fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

رفتن به کانال در Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

کانال Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 16 049 مشترک است و جایگاه 5 274 را در دسته دین و مذهبی و رتبه 2 238 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 16 049 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 30 اکتبر, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 511 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 3 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 23.32% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 10.33% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 3 742 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 1 658 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 29 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 31 اکتبر, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته دین و مذهبی تبدیل کرده‌اند.

16 049
مشترکین
+324 ساعت
+1077 روز
+51130 روز
آرشیو پست ها
ሥርዐተ ጸሎት ወስግደት ዘዐርብ ሰሙነ ሕማማት፡፡ እየሰገድን የምንላቸው ቃላት፡፡ እግዘኦ ተሣሃለነ፣ ለከ ኀይል፣ ለአምላክ ይደሉ፣ ኪራያላይሶን ኪራያላይሶን፡፡ …….. ፠፩ኛ ስግደት፤ የወንጌል ምንባብ እንዳበቃ በማስከተል ተግሣጽ ተነቦ እንደተፈጸመ፤ ‹‹ጸልዩ በእንተ ጽንዐ ዛቲ መካን›› የሚለውን ካህኑ ሲመራና ዲያቆኑ በየምዕራፉ ቃጭል ሲደውል፤ ሕዝቡ እየተቀበሉ እግዚኦ ተሣሀለነ (አቤቱ ይቅር በለን) በማለት ፳፪ት ጊዜ በግእዝ፥ በዕዝልና በአራራይ ዜማ እያዜሙ ይሰግዳሉ፡፡ ፠፪ኛ ስግደት፤ በመቀጠል ‹‹ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት›› የሚለውን ምቅናይ በመሪና በአንሺ ወገን መቀባበል ፲፪ ጊዜ ይበሉ፤ በመጨረሻም በ፲፫ኛው ከ‹‹ለከ ኃይል›› እስከ ‹‹ዕብል በአኰቴት›› ድረስ አንድ ጊዜ በኅብረት ይበሉ፡፡ /ከሆሳዕና ሠርክ እስከ ሰኞ ሰርክ መሪ በቀኝ፤ ተመሪ በግራ ሲሆን፡፡ ከማክሰኞ ሠርክ ጀምሮ ግን መሪ የነበረው ተመሪ፤ ተመሪ የነበረው መሪ ይሆናል፡፡/ #ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ለዓለም፤ አማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ዓለም፤ ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ለዓለም፤ ኃይልየ ወፀወንየ ውእቱ እግዚእየ፤ እስመ ኮንከኒ ረዳእየ እብል በአኰቴት፤ አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ፥ ትምጻእ መንግሥትከ፥ ወይኩን ፈቃድከ፥ በከመ በሰማይ ከማሁ በምድር፥ ሲሳየነ ዘለለዕለትነ፥ ሀበነ ዮም፥ ኅድግ ለነ፥ አበሳነ ወጌጋየነ፥ ከመ ንህነኒ ንኅድግ፥ ለዘአበሰ ለነ፥ ኢታብአነ፥ እግዚኦ ውስተ መንሱት፥ አላ አድኅነነ፥ ወባልሐነ፥ እምኵሉ እኩይ፥ እስመ ዚአከ፥ ይእቲ መንግሥት፥ ኃይል ወስብሐት ለዓለመ ዓለም፡ ፠፫ኛ ስግደት፤ በመቀጠል ‹‹ለአምላክ ይደሉ››ን መጀመሪያ በመሪ እየቀደሙ በአንሺ እየተከተሉ አንድ ጊዜ ይዝለቁ፤ በ፪ኛው ክፍል ደግሞ እያስተዛዘሉ ፩ድ ጊዜ ይበሉ፡፡ ለአምላክ ይደሉ፤ ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ዓለም፡፡ ለሥሉስ ይደሉ፤ ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ዓለም፡፡ ለማሕየዊ ይደሉ፤ ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ዓለም፡፡ ለዕበዩ ይደሉ፤ ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ዓለም፡፡ ለዕዘዙ ይደሉ፤ ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ዓለም፡፡ ለመንግሥቱ ይደሉ፤ ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ዓለም፡፡ ለሥልጣኑ ይደሉ፤ ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ዓለም፡፡ ለምኵናኑ ይደሉ፤ ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ዓለም፡፡ ለኢየሱስ ይደሉ፤ ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ዓለም፡፡ ለክርስቶስ ይደሉ፤ ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ዓለም፡፡ ለሕማሙ ይደሉ፤ ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ዓለም፡፡ ለመስቀሉ ይደሉ (ለዐርብ ብቻ)፤ ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ እስከ ዓለም፡፡  ቀጥሎ ያለውን የመዝጊያ ጸሎት እያዜሙና እየሰገዱ ፫ት ጊዜ መላልሰው ይዝለቁት፡፡ ለከ ይደሉ ኃይል፥ ወለከ ይደሉ ስብሐት፥ ወለከ ይደሉ አኰቴት፥ ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለመ ዓለም፡፡ ፠፬ኛ ስግደት፤ ዜማው አሁንም በቀኝና በግራ በመቀባበል ነው የሚባለው፡፡ በመሪ ወገን እየቀደሙ፤በአንሺ ወገን ደግሞ እየተከተሉ ፩ድ ጊዜ ይዝለቁ፤ ቀጥለውም በመሪና በተመሪ ወገን እያስተዛዘሉ ፩ድ ጊዜ ይዝለቁ፡፡ መሪ፤ ክርስቶስ አምላክነ፥ ዘመጽአ ወሐመ በእንቲአነ፥ በሕማማቲሁ ቤዘወነ፤ ተመሪ፤ ንሰብሖ፥ ወናልዕል ስሞ ኅቡረ፥ እስመ ውእቱ ገብረ መድኃኒተ በብዝኀ (በዕበየ) ሣህሉ፡፡ /በዐርብ፤ ዘሐመ ወሞተ በእንቲአነ/ #ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን ኪርያላይሶን፥ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፣ እብኖዲ ናይናን/ናይን/፥ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፣ ታኦስ ናይናን/ናይን/፥ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፣ ማስያስ ናይናን/ናይን/፥ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፣ ኢየሱስ ናይናን/ናይን/፥ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፣ ክርስቶስ ናይናን/ናይን/፥ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፣ አማኑኤል ናይናን/ናይን/፥ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፣ ትስቡጣ ናይናን/ናይን/፥ ኪርያላይሶን፡፡  ኪርያላይሶን የሚለውን ብቻ በመሪ ፳፩ ጊዜ፥ በተመሪ ወገን ፳ ጊዜ ይበሉ፤ ድምሩ ፵፩ ኪርያላይሶን ይኾናል፡፡ የየሰዐቱን መልክአ ሕማማት ያድርሱ፡፡ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/

‹‹ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው፤ እግዚአብሔር በክፉ ቀን ያድነዋል፡፡›› መዝ. 40፥1 የፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት በከተማችን ብሎም በሃገራችን በትንሣኤ በዓል ነዳያንን በማስፈሰክ አገልግሎት ቀዳሚው እንደኾነ ይታወቃል፤ ይህንንም አገልግሎት ለከዛሬ 50 ዓመታት በፊት በ1961ዓ.ም. በአንድ በግ ተጀምሯል፤ ሲጀመርም ነዳያንንና በአካባቢው ያሉ የአቅም ማነስ ያለባቸውን ምዕመናንን ታሳቢ አድርጎ ነው። በ1964ዓ.ም. ደግሞ ወደ 2 በግና አንድ እናት ባመጡት 1 ሌማት እንጀራና 1 ብረት ድስት ወጥ ከፍ አለ፨ እያደረ ወደ በሬ አደገ፨ በየዓመቱ እንደሚደረገው ዘንድሮም ነዳያንን፣ በጸበል ቦታ ያሉትን፣ በገዳም ውስጥ ያሉትን መነኰሳትና የአብነት ተማሪዎች ለማስፈሰክና ለመርዳት የሚያስፈልጉትን (ገንዘብ፣ ልብስ፥ ሳሙና፥ ንጽሕና መጠበቂያ፣ በሬ፥ በግ፥ ፍየል፣ የተማሪዎች የመማሪያ ቊሳቊሶችን) እንድትረዱ በመድኀኔዓለም ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

