አቡነ ተክለ ሃይማኖትና ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ፊሊዶሮ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → መርካቶ → ኮልፌ → ፊሊዶሮ፡፡ ፴. ቃሊቲ ደብረ መድኀኒት መድኀኔ ዓለምና አቡነ አረጋዊ ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ ሲሪቲ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ቃሊቲ → አቃቂ → ሲሪቲ፡፡ ፴፩. ደብረ መዊዕ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ\ክ፤ አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፥ ሐና ማንጎ ሰፈር፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → ሐና ማንጎ ሰፈር፡፡ ፴፪. መንበረ ልዑል ቅዱስ ገብርኤልና ቅድስት ድንግል ማርያም ቤ/ን፤ አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፥ 58 ማዞርያ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → 58 ማዞርያ፡፡ ፴፫. ቀበና ቤዛዊተ ዓለም ኪዳነ ምሕረት ቤ/ን፤ አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ቀበና ደልድዩ ጋር፥ ከኮከበ ጽባሕ ት.ቤት ፊት ለፊት፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ቀበና፡፡ ፴፬. ኮተቤ ሀገረ ገነት ጊዮርጊስ፥ ድንግል ማርያምና መግደላዊት ማርያምቤ/ን፤ አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ አንቆርጫ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ(ጊዮርጊስ) (4/6 ኪሎ) → ፈረንሳይ → አንቆርጫ፡፡ ፴፭. ደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ን፤ አድራሻ፤ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፥ መስቀል ዐደባባይ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ቦሌ (መስቀል ዐደባባይ/እስጢፋኖስ)፡፡ #ቅድስት_አርሴማ_በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_በዓሏ_የሚከበርባቸው_ #፳፬ ገዳማትና_አድባራት፡፡ ፩. ሲሪንቃ ቅድስት አርሴማ ገዳም አድራሻው፤ ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት፥ ወልዲያ፥ ሲሪንቃ፤ ትራንስፖርት፤ ከጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ወልዲያ → ሲሪንቃ፡፡ ፪. ጅሩ ሰንከታ ደብረ ልዕልና ቅድስት አርሴማ ገዳም፤ አድራሻው፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ጅሩ፤ ትራንስፖርት፤ ከመርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጅሩ፤ ወይም፤ ከጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ብርሃን → ጅሩ፡፡ ፫. ይርጋለም ጋኔ ቅድስት አርሴማ ገዳም፤ አድራሻው፤ ሲዳማ አማሮና ቡርጂ ሀገረ ስብከት፥ ይርጋለም፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ይርጋለም፡፡ ፬. ደብረ ሲና ሳር አምባ ቅድስት አርሴማ ቤ/ን፤ አድራሻው፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ደብረ ሲና፥ ሳር አምባ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ሲና፡፡ ፭. ደብረ ስብሐት ቀሃ ኢየሱስ ወቅድስት አርሴማ ቤ/ን፤ አድራሻው፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፥ የምሥራች፤ ትራንስፖርት፤ ከመርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር ከተማ → የምሥራች፡፡ ፮. ደብረ ታቦር ሎሚ ዱር ምዕራፈ ቅዱሳን አርሴማ፤ አድራሻው፤ ደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት፥ ደብረ ታቦር፤ ትራንስፖርት፤ ከመርካቶ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ታቦር → ሎሚ ዱር፡፡ ፯. ጂንካ በዓታ ለማርያምና ቅድስት አርሴማ ቤ/ን፤ አድራሻ፤ አርባ ምንጭ ሀገረ ስብከት፥ ጂንካ፤ ትራንስፖርት፤ ከአየር ጤና አውቶቡስ ተራ → አርባ ምንጭ → ጂንካ፡፡ ፰. አካኩ ምዕራፈ ቅዱሳን ዳግማዊት ሲሪንቃ ቅድስት አርሴማ ቤ/ን፤ አድራሻው፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ እንጦጦ፥ ከሽንቁሩ ሚካኤል አጠገብ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ (ጊዮርጊስ) (4 ኪሎ) → ሽሮ ሜዳ → ቊስቋም → አካኩ አርሴማ፡፡ ፱. ኵሉ ወይን አርሴማ ገዳም፤ አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ጫጫ፥ ፤ ትራንስፖርት፤ ከጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ጫጫ → ኵሉ ወይን፡፡ ፲. ደብረ ብርሃን ቅድስት አርሴማ ቤ/ን፤ አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ደብረ ብርሃን፤ ትራንስፖርት፤ ከጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ብርሃን፡፡ ፲፩. ወይንየ ጌቴ ሴማኒ ቅድስት አርሴማ ገዳም፤ አድራሻ፤ በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት፥ ግዳን ወረዳ፤ ትራንስፖርት፤ ከጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ግዳን፡፡ ፲፪. ቅበት ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ፤ (አሕዛብ ቤ/ኗን