cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ኢትዮጵያ

ስለ ሀገራችን ታሪክ ፣ ባህል ፣ ጥንታዊ ቅርሶች ፣ ገዳማት ፣ መጎብኘት ስላለባቸው ስፍራዎች መረጃ ለማግኘት ካስፈለገ ይህንን ቻናል ይቀላቀሉ ። ኢሉሚናቲን እናወግዛለን። የዚህ ቻናል አላማ ትውልዱ ሐይማኖቱንና ታሪኩን ያውቅ ዘንድ እና ሙሉ ትውልድ ይሆን ዘንድ ማገዝ ነው ። አንድነታችን ለህልዉናችን @HISCULHEROFETHIOPIA

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
391
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-1330 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

📌 ስንክሳር ዘሚያዚያ ፳፱ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን “ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን” (ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ) “በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን” (በገናና ኀይልና ሥልጣን) “ዐሠሮ ለሰይጣን” (ሰይጣንን ዐሰረው) “አግአዞ ለአዳም” (አዳምን ነጻ አወጣው) “ሰላም” (ፍቅር አንድነት ሆነ) “እምይእዜሰ” (ከእንግዲህስ) “ኮነ” (ሆነ) “ፍሥሐ ወሰላም” (ደስታ ሰላም) አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሚያዝያ ፳፱ ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ አርስጦስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ❖ ይኽም ቅዱስ በመጀመሪያ ከከበሩ ሐዋርያት ጋር የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ከተቀበለ በኋላ በሀገሩ ሁሉ ቋንቋ ተናገረ፡፡ ❖ ሐዋርያትንም እያገለገለ ከእነርሱ ጋር የከበረች ወንጌልን ሲሰብክ ብዙ ጊዜ መከራን ተቀበለ፡፡ ❖ ሐዋርያትም መርጠው ለኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን አስተዳደር ሾሙት፡፡ ❖ በዚኽችም በሹመት አገልግሎት ጥቂት ጊዜ ከቀየ በኋላ ብናጥስ በሚባል አገር ላይ ኤጲስ ቆጶስ አድርገው ሾሙት፡፡ ❖ በዚያም ብዙዎችን ጌታችንን ወደማመን መለሳቸው፤ የጣዖታት ቤቶችንም አፈራርሶ በምትካቸው አብያተ ክርስቲያናትን ሠራ፤ የአገሪቱንም ሰዎች ጌታችንን በማመን አጸናቸው፡፡ ❖ ሐዋርያው ቅዱስ አርስጦስ ታላላቅ አስደናቂ ተአምራትን ያደረግ ነበር፤ መራራ የሆኑ ውኃዎችን ለውጦ ጣፋጭ ያደርጋቸው ነበር፡፡ ❖ የደረቁ እንጨቶቸንም እንዲለመልሙና ፍሬ እንዲያፈሩ ያደርጋቸው ነበር፤ በደዌ የተጨነቁ ብዙ ህመምተኞችንም ይፈውሳቸዋል፡፡ ❖ በእንዲህ ያለ መልካም አገልግሎትም ጸንቶ ከኖረ በኋላ በሽምግልና ዘመኑ ሚያዝያ 28 ቀን በሰላም ዐርፎ ወደሚወደው እግዚአብሔር ሄደ፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፤ በጸሎቱ ይማረን
📌 ሚያዝያ 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1. ቅዱስ አርስጦስ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት) 2. አባ አካክዮስ ዘኢየሩሳሌም (ጻድቅና ንጹሕ) 3. አባ ገምሶ ሰማዕት 📌 ወርኀዊ በዓላት 1. የፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት 2. ቅድስት አርሴማ ድንግል 3. ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት 4. ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ 5. ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት 6. ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ (ጻድቅና ሰማዕት)
نمایش همه...
ከትንሳኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡- #ሰኞ #ማዕዶት_ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡ #ማክሰኞ #ቶማስ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29 #ረቡዕ #አልአዛር_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡ #ሐሙስ #አዳም_ሐሙስ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡ #አርብ #ቅድስት+ቤተክርስቲያን_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡ #ቅዳሜ ቅዱሳት_አንስት_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡ #እሁድ #ዳግም_ትንሳኤ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡
نمایش همه...
