📚منهج السلف طريقنا الى الله 📚
رفتن به کانال در Telegram
↘️በዚህ ቻናል የሚተላለፉት ↘️በሱና ኡስታዞች የተቀሩ ደርሶች ↘️የሱና ኡስታዞች ሙሀደራዎች ↘️በመቀጠል አስተማሪ ፁሁፎች ➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴ https://t.me/htt_asselfya
نمایش بیشتر3 819
مشترکین
-524 ساعت
+1617 روز
+15530 روز
آرشیو پست ها
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የሚጮሁትን የማይኖሩ ጉዶች!
ክፍል - 2
~
ሰለፎች ሙብተዲዕ ጋር አብሮ ከመቀማመጥ የከለከሉባቸው መረጃዎች በተጨባጭ አሉ። በርግጥ ከሰለፎች ከዚህ የተለየ ይዘት ያላቸው መረጃዎችም በተጨባጭ አሉ። ይህም ጉዳዩ 2 ሲደመር 2 ይሆናል አራት አይነት በጥሬው የሚያዝ እንዳልሆነ ይጠቁማል። (ራሱን ችሎ እመለስበታለሁ ኢንሻአላህ። እስከዚያ እንደለመዱት ይጩሁ።)
ለጊዜው ግን አንድ ነገር ላቅርብ። ያያዝኳቸውን ምስሎች ተመልከቱ። የመጀመሪያው ምስል ላይ በሰማያዊ የተጠቆመው፣ 2ኛው ላይ ደግሞ በቀይ የተጠቆመው የነሱ ሰዎች ናቸው።
ሙብተዲዕ ጋር ስለ መቀማመጥ ሰርክ የሚጮሁ ሰዎች የራሳቸው መስለሐ ያለበት ቦታ ግን እንዲህ ይጣዳሉ። የመጀመሪያው የባለፈው ረመዷን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በቅርቡ የተደገመ ነው። ምስሉ ሲሰራጭ ጊዜ "ሸይኽ ፉላን ሰርግ ላይ መገኘት ይቻላል ብለዋል" የሚል ማመሀኛ አምጥተዋል።
1ኛ ነገር ይሄ ሰርግ አይደለም አታምታቱ።
2ኛ ነገር ሰርግስ ቢሆን ሴቶች ጋር ተቀላቅሎ መቀመጥ ይቻላል? (በቀይ የሸፈንኩት ሴቶች ናቸው። ቪዲየዎቹ ላይ ደግሞ በሰፊው ማየት ይቻላል።) ደግሞ አያፍሩም ይህንን ዘገባ ግድግዳቸው ላይ ይለጥፋሉ።
በተጨማሪም ዩሱፍ አሕመድም (ባህር ዳር) ከሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ዘህረዲን ጋር ተቃቅፎ ሞቅ አድርጎ ሰላምታ ሲለዋወጥ ነበር። ቀደም ብሎም ከላይ ከሚታዩት ጋር ባንድ ላይ ፎቶ ተነስቷል።
በነገራችን ላይ ክፍለ ሃገር ላይ የመጅሊስ መዋቅር ውስጥ የገቡ አሉ። እሱን የምመጣበት ጊዜ አለኝ ፣ ኢንሻአላህ።
እና ቀመራችሁ እንዴት ነው? መለኪያችሁ ስሜት ብቻ ነው። የሰለፎች ንግግሮች የሚጠቀሱት እንዲሁ ለሽፋን ያህል ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
የሚጮሁትን የማይኖሩ ጉዶች!
ክፍል - 1
~
ወንድማችን ሳዳት ከማል የነዚህን ከራሳቸው ጋር እንኳ የማይግባቡ ጉዶች የተሳከረ አካሄድ ሲነቅፍ ጊዜ "በጀርሕ እና ተዕዲል ዒልም ላይ ተሳለቀ" ብለው ላንቃቸው እስኪበጠስ ሲጮሁ ነበር። የተቸው የነሱን ቅጣንባሩ የጠፋው አካሄድ እንደሆነ ጠፍቷቸው አይደለም። ሆነ ብለው ጩኸታቸው እንዲደምቅላቸው እና ቂላቂሎችን ለመጥለፍ አላማ ነው በዚያ መልኩ ያቀረቡት። ይሄው የራሳቸው ሰው በነብዩ ﷺ ሐዲሥ ላይ ሲሳለቅ ስሙት። (ሂሳቡ የራሳችሁ ነው።)
ደግሞ አያፍሩም ይስቁለታል!
