fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

رفتن به کانال در Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

کانال Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 16 042 مشترک است و جایگاه 5 280 را در دسته دین و مذهبی و رتبه 2 240 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 16 042 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 29 اکتبر, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 518 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 1 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 25.50% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 10.35% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 4 090 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 1 660 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 33 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 30 اکتبر, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته دین و مذهبی تبدیل کرده‌اند.

16 042
مشترکین
+124 ساعت
+917 روز
+51830 روز
آرشیو پست ها
እንዳያመልጥዎ!! 136ኛ ሳምንት የዐርብ ጕባኤ፡፡ ስለ ወጣቶች መንፈሳዊ ሕይወትና ፈተናዎች (ስለ እጮኝነት ጊዜና አመራረጥ፣ ስለ ድንግልናና ስለ ጋብቻ፣ ....)፡፡ የቀ/ደ/ሰ መድኀኔዓለም ወደ/ት/ቅ/ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት፡፡

‹‹ኵሉ አመክሩ ፤ ወዘሰናይ አጽንዑ፤ (ሁሉን መርምሩ፤ መልካሙን ያዙ)፡፡›› ፩ኛ ተሰሎንቄ ፭፥፳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ሃገራችን ሰላምና አንደነት ለሁለት ሳምንት (#እስከ_ሐምሌ_4_ቀን_2011_ዓ.ም.) የሚቆይ #ጸሎተ_ምሕላ አወጀ፡፡ ጸሎተ ምሕላውም በመላው ዓለም በሚገኙ አድባራትና ገዳማት የሚደረግ ይሆናል፡፡

#ደብር_ቅዱስ_ደብረ_ጽጌ_ማርያም_ቤተ_ክርስቲያን፡፡ ፎቶውን የምታዩት ቤተ ክርስቲያን ከአዲስ አበባ በ90 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው በታላቁ አባት አቡነ ተክለሃይማኖት የመሠረቱትና ኋላ ግራኝ አፍርሶት ቆይቶ በ1951 ዓ.