#ጸሎተ_ሐሙስ_ወሕጽበተ_እግር_ ሐዋርያቲሁ ከበበ፥ እግረ አርዳኢሁ ሐፀበ፤ ኮኖሙ አበ ወእመ፤ ወመሐሮሙ ጥበበ፡፡ (ሐዋርያቱን ሾመ፤ የደቀ መዛሙርቱን እግር አጠበ፤ አባትና እናት ኾናቸው፤ ጥበብንም አስተማራቸው፡፡) /ሊቁ ቅዱስ ያሬድ፣ ድጓ/

#መልክአ_ሕማማት፤ *መልክአ ሕማማት ማለት ስለ ጌታችን መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ሕማም፥ መከራ፥ ስቃይ፥ የሚናገር መጽሐፍ ሲሆን፤ ደራሲው ታላቁ ሊቅና የደብረ ባሕርይ ጋሥጫ መምህር #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ_ ነው፡፡ *መልክአ ሕማማት በባለ 3ት መስመር አርኬ የተደረሰ ግጥማዊ ድርሰት ሲሆን፤ የተደረሰውም በ7ቱ የጸሎት ጊዜያት አንጻር በመሆኑ ‹‹#ጸሎት_ዘሰባዐቱ_ጊዜያት›› በሚል መጠሪያም ይጠራል፡፡ የእያንዳንዱ ጊዜ ድርሰትም በዋነኛነት 3ት ክፍሎችን የያዘ ነው፤ እነርሱም፤ 1ኛ) ስብሐተ እግዝእትነ ማርያም /የእመቤታችን ምስጋና/ 2ኛ) ስበሐተ ኢየሱስ ክርስቶስ /የኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና/ 3ኛ) ስብሐተ ሥሉስ ቅዱስ /የሥሉስ ቅዱስ ምስጋና/ **በ7ቱ ጊዜያት ጸሎት ማድረስ እንደሚገባን ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 118 ላይ ‹‹ሰባት ጊዜ በቀን አመሰግንሃለሁ ይላል››፤ አባቶቻችን ሐዋርያትም ይህንኑ ደንግገዋል፡፡ /ዲድስቅልያ 37፣ ቀሌምንጦስ 1ና 7፣ አቡሊዲስ 25ኛና 27ኛ፣ ባስልዮስ 28ኛ አንቀጽ፣ ፍትሐ ነገሥት ገጽ 21/፡፡ ፠ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ መልክአ ሕማማትን ሲደርስም በ7ቱ የጸሎት ጊዜያት የተፈጸሙትን ድጊቶች ከ3ቱ የየጊዜያቱ የድርሰቱ ክፍሎች ምስጋና (የማርያም፣ የጌታ፣ የሥሉስ ቅዱስ ምስጋና) ጋር እያመሠጠረና እያራቀቀ፥ እያስዋበና ምሥጢር እያመጣ፤ እንደ ወርቅ እያንከባለለ፥ እንደ ሸማ እየጠቀለለ፥ በግጥም እያስጌጠ፥ በቃላት እየሰደረ፥ በዜማ እያሸበረቀ፥ መንፈስን እየመሰጠ፤ ነው የደረሰው፡፡ #የ7ቱ_የጸሎት_ጊዜያት_የሚባሉትም፤ ፠1ኛ) መንፈቀ ሌሊት(ሌሊት 6 ሰዐት)፤ ጌታችን የተወለደበት፥ የተጠመቀበት፥ የተነሣበትና ዳግመኛ የሚመጣበት ፥ … ሰዐት ነው፡፡ ፠2ኛ) ነግህ (ማለዳ፥ ጧት)፤ ጨለማን አርቆ ብርሃንን የሚያመጣበት፥ አባታችን ቅዱስ አዳም የተፈጠረበት፥ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ በጲላጦስ አደባባይ ፊት ቁሞ የተመረመረበት፥ …. ሰዐት ነው፡፡ ፠3ኛ) ሠለስት (ጠዋት ሦስት ሰዐት)፤ እናታችን ሔዋን የተፈጠረችበት፥ ነቢዩ ዳንኤል ጸሎት ያደረሰበት፥ እመቤታችን ከቅዱስ ገብርኤል ብሥራትን ሰምታ የጸነሰችበት፥ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ለኛ ሲል በጲላጦስ አደባባይ የተገረፈበት፥ ….. ሰዐት ነው፡፡ ፠4ኛ) ቀትር (6 ሰዐት)፤ አጋንንት የሚሰለጥኑበት ሰዐት ስለሆነ እንዳይሰለጥኑብን፥ አዳም ዕፀ በለስን በልቶ የሳተበት ስለሆነ እንዳንስት እንጸልያለን፡፡ በተጨማሪም ነቢዩ ሄኖክ ቤተ መቅደስን ያጠነበት፥ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ለኛ ሲል በመስቀል ላይ የተሰቀለበት፥ ….. ሰዐት ነው፡፡ ፠5ኛ) ተስዓት (ዘጠኝ ሰዐት)፤ ቅዱስ ጴጥሮስና ዮሐንስ ለጸሎት ወደ ቤተ መቅደስ የወጡበት፥ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ በፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋው የለየበት፥ ….. ሰዐት ነው፡፡ ፠6ኛ) ሠርክ (ዐሥራ አንድ ሰዐት)፤ ነቢዩ ኤልያስ መሥዋዕት የሰዋበት፥ ዕዝራ ጸሎትን ያቀረበበት፥ ሕዝቅያስ ጸልዮ ፀሐይን ወደ ዐሥር ደረጃዎች የመለሰበት፥ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ወደ በፈቃዱ ወደ አዲስ መቃብር የወረደበት፥ …… ሰዐት ነው፡፡ ፠7ኛ) ንዋም (የመኝታ ሰዐት)፤ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ በጌቴሴማኒ የጸሎትን ሥርዐት ያስተማረበት ፥ እንዲሁም ሌሊቱን በመላእክት ጥበቃ ከርኵሳን አጋንንት እንዲጠብቀን የምንጸለይበት …… ሰዐት ነው፡፡ #ለቡ(ልዩ ማስታወሻ)!! ይህ ታላቅ ጸሎት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስር ባሉ በሁሉም ገዳማትና አድባራት በሰሙነ ሕማማት የሚደርስ ሲሆን፤ በአንዳንድ ትላልቅ ገዳማት (እንደ ዋልድባ፣ ማኅበረ ሥላሴ፣ ደብረ ባሕርይ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ወደብረ ጎል አቡነ በጸሎተ ሚካኤል) ያሉ መነኰሳትና መናንያን ግን ከዓመት እስከ ዓመት ጸሎቱን በዜማ /በንባብ/ ያደርሱታል፡፡ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/

