fa
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

رفتن به کانال در Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

کانال Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 15 369 مشترک است و جایگاه 5 619 را در دسته دین و مذهبی و رتبه 2 193 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 15 369 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 24 ژوئن, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر -18 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 1 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 23.10% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 8.16% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 3 551 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 1 254 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 22 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 25 ژوئن, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته دین و مذهبی تبدیل کرده‌اند.

15 369
مشترکین
+124 ساعت
+477 روز
-1830 روز
آرشیو پست ها
በስመ አብ፤ ወወልድ፤ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!! ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከጥር ፳፱ እስከ የካቲት ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለ ፫ ተከታታይ ቀናት በመላው ዓለም የታወጀው የነነዌ ፆም እና ምሕላ መጠናቀቅን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ:: ++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++ በትንቢተ ዮናስ በሰፊው እንደተጠቀሰው የነነዌ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት ላይ ስለአመጹ እና ግብራቸውም በእግዚአብሔር ፊት አጸያፊ በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ዮናስን “ተነስተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ ክፋታቸውም ወደ ፊቴ ወጥቷልና በእርስዋ ላይ ስበክ” በማለት አዘዘው፡፡ ትንቢተ ዮናስ ምዕ ፩ ቁጥር ፪ ዮናስም ድምፁን ከፍ አድርጎ ለነነዌ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ሲሰብክ “የነነዌ ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ለጾም አዋጅ ነገሩ፤ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ፡፡ ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እርሱም ከዙፋኑ ተነስቶ መጎናጸፊያውን አወለቀ ማቅም ለበሰ፤ በአመድም ላይ ተቀመጠ፡፡ አዋጅም አስነገረ፤ በነነዌ ውስጥ የንጉሡንና የመኳንንቱን ትእዛዝ አሳወጀ፤ እንዲህም አለ ሰዎችና እንስሶች፤ ላሞችና በጎች አንዳችን አይቅመሱ፣ አይሰማሩ፣ ውኃንም አይጠጡ፤ ሰዎችና እንስሶችም በማቅ ይከደኑ፣ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ጩኸት ይጩኹ፤ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ፡፡ እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይጸጸት እንደሆነ ማን ያውቃል፡፡ እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውንም አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም” ትንቢተ ዮናስ ፫፡ ፭-፲ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ይህን የነነዌ ሰዎች ፆም መነሻ በማድረግ የነነዌ ሰዎችን በምሕረቱ የጎበኘ አምላክ እኛንም በምሕረቱ ይቅር ይለን ዘንድ በየዓመቱ በአዋጅ በመፆም አምላካችንን ስንማጸንበት ኖረናል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባዔ በጥር ፳፮ ቀን ፳፻፲፭ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በወሰነው መሠረት የካቲት ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም የተጠናቀቀው የነነዌ ፆምና ምሕላ ልዩ በሆነ በመንፈሳዊ የንስሐ ጸሎት በሰላም ተጠናቋል፡፡ በምሕላውም ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ጀምሮ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፤ ካህናት፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ አገልጋዮች እና ምእመናን እንደነነዌ ሰዎች ጥቁር ለብሰን ጠዋትና ማታ በጸሎት ፤ በምሕላ፤ ቀን በቅዳሴ እንዲሁም በሰባቱ የጸሎት ጊዜያት ፈጣሪያችንን ስንለምን እና ስንማጸን የቆየንበት ምክንያት በቤተክርስቲያናችን ላይ የመጣው ፈተና እጅግ በጣም ከባድ በመሆኑ ነው፡፡ በዚህ የጾምና የንስሐ ወቅት ምእመናን ልጆቻችን የአባቶቻችሁን ጥሪ ሰምታችሁ፤ የሹመኞችን ማዋክብና እስር ሳትፈሩ ጥቁር ለብሳችሁ ጠዋትና ማታ በጾምና በምሕላ፣ ቀን በቅዳሴ በቤተክርስቲያን ቅጥር እየተገኛችሁ ለአምላካችን ያቀረባችሁትን ጸሎት እና ምሕላ እግዚአብሔር ሰምቶ ለችግራችን መፍትሄ፣ ለሀገራችን ሰላምን እንደሚሰጠን እምነታችን ጽኑ ነው፡፡ እናንተም ምእመናን የቤተ ክርስቲያንን ጥሪ ሰምታችሁ ለሃይማኖታችሁ፣ ለሀገራችሁ አንድነትና ሰላም ያላችሁን ጥልቅ ፍቅር ስለገለፃችሁም ያገኘነው መንፈሳዊ ብርታት ሳንገልፅላችሁ አናልፍም፡፡ በእግዚአብሔር ቸርነት፣ በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም እና በቅዱሳን አማላጅነት፣ በመላእክት ተራዳኢነት በፍፁም ፍቅርና አንድነት የያዝነውን ጸሎት እና ምሕላ አጠናቀናል፡፡ ችግራችንን ለአምላካችን በለቅሶ እና በጩኸት ነግረናል፡፡ ከዚህ በኋላ መከራው ቢጸና፣ የመከራው ጊዜ እንኳን ቢረዝም እግዚአብሔር በመከራ ውስጥ ሊያፀናን እና ሊያበረታታን አስቦ በመሆኑ በፍፁም አንናወጽም፡፡ ከእነኚህ መከራዎች በኃላም ታሪክን ጽፈን ሃይማኖታችንን ጠብቀን እና አስጠብቀን በመንፈሳዊ ጽናት እና ተጋድሎ እንሻገራለን፡፡ ጥቃቱ የቤተ ክርስቲያንን እውነት በካዱና በእውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን መካከል ነው፡፡ ይህም የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሃይማኖት፤ ቀኖና እና አስተዳደራዊ ሕግጋትን ጥሰው ሕገወጥ የጳጳሳት ሢመት በመደረጉ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ቅዱስ ሲኖዶስ በሕገ ቤተ ክርስቲያንና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት በጥር ፲፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ይህን ጥሰት የፈፀሙትን ግለሰቦች አውግዛ ከቤተ ክርስቲያን ኅብረት የለየቻቸው ቢሆንም ጉዳዩ ከግለሰቦቹ በላይ በመንግሥት ስልጣን ላይ ባሉና ጽንፈኛ በሆኑ ፖለቲከኞች እንዲሁም የሌላ እምነት ተከታዮች ጭምር የሚደገፍ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያንን ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈላት ይገኛል፡፡ እየተፈጸመ ያለው ድርጊት በሰማያዊ መንፈሳዊ ዓለምና በምድራዊ ሥጋዊ ዓለም መካከል ስለሆነ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥም የቤተ ክርስቲያን ክብርና ተቋማዊ ልዕልና ተደፍሯል፡፡ የቤተክርስቲያን ቅጥሮች መሣሪያ በያዙ አካላትና በመንግሥት የጸጥታ መዋቅር በኃይልና በጉልበት ተወሯል፡፡ ሊቃነ ጳጳሳት አባቶች ለብዙ ዓመታት ከኖሩበት አህጉረ ስብከት ያለአንዳች የሕግ መሠረት በጸጥታ መዋቅሮች ተባረዋል፡፡ በነጻነት የመንቀሳቀስ መብቶቻቸው ተገድቦም በግዞት ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ተደርገዋል፡፡ ወደ አህጉረ ስብከታቸውም ተመልሰው መግባት እንዳይችሉ እቀባ ተደርጎባቸዋል፡፡ ካህናት አባቶች እና ምእመናንም ያለአንዳች የሕግ መሠረት በየእስር ቤቱ ያለበቂ ምክንያት በሕገወጥ መንገድ ታጉረዋል፡፡ በጸጥታ ኃይል ከመጠን በላይ ከመደብደባቸው የተነሳ የሞት፣ የከባድ እና ቀላል አካል ጉዳት እንዲደርስባቸው ምክንያት ሆኗል፡፡ በአጠቃላይም በመንግሥት ኃይሎች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተፈፅሞባቸዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ይህ ሁሉ በደል ቢፈጸምባትም ናዛዜ ሕዙናን የሆነው አምላካችን ለቤተ ክርስቲያናችን እና ለሀገራችን መፍትሔ እንዲያመጣልን፣ መንግሥትም ወደ ልቡ ተመልሶ ቤተክርስቲያንን እንዲያከብርና እንዲጠብቅ በሚል ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ይህን ጾም የነነዌ ሰዎች እንዳደረጉት ጥቁር ለብሰን በፍፁም ኃዘን ወደ አምላካችን እንድንጮህ ቅዱስ ሲኖዶስ ትእዛዝ ባስተላለፈበት ማግስት በሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሕገወጡን ቡድን በኃይል ለማስገባት በመንግሥት የጸጥታ መዋቅሮች በተወሰደ አሰቃቂ እርምጃ እስከ አሁን በደረሰን መረጃ ቁጥራቸው ከ፴ በላይ የሚሆኑ ካህናትን እና አገልጋዮችን ጨምሮ የቤተ ክርስቲያናችን ልጆች ቅጥሯ አይደፈርም፣ ቤተክርስቲያን በተወገዙ ግለሰቦች አትረክስም በሚል ለሃይማኖታቸው ሰማእትነትን ተቀብለዋል፡፡ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ልጆቿም በደረሰባቸው ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ምክንያት በሕክምና ላይ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ ሁሉ በደል በኋላም እስከ አሁን ድረስ የሞቱትን በአግባቡ መቅበርና የተጎዱትን በበቂ ሁኔታ ማሳከም ሳንችል ቀርተናል፡፡ እነዚህ ሰማዕታት በዚህ ኃጢያት በበዛበት ዘመን ለቤተክርስቲያን እስከሞት ድረስ በመታመን ለቤተ ክርስቲያንና ለምእመናን የጽናት ተምሳሌት በመሆናቸው ቤተክርስቲያን ስትዘክራቸው ትኖራለች፡፡ እንዲሁም ቤተ ክርስቲያን በልጆቿ ላይ እየደረሰ ባለው ሞት፤ እርዛት፤ እስራት እና መልከ ብዙ በሆነው መከራ ብታዝንም ለክርስትና እውነተኛነት ምስክሮች የሆኑ አዳዲስ ቅዱሳን ሰማእታትን በማግኘቷም እጅግ ደስ ትሰኛለች፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በቀጥታ ሥርጭት በመላው ዓለም ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን መግለጫ ይሰጣል። መግለጫውን በጥራት በፌስ ቡክ እና ዩቲዮብ ገጻችን ይከታተሉ። EOTC TV ++++++++++++++++++++++++++++++++++++ https://youtu.be/Wqgq1KebrOo