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ኢኽ^ዋንን በጨረፍታ፣ በዑለማዎች እይታ
~
ልብ በሉ! የማቀርበው የዑለማኦችን ንግግር እንጂ የራሴን አይደለም። ይህንን የማሳስበው ኢኽዋን ሲነካ ደርሰው አራስ ነብር ለሚሆኑ አካላት ለአፍታ ቆም ብለው ጉዳዩን እንዲያጤኑት ለማስታወስ ነው። አብዛኞቹ ኢኽዋን ሲነካ የሚንጨረጨሩ ወገኖቻችን በተሳሳተ ስብከት ስለተሞሉ እንጂ ለሐቅ ጥላቻ ኖሯቸው አይደለም። ስለዚህ ጉዳዩን ከተለያዩ አቅጣጫዎች እንዲመለከቱ በማገዝ ከሰመመናቸው እንዲነቁ መስራት ያስፈልጋል። ከነዚህ መንገዶች ውስጥ አንዱ ደግሞ የዑለማእ ንግግሮችን ማሳየት ነው። በኢኽዋን ክፉ ስብከት ተበክለው ዑለማኦችን እስከመወንጀል የደረሱ ቢኖሩም ዛሬም ድረስ ለታላላቅ የሱና ዑለማኦች ክብር ያላቸው ወገኖቻችን ቀላል አይደሉም። ወደ ዑለማኦቹ ንግግር አልፋለሁ።
1. አሕመድ ሻኪር (ግብፃዊ)፡-
“የሸይኽ ሐሰን አልበና እና የሙስሊም ወንድማማቾቹ ንቅናቄ የኢስላማዊ ደዕዋን ወደ አፍራሽ የጥፋት ደዕዋ የገለበጡ ናቸው። ኮሙኒስቶች እና አይሁዳውያን እንደሚረዱት በተጨባጭ እናውቃለን።” [ሹኡኑ ተዕሊም ወልቀዷእ፡ 48]
2. ኢብኑ ባዝ፡-
“አላህ መልካም ይዋልልዎትና ህዝቦቼ ወደ 73 ቡድኖች ይከፋፈላሉ። አንዷ ስትቀር ሁሉም የእሳት ነው የሚለውን የነብዩ ﷺ ሐዲሥ መሰረት በማድረግ ሺርካ ሺርክና ቢድዐዎች ያለባቸው የተብሊግ ቡድን እና ቡድንተኝነትና በመሪዎች ላይ በማመፅ ሰሚና ታዛዥ ባለመሆን ልዩነት የሚፈጥሩት ኢኽዋነል ሙስሊሚን እነዚህ ሁለት አንጃዎች ከጠፊዎቹ አንጃዎች ውስጥ ይካተታሉን?”
መልስ፡- ከ72ቱ ውስጥ ይገባሉ። የአህሉ ሱናን ዐቂዳ የጣሰ ከ72ቱ ውስጥ ይገባል። “ህዝቦቼ” ሲሉ የተፈለገው ለጥሪያቸው አዎንታዊ መልስ የሰጡትና እሳቸውን መከተልን ያንጸባረቁትን ነው። እነዚህም 73 ናቸው። የምትድነዋ ያቺ የተከተለቻቸውና በዲናቸውም ላይ የፀናችው ናት። በ72ቱ ውስጥ ግን ከ ሃ ዲም ይኖራል፤ ወንጀለኛ ይኖራል። ሙብተዲዕም ይኖራል። ብዙ ክፍል ነው።
ጠያቂ፡- ስለዚህ እነዚህ ሁለት አንጃዎች ከ72ቱ (ጠፊ አንጃዎች) ውስጥ ይገባሉ ማለተ ነው?”
ኢብኑ ባዝ፡- አዎ! ከ72ቱ ውስጥ ናቸው።” [ሸርሑል ሙንተቃ የካሴት ቅጂ]
ይሄ ፈትዋ ከመሞታቸው ሁለት አመት ወይም ከዚያ ባነሰ ጊዜ ጧኢፍ ውስጥ የተናገሩት ነው።
3. ሸይኽ ሙቅቢል አልዋዲዒይ (የመናዊ)፡-
ጥያቄ፡- በዘመናችን የሚገኙት የሱሩሪያና የኢኽ^ዋን ቡድኖች ከሱና ከሚወጡ ቡድኖች ውስጥ ናቸውን?”
መልስ፡- ከአህሉ ሱና አይቆጠሩም። ክብረ ቢስ ናቸው። የሚቀረው በተናጠል አባላቶቻቸው ላይ ብይን መስጠት ነው። አባሎቻቸው ላይ በተናጠል ብይን መስጠት አንችልም። ምክንያቱም አላዋቂ መሀይም ሊሆን ይችላልና። የኢኽ^ዋንና የሱሩሪያን ሰበካ የሚያውቅ ወደዚያ የሚጣራና ለነሱ በጭፍን የሚሞግት የሆነው ቁንጮ ግን እሱ ከምትድነዋ አንጃ ውስጥ አይደለም ልንል ይቻለናል።” [ቱሕፈቱል ሙጂብ፡ 10]
ጥያቄ፡- ከኢኽ^ዋን አልሙስሊሚን አንፃር የአህሉ ሱና ወልጀማዐ አቋም ምን ሊሆን ይገባል?”