አቃጥለዋት የነበረችው) አድራሻ፤ ሃድያና ስልጤ ሀገረ ስብከት፥ ቅበት፤ ትራንስፖርት፤ ከአየር ጤና አውቶቡስ ተራ → ስልጢ፡፡ ፲፫. ባሌ ጋሰራ በኔባ አርሴማ ቤ/ን፤ አድራሻ፤ ባሌ ሀገረ ስብከት፥ ባሌ፤ ትራንስፖርት፤ ከቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ባሌ፡፡ ፲፬. ናዝሬት ቅድስት አርሴማ ቤ/ን፤ አድራሻ፤ ደቡብ ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ናዝሬት (አዳማ)፤ ትራንስፖርት፤ ከቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ናዝሬት (አዳማ)፡፡ ፲፭. ደብረ ናዝሬት ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን፤ (በድርብነት) አድራሻ፤ ደቡብ ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ናዝሬት (አዳማ)፤ ትራንስፖርት፤ ከቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ናዝሬት (አዳማ)፡፡ ፲፮. ቦንጋ ዋቻ ኦቤራ ጌቴ ሴማኔ ቅድስት አርሴማ ገዳም፤ አድራሻ፤ ጂማ ሀገረ ስብከት፥ ቦንጋ፥ ዋቻ ኦቤራ ፤ ትራንስፖርት፤ ከመርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጂማ → ቦንጋ፡፡ ፲፯. ዋሻ መድኃኔ ዓለም አቡነ ሙሴ ቅድስት አርሴማ ገዳም፤ አድራሻ፤ ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት፥ ዳውንት፤ ትራንስፖርት፤ ከጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ወልዲያ → ዳውንት፡፡ ፲፰. ቱሉ አርቦ ሾላ ገነት ቀስተ ደመና ቅድስት አርሴማ ወአቡነ ዘርዓ ቡሩክ ወመስቀለ ክርስቶስ ገዳም፤ አድራሻ፤ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ወልመራ ወረዳ፥ ቱሉ አርቦ፤ ትራንስፖርት፤ ከመርካቶ አውቶቡስ ተራ → ወልመራ → ቱሉ አርቦ፡፡ ፲፱. አሸተን ማርያና አርሴማ ገዳም፤ አድራሻ፤ ላስታ ላሊበላ ሀገረ ስብከት፥ ላበላ ከተማ፥ አሸተን፤ ትራንስፖርት፤ ከጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ላሊበላ → አሸተን፡፡ ፳. ሜሪላንድ ጽርሐ ጽዮን መንፈስ ቅዱስና ምዕራፈ ቅዱሳን ቅድስት አርሴማ፤ አድራሻ፤ ሰሜን አሜሪካ ሜሪላንድ ሀገረ ስብከት፥ አሜሪካ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ → ሜሪ ላንድ፡፡ ፳፩. ባሌ ጎባ ቅድስት አርሴማ ቤ/ን፤ አድራሻ፤ ባሌ ሀገረ ስብከት፥ ጎባ፤ ትራንስፖርት፤ ከቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ባሌ ጎባ፡፡ ፳፪. ባህር ዳር ቅድስት አርሴማ፤ ፳፫. ገደቢዬ አርሴማ፤ (ደባርቅ አጠገብ) ፳፬. ደባርቅ አርሴማ፤ (ሰሜን ጎንደር) የአድራሻ ምንጭ ---› ክብረ በዓላት /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like ሰላም ለዘአዕረፉ ምስሌኪ ፳ወ፯ቱ ሰማዕታት፤ ረድኤቶሙ ትረድ ላዕሌየ ዘምስለ ብዙኅ ምሕረት፡፡ ወኀበ ሀለወ ስሞሙ ምስለ ስምኪ ቅድስት፤ ዓዲ ኢይቅረብ አርሴማ ሕማመ ብድብድ ወሞት፤ በኵሉ አዝማን ወበኵሉ ዓመታት፡፡

#ታኅሣሥ_6_የአርሴማ_ቅድስት_ወሰማዕትና_የእርሷ_ማኅበርተኞች_ድል_አድራጊዎች_27_ሰማዕታት_ሥጋቸው_በክብር_የፈለሰበትና_ቤተ_ክርስቲያኗ_ቅዳሴ_ቤት_የተከበረበት_ዕለት ነው፡፡ 1ኛ. አርሴማ፤ ቅድስት ወሰማዕት ኃያል ተጋዳሊት 2ኛ. ኢያሚኖስ፤ ጸሎትን የሚያሳርግ ካህን 3ኛ. አፍጢኖስ፤ ከብዙዎች የተመረጠ 4ኛ. በርቲኖስ፤ ጻድቅና ቸር 5ኛ. ጢሞና፤ በመላላክ ሥራ አገልጋይ የኾነ 6ኛ. ጢሞዓና፤ ተአጋሽና ጸዋሚ 7ኛ. ዘኬዎስ፤ ከከበሩ የከበረ 8ኛ. እስጢፋኑ፤ ተጋዳይና የበደሉትን ይቅር ባይ 9ኛ. አርሞና፤ ከጎልማሶች ይልቅ ደም ግባቱና መልኩ ያማረ 10ኛ. ኪርያኮስ፤ ሥጋውን ያላረከሰ ንጹሕ 11ኛ. አንጥያኮስ፤ ቡሩክ የኾነ የአቡሪ ልጅ 12ኛ. ያዕቆብ፤ የእግዚአብሔር ታማኝ የኾነ 13ኛ. ቡራኬሌስ፤ በሰው ዘንድ ተወዳጅ የኾነ 14ኛ. አስቂርያቆስ፤ ክርስቶስን የሚወደው 15ኛ. አስኪርያኖስ፤ ባለሟል የኾነና ግርማው የሚያስፈራ 16ኛ. ሚርያኖስ፤ ፊቱና መልኩ ደስተኛ የኾነ 17ኛ. ትትግርጦስ፤ ወደ ንስሐ የተመለሰ 18ኛ. ያስቲኖስ፤ የሚፈርድና የሚበይን 19ኛ. ጥልያኖስ፤ ያላመኑ ሰዎችን የሚገስጽ 20ኛ. ዑልያኖስ፤ የዚህ ዓለም ጥበብ መምህር የኾነ 21ኛ. ጴርቅላስ፤ በስም አጠራርና በሽምግልና መልካም የኾነ 22ኛ. ኬብያኖስ፤ ተጋዳይ የኾነ 23ኛ. ጴጥሮስ፤ የጠራ የባሕርይ ዕንቊ 24ኛ. ጰኵንዮስ፤ የሮምያ ሹም 25ኛ. ሐናንያ፤ የዋህና ሽንገላ የሌለው 26ኛ. ሐሊባኖስ፤ ጾምና ጸሎትን የሚወድ 27ኛ. ኤስያኖስ፤ በመንፈስ ቅዱስ ጎልማሳ የኾነ 28ኛ. ኤልያብ፤ በረኛና የሰማዕት መጀመሪያ፡፡ —- #ታኅሣሥ ፮፤ #በዓለ_ቅዳሴ_ቤታ_ለቅድስት_አርሴማ_፡፡ #ቅድስት_አርሴማ_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ__በዓሏ_የሚከበርበት_ #፩ #ገዳም ፩. #አርመን_ቅድስት_አርሴማ_፤ #ክብርት_ዐጽሟ_ያረፈበት_ አድራሻው፤ አርመን፥ ሰፈረ ሰላም (አባኮት)፤ #ቅድስት_አርሴማ_በመዲናችን_በአዲስ_አበባ__በዓሏ_የሚከበርባቸው_ #፴፭ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ ፩. ቃሊቲ መካነ ሰላም ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ፤ አድራሻው፤ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ ሰፈረ ሰላም (አባኮት)፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ(መገናኛ) → ቃሊቲ → ሰፈረ ሰላም፤ ፪. ግራር ደብረ ዐባይ ቅድስት አርሴማ፤ አድራሻው፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ግራር ኮንዶሚኒየም፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → መርካቶ → ኮልፌ → ግራር፤ ፫. የካ አባዶ ደ\ል ቅድስት አርሴማና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ የሐንስ ቤ/ን፤ አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ አባዶ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) → አባዶ ፬. ወይራ ሰፈር ገነተ ሰማይ ቅድስት አርሴማና አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ቤ/ክ፤ አድራሻው፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ወይራ ሰፈር፥ ጦጣ ገደል(ዶሮ ርባታ)፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ አራዳ ሸዋ ዳቦ ቤት → ወይራ ሰፈር → ዶሮ ርባታ፤ ወይም፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → ጦር ኃይሎች → ወይራ ሰፈር፡፡ ፭. ጎፋ መካነ ብርሃን ቅዱስ ዑራኤል ወቅድስት አርሴማ ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፥ ጎፋ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → ጎፋ፡፡ ፮. ሸጎሌ ኮዳነ ምሕረት ወቅድስት አርሴማ፤ አድራሻ፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ ጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → አዲሱ ገበያ (ቶታል) ፡፡ ፯. ጎጆ አርሴማ ወአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን፤ አድራሻ፤ ክፍለ ከተማ፥ ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) → ፡፡ ፰. ደብረ መድኀኒት አቡነ ሀብተማርያም ወቅድስት ልደት ወቅድስት አርሴማ ገዳም፤ አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ካኦ ጀጄ ዱቄት ፋብሪካ ቃሎ ተራራ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → በአስኮ መስመር → ካኦ ጄጄ → ቃሉ ተራራ፡፡ ፱. ቦሌ 24 ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልና ቅድስት አርሴማ ቤ/ን፤ አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ 24ት (አዲሱ ስታዲየም)፡፡ ታክሲ፤ ከፒያሳ → መገናኛ → 24ት፡፡ ወይም ታክሲ፤ ከፒያሳ → ቦሌ → 24ት፡፡ ፲. ቦሌ አራብሳ ዋሻ መካነ ቅዱሳን ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ ልደታ ለማርያም ፣ ኪዳነ ምሕረት ፣ ሚካኤልና አርሴማ ቤ/ን፤ አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ አራብሳ፡፡ ታክሲ፤ ከፒያሳ → መገናኛ → አራብሳ፡፡ ፲፩. ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ዑራኤልና ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ኤረር በር (በጎሮ መንገድ አለማየሁ ሕንፃ ገባ ብሎ)፡፡ ታክሲ፤ ከፒያሳ → መገናኛ → ጎሮ፡፡ ፲፪. ቦሌ ሰሚት ምስራቀ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ሰሚት ኮንዶሚኒየም፡፡ ታክሲ፤ ከፒያሳ → መገናኛ → ሰሚት ኮንዶሚኒየም፡፡ ፲፫. አያት መካነ ሕይወት መድኀኔ ዓለምና ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ሮል ሳሙና ፋብሪካ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → መገናኛ → አያት ጠበል፡፡ ፲፬. ቀበና ምሥራቀ ፀሐይ መድኀኔ ዓለም ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ አራዳ ክፍለ ከተማ፥ ቀበና፡፡ ታክሲ፤ ከፒያሳ → በመገናኛ → ታክሲ ቀበና፡፡ ፲፭. መንበረ ክብር ቅዱስ ሚካኤል፣ አቡነ ተክለ ሃይማኖትና ቅድስተ አርሴማ ገዳም፤ አድራሻ፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ ቀጨኔ፡፡ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ቀጨኔ፡፡ ፲፮. ሐመረ ወርቅ ማርያምና አርሴማ ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፥ ወርቁ ሰፈር፡፡ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ቃሊቲ፡፡ ፲፯. ምስራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት አርሴማና አቡነ አዳም ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፥ አዲስ ሰፈር፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → ጀርመን ዐደባባይ፡፡ ፲፰. ጀሞ ደብረ ኀይል ቅዱስ ገብርኤልና ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፥ ጀሞ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → ጀሞ፡፡ ፲፱. አቃቂ ፈንታ ደብረ ጽጌ ቅዱስ ሩፋኤልና ቅድስት አርሴማ፤ አድራሻ፤ አቃቂ ቃሊቲ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፥ ፈንታ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ቃሊቲ → አቃቂ → ፈንታ፡፡ ፠፨፠ እንዲሁም በድርብነት፤ ፳. ኮተቤ ማኅደረ ቅዱሳን አቡነ ገብረመንፈስቅዱስና ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ የካ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፥ ሎቄ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ(መገናኛ) → ሎቄ፡፡ ፳፩. ኮተቤ ሃገረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ፥ ቅድስት ማርያምና ቅድስት መግደላዊት ማርያም ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ አንቆርጫ፤ ታክሲ፤ ከአራዳ ጊዮርጊስ (ከ4 ኪሎ) (ከ6 ኪሎ) → ፈረንሳይ→ አንቆርጫ፡፡ ፳፪. ጉራራ ምስራቀ ፀሐይ ቅድስት ኪዳነ ምሕረትና ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ጉራራ፤ ታክሲ፤ ከአራዳ ጊዮርጊስ (ከ4 ኪሎ) (ከ6 ኪሎ) → ፈረንሳይ→ ጉራራ፡፡ ፳፫. ደብረ ተአምራት ዳግማዊት ጻድቃኔ ቅድስት ማርያም፤ አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፥ ታቦት ማደርያ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → ታቦት ማደርያ፡፡ ፳፬. ደብረ ቢታንያ አቡነ ተክለ ሃይማኖትና ቅድስት ልደታ ለማርያም፤ አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፥ ካራ ቆሬ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → ካራ ቆሬ → 2 ቊጥር ማዞርያ፡፡ ፳፭. አዲስ አምባ ደብረ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረትና ደብረ ፍስሐ ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፥ አዲስ ሰፈር፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ሜክሲኮ → አዲስ ሰፈር፡፡ ፳፮. ገዳመ ኢየሱስ፤ አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ሆላንድ ኤምባሲ፡፡ ታክሲ፤ ከፒያሳ → መርካቶ → ኮልፌ፡፡ ፳፯. . ኮልፌ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ስልክ ላፍቶ፥ ጠሮ፡፡ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ዊንጌት → ጠሮ አራት መንታ፡፡ ፳፰. አለም ባንክ ጀሞ ደብረ ራማ ቅዱስ ገብርኤል፤ አድራሻ፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ አለም ባንክ፤

ከታኅሣሥ 27/2011 ዓ.ም ደብራችንን በአለቅነት ሲመሩ የነበሩት መልአከ ሰላም ስዩም ወ/ገብርኤል ከታላቁ ደብራችን ከቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ ተነስተው
ከታኅሣሥ 27/2011 ዓ.ም ደብራችንን በአለቅነት ሲመሩ የነበሩት መልአከ ሰላም ስዩም ወ/ገብርኤል ከታላቁ ደብራችን ከቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ ተነስተው ወደ የካ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ሲዞሩ ፤ መልአከ ሰላም አምደ ወርቅ ደሴ ከደብረ ቀራንዮ መድኀኔዓለም ፤ ደብራችንን በአስተዳዳሪነት እንዲመሩ ትላንት በ01/04/2014 ዓ.ም ተመድበዋል፡፡ ለክቡር አባታችን መልአከ ሰላም አምደወርቅ ደሴ መልካም የአገልግሎት ዘመን እንዲሆንልዎ እንመኛለን፡፡ለክቡር አባታችን ፤እሑድ ታኅሣሥ 10/2014 ዓ.ም አቀባበል ይደረግላቸዋል ፡፡

#ክብረ_በዓሉ_ከሚከብርባቸው አድባራትና ገዳማት በአዲስ_አበባ_ ፩. ዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም፤ (ግቢ ገብርኤል) ጋራ፤ ፪. ቦሌ አራብሳ ዘንዶ አስራ በዓታ ማርያም፤ መንግሥት (ግቢ ገብርኤል) ጋራ፤ ፫. ቂሊንጦ መካነ ፍስሐ ቅዱስ ሚካኤልና በዓታ ለማርያም ቤ.ክ.፤ ቂሊንጦ አደባባይ፤ ፬. ኮልፌ ደብረ ብርሃን ቅድስትሥላሴ ቤ.ክ፤ ጠሮ፡፡ ታክሲ፤ ከአራዳ ጊዮርጊስ ሞቢሉ ጋር (4 ኪሎ) → ፈረንሳይ/ኢየሱስ/፤ ፮. ላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤ ላፍቶ፡፡ ፯. ፉሪ መካነ ቅዱሳን አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ እና ቅዱስ ሚካኤል ለቡ(ፉሪ)፡፡ ፰. ቶታል ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤ.ክ.፤ ሰፈረ ገነት፡፡ ፱. ኮተቤ የካ ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት፤ (ብረታ ብረት)፡፡ ፲. ቱሉ ዲምቱ ደብረ ሰላም ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅዱስ ሚካኤል ቤ.ክ.፤ አቃቂ ኬላ፡፡ ፲፩. ደብረ ሰሊሆም መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስና መድኃኔ ዓለም ቤ.ክ.፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ቃሊቲ → በርታ ሰፈረ ሰላም፡፡ በመላው ኢትዮጵያ ፲፫. ደብረ ኤረር በዓታ ወልደታ፤ (በ4ኛው ክፍለ ዘመን በአብርሃ ወአጽብሃ የተመሠረተ፤ የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ምድር፤ የምሥጢር ቦታ) (ዱከም) → ደብረ ኤረር፡፡ ፲፬. ባሕር ዳር ጽርሐ አርያም ደብረ ሲና በዓታ ለማርያም ቤ.ክ. (በ1313 ዓ.ም. በአቡነ ዘዮሐንስ የተመሠረተች)፤ ባሕር ዳር ፲፭. ጎንደር ደብረ ኀይል ወደብረ ጥበብ በዓታ ለማርያም /ወዑራኤል/፤ (የታች ቤት አቋቋም ዋና ምስስከር) (በጎንደር ዘመነ መንግሥት በ17ኛው ክፍለ ዘመን የተመሠረተች) ጎንደር ፲፮. ጂንካ በዓታ ለማርያምና ቅድስት አርሴማ ቤ.ክ.፤ ጂንካ፡ የመልአኩ የፋኑኤል በዓል ከሚከብርባቸው ፩. ካራ ቆሬ ቅዱስ ፋኑኤል፤ ካራ ቆሬ፡፡ ፪. መዝገበ ምሕረት ቅዱስ ፋኑኤል ቤ.ክ.፤ አያት አደባባይ፡፡ ፫. ቅዱስ ፋኑኤል #የአቡነ_ዜና_ማርቆስ በዓል… ፩. ደብረ ብሥራት አቡነ ዜና ማርቆስ ጅሩ → ደብር፡፡ ፪. ምሁር አክሊል አቡነ ዜና ማርቆስ ወልቂጤ → ምሁር፡፡ ፫. ጣፎ አቡነ ዜና ማርቆስ → ጣፎ፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like አቅጣጫ ከገዳማትና አድባራት..