🛎 ስንክሳር ዘሚያዚያ ፳፰ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ (ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ) “በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን” “ዐሠሮ ለሰይጣን” (ሰይጣንን ዐሰረው) “አግአዞ ለአዳም” (አዳምን ነጻ አወጣው) “እምይእዜሰ” (ከእንግዲህስ) “ኮነ” (ሆነ) “ፍሥሐ ወሰላም” (ደስታ ሰላም) አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሚያዝያ ፳፰ በኮራሳት ተራራ በገድል ተጠምዶ የሚኖር ቅዱስ ሜልዮስ በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ ❖ ይኽም ቅዱስ አባት ኮራሳት በምትባል አገር በተራራ ባሉ ዋሻዎች ከሁለት አርድእት ጋር ይኖር ነበር፤ እርሱም በተጋድሎ ሕይወቱ እጅግ የተመሰገነ ነው፡፡ ❖ እግዚአብሔርም በአባ ሜልዮስ እጅ ብዙ አስገራሚ ተአምራትን አደረገ፤ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን በመንገድ ሲሄድ የሞተ ሰው አገኘ፤ የአገሪቱ ሰዎችም አንዱን መነኮስ ‹‹የገደልከው አንተ ነህ›› ብለው ይዘው አስጨነቁት፡፡ ❖ የከበረ አባ ሜልዮስም ወደ ጌታችን ከጸለየ በኋላ ሬሳውን ‹‹በውኑ የገደለህ ይኽ መነኩሴ ነውን መንፈስ›› አለው፤ የሞተውም ሰው አፈፍ ብሎ ተነሥቶ ‹‹እርሱስ አልገደለኝም ነገር ግን ብዙ ገንዘቤን ከአንድ ቄስ ዘንድ አደራ አስጠበቅሁ ስለዚህም ገደለኝ ከዚህም ጣለኝ›› ብሎ መሰከረ፡፡ ❖ ዳግመኛም አባ ሜልዮስን ‹‹ወደዚያ ቄስ ዘንድ ሄደህ ገንዘቤን ተቀብለህ ለልጆቼ ስጥልኝ›› ብሎ ለመነው፡፡ ❖ አባ ሜልዮስም ‹‹እስከትንሣኤ ቀን በሰላም አርፈህ ተኛ›› ብሎት ተመልሶ ዐረፈ፤ የኮራት ንጉሥ ሁለቱ ልጆች ሠራዊቶቻቸውን ይዘው ለአደን ወደ ተራራው ቢወጡ የከበረ ቅዱስ አባ ሜልዮስን ማቅ ለብሶ ጠጉሩም የረዘመ ሆኖ አገኙት፡፡ ❖ የንጉሡ ልጆችም አባ ሜልዮስን ባዩት ጊዜ ፈርተውት ‹‹ሰው ነህን ወይስ መንፈስ›› ብለው ጠየቁት፡፡ ❖ እርሱም ‹‹በዚህ ተራራ ውስጥ የምኖር ለጌታዬ ለኢየሱስ ክርስቶስ የምሰግድ ሰው ነኝ›› አላቸው፡፡ ❖ እነርሱም ይህን ሲናገር ሰምተው ‹‹ከእሳትና ከፀሐይ በቀር አምላክ የለም እንዳንገድልህ ሠዋላቸው›› አሉት፡፡ ❖ አባ ሜልዮስም የሰው ፍጥረት ሁሉ እሳትንና ፀሐይን ለፈጠረ አምላክ ብቻ መገዛት እንዳለት ነገራቸው፡፡ ❖ የንጉሡ ልጆችም አባ ሜልዮስን ከሁለቱ አርድእቱ ጋር ይዘው ጽኑ ሥቃይ አሠቃዩአቸው፡፡ ❖ በዚህ ወር በ13ኛው ቀን የሁለቱን አርድእት አንገታቸውን በሰይፍ ቆረጧቸውና የሰማዕትነታቸው ፍጻሜ ሆነ፡፡ ❖ አረጋዊ ቅዱስ አባ ሜልዮስን ግን ለ15 ቀናት ሲያሠቃዩት ኖሩ፤ ከዚህም በኋላ ከመካከላቸው አቁመው አንዱ በፊት አንዱ በኋላ ሆነው በፍላጻ እየነደፉ በእጅጉ ያሠቃዩት ጀመር፡፡ ❖ አረጋዊ አባ ሜልዮስም ‹‹እኔን በፍላጻዎቻችሁ ለመግደል እንዳሠቃያችሁኝ እናንተም ደግሞ በገዛ ፍላጻዎቻችሁ ትሞቱ ዘንድ አላችሁ›› በማለት ትንቢት ተናገረባቸው፡፡ ❖ እነርሱም ቃሉን በመናቅ ነፍሱን እስከሚያሳልፍና ምስክር ሆኖ የሰማዕትነት አክሊልን እስከሚቀበል ድረስ ነደፉት፤ በማግሥቱም እንደልማዳቸው ለአደን በወጡ ጊዜ የዱር አህያ አገኙ፡፡ ❖ ተከታትለውም ቀስታቸውን አስፈነጠሩ፤ እግዚአብሔርም ፍላጻቸውን ወደራሳቸው መልሶ ቅዱስ አባ ሜልዮስ እንደተናገረ በራሳቸው ፍላጻ ሞቱ፡፡ የአረጋዊ አባ ሜልዮስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፤ በጸሎቱ ይማረን
📌 ሚያዝያ ፳፰ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1. ቅዱስ ሜልዮስ ዘደብረ ኮራሳን (ጻድቅና ሰማዕት) 2. አባ ኢያሱና አባ ዮሴፍ (ደቀ መዛሙርቱ) 3. ቅዱስ ብስጣውሮስ ሰማዕት (ተንባላት የገደሉት) 📌 ወርኀዊ በዓላት 1. አማኑኤል ቸር አምላካችን 2. ቅዱሳን አበው (አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ) 3. ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ 4. ቅድስት ዓመተ ክክርስቶስ 5. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ (ሰማዕት)