መልስ፡- ከኢኽ^ዋን አልሙስሊሚን አንፃር የአህሉ ሱና ወልጀማዓ አቋም መንገዳቸው የፈጠራ መንገድ እንደሆነ ይፈርዳሉ። በተናጠል አባላቱ ዘንድ ስንመጣ መንገዱን ካወቀ በኋላ የሚፀናበትም እንዲሁ ሙብተዲዕ ነው። መንገዱን ሳያውቅ እንዲሁ ኢስላምንና ሙስሊሞችን እረዳለሁ ብሎ የሚያስብ ግን እንደ ስህተተኛ ይቆጠራል።” [ቱሕፈቱል ሙጂብ፡ 10]
ሐሰን አልበና እና ሰይድ ቁጥብ ወደ አላህ በሚደረገው ጥሪ ላይ ኢማሞች (መሪዎች) ናቸው የሚል አለ” ተብለው ሲጠየቁ “አዎ ኢማሞች ናቸው። ነገር ግን ኢማምነታቸው ለቢድዐ ባለቤቶች ነው…” ብለው ነው የመለሱት።
4. ሸይኽ ፈውዛን
ጥያቄ፡- እነዚህ አንጃዎች ከ72ቱ ጠፊ አንጃዎች ውስጥ ይገባሉን?
መልስ፡- አዎ። ወደ ኢስላም ራሱን ከሚያስጠጋ ውስጥ በደዕዋ ወይም በዐቂዳ ወይም በሆነ የኢማን መሰረቶች ውስጥ የአህሉ ሱና ወልጀማዐን ዐቂዳ የሚጣረስ ሁሉ ከ72ቱ አንጃዎች ውስጥ ይገባል። ዛቻውም ይመለከተዋል። በተቃርኖው ልክ ውግዘትና ዛቻም ይኖረዋል።” [አልአጅዊባ]
5. ሸይኽ ዐብዱል ሙሕሲን አልዐባድ
ስለተብሊግና ኢኽ^ዋን ቡድኖች ሲጠየቁ እንዲህ ብለው መልሰዋል፡-
እነዚህ የተለያዩ አዳዲስ ቡድኖች መጤዎች ናቸው። በ14ኛው ክ/ዘመን ነው የተወለዱት። … ለምሳሌ የኢኽዋን ቡድን ከነሱ ዘንድ የገባ ወዳጃቸው ነው። ይወዳጁታል። ከነሱ ያልሆነን ከሱ ተቃራኒ ይሆናሉ። ከነሱ ጋር ከሆነ ግን ቆሻሻ ከሆኑ የአላህ ፍጡሮች ቢሆንም፣ ራ*ፊ*ዳ (ሺዐ) ቢሆንም ወንድማቸው ወዳጃቸው ነው። ለዚህም ነው አካሄዳቸው ያለፈ ያገደመን የሚሰበስበው። ሶሐባን የሚጠላ ራ*ፊ*ዲ ለምን አይሆንም?!...” [ፈታወል ዑለማእ ፊልጀማዓት ወአሠሪሃ ፊ ቢላዲል ሐረመይን]
6. ሷሊሕ ኣሊ ሸይኽ
የኢኽ^ዋን አልሙስሊሚን ቡድንን በተመለከተ ጎላ ካሉ መታወቂያዎቻቸው ውስጥ አንዱ ትክክለኛ ማንነታቸውን መደበቅ፣ መለዋወጥ፣ ይጠቅመናል ብለው የሚያስቡት ዘንድ መቀራረብ፣ ትክክለኛ ገፅታቸውን ግልፅ አለማውጣት ነው። ማለትም በሆነ በኩል ሲታይ ባ*ጢ*ኒ*ያ ናቸው።…
ሌላኛው ኢኽዋኖችን ከሌሎች የሚለያቸው እነሱ ሱናን አያከብሩም። የሱና ሰዎችንም አይወዱም። ምንም እንኳን ይህንን አደባባይ ባያወጡትም። ግና በተጨባጭ ሱናን አይወዱም። ወደሱና ሰዎችም አይጣሩም። ..” [ፈታወል ዑለማእ ፊልጀማዓት ወአሠሪሃ ፊ ቢላዲል ሐረመይን] የቻለ ሙሉውን ይስማ።
ይህንን እንደ ሰደድ እሳት የተሰራጨ ብልሹ አስተሳሰብ የዑለማዎችን ፈትዋዎች በማጣቀስ፣ የኢኽ^ዋኖች ከባባድ የዐቂዳ ጥፋቶችን ሚዛናዊ የሆነና ለዐቂዳው ዋጋ የሚሰጥ ሰው አይቶ እንዲፈርድ በማቅረብ ማጋለጥ ያስፈልጋል። አቡበክር ብኑ ዐያሽ ረሒመሁላህ “ሱኒይ ማነው?” ተብለው ሲጠየቁ ሱኒይ ማለት “ስሜቶች (ቢድዐዎች) ሲወሱ (ሲጋለጡ) ለየትኛዋም ወግኖ የማይቆጣ ነው” ይላሉ። [አሸሪዐህ፡ ቁ.፡ 2112]
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ የካቲት 02/2009)
* የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
* የዋትሳፕ ቻናል፦
https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M