#ሥርዐተ_ጸሎት_ወስግደት_ዘሰሙነ_ሕማማት፡፡ በሰሙነ ሕማማት የሚባሉትን በአጭሩ ስንቃኛቸው፡፡ (ለዐርቡ ጸሎት እንደ ዘማች ስለሚያገለግል) ነገ ከምንለቀው የዐርቡ ጸሎት ጋራ አብራችሁ ተጠቀሙበት፡፡ /ይህን ጽሑድ በአድካሚ ሁኔታ እንደ ንብ ቀስመንና ሰብስበን አዘጋጅተንላችኋል፤ ላልደሰረሰው አዳርሱ፤ ማተሚያ ቤት ያላችሁ አትማችሁ ስጡ፡፡/ ፠የሰሙነ ሕማማት ጸሎት የሚደረገው በ7ቱ የጸሎት ጊዜያት መሠረትነት 7ት ጊዜ ነው፡፡ ለዚሁ አገልግሎት ታላቁ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በ7ቱ ጊዜያት ከፋፍሎ የደረሰው መልክአ ሕማማትም አብሮ በዜማ ይደርሳል፡፡ ፠ደወልና ቃጭል ይመታል፤ ፠ጸሎታት(ሙሉ ውዳሴ ማርያምና ዳዊት)ና (የኦሪትና የነቢያት) ምንባባት ይደርሳል፤ ፠የተአምር መቅድምና ምንባብ ይነበባል፤ የተአምራት መርገፍ በዜማ ይባላል፡፡ ፠የወንጌል አቡን በቅብብሎሽ ይደርሳል፤ ፠ምስባክ ይሰበካል ፥ ወንጌል ይነበባል፡፡ #1ኛ_ስግደት፤ ‹‹ጸልዩ በእንተ ጽንዐ ዛቲ›› እያለ ቃጭል ሲያሰማ 22ት ጊዜ ‹‹እግዚኦ ተሣሃለነ›› እየተባለ ይሰገዳል፡፡ #2ኛ_ስግደት፤ ‹‹ለከ ኀይል ክብር ወስብሐት›› የሚለውን በቅብብሎሽ 6ት ፥ 6ት ጊዜ (በድምሩ 12)፤ 7ኛውን በኅብረት እየተሰገደ ይባላል፡፡ #3ኛ_ስግደት፤ ‹‹ለአምላክ ይደሉ›› የሚለውን 1ኛውን ዙር በቅብሎሽ፤ 2ኛውን ዙር እያስተዛዘሉ፤ ከስግደት ጋራ ይባላል፡፡ #4ኛ_ስግደት፤ ‹‹ክርስቶስ አምላክነ…›› የሚለውን በመሪና ‹‹ንሰብሖ ..›› ወናልዕል ስሞ የሚለውን በቅብብሎሽ ብለው በዚያው ቀጥለው፤ ‹‹ኪራያላይሶን፥ ኪራያላይሶን፥ ኪራያላይሶን›› የሚለውን በመሪ 21 ጊዜ፤ በተመሪ 20 ጊዜ (በድምሩ 41 ጊዜ) እየተሰገደ ይደርሳል፡፡ ፠የየሰዓቱን (የሌሊት፣ የነግህ፣ የጠዋት 3 ሰዐት፣ የቀትር/6 ሰዐት/፣ የተሰዐት/9ኝ ሰዐት/፣ የሰርክ /11 ሰዐት/፣ የንዋም) መልክአ ሕማማት በዜማ ይደርሳል፡፡ ፠ካህኑ ቡራኬ ሰጥቶ፤ ዲያቆኑ ደግሞ ‹‹ሑር በሰላም›› ብሎ ሕዝቡን ያሰናብታል፡፡ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/