እንኳን አደረሳቹህ | ታኅሣስ 3 #✤ በኣታ ለማርያም፤ ✤ በዓለ ሢመቱ ለቅዱስ ፋኑኤል ሊቀ መላእክት፤ ዕረፍቱ ለአቡነ ዜና ማርቆስ እመቤታችን አባትና እናቷ ኢያቄምና ሐና በስዕለት(ለቤተ መቅደስ ሊሰጡ ብፅዓት ገብተው) ያገኟት ናት፡፡ በአባት በእናቷ ቤትም ፫ ዓመት ተቀመጠች፤ ከእንግዲህ ወዲያማ ስእለት መብለት ይሆንብን የለምን ወስደን እንስጥ ብለው ይዘዋት ወደ ቤተ መቅደስ ሲሄዱ ዘካርያስም ሕዝቡን ሰብስቦ ጉባኤ አድርጎ ቆያቸው። **ከዚያውም ደርሰው እነሆ ተቀበሉን አሏቸው እነርሱም እንቀበላለን ብለው ቢያዩዋት ከፀሐይ ፯ እጅ አብርታ፥ ከመብረቅ ፯ እጅ አስፈርታ፥ ዕንቈ ባሕርይ መስላ ታየቻቸው፤ እነርሱም እኛ ይህችን የመሰለች ፍጡር ምን እናደርጋታለን? ምን እናበላታለን? ምን እንጋርድላታለን? ብለው ሲጨነቁ በዚህም መካከል እመቤታችንን እግዝእትነ ማርያም መንፈሳዊ ረኀብ ተነስቶባት ምርር ብላ አለቀሰች። ያን ጊዜ መልአኩ ፋኑኤል በመሶበ ወርቅ ኅብስት ሰማያዊ፤ በብርሃን ጽዋዕ ስቴ ሕይወት ይዞ ረቦ ታያቸው፡፡ ሕዝቡም ዘካርያስን አባታችን ይህ የወረደው ክብር ላንተ ነው የሚኾነውና ተነስተህ ታጥቀህ እጅ ነስተህ ሰግደህ ተቀበል አሉት፤ ዘካርያስም እሽ ብሎ እጅ ነስቶ ሰግዶ እቀበላለሁ ብሎ ሲጠጋ ወደ ሰማይ ራቀው፥ መጠቀው፡፡ ከሕዝቡም እያንዳንዱ እየተነሱ እንቀበላለን ብለው ቢያዩ ወደ ሰማይ ራቃቸው፥ መጠቃቸው፡፡ **ከዚህም በኋላ ዘካርያስ ሐናን ጠርቶ ለናንተ ለእንግዶች የወረደ ክብር እንደሆነ ሕፃኒቱን ይዘሽ ወደዚያ ፈቅ ብለሽ ተቀመጪ አላት፡፡ እርሷም ሕፃኒቱን ይዛ ወደዚያ ፈቅ ብላ ተቀመጠች፡፡ መልአኩም ከራሳቸው ላይ ረቦ አልወርድም አለ፡፡ ***ሁለተኛም ዘካርያስ ሐናን ጠርቶ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ነገር የሚያውቅ የለም፤ ሕፃኒቱን ከዚያው ትተሽ አንቺ ወዲህ ነዪ አላት፤ እሽ ብላ ሕፃኒቱን እዚያው ትታ ወደነሱ ሄደች፡፡ ያን ጊዜ መልአኩ ፋኑኤል ወርዶ ፩ ክንፉን ጋርዶ ፩ ክንፉን አጎናፅፎ ኅብስቱን አብልቷት፥ ወይኑን አጠጥቷት፤ እመቤቴ ሆይ መንገድ ባስመታሁሽ ማሪኝ ብሎ የብርሃን መሶብ፥ የብርሃን ጽዋ ይዞ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ **ሕዝቡም የምግቧማ ነገር ከተያዘ ከሰው ጋራ ምን ያጋፋታል፤ ቦታዋ ከቤተ መቅደስ ይሁን እንጂ ብለው ዙፋኑን ዘርግተው፥ ምንጣፏን አንጥፈው፥ መጋረጃውን ግራና ቀኝ ጋርደው ከቤተ መቅደስ አኖሯት፡፡ ***ይኸውም የተደረገው ታኅሣሥ ፫ ዕለት ነው፤ በአታ የሚለው ስያሜም የተሰጠው በዚሁ ነው፡፡ ‹‹አመ ፫ ለታኅሣሥ በኣታ›› እንዳለ መቅድመ ተአምር፡፡ በዚህም፤ #መቅደሲቱ_ወደ መቅደስ ገባች፤ #ቅድስቲቱ_ወደ ቅድስት ገባች፤ #ክብርቲቱ_ወደ ክብርት ቤቷ ገባች፤ #ልዩ_የሆነችው_ወደ ልዩ ሥፍራ ገባች፤ #ቅድስተ_ቅዱሳኗ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ገባች፤ #ንጽሕተ_ንጹሐኗ ወደ ንጽሕ አዳራሽ ገባች፤ #ቤተ_መቅደሷ ወደ ቤተ መቅደስ ገባች፡፡ ሊቃውንትም ‹‹መቅደስ ዘኢትትነሠት /የማትፈርሺ መቅደስ ነሽ››/ እያሉ አመሠገኗት፡፡ **እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም ኅብስት ሰማያዊ እየተመገበች፤ ስቴ ሕይወት እየጠጣች ከመላእክት ጋራ እየተጫወተች 12 ዓመት በቤተ መቅደስ ተቀመጠች፡፡ ‹‹ከመዝ ነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ፤ ወመላእክት ያመጽኡ ወትረ ሲሳየኪ ከመዝ ነበርኪ ፲ተ ወ፪ተ ዓመተ እንዘ ትትናዘዚ እምኀበ መላእክት ወስቴኪኒ ስቴ ሕይወት ውእቱ። ወመብልዕኪኒ ኅብስት ሰማያዊ››። እንዳለ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ***ምግቧ ከየት የተገኘ ነው ቢሉ በገበሬ እጅ ያልተዘራ በቤተ ሰብእ እጅ ያልተሠራ በእግዚአብሔር እጅ የተፈጠረ ያማረ የተመረጠ ነው እንጂ ፡፡ ‹‹ኦ ድንግል አኮ ኅብስተ ምድራዌ ዘተሴሰይኪ፤ አላ ኅብስተ ሰማያዌ እም ሰማየ ሰማያት