fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

رفتن به کانال در Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

کانال Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 15 949 مشترک است و جایگاه 5 311 را در دسته دین و مذهبی و رتبه 2 239 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 15 949 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 22 اکتبر, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 412 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 1 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 25.65% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 10.94% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 4 091 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 1 745 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 28 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 23 اکتبر, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته دین و مذهبی تبدیل کرده‌اند.

15 949
مشترکین
+124 ساعت
+1607 روز
+41230 روز
آرشیو پست ها
#ሥርዓተ_ማኀሌት ዘወርኃ ጽጌ ‹‹ዘላይ ወዘታች››ቤት ፫ኛ ዙር ዓመት ፤፪ኛ ሳምንት ጥቅምት፲ በዓለ ፬ቱ እንሰሳ ዘውእቶሙ #ኪሩቤል ፤#ወኪሮስ ገዳማዊ:: #like እና #share ...
+4
#ሥርዓተ_ማኀሌት ዘወርኃ ጽጌ ‹‹ዘላይ ወዘታች››ቤት ፫ኛ ዙር ዓመት ፤፪ኛ ሳምንት ጥቅምት፲ በዓለ ፬ቱ እንሰሳ ዘውእቶሙ #ኪሩቤል ፤#ወኪሮስ ገዳማዊ:: #like እና #share ...

#ሥርዓተ_ማኀሌት ዘወርኃ ጽጌ ‹‹ዘላይ ወዘታች››ቤት ፫ኛ ዙር ዓመት ፤፪ኛ ሳምንት ጥቅምት፲ በዓለ ፬ቱ እንሰሳ ዘውእቶሙ #ኪሩቤል ፤#ወኪሮስ ገዳማዊ:: #like እና #share ... መሉውን ሥርዓተ ማኀሌት የፌስቡክ 👇ገጻችን ላይ ያግኙ 👉 https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool

#እንኳን #ለአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ_በዓል_በሰላምና_በጤና_አደረሳችሁ፡፡ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (አቦ፥ አቡዬ)፤ * እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ብርሃነ ዓለም የኾኑ፤ * እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ክብርን የተሞሉ፤ * ኰከበ ገዳም፥ መናኔ ዓለም፥ ምድራዊ መልአክ፤ * ስማቸውን ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ያወጣላቸው፤ * በአክናፈ መባርቅት ተጭነው የሚጓዙ፤ * 60 አናብስትና 60አናብርት ይታዘዙላቸው የነበሩ፤ የእግራቸው ትቢያ ለአራዊቶቹ ምግብ የኾነላቸው፤ * ለብዙ አእላፍ ቅዱሳን ወላዴ የኾኑና በረከትን የሰጡ ታላቅ አባት (ለአብነትም፤ ለቅዱስ #ላሊበላ፥ ለአቡነ #ሳሙኤል ዘዋልድባ፥ ለአባ #አንበስ ዘደብረ ሐዘሎ፥ ለአባ ብንያም ዘግብፅ) ፠፠፠ #ምድረ_ከብድ_፤ /ዝ_ምድር_ክቡድ_ውእቱ_/ ፤ #ዝቋላ (#ዝ_ቆላ)  ምድረ ከብድ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ለመጀመሪያ ጊዜ ያረፉባት ቦታ ናት፤ ቀጥሎ ወደ ደብር ቅዱስ #ዝቋላ (#ዝ_ቆላ) ለጸሎት ሂደው ለሃገራችን ኢትዮጵያና ለዓለማችን ምሕረትና በረከትን ከአምላካችን ለ100 ዓመታት በባሕር ውስጥ ሆነው ለምነዋል፤ *ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል፤ ቊራም በሰይጣን ተመስሎ መጥቶ ዓይናቸውም ቢያጠፋውም ከ7 ሱባዔያት በኋላ ሊቀ መላእክት ሚካኤልና ገብርኤል ዓይናቸውን መልሰውላቸዋል፡፡ *ወደ ዝቋላ በመመለስም አጋንንትም ከምድረ ዝቋላ አጥፍተዋል፤ ፠ እንደገና ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው በነበሩበት ጊዜ ታላላቆቹና በአንበሳ ዘባን ላይ የሚሄዱት #አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ ፣ #አባ_አንበስ_ዘደብረ_ሐዘሎ_አፋር)፣ #አባ_ብንያም_ዘግብፅ ከአባታችን ቡራኬ ለመቀበል መጡ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተሰውረው ነበርና፤ የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ አናብስት የ3ቱን አባቶች አናብስት በሉባቸው፤ በ7ኛው ቀን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተገልጠው የኾነውን ነገር በማየት የተበሉትን አናብስት እንዲመልሱ የራሳቸውን አናብስት አዘዟቸው መልሰውም እንደነበሩ በተዓምራት አስነስተው ሰጧቸው፤ በደመና ጠቅሰው ቅዱስ ፋኑኤል 3ት ሰማያዊ ኅብስትና 3ት ጽዋዕ ይዞ ለእንግዶቻቸው ይዘው ሠረገላ በሚባለው ዋሻ አመጡላቸውና ሰጥተው ሸኟቸው፤ እነዚህን ቅዱሳን በሸኙ በ7ኛው ቀን ወደ ተለያዩ ሃገራት ሄደው አስተምረዋል፡፡ ፠ እድሜያቸው ረዥም እንደመሆኑ፤ ቅዱሱ ንጉሥ አፄ ላሊበላን ጨምሮ ሌሎችም ቅዱሳን ወደ ርሳቸው እየመጡ በረከትን ተቀብለዋል፡፡ ፠#በግብፅ_300_ዓመታት_፥ #በኢትዮጵያ_ምድር_ላይ_262_ዓመታት (በዋነኛነት #በምድረ_ከብድና_በዝቋላ_ ቢኖሩም ሌሎችም የመሠረቷቸውና የኖሩባቸው ገዳማት አሉ፤ ለአብነትም ደቡብ ወሎ የሚገኘውን #ገዘዛ_አቦን_ መጥቀስ ይቻላል) ፠ በድምሩ 562 ዓመታት ከኖሩ በኋላ በንጉሥ ሕዝብናኝ(እንድርያስ) ዘመነ መንግሥት፤ መጋቢት 5 ቀን ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ብዙ ቃል ኪዳንን ጌታችን ሰጣቸው፥ 12 አክሊላትንም አቀዳጃቸው፤ የነበሩባት ምድረ ከብድ ገዳም ግን ራደች፥ ተንቀጠቀጠች፥ በብርሃንም ተጥለቀለች፤ ዝቅ እያለችም መንሸራተት ጀመረች፤ ጌታችንም አንቺ መሬት ሆይ ጽኚ ይህንን ኹሉ ስለቻልሽ ምድር ክቡድ /ኋላ ምድረ ከብድ/ ተብለሽ ተጠሪ አላት፤ የጻድቁም ነፍስ ከሥጋቸው ከሌሊቱ 6 ሰዓት ተለየች፡፡ ፠ ይህችውም ምድረ ከብድ ጻድቁ የኖሩባትና የቀደሱባት፥ የመሠረቷትና ያነፅዋት፣ ሠራዊተ መላአክት የከተሙባት፣ ታላላቅ አበው መጥተው በረከት ከአባታችን የተቀበሉባት፣ አርምሞና ጸጥታ የማይለያት፤ አጸዷና ቅጥሯ ልቡናን የሚመስጥ፤ ከአ.አ 125 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ናት፡፡ አምላከ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት፥ በረከትን ይክፈለን፡፡ (ሥርዐተ ማኅሌቱን የኢንተርኔት አቅርቦት በሌለባቸው ቦታዎች አድርሱልን፤ በተለይም ወደ ምድረ ከብድ፥ ዝቋላ፥ ገዛዛ አቦና ሌሎች የአባታችን ክብረ በዓል በሚከበርባቸው አድባራትና ገዳማት ያላችሁ አድርሱልን፡፡) /የቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/ ፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool/ ፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem ፠ በዩቲዩብ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ ፍኖተ ሕይወት https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