ይግባኝ ለክርስቶስ ፬ወ ፭፡፡ #በስሪላንካ ያለች ጽዮን ቤተ ክርስቲያንን ባሰብናት፥ ድምጿን በሰማናትና ገጿን ባየናት ጊዜ አለቀስን፤ ቤተ ክርስቲያን ሆይ! ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ፤ ባላስብሽ አንደበቴ ከጕሮሮዬ ጋር ይጣበቅ፡፡ ቤተ ክርስቲያንን እስከ መሠረቷ ድረስ ፈጽሞ አፍርሱ የሚሉትን ጎስቋሎችን የሚበቀላቸው አምላካችን ብፁዕ ነው፡፡ /መዝ. 136/ #ኢሀሎኑ በዝ ስሪላንካ ሰማይ፥ አምላከ አዶናይ፡፡ #በጠራሁህ ቀን ፈጥነህ ስማኝ፤ ምንም በመከራ መካከል ብሄድ አንተ ታድነኛለህ፤ በአሕዛብ ቊጣ ላይ እጆቼን ዘረጋህ፤ ቀኝህም አዳነኝ፤ እግዚአብሔር ይበቀልልኛል፤ አቤቱ ይቅርታህ ለዘለዓለም ነው፡፡ /መዝ. 137/ በስሪላንካ መዲና ኮሎንቦ እሑድ ሚያዝያ 13 የEastern Sunday (የትንሣኤ እሑድን) በዓል በሦስት አብያተ ክርስትያናት በማክበር ላይ በነበሩ የክርስቲያን እምነት ተከታዮች ላይና በሦስት ሆቴሎች በድምሩ ስድስት በደረሰ የቦንብ ጥቃት 137 ሰዎች ማረፋቸውና በመቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገለጸ፡፡ የሟቾች ቊጥር ወደ 300 እነደሚጠጋም እየተነገረ ነው፡፡ ዘጠኝ የሚሆኑት የውጭ ዜጎች ናቸው፡፡ አብዛኞቹም ሕሊናቸው ንጹሕና ብሩሕ የሆነው ሕፃናጽ ናቸው፡፡ ስለ ክርስቶስ መሞት ሕይወት ነው፣ ሰውን መግደል ኀጢአት፤ የኃጢአትም ኀጢአትም ነው፤ ሰውንም በመግደል ጽድቅ የለም፤ አይኖርምም፤ ልብ ያለው ልብ ይበል፤ እንደእርሱ በአምላክ አርአያ የተፈጠረን ሰው ገድሎ እጸድቃለሁ ማለት አላዋቂነትና ስንፍና ነው፤ የሚያጸድቅማ ቢሆን የገደሉ ለምን ሕሊናቸው ይታወካል!!!!!!!?????፡፡ ‹‹ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ!፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ:: ማቴ. 10፥28::