ም. በመጀመሪያው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ድጋሜ የታነጸው ደብር ቅዱስ ደብረ ጽጌ ማርያም ገዳም ነው፡፡ ይህ ገዳም፤ ✜ አቡነ ተክለሃይማኖት በአቅራቢያው ካለው ደብረ ከርቤ ከሚባል ገዳም ጋር የመሠረቱትና ይቀድሱበት የነበረ ታላቅ ገዳም ነው፡፡ ✜ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የጋራ መናገሻ መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያንን ባርከው ሲመለሱ ዓረፍተ ዘመናቸው ደርሶ ያረፉበት ሲኾን፤ ኋላ ደቀ መዛሙርቶቻቸው ወደ መሠረቱት ታላቁ ገዳም ወደ ጋሥጫ ይዘው ወስደው በሰላም አሳርፈዋቸዋል፡፡ ✜ አፄ ዮሐንስና አፄ ምኒልክ ተጣልተው ቆይተው ኋላ እርቅ ያወረዱት በዚሁ ገዳም ነው፡፡ ✜ በግራኝ ወረራ ጠፍቶ ቆይቶ፤ ድጋሜ ደግሞ በጣሊያን ብዙ መከራ ደርሶበት ከቆየ በኋላ፤ በመጀሪያው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ በ1951ዓ.ም. በራሳቸው ገንዘብ በድጋሚ በሚደንቅ የሕንፃ አሠራር አስፋፍተው ያሠሩትና የገደሙት ገዳም ነው፡፡ ዳግመኛ ሲያሳንጹትም ከታላላቅ ቅዱሳን ገዳማት አፈር አስመጥተው ያስነሰነሱበት፣ የከበሩ ንዋያትን ከመሠረቱ በታች ያኖሩለት ታላቅ ገዳም ነው፡፡ ✜ ገዳሙን ከአቡነ ባስልዮስ በኋላ ህልውናው ተጠብቆ እንዲቀጥል፤ በበላይነት ኀላፊነቱን የቤተ ክህነት መንፈሳዊ ጕባኤ ተረክቦ እንዲያስተዳድር አደራ የሰጡት ገዳም ነው፡፡ ✜ አቡነ ባስልዮስ በድጋሜ ሲገድሙት በኢትዮጵያ የሚሰጡ መንፈሳዊ ትምህርቶች ኹሉ እንዲሰጡበት አድርገው ነበር፤ ምንም እንኳን አሁን በተወሰነ መልኩ ቢደበዝዝም ንከባብ እስከ ትርጓሜ ቤት ያሉ ጕባኤያት አሁንም እየተካሄዱበት የሚገኝ የቤተ ክርስቲያናቸው ማገር የኾነ የትምህርት ማዕከል ነው፡፡ ✜ ጳጳሳትን (ከ17 በላይ)፣ ሊቃውንትንና መምህራንን ያፈለቀና እያፈለቀ የሚገኝ ዐዘቅተ ጥበብ ገዳም ነው፡፡ ✜ ከአምስት በላይ ፈዋሽ ጸበል ያለበት ገዳም ነው፡፡ ✜ 3 መቅደሶች (መቅደሰ ማርያም መቅደሰ ሚካኤልና መቅደሰ ተክለ ሀይማኖት ያሉበት፤ (በአዘቦት ቀን በ7 ደናግል መነኰሳት የሚቀደስባት፤ በትንዓኤና በዘመነ ጽጌ በ21 ደናግል መነኰሳት በ3ቱም መቅደሶች የሚቀደስበት ታላቅ ገዳም ነው፡፡) ✜ ከዓመት እስከ ዓመት ሌሊትና ቀን ስብሐትና ጸሎት የማይታጎልበት (በዐቢይ ጾም ዳዊት ሲስተዛዘል ዳዊት የሚያስተዛዛለው /የሚደግመው ከመብዛቱ የተነሣ/ እንኳን አንድ አንድ ንጉሥ (10 ምዕራፍ) ይቅርና አንድ አንድ ምዕራፍ እንኳን ማዳረስ ባለመቻሉ በሦስት ፈረቃ ዳዊት የሚተዛዘልባት ታላቅ የመምህራንና የተማሪዎእ መሰባሰቢያ ገዳም ነው፡፡ ✜ በአካባቢው የሚገኘው ‹‹ደብረ ጽጌ›› ከተማ ስያሜውን ያገኘው ከዚሁ ደብረ ነው፡፡ #ኢየሩሳሌም_ደብረ_ገነት_ኪዳነ_ምሕረት_ በመምህር ወልደ ሰማዕት አማካኝነት፤ አፄ ዮሐንስ ፬ኛ አስጀምረውት አፄ ምኒሊክ ያስፈጸሙት እስራኤል ከሚገኙ አፅመ ርስታችን አንዱና ዋነኛው፡፡

