fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید 👈

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

رفتن به کانال در Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

کانال Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 15 786 مشترک است و جایگاه 5 335 را در دسته دین و مذهبی و رتبه 2 221 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 15 786 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 11 اکتبر, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 71 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 0 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 8.70% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 5.07% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 1 360 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 792 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 12 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 12 اکتبر, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته دین و مذهبی تبدیل کرده‌اند.

15 786
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+1017 روز
+7130 روز
آرشیو پست ها
ረቡዕ ፤ መስከረም 18 የተካሄደው የተማሪዎች #የአጋፔ መርኀ ግብር፡፡ የፎቶ ማስታወሻ

/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/ #share

✤እንኳን ለመስከረም 21፤ብዙኃን_ማርያም #ብዙኃን_ሊቃውንት_ለተሰበሰቡበት_ብዙኃን_ማርያም_፤ #ክቡር_መስቀሉና_ሌሎችም_ንዋያተ_ቅድሳት-በግሸን_ደብረ_ከርቤ_አምባ_ላይ_በክብር_ላረፉበት_ዕለት፤ #ለቅዱስ_ቆጵርያኖስ_(ኃይለኛ ሥራየኛ ጠንቋይ የነበረውና በኋላም አምኖ ለክርስቶስ ምስክር ሆኖ አንገቱን የተሰየፈው )ና ፡ ቆጵርያኖስን ያሳመነችውና ስሟ በተጠራበት ቦታ ሰይጣናት እንደ ትቢያ ሆነው የጠፉት ታላቋ ቅድስት ድንግሊቱ ዮስቴና በሰማዕትነት ላረፉበት ዕለት፤ #ሃይማኖታቸው_ለቀና_ለ318ቱ_አበው_ሊቃውንት (#በ325 ዓ.