በሰሙነ ሕማማት የሚባሉ የአምላክ ስሞችና ትርጕማቸው፡፡ /ምንጭ፤ ቅዱስ ያሬድ፣ ድጓ/

#የሰሙነ_ሕማማት_ዕለታት_ስያሜዎች †ሰኞ፤ መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ፤ አንጽሖተ ቤተ መቅዳስ የተፈጸመበት ሰኞ:: †ማግሰኞ፤ የጥያቄና የትምህርት ቀን:: †ረቡዕ፤ ምክረ አይሁድ፥ የዕንባ ቀን፥ የመልካም መዓዛ ቀን:: †ሐሙስ፤ ጸሎተ ሐሙስ፥ ሕጽበተ ሐሙስ፥ የምሥጢር ሐሙስ፥ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ፥ የነጻነት ሐሙስ:: †ዐርብ፤ የስቅለት ዐርብ:: †ቅዳሜ፤ ቀዳም ሥዑር (ሹር ቅዳሜ)፤ ለምለሚቱ ቅዳሜ፥ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ፥ ሰንበት ዐባይ፥ ቅዱስ ቅዳሜ፡፡ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/

የ2011 የተፂዕኖ (ሆሳዕና) በዓል በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን፡፡ *ተፂዕኖ ዲበ ዕዋል ኢየሩሳሌም ቦአ ሃገረ /በአህያ ውርንጫ ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ/

የሆሳዕና አከባበር፤ ፎቶ ላይ የምትመለከቱት፤ *በሃገራችን በግንባር ቀደምትነትና በፊታውራሪነት የሆሳዕና በዓል እጅግ በጣም በተለየ ሁኔታ፤ ከዋይዜማው ጀምሮ የሚከበርባት ርዕሰ ገዳማት ወአድባራር አኵሱም ደብረ ጽዮን ማርያም፡፡ *ከአፄ ምኒልክ ዘመን ጀምሮ በአኵሱም ደብረ ጽዮን የሚካሄደውን ሥርዐት ቀድታ በማምጣት ለአዲስ አበባ ዛሬ ለምናየው የሆሳዕና ሥርዐት አብነት የሆነችውና በአዲስ አበባ በደማቅ ሁኔታ የሚከበርባት ርዕሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ማርያም፡፡ *በአዲስ አበባ ጥንታውያን ከኾኑ አድባራት መካከል የኾነውና የሆሳዕና ሥርዐት በደመቀ ሁኔታ የሚከበርበት ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን፡፡