ሰኔ ጐልጐታ ወሕንፀተ ቤተክርስቲያን ወሥርዐተ ማኅሌት፡፡ ሰላም፤ እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ለቅድስተ ቅዱሳን ለድንግል ማርያም ሰኔ ጐልጐታና ሕንፀተ ቤተ ክርስቲያን (ለመጀመሪያ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ለታነጸበት) ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ፡፡ ✤✤ ሰኔ ጎልጎታ፤ ‹‹ሰኔ ጐልጐታ፤ ችግር የምትፈታ፤ ወጣቱ በርታ ፥ ማዕተብ አትፍታ፡፡›› /እማሆይ ማናዬ ዘቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም/ ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም በዚህ ቀን (ሰኔ 21) ልጇን ወዳጇን ጐልጐታ በሚባል ቦታ ላይ እንበዋ እንደ ጅረት እስኪፈስ ድረስ ለኃጥአን ምሕረትን ለምናዋለች:: ጌታችንም ‹‹ስምሽን የጠራውን፤ በቃል ኪዳንሽ ያመነውን ሁሉ እምርልሻለሁ፡፡›› ብሎ ቃል ኪዳን ሰጥቷታል፡፡ ✤✤ ሕንፀተ ቤተ ክርስቲያን፤ ሰኔ 21 ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ሲኾን፤ ሕንጸተ ቤተክርስቲያን ይባላል፡፡ በሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን በአምላክ እናት ስም የታነጸችው በዚሁ እለት በሰኔ 20 ቀን ነው፡፡ አናጺውም ደግሞ እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን፤ ቦታው በፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው፤ ጥንተ ነገሩስ (ታሪኩ) እንደምን ነው ቢሉ፤ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና አምላካችን መደኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርቱን ‹‹ሑሩ ወመሐሩ ኵሎ አሕዛበ፤ አሕዛብን ሁሉ ሒዱና አስተምሩ፡፡›› /ማቴ. 28፥19/ ባላቸው ቃል መሠረት ሐዋርያት በወንጌል ያርሷት ዘንድ በዕጣ ተካፍለዋታል:: የሰው ልጅ ድኅነቱ የሚፈጸመው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበል ነውና (ዮሐ. 6፥ 56) አበው ሐዋርያት ቊርባንን በተመረጡ ሰዎች ቤት እያዘጋጁ ቀድሰው ይቆርቡና ያቆርቡ ነበር:: በመጀመሪያ በጽርሐ ጽዮን፣ ቀጥሎም በተለያዩ ሰዎች ቤት እንዲህ ይከናወን ነበር፡፡ ለጸሎት ሥራ ደግሞ አንዳንዴ ምኵራበ አይሁድን ይጠቀሙ ነበር:: እየቆየ ሲሔድ ግን ከአሕዛብ ያመኑ ሰዎች ቊጥር እጅጉን በመብዛቱ /በተለይ ቅዱስ ዻውሎስ ያሳመናቸው ለጸሎት እያሉ ወደ ጣዖት ቤት መግባት አመጡ::/ በዚህ ምክንያት መምህራን ሕዝቡን ‹‹ካመናችሁ በኋላ እንዴት ወደ ጣዖት ቤት ትገባላችሁ?›› ቢሏቸው ‹‹እኛ ምን እናድርግ! የምንጸልይበት ቤት የለን›› ሲሉ መለሱላቸው:: ነገሩ ሲያያዝ ከደጋጉ ሐዋርያት ዻውሎስና በርናባስ ደረሰ:: ወዲያውኑ አንዳንድ ወንድሞች ቤት ‹‹ለምን አናንጽም?