ም #አርዮስን_አስተምረው_ለመመለስ_#በኒቅያ_የተሰበሰቡባት_ዕለት )፣ /የጉባኤውም ፍጻሜ ኅዳር ዘጠኝ ነው/ እንዲሁም #ከ72ቱ_አርድእት_አንዱ_ለሆነው_ለሐዋርያው_ቅዱስ_ጢባርዮስ_ዕረፍት በሰላምና በጤና አምላከ አበው መድኀኔዓለም አደረሳችሁ አደረሰን፡፡ ✤✤✤✤ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓሏ መስከረም ፳፩ ቀን መከበሩ ስለ ሁለት ነገር ነው፡፡ ፠1ኛ) መስከረም ፳፩ የምናከብርበት አንደኛው ምክንያት መስቀልን አስመልክቶ ነው፡፡ መስቀሉ በመስቀልኛ ቦታ በግሸን ደብረ ከርቤ በክብር ያረፈበት ዕለት ነው፡፡ #ግሸን_ደብረ_ከርቤ ደብረ #ንገሥት ፣ ደብረ #ነጐድጓድ ፣ ደብረ #እግዚአብሔር በሚባሉ ስም ትጠራ ነበር ፡፡ በመጀመርያም የተመሠረትቸው በአፄ ካሌብ ዘመን ነበር ፡፡ሁለት ጽላቶች ከናግርን (አጼ ካሌብ ድል አድርጎ ከተመለሰ በኃላ ) በአባ ፈቃደ ክርስቶስ አማካኝንት (መነኰስ) አምጥተዋል ፤ ከዛም ሲመጡ ወደ ጊሸን ተራራ ሊወጡ ሲሉ በዚያ ንብ ሰፎ ማር ሲንጠባጠብ በማየታቸወው በግእዝና አረብኛ ቋንቋ #አምባ አሰል ብለው ጠሩት ትሩጉሙም የማር አማባ ማት ነው እስካሁንም አካባቢው አምባሰል እየተባለ ይጠራል፡፡ የመጡትንም ጽላቶች በማስገባት የመጀመሪያውን ቤ.ክ ሠረተው ደብሩን መስርተዋል፡፡ በሺህ አንድ መቶ ሃያ ሰባት ዓመት ሰማዕታት ሃይማኖታቸው የቀና የዳግማዊ ዳዊት ልጅ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ከአፄ ይኩኖ አምላክ ከተረፈው የመንግሥት ቅብዓት ተቀብተው ነገሡ፡ ስመ መንግሥታቸውም #ቆስጠንቲኖስ ተባለ፡ በተወለዱም በሃምሣ ዓመት ‹‹ መስቀሌን በመስቀል ላይ አስቀምጥ የሚል ራዕይ አይተው ›› ጠይቀው ሲረዱ አባታቸው የተረከበው መስቀል በመካ መዲናው አሕዛብ ሹም እንዳለ ተረዱ ክተት ሰራዊት ብለው አደሊዋ ድረስ ዘመቱ በዚህ ጊዜ የምስሩ ንጉሥ የአባትህ ገንዘብ እኔጋ ስላለ እባክህ ከእኔ ጋር አተዋጋ መስቀሉን ፣ ሥዕላቱን እና ንዋያተ ቅዱሳቱን እስጥካለሁ አላቸው ( ማብራርያ መስከረም 17 የለጠፋነውን ጽሑፍ ተመልከቱ ) ይህንን ተቀብለው ተመልሰው ለ3 ዓመታት መስቀለኛ ቦታ ፈለጋ በኢትዮጵያ ተራሮች ዞሩ ቅዱስ ዑራኤልም ይራዳቸው ነበር ፡፡ ከሥስት ዓመት ቦኃላም አምባሰል ደርሰው ቦታዋ በመስቀል አምሳል የተቀረጸች መሆኗን አዩ፡፡ መግቢያው ቦታ እጅግ አስቸጋሪ ስለነበር አረፈው በነበሩበት ጊዜ ቅዱስ ዑራኤል ተገልፆ ይህች ደብረ ከዛሬ ጀምሮ ደብረ ከርቤ ትባላለች ፡፡ደብረ ነጐድጓድ ትባለ የነበረውም የካህናትና የነገሥታት መኖርያ ስለሆነች ነው ፡፡ሥላሴን የሚክዱ ሊኖሩባት አይችሉም ፡፡ ወደ ውስጥ ስትገባ ሁለት አብያተ ቤ.ክ ታገኛለህ አንዲቱ #በእግዚአብሔር አብ ስም የተሠራች ናት፡፡ አንዲቱ ደግሞ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም የታነጸች ናት፡፡ እመቤታቸንም ተገልጻለት #በኢትዮጵያ በተሰደድኩበት ጊዜ ለልጅ ልጅ መታሰቢያ ርስት ትሁንሽ ብሎ ስምሽ እስከ ዕለተ ምጽአት ሲመሰገን ይኑርባት ብሎ ሰጥቶኛል እና ሄድ ብላ ቦታዋን #ጠቆመችው፡፡ በ1446 ዓ.ም መስከረም 21 ወደ ተራረው ገብተው አይተው ተደሰቱ በታዘዙትም መሠረት ቅዱስ መስቀሉን በእግዚአብሔር ስም በተሰራው መቅድስ #አስቀመጠው፡፡ መስከረም 21 ቀንም መስቀሉ የተቀመጠበት የእግዚአብሔር አብ ቤ.