#_ለሰንበት ት/ት ቤታችን ስትደክሙ ለነበራችሁ ሁሉ #_እንኳን_ደስ_አላችሁ!!! #_ብጹዕ_ወቅዱስ_አቡነ_ማትያስ_ፓትርያሪክ_የቅዱስነቶ_በረከት_በእኛ_በልጆችዎ_ላይ_ይደርብን!! #ሰንበት ት/ት ቤቱ ለብጽዕ ወቅዱስ ፓትሪያሪክ ልዩ ጽ/ቤት ባቀረበው ይግባኝ መሰረት ቅዱስነታቸው አሁንም በረከታቸው ይደርብንና ልጆቼ ተበድለዋል፣ እውነታው ሊወጣላቸው ይገባል፣ ልጆቼ በምንም ጉዳይ ሊያዝኑ አይገባም ብለው...........መሉውን በፌስቡክ ገጻችን ያንብቡ https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool/

#ጥቅምት_3_የቤተ_ክርስቲያን_ማኅቶት ፥ #አፈ_በረከት_ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ፤#_ፅንሰቱ_ነው፡፡ #SHARE ፠ይህ አባት ከ40 በላይ መጻሕፍትን የደረሰና ብዙ መጻሕፍትን እያጻፈ ለመላው ገዳማት ያዳረሰ፤ ጸሓፊ፥ ቅዱስና ጻድቅ፥ ፈላስፋና ደራሲ፥ መናኝና ባሕታዊ፥ ሊቅና ተመራማሪ፥ ገጣሚና በለቅኔ፥ የመጻሕፍት ተርጓሚና የዘመን አቈጣጠር (የአቡሻህር) ሊቅና ተንታኝ፥ አርክቴክትና መሐንዲስ ነው፤ በዚህም ምክንያት በተለያዩ ስያሜዎች ይጠራል፤ ፠ዳግማዊ ቄርሎስ (ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ)፥ ፠ ዐምደ ሃይማኖት ፠ ዳግማይ ቅዱስ ያሬድ፤ ፠ የወርቃማ ዘመን ወርቃማ ደራሲ፤ ፠ የቤተ ክርስቲያን ማኅቶት፥ ፠ አፈ በረከት ፠ የከሃድያን ዘላፊ፥ የቅዱሳን ፀሐይ …….ተብሏል፡፡ እንዲሁም፤ + እንደ ቅዱስ ላሊበላ ቤተ መቅደሱን ራሱ ፈልፍሎ ያነፀ #የሕንፃ_ባለሙያ ነው። + ከጓደኛው ከአባ ጽጌ ድንግል ጋር ሁኖ የወለቃ ወንዝ ድልድይን የሠራ መሐንዲስ፤ እስከ ዛሬም ድረስ ድልድዩን ሕዝቡ ይጠቀምበታል፡፡ + እንደ ቅዱስ አትናቴዎስ መናፍቃንን የረታ #ብርቱ_የቤተ_ክርስቲያን_ጠበቃ ነው። + እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ በርካታ መጻሕፍትን የጻፈ (የደረሰ) #ደራሲ ነው፡፡ + እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ወንጌልን ዙሮ ያስተማረ #ሐዋርያ ነው፡፡ + እንደ ፍጹማን መነኰሳት በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስኖ በተጋድሎ ጸንቶ የኖረ #መናኝ_ጻድቅ ነው፡፡ + እንደ ቅዱስ ያሬድ በሰማያዊ ዜማ አምላኩን ያመሰገነ #የዜማ_ሊቅ #የዜማ_ደራሲ ነው። + እንደ ዕዝራ ሱቱኤል ሰማያዊ መጠጥ ጠጥቶ ምስጢራት የተገለጹለት #ድንቅ_ተመራማሪ #የጥበብ_አባት ነው:: (ለምሳሌ፤ በሰዓታት ድርሰቱ ውስጥ ዑደተ ማይን፣ በሌሎች ድርሰቶቹም ስለ አእባንና እጽዋት ቀድሞ ነግሮናል፣ እንዲሁም የውኃ ማቆር ቴክኖሎጂን በዘመኑ ተግባራዊ አድርጓል። + እንደ ሰማዕታት ከነገሥታቱ ስለ ሃይማኖት ብዙ ጸዋትወ መከራ የተቀበለ #ሰማዕት ነው፡፡ + አቡነ አረጋዊ ደብረ ዳሞን፤ አቡነ ኢየሱስ ሞ ሐይቅ እስጢፋኖስን፤ አቡነ ተከለ ሃይማኖት ደብረ ሊባኖስን፤ አቡነ ሳሙኤል ዋልድባን፤ አቡነ ዐምደ ሥላሴ ማኅበረ ሥላሴ ገዳምን እንደመሠረቱና የተመሠረተውንም እንዳስፋፉ፤ እርሱም ደብረ ባሕርይ ጋሥጫን የመሠረተ ቅዱስ ነው፡፡ + በሰዓታት ድርሰቱ ቤተክርስቲያን አምላኳን ፳፬ ሰዓት ያለማቋረጥ እንድታመሰግን ያስቻለ ምድራዊ #መልአክ ነው፡፡ + "አኀዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋከ" እስከሚል ድረስ ጸጋ የበዛለት አባት ነውና ስንቱን እንናገረው? አይቻለንምና!!!፡፡ (በፎቶ ላይ የምታዩት ገዳም፤ በዓለም ብቸኛው የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ገዳም የኾነው ደብረ ባሕርይ ነው፡፡ የቦታው አቀማመጥ እጅግ በጣም ማራኪና እንደ ደብረ ዳሞ ሲሆን የሚወጣው በመሰላል ነው፡፡)፤ ገዳሙ የሚገኘው በደቡብ ወሎ በቦረና አውራጃ ነው፡፡ (አስተጋባኢ /ይህንን ጽሑፍ ከአባቶች በመጠየቅ ፥ መጻሕፍትን በማንበብ ፥ ከታላቁ ገዳም ደብረ ባሕርይ ጋሥጫ ድረስ ሂዶ ያዘጋጀው የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ሰሌዳ መጽሔት ዝግጅት ክፍል ነው/፡፡) አምላከ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የሀበነ በረከተ ወረድኤተ፡፡

ወረብ፤_ወበእንተዝ_ማርያም_ወረብ_ዘደብረ_ሰላም_የቤቱ_ቀለም_፣_አጋፋሪ_ይሁኔ_ፈቃዱ.mp32.89 MB

ወረብ፤_ሠርፀ_መንግሥት፣_ከቅኝት_እስከ_ቸብቸቦ፤_ዘደብረ_ሰላም_የቤቱ_ቀለም_፣_መሪጌታ_ሙሉጌታ_ተክለያሬድ.m4a8.91 KB

ወረብ፤_ሚ_ቡርክት፣_ቅኝት_፤_ዘደብረ_ሰላም_የቤቱ_ቀለም_፣_አጋፋሪ_ይሁኔ_ፈቃዱ.mp32.17 MB

#የማኀሌተ_ጽጌ የሦስተኛ ዙር አመት፤ አንደኛ ሳምነት #ወረቦች ወረብ፤ #_ሚ_ቡርክት ቅኝት ፣ ወረብ ዘደብረ_ሰላም ፤ የቤቱ_በቀለም ፣_በአጋፋሪ_ይሁኔ_ፈቃዱ ወረብ፤ #_ወበእንተዝ_ማርያም፣ ወረብ_ ዘደብረ_ሰላም ፤ የቤቱ_ቀለም ፣_በአጋፋሪ_ይሁኔ_ፈቃዱ ወረብ፤ #ሠርፀ_መንግሥት ፤ወረብ ዘደብረ ሰላም ፤ የቤቱ_በቀለም ፤በመሪጌታ ሙሉጌታ ተክለያሬድ

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት - آمار و تحلیل کانال تلگرام @finotehiwott