›› ብለው ነበር:: ቅዱስ ዻውሎስ ግን ‹‹ሊቀ ሐዋርያቱ ሳይፈቅድ አይሆንም›› አለ:: (ለዚህ ነው ዛሬም ሊቀ ዻዻስ ካልፈቀደ ቤተክርስቲያን የማይታነጸው፡፡) ከዚያ ቅዱሳን ዻውሎስና በርናባስ ሐዋርያቱ ወዳሉበት ሔደው ነገሩን ለቅዱስ ዼጥሮስ አስረዱ:: ሊቀ ሐዋርያቱ ቅዱስ ዼጥሮስም ‹‹የጌታችን ፈቃዱ መኾኑን እናውቅ ዘንድ ተያይዘን ሱባዔ እንግባ›› ብሎ አዋጅ ነገረ:: በዓለም ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ በአንድ ልብ ሱባዔ ገቡ:: በሱባዔያቸው መጨረሻም ክብር ይግባውና ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መላአክትን አስከትሎ በግርማ ወደ እነርሱ ወረደ፤ እመቤታችን በቀኙ ነበረች፡፡ ኹሉንም ሐዋርያት በሩቅም በቅርብም ያሉትን ደቀ መዛሙርቱን በደመና ጠቅሶ ፊልጵስዩስ በሚባል ሃገር ሰበሰባቸው፡፡ ከዚያም በስተምሥራቅ ከከተማ ወጣ ወዳለ ሥፍራ ወሰዳቸው፡፡ በዚያም ተራርቀው የነበሩ 3 ደንጊያዎች ነበሩ፡፡ 3ቱንም ድንጋዮችን በተአምራት አቀራርቦ አንሥቶ ጎተታቸው፡፡ ድንጋዮቹም እንደሰም ተለጠጡ፣ እንደ ግድግዳም ሆኑ፡፡ ቁመቱን ወርዱን መጥኖ ለሐዋርያቱ ሰጣቸው፡፡ እነርሱም እሳት እንዳየው ሰም በእጃቸው እየለመለሙ (እየሳቡ) ቁመቱን 24፥ ወርዱን 12 ክንድ አድርገው ዕጽብት፥ ግርምት የምትኾን 3 ክፍል ያላትን የመጀመሪያዋን ቤተክርስቲያን በ52 ዓ/ም ሰኔ 20 ቀን አነጹ፡፡ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ፤ ጌታችንም በሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም አምሳያ አድርጎ አነጻት፤ ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ለሐዋርያቱ ‹‹እንግዲህ እናንተም እንዲህ አድርጋችሁ ሥሩ፡፡›› ብሏቸው ዐረገ፡፡ ✜ በማግስቱ ሰኔ 21 ዕለት ደግሞ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አእላፍ መላእክትን፣ ሰማያውያን ቅዱሳንን እና እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምን ይዞ ወረደ:: ሐዋርያቱ አብዛኞቹ እዛው ሲጸልዩ አድረው ነበርና ጌታችን ከቅዳሴው በፊት 2 ነገሮችን አሳየ፤ አስቀድሞ ቤተክርስቲያኗን በድንግል እናቱ ስም አክብሮ ሥርዐተ ቤተክርስቲያንን አሳየ:: ቀጥሎ ደግሞ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስን ከመካከል አቁሞ ‹‹አርሳይሮስ›› ሲል ሾመው:: ይኼውም የዓለም ሁሉ ሊቀ ዻዻሳት (ፓትርያርክ) ማለት ነው:: በዚህ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት ‹‹አክዮስ›› እያሉ 3 ጊዜ አሰምተው ጮሁ:: አክዮስ ማለት በግዕዙ ‹‹ይደልዎ›› በአማርኛው ደግሞ ‹‹ይገባዋል፤ ያስምርለት›› እንደ ማለት ነው:: ጌታችን ይህን ከከወነ በኋላ ይቀድስ ዘንድ ጀመረ:: አማናዊት ማኅደሩን ድንግል ማርያምን መንበር አድርጎ፣ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደ ተራዳኢ ካህን