ክ ቅዳሴ ቤቱ ሆነ ፡፡ ጌታችን በዘባነ ኪሩቤል ላይ ሆኖ አእላፍ መላእክትን አስከትሎ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር መጣ ፡፡ እጅግም ብዙ ቃል ኪዳን ገባለት፡፡ ለቦታዋም ታላቅ ክብርን ሰጣት ደብረ ታቦርም ትሁንልህ አለው ፡፡ ፠፠፠ #ብዙኃን_ማርያም፤ ፠2ኛ) ደግሞ ጉባኤ ኒቅያን ይመለከታል፤ ለ፲፰ኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ ለተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ ካሉት ደቀ መዛሙርት መካከል አርዮስ፣ አኪላስና እለእስክንድሮስ የሚባሉት ዋነኞቹ ነበሩ፡፡ አርዮስ እውቀቱ በመምህሩ የተመሠከረለት ሊቅ ነበር፡፡ ነገር ግን “እጅግ ጥበብ ያደርሳል ከሞት” እንዳለ ሰሎሞን የተጻፈውን ትቶ ባልተጻፈው ላይ ፍልስፍና ጀመረ፡፡ በምሳ. ፰÷፳፪ ላይ ያለውን ቃል በተሳሳተ መንገድ ፈታው፤ ነገር ግን ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ ጠርቶ ቢመክረው ቢገስጸው እንቢ በማለት የክህደት ትምህርቱን ቢቀጥልበት ከሹመቱ አውርዶ አወገዘው፡፡ ተፈጻሜተ ሰማዕት ከደቀመዛሙርቱ መካከል አኪላስን ተክቶ ኅዳር ፲፱ ቀን በሰማዕትነት አረፈ፡፡ አኪላስም የጓደኝነት ፍቅር አድልቶበት አርዮስን ከውግዘት ቢፈታው በመቅሠፍት ሞት ሞተ፡፡ በመንበሩም እለእስክንድሮስ ተተካ፡፡ በዚህ ጊዜ የአርዮስ የክህደት ትምህርት በሀገሪቱ ሞላ፡፡ ይህ ነገርም እየተባባሰ በመሔዱ በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ዘንድ ተሰማ፡፡ ንጉስ ቈስጠንጢኖስም ይህን ሲሰማ ለአርዮስ ጥያቄ መልስ ይሠጥበት ዘንድ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ጕባኤ እንዲደረግ ሰኔ ፳፩ ቀን አዋጅ አስነገረ፡፡ ይህንን አዋጅ የሰሙት ሊቃውንት ሁሉ መስከረም ፳፩ ቀን የእመቤታችን እለት ተሰባሰቡ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ “ለምን ቈስጠንጢኖስ መልዕክት ከላከበት ጊዜ በኋላ ወዲያውኑ ለምን አልመጡም? ለምን ዘገዩ?” የሚለው ጥያቄ ይነሳል፡፡ ምክንያቱም፤ #አንደኛ መጓጓዣ ችግር ስለነበር፤ #ሁለተኛ ሁሉም ሊቃውንት አስተማሪዎች በመሆናቸው ለምዕመናኑ (ለተማሪዎቻው) ሌላ መምህር ማዘጋጀት ስለነበረባቸው፤ #ሦስተኛ ደግሞ በእድሜ የገፉ ስለነበሩ አንድም ሊቃውንቱ ሲያስተምሩ በአላውያን ነገሥታት ባላመኑ ሰዎች ግፍ ይድርስባቸው ስለነበር ነው፡፡ ለምሳሌ ቶማስ ዘመርዓስ በእነዚህ ሰዎች በግፍ እግሩና እጁ ተቆርጦ ስለነበር ለማስተማር በቅርጫት ይዘውት ነበር የሚጓዘው፡፡ ወደ ጕባኤውም ሲመጣ ደቀ መዛውርቱ ያመጡት #በቅርጫት ይዘውት ነበር ( ማብራርያ የጥቅምት 14 የለጠፍነውን እይ ) ፡፡ ከዚህ በኋላ 2,340 ሊቃውንት መስከረም ፳፩ ቀን ተሠባሰቡ፡፡ ከእነዚህ መካከል ግን 318ቱ ሊቃውንት ‹‹ዘእሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ ›› በማለት በሃይማኖታቸው የጸኑ ነበሩ፡፡ ጉባኤውን ከመጀመራቸው በፊት አርባ (፵) ቀን ሱባኤ እስከ ኅዳር ዘጠኝ (፱) ቀን ይዘውና ጕባኤውን አድርገው በአንዲት ቀን ያንን ታላቅ መናፍቅ አርዮስን ድል ነሥተውታል፡፡ ከዚህ ጋር አያይዘውም የኃይማኖታችን መሠረት የሆነውን ጸሎተ ሃይማኖትን አዘጋጅተዋል፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like