መረጃ! አየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ካቴድራል ደወሏን አሰምታለች። ሕገ ወጡ ቡድን በመንግሥት የጸጥታ ኃይል ታጅቦ እየመጣ ነው መባሉን ተከትሎ ነው ቤተ ክርስቲያኗ ጥሪዋን ያሰማች
መረጃ! አየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ካቴድራል ደወሏን አሰምታለች። ሕገ ወጡ ቡድን በመንግሥት የጸጥታ ኃይል ታጅቦ እየመጣ ነው መባሉን ተከትሎ ነው ቤተ ክርስቲያኗ ጥሪዋን ያሰማችው። ይህንን ጥሪ በመስማት በርካታ ኦርቶዶክሳውያን ወደ ካቴድራሉ እየጎረፉ ይገኛሉ። በሕገ ወጡ ሹመት ከተሳተፉት ሰዎች መካከል የቀድሞ የካቴድራሏ አስተዳዳሪ ይገኙበታል።

ጸቡ ከክርስቶስ ጋር ነው ። አንድ ሲኖዶስ ፣አንድ ፓትርያርክ የምንልበት ምክንያት ይሄ ነው ። ከክርስቶስ የተገኘውና በቅዱሳን ሐዋርያት በኩል ወደ እኛ የመጣው ያልተቋረጠው የእስከንድርያው መንበረ ማርቆስ ስልጣነ ክህነት ቅብብሎሽ (apostolic succession)ይሄ ነው ። #share #share በማድረግ ሕዝቡን አስተምሩ ኢየሱስ ክርስቶስ 1. ማርቆስ 2. አንያኖስ 3. ሜልያስ 4. ክርዳኑ 5. አምብርዮስ 6. ዮስጦስ 7. አውማንዮስ 8. መርክያኖስ 9. ክላውያኖስ 10. አክርጵያኖስ 11. ዮልዮስ 12. ድሜጥሮስ 13. ያሮክላ (ሔራክልስ) 14. ዲዮናስዮስ 15. መክሲሞስ 16. ቴዎናስ 17. ጴጥሮስ (ተፍጻሜተ ሰማዕት) 18. አኪላስ 19. እለእስክንድሮስ 20. አትናቴዎስ 21. ጴጥሮስ 2ኛ 22. ጢሞቴዎስ 23. ቴዎፍሎስ 24. ቄርሎስ 25. ዲዮስቆሮስ 26. ጢሞቴዎስ 2ኛ 27. ጴጥሮስ 3ኛ 28. አትናቴዎስ 2ኛ 29. ዮሐንስ 30. ዮሐንስ 2ኛ 31. ዲዮስቆሮስ 2ኛ 32. ጢሞቴዎስ 3ኛ 33. ቴዎዶስዮስ (ቴውዳስስ) 34. ጴጥሮስ 4ኛ 35. ድምያኖስ 36. አንስጣስዮስ 37. አንድራኒቆስ 38. ብንያሚን 39. ያቃቱ (አጋቶን) 40. ዮሐንስ 3ኛ 41. ይስሐቅ 42. ስምዖን 43. እለእስክንድሮስ 2ኛ 44. ቆዝሞስ 45. ቴዎድሮስ 46. ካኤል (ሚካኤል) 47. ሚናስ 48. ዮሐንስ 4ኛ 49. ማርቆስ 2ኛ 50. ያዕቆብ 1ኛ 51. ስምዖን 2ኛ 52. ዮሳብ 1ኛ (ዮሴፍ) 53. ካኤል (ሚካኤል) 2ኛ 54. ቆዝሞስ 2ኛ 55. ስንትዮ 1ኛ 56. ሚካኤል 1ኛ 57. ገብርኤል 1ኛ 58. ቆዝሞስ 3ኛ 59. መቃርዮስ 1ኛ 60. ታውፋኔዎስ 61. ሚናስ 2ኛ 62. አብርሃም 63. ፊላታዎስ 64. ዘካርያስ 65. ስንትዩ 2ኛ 66. ክርስቶዶሉ (ገብረ ክርስቶስ) 67. ቄርሎስ 2ኛ (ጌርሎስ) 68. ሚካኤል 2ኛ 69. መቃርዮስ 2ኛ (መቃርስ) 70. ገብርኤል 2ኛ 71. ሚካኤል 3ኛ 72. ዮሐንስ 5ኛ 73. ማርቆስ 3ኛ 74. ዮሐንስ 6ኛ 75. ቄርሎስ 3ኛ 76. አትናቴዎስ 3ኛ 77. ገብርኤል 3ኛ 78. ዮሐንስ 7ኛ 79. ታውዳስዮስ 2ኛ 80. ዮሐንስ 8ኛ 81. ዮሐንስ 9ኛ 82. ብንያሚን 2ኛ 83. ጴጥሮስ 5ኛ 84. ማርቆስ 4ኛ 85. ዮሐንስ 86. ገብርኤል 4ኛ 87. ማቴዎስ 1ኛ 88. ዮሐንስ 5ኛ 89. ዮሐንስ 11ኛ 90. ማቴዎስ 2ኛ 91. ገብርኤል 6ኛ 92. ሚካኤል 4ኛ 93. ዮሐንስ 12ኛ 94. ዮሐንስ 13ኛ 95. ገብርኤል 7ኛ 96. ዮሐንስ 14ኛ 97. ገብርኤል 8ኛ 98. ማርቆስ 5ኛ 99. ዮሐንስ 15ኛ 100. ማቴዎስ 3ኛ 101. ማርቆስ 6ኛ 102. ማቴዎስ 4ኛ 103. ዮሐንስ 16ኛ 104. ጴጥሮስ 6ኛ 105. ዮሐንስ 17ኛ 106. ማርቆስ 7ኛ 107. ዮሐንስ 18ኛ 108. ማርቆስ 8ኛ 109. ጴጥሮስ 7ኛ 110. ቄርሎስ 4ኛ 111. ጴጥሮስ 8ኛ 112. ቄርሎስ 5ኛ 113. ዮሐንስ 19ኛ 114. መቃርዮስ 3ኝእ 115. ዮሳብ (ዮሴፍ) 2ኛ 116. ቄርሎስ 6ኛ 117. ባሲልዮስ 118. ቴዎፍሎስ 119. ተክለሃይማኖት 120. መርቆሬዎስ 121. ጳውሎስ 122. ማትያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሐዋሪያዊት ናት የምንለው በምክንያት ነው ። ሀዋሪያቶች በሰበሰቧት በአንዲት ቤተክርስቲያን እናምናለን ! #አንዲት_ቤተክርስቲያን #አንድ_ሲኖዶስ #አንድ_መንበር #አንድ_ፓትርያርክ