ቆሞ፣ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሠራኢ ዲያቆን ኾኖ፣ ሐዋርያት ድንግልን ከበው፣ መላእክተ ብርሃን በክብራቸው ቆመው ጌታችን ቀድሶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወዳጆቹ አቀበለ:: በዚያች ዕለት በፍጡር አንደበት ተከናውኖ ሊነገር የማይችል ደስታ ተደረገ:: ከቅዳሴ በኋላ ጌታችን ሐዋርያትን አዘዛቸው:: ‹‹ከዚህ ቀን ጀምሮ በመላው ዓለም በእናቴ በማርያም ስም አብያተ ክርስቲያናትን አንጹ፤ ይህችን እለት የሚያከብራትን አከብረዋለሁ::›› ብሏቸው ከድንግል እናቱና ከመላእክቱ ጋር ዐረገ:: ✤✤ ሥርዐተ ማኅሌቱ እንደየደብራችሁ ይትበሃል ትጠሙበበት ዘንድ የሁለቱንም (የላይ ቤት የግምጃ ቤትና የታች ቤት የበአታን) አብነት አስቀምጠንላችኋል፤ በቢጫ የተቀለመው የላይ ቤት (የግምጃ ቤት) አብነትን ለምትከተሉ አድባራት ሲኾን፤ ሰማያዊ የተቀለመው ደግሞ የታች ቤትን (የበዓታን) የአቋቋም ይትበሃል ለምትጠቀሙ ሲኾን፤ ሁለቱም የላይ ቤቱና ያየታች ቤቱ የሚተባበሩበት ላይ ደግሞ ዘግምጃ ቤት ወዘበዓታ ብለን በፈዛዛ ጥቁር አስቀምጠንላችኋል፡፡ መልካም ማኅሌት፨ (ሥርዐተ ማኅሌቱን ላልደረሰው በ Facebook, Telegram, Viber, Xender, Imo, Messsenger, Bluetooth, Email በማድረስ ይተባበሩ፡፡) ኦ አበው ወእማት አኃው ወአኃት ኢትርስዑነ በጸሎተክሙ (በዘጸለይክዋ በዝንቱ ሥርዐተ ማኅሌት) ለትምህርተ ቤትነ ቀ.ደ.ሰ.መድኀኔዓለም ወደ.ት.ቅ.ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት፡፡ ✼ የድንግል እመቤታችን ልመናዋ ክብሯ፣ ጣዕመ ፍቅሯና በረከቷ በሁላችን ላይ ይደርብን::

መሐሮሙ እግዚኦ ለነፍሳተ አግብርቲከ፤ ኀይለ ገብርኤል፣ ወልደ ጊዮርጊስ፣ ገብረ ኪዳነ ማርያም፣ ገብረ ሕይወት፣ ገብረ እግዚአብሔር፣ …፡፡ (አቤቱ አምላካችን ሆይ፤ የጄነራል ሰዐረ መኰንንን፣ የዶ.ር አምባቸው መኰንንን፣ የሜጀር ጄነራል ገዛኢ አበራን፣ የብርጋዴር ጄነራል አሳመነው ጽጌን፣ የእዘዝ ዋሴን፣ የምግባሩ ከበደን ነፍስ ይማርልን፤ ነፍስ ይማርልን፤ ከደጋጎቹ ከአብርሃም ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋራ ያኑርልን፡፡) ፠፠ስላላየነውና ስላልሰማነው፤ ስለማናውቀውና ስላልደረስንበት ነገር በእርግጠኝነት አናውራ!፤ አንናገርም!!፡፡ ‹‹በአፍህ ቃል ተጠመድህ፤ በአፍህ ቃል ተያዝህ፡፡›› መጽሐፈ ምሳሌ 6÷2/ ፨ ‹‹የእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ ከእኛ ዘንድ አልተመለሰምና ማቅ ልበሱ፥ አልቅሱም ዋይም በሉ፡፡›› ትንቢተ ኤርሚያስ 4፥8 ‹‹የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ፡፡›› ትንቢተ ኤርምያስ 3÷7/ *‹‹በሚያልፈው ዓለም የማይለፈውን ፍቅር እንኑርበት፥ በሚያልፈው ዓለም የማይልፈውን ሰላም እንመላለስበት›› /ብፁዕ አቡነ አብርሃም/ *አክለክሙ ዘኀለፍክሙ መዋዕል::