ዘበሰለ፡፡ ኦ ድንግል አኮ ስቴ ምድራዌ ዘሰተይኪ አላ ስቴ ሰማያዌ እምሰማየ ሰማያት ዘተቀድ›› (ድንንግል ሆይ ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለሽም፤ ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን እንጂ፡፡ ድንግል ሆይ ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለሽም፤ ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጥን ነው እንጂ፡፡) /እንዳለ ሊቁ አባ ሕርያቆስ/። ***ስታድግም በንጽሕናና በቅድስና ነው፡፡ ‹‹ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለም በንጽሕና በቅድስና ኖርሽ እንጂ።›› /እንዳለ ሊቁ አባ ሕርያቆስ/ ***እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቤተ መቅደስ ሳለች አይሁድ ብዙ የክፋት ምክር ይመክሩ ነበር። ከዚህም ውስጥ አንዱ መጥቁል ወደሚባል ጠንቋይ ሄደው ‹‹ፍታሕ ማዕከሌነ ኢያቄም ወሐና›› ብለው እመቤታችንን እንዲያጠፋ እጅ መንሻን ሰጡት፤ መጥቁልም በመካከል አይሁድ በኋላ ሁነው ነጋሪት እየጎሰሙ፥ እምቢልታ እየነፉ እመቤታችንን እግዝእትነ ማርያምን ለመግደል ለቤተ መቅደስ ፪ ምንዳፈ ሐፅ ሲቀራቸው፤ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከ እዚያ ድረስ ያልተደረገና ያልተነገረ መብረቅ ነጎድጓድ ወርዶ አጋንንትንም፥ መጥቁልንም፥ አይሁድንም ቀጥቅጦ አጠፋቸው። እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም በማግሥቱ ወጥታ አይታ መጥቁል ሆይ እኔን አጠፋ ብለህ መጥተህ አንተ እንዲህ ሆንህ ካንተ መከራ መዓት ያወጣኝ አምላክ ይክበር ይመስገን ብላ ፈጣሪዋን አመሰገነች፡፡ ከዚህ በኋላ በድኑ ለዝክረ ነገር የ፫ ቀን መንገድ እየሄደ ይሸት ጀመር። እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም ‹‹ዮሰሜር፣ አድሜሽ፣ ድቸር፣ አዶናዊሮስ፣ ሰራሰቅሰሬል›› ብላ የአምላክ ኅቡዕ ስምን ብትደግም መሬት ተከፍቶ ዋጣቸው ከነሥጋቸውም ሲኦል ወረዱ፡፡ ከዚህ በኋላ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እጅግ ታፈረች የሚናገራት ጠፋ ‹‹ኦ ግርምት ድንግል›› /እንዳለ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም/። ✤#በዓለ_ሢመቱ_ለቅዱስ_ፋኑኤል_ሊቀ_መላእክት፤ #ሰዳዴ አጋንንት ነው፤ /ሄኖክ 10፥8፣ ድርሳን ዘፋኑኤል/ #መጋቤ ድንግል ነው፡፡/ተአምረ ማርያም/ #ማኅሌታዊ ነው፤ #በመንበረ መንግሥቱ ዙሪያ ከሚቆሙት ሊቃነ መላእክት አንዱ ነው፡፡ /ሄኖክ 20፥39/ #በአራቱ የዓለም ማዕዘናት ሹም አንዱ ነው፡፡ #ለመልካም ነገሮች ከሚራዱ መላእክት አንዱ ነው /መዝ. 33፥7/ #ካህነ ንስሐ ነው /ሄኖክ 10፥5/ #ዐቃቤ ጻድቃን ነው፡፡ /2ኛ ነገ. 6፥14/ #ምስለ_አብያጺሁ_ከመ_አብ_እንዘ_ይሴስየኪ_መና፤ #ፋኑኤል_ጽጌ_ነድ_ዘይከይድ_ደመና፡፡ ✤#ኢትዮጵያዊው_አቡነ_ዜና_ማርቆስ_በዓለ_ዕረፍታቸው ነው፡፡ እኒህ ታላቅ አባት በምድረ ጉራጌ በሚገኘው በምሁር ኢየሱስ ገዳም 40 ዓመታትን ሱባኤ የገቡ፤ ምድረ ጉራጌን (ሙሉ ሸዋን ጨምሮ እስከ ደቡብ) እንዲሁም በሌሎችም የሃገራችን ክፍሎች ያስተማሩ፤ በርካታ ሊቃውንትን /አባ ጽጌ ድንልንና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታን ጨምሮ ሌሎችን ሊቃውንትም/ ያፈሩ ፈርጥ ሲኾኑ፤ በስተመጨረሻ በተአምራት የተሞላውን ታላቁን ገዳም ደብረ ብሥራትን (ጅሩ) መሥረተው በክብር አርፈዋል፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/