نمایش همه...
⚜💐🎚⚜💐🎚⚜💐🎚⚜💐🎚⚜💐 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን "በሕማሙ ሕመማችንን ሻረ በሞቱም ሞትን አጠፋው።" ሃይማኖተ አበው ዘኤጲፋንዮስ ም.58፥51 ✝ ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን 👉 በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን ✝ አሰሮ ለሰይጣን 👉 አግዓዞ ለአዳም ✝ ሰላም 👉 እምይእዜሰ ✝ ኮነ 👉 ፍስሐ ወሰላም እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም በጤና አደረሰን አደረሳችሁ!!! 🕊🕊🕊 እግዚአብሔር አምላካችን ለሀገራችን ለኢትዮጵያ ለህዝቦቿም ሰላም ፍቅር አንድነትን ያድለን፤ አንድም ያድርገን አሜን መልካም የትንሣኤ በዓል። 🕊🕊🕊 የደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍና ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ኆኅተ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት
نمایش همه...
"ከሙታን ተነሥቶ ሲኦልን ረግጦ በሞቱ ሞትን ደመሰሰው” (መጽሐፈ ኪዳን) እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሰን! @beteafework       @beteafework
نمایش همه...
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 📌 ቀዳም_ሥዑር (የተሻረች ቅዳሜ) የዐቢይ ጾም የመጨረሻዋ ቅዳሜ ብዙ ስያሜዎች አሏት፦ 👉 ቀዳም_ሥዑር፡- በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም በቀዳም ሥዑር ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ፣ እየተዘመመ እየተመረገደ እየተጸፋ ያድራል፡፡ ጥዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡ 👉 ለምለም_ቅዳሜ፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡ በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡ (የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡ ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡) 👉 ቅዱስ_ቅዳሜ፡- ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡ (ስምዐ ተዋሕዶ የስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት ሚያዝያ 2004 ዓም)
نمایش همه...
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ⚡️📌⚡️ አክፍሎት (ማክፈል) በሰሙነ ሕማማት ዕለተ አርብ ከስግደት በሗላ ምዕመናን በየቤታቸው ጥቂት ነገር ቀምሰው እስከ እሁድ /የትንሳኤ ሰዓት/ ይሰነብታሉ፡፡ ይህ አክፍሎት ይባላል ከአርብ እስከ ቅዳሜ ሌሊት ለእሁድ አጥቢያ ማክፈል የብዙዎች ነው። አንዳንዶች ግን ከሐሙስ ጀምረው ያከፍላሉ፡፡ ይህም እመቤታችን፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ የጌታን ትንሳኤ ሳናይ እህል ውሃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤ መቆየታቸውን ተከትሎ የመጣ ትውፊት ነው ይህንን ትውፊት አስመልክቶ ሄሬ ኔዎስ፣ አውሳብዮስ የተባሉ ጸሐፍት፣ ሐዋሪያት በሰሙነ ሕማማት ከደረቅ ዳቦ እና ከትንሽ ውሃ በቀር እንደማይመገቡ እና ከሐሙስ ጀምረው እንደሚያከፍሉ ጽፈዋል ይህም ብቻ ሳይሆን ሐዋሪያት ሌሎቹንም እንድያከፍሉ እንዲያሳስቡና ከሐሙስ ጀምሮ ያልተቻላቸው ቢያንስ ከአርብ ጀምሮ እንዲያከፍሉ ማዘዛቸውን ጽፈዋል፡፡ የኛ ቤተክርስቲያን ትምህርትም ይሄው ነው፡፡ 👉 ምንጭ፦ ስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት
نمایش همه...