በወለቴ ያለችው ቤተክርስቲያን ትጣራለች! በሻሸመኔ የብዙ ንፁሀንን ደም ያፈሰሰው ሕገ ወጡ ቡድን በመንግስት በታጠቁ ኃይሎችን ወደ ቤተክርስቲያኗ እየተኮሰ ይገኛል ! ምንጭ፡ ተሚማ

እንዲሁም የደብሩ የአካባቢ ወጣቶች የሆኑ ዘካርያስ ዓለማየሁና ጸጋ ደምሴ የተባሉ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች በትላንትናው ዕለት ታሥረዋል። ወጣቶቹ በአሁኑ ሰዓት ሾላ የካ ፖሊስ ጣቢያ ታሥረው የሚገኙ ሲሆ
እንዲሁም የደብሩ የአካባቢ ወጣቶች የሆኑ ዘካርያስ ዓለማየሁና ጸጋ ደምሴ የተባሉ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች በትላንትናው ዕለት ታሥረዋል። ወጣቶቹ በአሁኑ ሰዓት ሾላ የካ ፖሊስ ጣቢያ ታሥረው የሚገኙ ሲሆን ነገ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡም ተገልጿል። ወጣቶቹን ለእሥር ያበቃቸው ምክንያት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ወጣቶችን ታነሳሳላችሁ የሚል እንደሆነም ነው ለተ.ሚ.ማ የደረሰው መረጃ የሚያመለክተው።

የፈረንሣይ ጉራራ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት ሰብሳቢ ዲ/ን ታምራት ጥጋቡ እንዲሁም የደብሩ የአካባቢ ወጣቶች የሆኑ ዘካርያስ ዓለማየሁና ጸጋ ደምሴ የተባሉ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች በትላንትናው ዕለት ታሥረዋል። ወጣቶቹ በአሁኑ ሰዓት ሾላ የካ ፖሊስ ጣቢያ ታሥረው የሚገኙ ሲሆን ነገ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡም ተገልጿል። ወጣቶቹን ለእሥር ያበቃቸው ምክንያት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ወጣቶችን ታነሳሳላችሁ የሚል እንደሆነም ነው ለተ.ሚ.ማ የደረሰው መረጃ የሚያመለክተው።

#ተፈጸመ_ዝንቱ_ጸሎት . . . | የካቲት 1 2015 ዓ.ም በቀጨኔ ደብረሰላም መድኀኔዓለም እና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ። በቅዱስ ሲኖዶስ በወጣው መመርያ መሠረት ሥርዓተ ጸሎቱ (ምሕላው) በደብራችን ተጨምሮ ተፈጽሟል ። #ኢንፈርህ_ሞተ #ሞትን_አንፈራውም

በእንተ ፍቅረ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኬንያ ፣ እስእለኪ ማርያም በሃሌ ሉያ ፣ ሐዘና ስምዒ ወብካያ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ ፡፡ #Orthodox_Quotes
በእንተ ፍቅረ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኬንያ ፣ እስእለኪ ማርያም በሃሌ ሉያ ፣ ሐዘና ስምዒ ወብካያ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ ፡፡ #Orthodox_Quotes