*በጥንታዊው ደብረ ኃይል እንጦጦ ቅዱስ ራጕኤል ወኤልያስ፤ *በደብረ ኤልያስ ጎጃም፤ *በገርጂ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን (በድርብነት አለ) *መካነ ሕያዋን ቅዱስ ኤልያስ ኋላ መካነ ሕያዋን ጎፋ ቅዱስ ገብርኤል የተባለ ፤ *በሻሸመኔ ልደታና በሌሎችም የቅዱስ ኤልያስ አድባራትና ገዳማት ይከበራል፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like

እንኳን ለቅዱስ ኤልያስ ዓመታዊ ክብረ በዓል (የልደት ቀን) በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፥ አደረሰን፡፡ በቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ ካሉት ቅዱሳን ነቢያት ዝናም በማቆም ብቸኛ ነቢይ፡፡ ✤ የሰማርያው ነቢይ ኤልያስ ከቅዱሳን አበው ነቢያት አንዱ ሲኾን አባቱ ኢያሴዩ ይባላል፡፡ በነቢይነትም ሆነ በብቃት ኤልያስን የሚያክል፤ በሥራው የሚወክል ከእሱ በፊትም ኾነ በኋላ በተአምራት የተሞላ እሳት ለበስ ነቢይ እሱ ከመረጠው ከደቀ መዝሙሩ ከኤልሳዕ በቀር አልተነሳም፡፡ ነቢዩ ኤልያስ ከኢዮርብዓም እስከ እርሱ ድረስ ለአያሌ ዓመታት በሰይጣን ግፊት በሰው ሠራሽ ጣዖት የተመረዘ በኃጢአትም ረዘረዘ፣ የግፈኛው አክአብና የዘማዊቷ ኤልዛቤልን መንግሥት በሦስት ዓመት ከመንፈቅ በከባድ ድርቅ በመናጥ፣ እንዲሁም አፈር እንደበላው ብረት የዛገ አስተሳሰባቸውን በሰው ደምና በቅሚያ ገንዘብ የተሞላ ሰውነታቸውን በማን አለብኝነት ያበጠ ልባቸውን እንደሰም በማቅለጥ የሚይዙትንና የሚጨብጡትን ያሳጣ በፈጣሪው ለዚህ ሥራ የተመረጠ ሰመ ጥር ነቢይ ነው፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ ነውና፡፡ ኤልያስ የከተማ ነቢይ ብቻ አይደለም ባሕታውያን ተብለው ከሚጠሩት ነቢያተ ጽድቅም አንዱ እንደነበር ሕልውናው ምስክር ነው፡፡ (( ኤልያስ ብዙ ነገር ስለሚያስተምር የቀና እምነቱን ውጤት ጥቂት መመልከት እኔ ማነኝ ለሚሉት እጅ ይዞ ይመራል፡፡ ✤ 1. ለሦስት ዓመት ከመንፈቅ ሰማይ ዝናም ለዘር ጠል ለመከር ከመስጠት እንዲከለከል ምድርም የተከሉባትን እንዳታጸድቅ የዘሩባትን እንዳታበቅል ለባለንብረቱ አመለከተ ይህም ጥያቄው ከእግዚአብሔር መልስ አግኝቷል፡፡ ነገሥ 17፥1-2፡፡ ከዚህ ላይ የሊቀ ነቢያት ሙሴንና የኢሳይያስን ቃል ያስጠቅሳል ዘዳ 32፥1-4፣ ኢሳ 1፥2-5፡፡ በእነዚህ እስከፊ ዓመታት ውስጥ በመሪዎች አመፅ በኤልያስ ተግሣጽ የሚመለከተውም የማይመለከተውም የሚልሰውና ሚቀምሰው አጥቶ በዋለበት እንደ ቅጠል ረገፈ እንደሻሸተ ነጠፈ፡፡ የኀጥአን ፍዳ ጻድቅ ይደፋ ይሏል ይህ ነው፡፡ ዛሬም በአምስቱ ክፍለ ዓለም የብዙኃኑ እልቂት ሲፈጸም የሚታየው በጥቂት እግዚአብሔር የለሽ ሰይጣን ጁንታዎች ሽፍቶች መሆኑን ከአክአብና ኤልዛቤል ይማሯል፡፡ ይህን የኤልያስን ጠበቅ ያለ እገዳ ከስምንት መቶ አምሳው ነቢያተ ሐሰት ካህናተ ጣዖት አንዱም ወደ ሚመለከተው በጸሎቱም ሆነ በመሥዋዕቱ አመልክቶ ሊያስነሳ ወይም ለማስነሳት የቻለ የለም፡ ጠንቋዮችና አታላዮች በብሉይ ኪዳን ብዙ ጊዜ ከቤተ መንግሥት ተለይተው አይርቁም፡፡ 1ኛ ነገሥ 18፥22፣ዳን 2፥1-14፡፡ ✤ 2. አመጸኞች አክአብንና ኤልዛቤልን ምንነታቸውን ካሳወቀ በኋላ የዘጋውን ለመክፈት ወደ ፈጣሪው በመጸለይ ዝናም አዝንሟል፡፡ 1ኛ ነገሥ. 18፥41-46፣ ያዕ 5 17-18 እግዚአብሔር ለወዳጆቹ የገባውን ቃል ኪዳን አያጥፍም አቁም ሲሉት ያቆማል ስጥ ሲሉት ይሰጣል እንጂ ምን አገባቸው ብሎ እንደፈለገው አያደርግም፡፡ የእግዚአብሔር ሐዋርያ ስለ ኤልያስ ማንነት ሲያደንቅ ኤልያስ እንደኛ ሰው ነበር ዝናም እንዳይዘንም ከለከለ እንደገናም እንዲዘንም አደረገ በማለት በዘመኑ የነበሩ ክርስቲያኖች ከቀና ክርስትናቸው ምን እንደሚጠበቅባቸው ከእምነታቸው ምን ማግኘት እንዳለባቸው ይጠይቃል ያዕ.5፥13-20፡፡ ዛሬስ ምን ይመስሎታል፡፡ ኤልያስ በቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ ካሉት ቅዱሳን ነቢያት ዝናም በማቆም ብቸኛ ነቢይ ነው፡፡ ነገር ግን በረዶ ያዘነመላቸው አንደኛ ሙሴ ዘፀ 9፥13-21 ሁለተኛ ኢያሱ 10፥9-12 ሦስተኛም ሳሙኤል 1ኛ ሳሙ 12፥1-19 ይመለከታል፡፡ ✤ 3. በተፈጥሮ የማይመስላቸው በቋንቋም የማይግባባቸው እንኳን ለሰው ሥጋ ሊያመጡ ከሰው ሥጋ የሚነጥቁ አሞራዎች ከየት እንደሚያመጡት የማይታወቅ እንጀራና ሥጋ ለምግብ እንዲያመላልሱለት አደረገ 1ኛ ነገሥ 17፥6-7፡፡ እነዚህ አሞራዎች ለሦስት ዓመት ከመንፈቅ በጋ ከክረምት የለምንም እረፍት ኤልያስን ሲያገለግሉ ኖረዋል፡፡ እምነት ካለ ተአምር መሥራት አይገድም ይህንም ከኤልያስ ይማራል፡፡ ✤ 4.