ሥርዐተ ማኅሌት ወዜናሁ ዘሠኔ ፲፯፤ በዓለ አባ ገሪማ (ይስሐቅ) ዘመደራ፡፡ * በዓለም ላይ በእድሜ ረጅም ዓመታት (ከ1500ዓመታት በላይ) ያስቈጠረውን የብራና ወንጌል ጽፈው ያቆዩልን፤ * ዓድዋ የሚለውን ስያሜ ያወጡ፤ * አሁንም ድረስ ከደረቅ ዓለት ላይ ጠበል እንዲፈልቅ ቃል ኪዳን የተሰጣቸው፤ ሂዳችሁ እዩ!! * በአንድ ቀን ዘርተው ለ9 ሰዓት ቅዳሴ መሥዋዕት ያደረሱ፤ በዚህና በሌሎች ምግባሮቻቸው ወንድሞቻቸው የሚኾኑ ቅዱሳን ሳይቀር ገሪማ ገረምከን ብለው የመሰከሩላቸው፤ * የኢትዮጵያ ታሪክን የያዘ ታላቁን መደራ ገዳም የሠረቱ፤ የታላላቅ የአድዋ ጀግኖቻችን መሪያቸው ራስ አሉላ አባ ነጋን ጨምሮ አጽማቸው ያረፉበት ነው፡፡ (ክብረ በዓላቸው ሰኔ 17 በዐድዋ በሚገኘው በመደራና በአዲስ አበባ በካራ አሎ መድኀኔ ዓለም በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡) #አባ_ገሪማ_(ይስሐቅ)#ዘመደራ (ክብረ በዓላቸው በዓድዋ በሚገኘው ገዳማቸው፣ በጎንደር ተክለሃይማኖት፣ በአዲስ አበባ ካራአሌ መድኀኔዓለም ወአቡነ ገሪማ ገዳም) በአልአሜዳ ዘመነ መንግሥት በ፬፻፹ ዓ.ም ወደ አገራችን ወደ ኢትዮጵያ በሃይማኖት ምክንያት ከሶርያና ከታናሽ እስያ ተሰደው ከመጡት ተስዓቱ (ዘጠኙ) ቅዱሳን መነኮሳት (አባ አሌፍ፣ አባ አረጋዊ፣ አባ አፍጼ፣ አባ ሊቃኖስ፣ አባ ገሪማ፣ አባ ጉባ፣ አባ ይምአታ፣ አባ ጰንጠሌዎን እና አባ ጽሕማ) መካከል በትምህርታቸው የላቁ፣ ቅዱስ ያሬድ በድጓው (በመዝሙር)፣ በዝማሬና በመዋሥዕት ድርሰቱ ውስጥ ‹‹ገሪማ ገረምከኒ አስኬማከኒ አልባቲ ሙስና፤ አባ ገሪማ አስገረምኸኝ፡፡ ለምንኵስናህም እንከን የለባትም›› በማለት የደረሰላቸውና አድዋ የሚለውን ስያሜ የሰየሙ፣ በዓለማችን ላይ እስካሁን ከተገኙት የብራና ወንጌሎች መካከል በእድሜው ረዥሙንና ባለሠንጠረዡን /ከ1400ዓመታት በላይ/ የጻፉ፣ እስከ አሁንም ድረስ የሚያስደንቅ ከደረቅ ዓለት ላይ እንደ እንባ የሚወጣው ፈዋሽ ጠበል ያፈለቁ አባ ገሪማ ዘመደራ ናቸው፡፡ እነዚህ ዘጠኙ ቅዱሳን በመላው ኢትዮጵያ ተዘዋውረው ወንጌልን ሰብከዋል፤ በወቅቱ ብሔራዊ ቋንቋ የነበረዉን ግእዝን በሚገባ አጥንተው ቅዱሳት መጻሕፍትን ከሱርስትና ከጽርዕ ቋንቋዎች ወደ ግእዝ ተርጕመዋል፡፡ እንደዚሁም ገዳማትንና አብያተ ክርስቲያናት አሳንጸዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችንም ከፈጸሟቸው መንፈሳውያን ተልእኮዎች፣ ካደረጓቸው ተአምራትና መልካም ሥራዎች አኳያ ቅዱሳን በሚል መዓርግ ትጠራቸዋለች፤ በስማቸውም ጽላት ቀርፃ በዓላቸውን ታከብርላቸዋለች፡፡ የአባ ገሪማ አባት መስፍንያኖስ የሮም አገር ንጉሥ ነበረ፤ ሚስቱም ሰፍንግያ ትባላለች፡፡ መካን ስለነበረች በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በመማጸን ልጅ እንዲሰጣት እግዚአብሔርን ስትለምን ከኖረች በኋላ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ይስሐቅ አለችው፡፡ የያን ጊዜው ይስሐቅ የኋላው አባ ገሪማ በመንፈሳዊ ሥርዓት ካደገ በኋላም የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ተምሮ በዲቁና ማገልገል ጀመረ፡፡ ይስሐቅ ወላጅ አባቱ ሲሞትም በአባቱ ዙፋን ተተክቶ ለሰባት ዓመታት ሮምን በንጉሥነት ሲያስተዳድር ከቆየ በኋላ በዋሻ ይኖሩ የነበሩት አባ ጰንጠሌዎን ዘጾማዕት ‹‹ይስሐቅ ሆይ፣ ሙታኖቻቸውን ይቀብሩ ዘንድ ሙታንን ተዋቸውና የማያልፈዉን የክርስቶስን መንግሥት ትሻ ዘንድ ወደ እኔ ና›› ብለው መልእክት ላኩበት፡፡ መልእክቱ እንደ ደረሰውም መንግሥቱን ትቶ በሌሊት ወደ አባ ጰንጠሌዎን ሲሔድ ቅዱስ ገብርኤል ተገልጾ በብርሃናውያን ክንፎቹ ተሸክሞ ዐሥር ወር የሚወስደዉን መንገድ በሦስት ሰዓታት አስጉዞ ከአባ ጰንጠሌዎን በዓት አደረሰው፡፡ አባ ይስሐቅ (አባ ገሪማ) በአባ ጰንጠሌዎን እጅ ከመነኰሱ በኋላ በጾም፣ በጸሎትና በስግደት ተጠምደው ቆዳቸው ከዐፅማቸው እስኪጣበቅ ድረስ ተጋድሎ ሲፈጸሙ ቆዩ፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ መደራ ሔደው በእግዚአብሔር ኃይል ድንቆችንና ተአምራትን እየያደረጉ፣ በሽተኞችን እየፈወሱ፣ አጋንንትን እያስወጡ ብዙ ዓመታት ኖሩ፡፡ ካደረጓቸው ተአምራት መካከልም በጠዋት ሥንዴ ዘርተው፣ በሠርክ ሰብስበው መሥዋዕት ካሳረጉ በኋላ በማግሥቱ ከግራር ዛፍ ላይ በሬዎችን አውጥተው ሥንዴዉን አበራይተው ሰባ ሰባት የእንቅብ መሥፈሪያ መሰብሰባቸው አንደኛው ሲኾን፤ በዓለት ላይ የተከሏት ወይን ወዲያው በቅላ፣ አብባ ፍሬ እንድታፈራ ማድረጋቸውና በወይኑም መሥዋዕት ማሳረጋቸው ደግሞ ሌላኛው ተአምር ነው፡፡ አባ ገሪማ መጽሐፍ እየጻፉ ሳሉ ፀሐይ ሊጠልቅ በተቃረበ ጊዜ ጸሎት አድርሰው ጽሕፈታቸዉን እስኪፈጽሙ ድረስ እንደ ኢያሱ ፀሐይን በቦታው እንዲቆም ማድረጋቸውም በመጽሐፈ ስንክሳር ተመዝግቧል፡፡ ከእጃቸው የወደቀው ብርዕ ወዲያው በቅሎ፣ አቈጥቍጦ እንደ አደገ፤ ምራቃቸዉን ትፍ ያሉበት ሥፍራም እስከ ዛሬ ድረስ ሕሙማንን እንደሚፈውስ መጸሐፈ ስንክሳር ይናገራል፡፡ በአንዲት ዕለትም መቅኑናቸውን ተቀብለው ከመነኮሳት ጋር ሲሔዱ መንገድ ላይ ቤተ ክርስቲያን አግኝተው ሲጸልዩ ካህናቱ ቅዳሴ እንዲያሟሉላቸው ጠየቋቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ሌሎቹ ምግብ በልተው ነበርና ‹‹አንችልም›› ሲሉ አባ ይስሐቅ ምግብ አልተመገቡም ነበርና መቅኑናቸዉን አስቀምጠው ቅዳሴውን አሟሉ፡፡ ባልንጀሮቻቸው ግን በልተው የቀደሱ መስሏቸው ወደ አባ ጰንጠሌዎን መጥተው ‹‹ቀሲስ ይስሐቅ ከበላ በኋላ ቀደሰ›› ብለው ከሰሷቸው፡፡ አባ ጰንጠሌዎንም አባ ይስሐቅ ሲመለሱ ‹‹የምጠይቅህ ምሥጢር ስላለኝ ሰዎችን ከአጠገብህ ገለል አድርጋቸው›› ሲሏቸው አባ ይስሐቅም ‹‹ሰዎች ብቻ ሳይኾኑ ዕንጨቶችና ድንጋዮችም ገለል ይበሉ›› ብለው መለሱላቸው፡፡ ወዲያዉኑም ዕንጨቶችና ድንጋዮች አንድ ምዕራፍ ያህል ከቦታቸው ሸሹ፡፡ በዚህ ጊዜ አባ ጰንጠሌዎን ‹‹ኦ ወልድየ ይስሐቅ ገረምከኒ፤ ልጄ ይስሐቅ ሆይ! ገረምኸኝ›› እያሉ አደነቋቸው፡፡ አባ ገሪማን ሳያዉቁ የከሰሷቸው መነኮሳትም ይቅርታ ጠይቀዋቸዋል፡፡ አባ ገሪማ ተብለው መጠራት የጀመሩትም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡ ይህንን መሠረት በማድረግ ‹‹ገሪማ ገረምከኒ አስኬማከኒ አልባቲ ሙስና፤ አባ ገሪማ አስገረምኸኝ፡፡ ለምንኵስናህም እንከን የለባትም›› በማለት ቅዱስ ያሬድ በመዝሙሩ አመስግኗቸዋል፡፡ ከዚያም በትግራይ ክፍለ ሀገር ልዩ ስሙ መደራ ከሚባል ቦታ ገብተው በዓት ሠርተው ለ፳፫ ዓመታት በትኅርምት ኖረው መልካም ተጋድሏቸውንና የቀና አካሔዳቸዉን በፈጸሙ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰኔ ፲፯ ቀን ተገልጦ ስማቸውን የሚጠሩትን፣ መታሰቢያቸዉን የሚያደርጉትን፣ ገድላቸዉን የሚጽፉ፣ የሚያነቡና የሚተረጕሙትን፣ ቤተ ክርስቲያን የሚያንጹትንና የሚያገለግሉትን ስማቸውን በሕይወት መጽሐፍ እንደሚጽፍላቸው ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡ አባ ገሪማም ይህንን ታላቅ ሀብት የሰጣቸዉን እግዚአብሔርን አመስግነው ከተደሰቱ በኋላ በብርሃን ሠረገላ ተነጥቀው ብሔረ ሕያዋን ገብተዋል፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን በተለይ በገዳማቸው በመደራ አባ ገሪማ የተሠወሩበት ሰኔ ፲፯ ቀን በየዓመቱ በድምቀት ይከበራል፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይኹን፡፡ እኛንም በጻድቁ ጸሎት ይማረን፤ በረከታቸዉም ከእኛ ጋር ትኑር፤ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ ሰአል ለነ አባ ገሪማ፤ ቅድመ መንበሩ ለንጉሠ ራማ፤ ሰአል ለነ አባ፤ ጸሎትከ ወትረ ይዕቀበነ:: ምንጭ፡- መጽሐፈ ስንክሳር፣ ሰኔ ፲፯ ቀን፡፡ መዝገበ ታሪክ ክፍል ፪፣ መ/ር ኅሩይ ኤርምያስ፣ ገጽ ፺፱-፻፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን ድኅረ ገጽ ኦ አበው ወእማት አኃው ወአኃት ኢትርስዑነ በጸሎተክሙ ለትምህርተ ቤትነ ቀ.ደ.ሰ.መድኀኔዓለም ወደ.ት.ቅ.ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት፡፡

ገሪማ ገረምከኒ (ገሪማ ሆይ ገረምከኝ) ፎቶዎቹ፤ ፠በዓለም በዕድሜ ብዛት ረጅም ዕድሜን ያስቈጠረውና 1500 ዓመታትን ያስቈጠረውን የ‹‹አባ ገሪማ ወንጌል››፤ መደራ፤ ዓድዋ አጠገብ የሚገኝ፡፡ ፠ከደረቅ ዓለት ላይ እንደ እንባ የሚፈልቀው የአቡነ ገሪማ አስደናቂና ደዋሽ ጠበል፡፡ (ክብረ በዓላቸው በዓድዋ በሚገኘው ገዳማቸው መደራ፣ በጎንደር ተክለሃይማኖት፣ በአዲስ አበባ ካራአሎ መድኀኔዓለም ወአቡነ ገሪማ ገዳም በደማቅ ሁኔታ ይከበራል፡፡)

ሃሌ ሃሌ ሉያ ለቤተ ክርስቲያን፤ ሐነፃ ላሊበላ ለቤተ ክርስቲያን፡፡ /ወረብ ዘሸዋ፤ በየካ ሚካኤል በሰኔ የሚወረብ የቤቱ የሸዋ ወረብ ቀለም/፤ ዛሬ የሐናፄ መቅዱስ ቅዱስ ላሊበላ(ላልይበላል) ክብረ በዓሉ ነው፡፡