(መስከረም ፲፯ን ከ16ቱ አብያተ ክርስቲያናት የት ሊያከብሩ ዐስበዋል?) #መስከረም ፲፯፤ #በዓለ_አስተርእዮተ_መስቀለ_ኢየሱስ፡፡ #በአዲስ_አበባ_የመስቀለ_ኢየሱስ_ክብረ_በዓል_የሚከበርባቸው_ #፫ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ ፩. ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ፤ አድራሻው፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ ቀጨኔ፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ(መርካቶ) → ቀጨኔ (መድኀኔ ዓለም)፤ ፪. ደብረ ዕንቊ ልደታ ለማርያም ቤ/ክ፤ አድራሻ፤ የካ ክፍለ ከተማ፥ ቀበና (ራሽያ/እንግሊዝ/ ኤምባሲ ጀርባ)፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) → ቀበና፡፡ ፫. ደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊና ገብረ ክርስቶስ ቤ/ክ፤ አድራሻው፤ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ፥ ዘነበ ወርቅ (አለርት ሆስፒታል)፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ ሸዋ ዳቦ ቤት → ዘነበ ወርቅ (አየር ጤና በሚለው ታክሲ) ወይም ከሜክሲኮ (ጦር ኃይሎች) → ዘነበ ወርቅ #በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የመስቀለ_ኢየሱስ_ክብረ_በዓል_የሚከበርባቸው_ #፲፫ #ገዳማትና_አድባራት፡፡ ፩. ደብረ ከርቤ ግሸን ማርያም፤ መስቀሉ በክብር ያረፈባት፤ ባለ መስቀልኛ ቦታ አድራሻው፤ ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት፥ አምባሰል፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ → አምባሰል (ግሸን)፡፡ ፪. ዓሲምባ መስቀለ ኢየሱስ ቤ/ን ፤ በዐፄ ገብረ መስቀል ዘመን የተመሠረተ፤ በአባ ዘወንጌል አስተባባሪነት ሕንፃ ቤ/ኑ በአዲስ መልክ የታነጸ፡፡ አድራሻው፤ ምሥራቅ ትግራይ ሀገረ ስብከት ፥ ኢርብ ወረዳ → ዓሲምባ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → መቀለ → ዓዲግራት → 80 ኪ.ሜ. ዓሲምባ፡፡ ፫. ደብረ ሊባኖስ ገዳም መስቀል ቤት፤ (በዓመት አንዴ ብቻ የሚቀደስበት)፡፡ አድራሻው፤ ሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ፥ ደብረ ሊባኖስ ገዳም፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ሊባኖስ (ገዳም)፡፡ ፬. ደብረ ብርሃን ጎሽባዳ አዳኙ መስቀለ ኢየሱስ፤ (መስቀሉ ያረፈበት) አድራሻው፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ደብረ ብርሃን፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ብርሃን → (17 ኪ.ሜ.) ጎሽ ባደ፡ ፭. ባሶና ሞይ ሜዳ መስቀለ ኢየሱስና ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤ (መስቀሉ ያረፈበት) አድራሻው፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ባሶና ወረዳ ሞይ ሜዳ ቀበሌ፥ መስቀለ ኢየሱስ ንዑስ ቀበሌ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ብርሃን → ባሶና /ሞይ ሜዳ/፡፡ ፮. ቡልጋ ሀገረ ማርያም ግርማ አገር መስቀለ መስቀለ ኢየሱስ ቤ/ክ፤ አድራሻው፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ቡልጋ ሀገረ ማርያም ወረዳ፥ ግርማ አገር ቀበሌ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → በደብረ ብርሃን መስመር → ቡልጋ/ግርማ አገር ቀበሌ/፡፡ ፯. አንኮበር መስቀለ ኢየሱስ፤ አድራሻው፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ አንኮበር፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ብርሃን → (42 ኪ.ሜ.) አንኮበር፡፡ ፰. ደራ ቁላላ መስቀለ ኢየሱስ ከምትባል አጥቢያ አድራሻው፤ ደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት፥ ደራ ወረዳ፥ ቁላላ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ባሕር ዳር → ወረታ → ደራ ወረዳ /ቁለላ/፡፡ ፱. ደራ ጉንደ መስቀል መካነ ሰላም መስቀለ ኢየሱስ ገዳም፤ አድራሻው፤ ሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፥ ደራ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደራ መካነ ሰላም፡፡ ፲. ወላይታ ኮንታ አደ ኦፋ መስቀለ ኢየሱስ እና ቁስቋም ማርያም ቤ/ን ፤ አድራሻው፤ ወላይታ ኮንታ ሀገረ ስብከት ፥ በዳሞት ጋሌ ወረዳ፥ አደ ኦፋ ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አየር ጤና አውቶቡስ ተራ → ወላይታ፡፡ ፲፩. ሐዋሳ ሎቄ ደብረ መድኀኒት መስቀለ ኢየሱስ ቤ/ን ፤ አድራሻው፤ አዋሳ ሲዳሞ ሀገረ ስብከት ፥ አዋሳ ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → አዋሳ፡፡ ፲፪. ሰባት ቤት ጉራጌ እዣ ኩበና ሚካኤል፤ (በድርብነት ይከብራል)፡፡ አድራሻው፤ ጉራጌ ሀገረ ስብከት ፥ እዣ (ከደቡቡ ቁልቢ ደብረ ወርቅ አትርፎ ጊዮርጊስ ቤ/ን አጠገብ)፡፡ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. አየር ጤና አውቶቡስ ተራ → ጉራጌ/እዣ/፤ ፲፫. ዶዶላ መስቀለ ኢየሱስ፤ አድራሻው፤ ደቡብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ፥ ዶዶላ፤ ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቃሊቲ አውቶቡስ ተራ → ሻሸመኔ → ዶዶላ፡፡