ለአንዲት መበለት ዱቄትና ዘይት አበረከተ፡፤ ኤልያስ ቁራሽ እየለመነ ያደረገውን ተአምር ልብ ይሏል፡፡ 1ኛ ነገሥ. 17፥16-24፡፡ ✤ 5. ዱቄትና ዘይት ያበረከተላት ሴት ልጇ ቢሞት ከሞት አስነሳው 1ኛ ነገሥ. 17፥20-23 ይህች ሴት በእምነቷ አርአያነት ያላት ደገኛ ሴት ናት፡፡ ኤልያስን የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ከአንተ ጋር ምን አለኝ፣ ኀጢአቴንስ ታስብ ዘንድ ልጄንስ ትገድል ዘንድ ወደ እኔ መጥተሃልን ብላዋለች፡፡ ኤልያስም በእግዚአብሔር ኀይል ማንኛውንም ችግር ለመፍታት ሙሉ መብት ነበረውና ወዲያውኑ የሞተውን ብላቴና ጠጋ ብሎ ወደ ፈጣሪው በጸሎት በማመልከት አስነስቶ የብላቴናውን እናት አስደስቷል 1ኛ ነገሥ 17 17-24 ሐዋርያ እምነት ጀግኖችን በመዘገበበት አንቀጽ ይችን ሴት ልብ ይሏል፤ ዕብ 11፥35፡፡ ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ያሉ እናቶች ያስፈልቷል፡፡ ይህችን ሴት የሚመስሉ እናቶች 2ኛ ነገሥ. 4፥18-38 ፣ሉቃ 7፥11-17 ተመዝግበዋል፡፡ በሐዋርያት ሥራም ያሉት እናቶች ከእነዚህ ጋር ያነጻጽሯል የሐዋሥ 9 36-43፡፡ ✤ 6. ለብዙ ጊዜ በቤተ መንግሥት ተሰግስገው አክአብና ኤልዛቤልን በሐሰት ሲደልሉ ግብዝ ሕብረተሰቡን ሲያታልሉ ለፍቶ ያገኘው ገንዘቡን ሲሸልጉ በኀጢአት ሊያስወጉ የነበሩ ነቢያተ ሐሰትና ካህናተ ጣዖትን በሕብረተሰቡ ፊት እስከ መምህራቸው ሰይጣን በቅሌት አከናንቦ ሲያስቅባቸው ውሏል፤ 1ኛ ነገሥ 18 20 -29፡፡ ሰይጣን በሰማርያ በምድር እንደዚያ ቀን ሰው መዘባበቻ በመሆን የውርደት ቀን ገጥሞት አያውቅም፡፡ በገዛ አገሩና መንደሩ፡፡ 7. ወደ ፈጣሪው በጸሎት በማመልከት ያቀረበው ንጹሕ መሥዋዕቱን ከሰማይ እሳት ወርዶ በሰው ፊት በላለት 1ኛ ነገሥ 18 30-40፡፡ በዚህም ማንነቱን በሰይጣንና በሰይጣን አቀንቃኞች ፊት አስመስክሯል፡፡ ✤ 8. ምግብና መጠጥ መልአክ ከሰማይ አመጣለት ያንን ተመግቦ ለአርባ ቀን ያለምንም ምግብ መጠጥ ተጉዟል 1ኛ ነገሥ 19፥5-7 ✤ 9. እሳት ከሰማይ በማዝነም ሊጣሉት የመጡትን መምለኪያነ ጣኦት ምሉአነ ኀጢአት የሰይጣን ሠራዊት በሰው ደም የሰከሩ በዲያብሎስ የሚመሩ ጠላቶቹን አጋይቷል 2ኛ ነገሥ 1 9-13 ✤ 10. በመጎናጸፊያው የዮርዳኖስን ባሕር ከፍሎ ከነ ደቀመዝሙሩ በደረቅ ተሸግሯል 2ኛ ነገሥ. 2፥11 ✤ 11. ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ918 ዓመተ ዓለም ሳይሞት በሕይወቱ መራራው ሞት ዕያየው በብርሃን ሠረገላ ወደሰማይ አርጓል 2ኛ ነገሥ. 2 6-9 ✤ 12. እንደ እያስፈላጊነቱ ከፈጣሪው ጋር ለብዙ ጊዜ ተነጋግሯል ከአንድ እስከ አስራ አንድ ያደረጋቸውን ተአምራት የፈጸመለት ታማኝ ፈጣሪው ሰው በሆነበት ወራት በተራራ ከጓደኞቹ ጋር ብርሃነ መለኮቱን ገለጠለት ማቴ 17 ፥3 ፡፡ ከዚህ ዓለም ከተሰናበቱ በኋላ ወደዚህ ዓለም መጥተው የፈጣሪጣቸውን ሰው መሆን ያዩ ከነቢያተ ጽድቅ ሙሴና ኤልያስ ብቸኞች ናቸው ብፁዓን ከተባሉት ሐዋርያትም ተቆጥረዋል፤ በዚህም ቅዱሳን ከሞት በኋላ እንደሚያማልዱም መስክሯል፡፡ ማቴ 13፥16-17፡፡ ኤልያስ ሰው መባል ወይም ተብሎ በመጠራት እንደማንኛውም ሰው መሆኑ መልአክ አለመሆኑን ሐዋርያ ነግሮናል ያዕ 5፡17-20፡፡ ከኤልያስ ብዙ ነገር ወይም ተግባር ስለሚማሩ ከቅዱስ መጽሐፍ ከ 1ኛ ነገሥ 17፡1 ጀምረው እስከ 2ኛ ነገሥ 2፡11 ረጋ ብለው ይመርምሩ ክርስትናዎትንም ይፈትሹ፡፡ ታኅሣሥ 1 ፤ ክብረ በዓሉ የሚከበርባቸው፤