❮❮ ዮሴፍ ወኒቆዲሞስ ገነዝዎ ለኢየሱስ - ዮሴፍ ኒቆዲሞስም ጌታችን መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስን ገነዙት ❯❯ 📜 ወንጌለ ማቴዎስ 27 📜 ⁵⁷ በመሸም ጊዜ ዮሴፍ የተባለው ባለ ጠጋ ሰው ከአርማትያስ መጣ፥ እርሱም ደግሞ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ነበረ፤ ⁵⁸ ይኸውም ወደ ጲላጦስ ቀርቦ የኢየሱስን ሥጋ ለመነው። ⁵⁹ ጲላጦስም እንዲሰጡት አዘዘ። ዮሴፍም ሥጋውን ይዞ በንጹሕ በፍታ ከፈነው፥ ⁶⁰ ከዓለት በወቀረው በአዲሱ መቃብርም አኖረው፥ በመቃብሩም ደጃፍ ታላቅ ድንጋይ አንከባሎ ሄደ። ⁶¹ መግደላዊት ማርያምም ሁለተኛይቱም ማርያም በመቃብሩ አንጻር ተቀምጠው በዚያ ነበሩ። ⁶² በማግሥቱም ከመዘጋጀት በኋላ በሚሆነው ቀን፥ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ወደ ጲላጦስ ተሰበሰቡና፦ ⁶³ ጌታ ሆይ፥ ያ አሳች በሕይወቱ ገና ሳለ፦ ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ እንዳለ ትዝ አለን። ⁶⁴ እንግዲህ ደቀ መዛሙርቱ መጥተው በሌሊት እንዳይሰርቁት ለሕዝቡም፦ ከሙታን ተነሣ እንዳይሉ፥ የኋለኛይቱ ስሕተት ከፊተኛይቱ ይልቅ የከፋች ትሆናለችና መቃብሩ እስከ ሦስተኛ ቀን ድረስ እንዲጠበቅ እዘዝ አሉት። ⁶⁵ ጲላጦስም፦ ጠባቆች አሉአችሁ፤ ሄዳችሁ እንዳወቃችሁ አስጠብቁ አላቸው። ⁶⁶ እነርሱም ሄደው ከጠባቆች ጋር ድንጋዩን አትመው መቃብሩን አስጠበቁ።
نمایش همه...
1
"ሮማውያን የሚሰቅሉትን ሰው ምን ያህል ዕርቃኑን እንደሚያዋርዱት አይሁድ በተግባር አይተው ስለሚያውቁ ጌታችን በዚህ በአሰቃቂ አሟሟት እንዲሞትና ‹እውነት እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ቢሆን ኖሮ ይህ ሁሉ መከራ ደርሶበት ይሰቀል ነበር?› እያሉ እንደ ማስረጃ በማቅረብ ‹ክርስቶስ አይደለም!› ለማለትና ክርስቲያኖችንም ለበዓል በመጣው ሕዝብ ፊት በጌታ መሰቀል ለማሸማቀቅ ነበር፡፡ እነርሱ ለማሸማቀቅ ብለው እንዲሰቀል ቢያደርጉም እኛ ግን በመሰቀሉ አፍረን አናውቅም፡፡ ‹‹የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን›› ፤ መመካት ቢያስፈልግም ‹‹ከጌታዬ ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ›› እያልን እንድናፍር ባዘጋጁት የጌታችን መሰቀል እንመካበታለን፡፡ (ገላ. ፲፮፥፲፬ ፩ቆሮ.፩፥፳፫)"
نمایش همه...