* ፌስቡክ
https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የኮርስ እና የሙሐደራ ፕሮግራም በጂንካ ጃሚዑ-ሰላም መስጂድ‼️
👉ነገ ቅዳሜ ጥር 18, 2016 E.C እና እሁድ ጥር 19, 2016 E.C 🪐በጂንካ ከተማ 🕌ጃሚዑ-ሰላም መስጂድ 🏝 የኮርስና የሙሐደራ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል።
🎤የኮርስ ፕሮግራሙ በሁለት ወንድሞች የሚቀርብ ሲሆን፤ ዝርዝሩም እንደሚከተለው ይሆናል።
1) 📖መንዘመቱ አቢ ኢስሃቅ ኢልቢሪ እና ላሚያ
🎤በወንድም አብዱረዛቅ ባጂ
قصيدة أبي إسحاق الألبيري(التائية) و لامية شيخ الإسلام ابن تيمية
الأخ عبد الرزاق الباجي الشافعي
2) 📖ቀዋዒዱል አርበዓህ:
🎤በኡስታዝ አብዱናሲር መኑር አልጃቢሪ
القواعد الأربع
الأستاذ عبد الناصر منور
3) ልዩ ልዩ መሐደራዎች
🎤 በወንድም ኸድር ነጅሙ
አድራሻ:ጂንካ ከተማ ጃሚዑ-ሰላም መስጂድ::
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ብትኖር ይሻልሃል
~
ህይወት ውድ ነች። የጌታህን ውድ አደራ ጠብቅ። የረባ ትርጉም በሌለው ጉዳይ ላይ አጉል መስዋእትነት አትክፈል። በደመ ነፍስ እየተጓዝክ የማንንም ሰላም አታውክ። በህዝብ ስም እየማልክ የህዝብ ሰላም አትንሳ። በህዝብ ስም እያነባህ የህዝብ ሐቅ አትንካ።
ግዴለህም በጊዜ ተመከር። እምቢ ካልክ ግን መከራ ይመክርሃል። እወቅ! የግፍ ፅዋ ያስከፍላል። የሰው እንባ ከባድ ነው። ከኣኺራ በፊት ዱንያ ላይ አሳፋሪና አዋራጅ ፍፃሜ ላይ ይጥላል። ከሰመመንህ በጊዜ ንቃ። በራስህ ጩኸት አትደንቁር። እምቢ ካልክ አምሳ አጣሁ ብለህ ለያዥ ለገናዥ ስታስቸግር መቶው ይርቅሃል። እምቢ ካልክ የለመነህን ተቆርቋሪ ምክር ለምነህ ታጣዋለህ። የተሳፈርክበት ባቡር አቅጣጫው ሌላ ነው። ካለምክበት ላትደርስ ጉዞህን አትቀጥል። ሳትርቅ ውረድ። ግዴለህም ውረድ። ለህዝብ ስትል ውረድ። ለቤተሰብህ ስትል ውረድ። ለራስህ ስትል ውረድ። ጠብ የምታደርገው ላይኖር ህይወት አትክፈል። መኖርህ ለሚቆረቆሩልህ ሁሉ ትርፍ ነው። ሞትህ የቤተሰብ እዳ ነው።
ሃሳቤ #በተሳሳተና በማያዋጣ ትግል አጉል መስዋእትነት እየከፈልክ ላለኸው ሙስሊም ወንድሜ ነው! በቅንነት ላትረዳኝ በመልካም ላታስበኝ ምን አደከመኝ ማለት እችል ነበር። ግና ህይወትህ ያገባኛል ብዬ ነው መፃፌ። እንጂ ምን አገባኝ ማለት ማንን ያቅታል? አላህ ማስተዋሉን ያድልህ።
Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
ሒልየቱ ጧሊቢል ዒልም
ክፍል - 10
የሱና ብርሃን ትምህርት ቤት ግሩፕ ላይ በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር በየ ሳምንቱ የሚሰጥ ትምህርት።
የቴሌግራም ቻናል፡‐
https://t.me/fejir_tube
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
تزوج عليها زوجة (ثانية)
فرفعت عليه قضية لتطلب الطلاق من زوجها (الشاب)
فخلعها القاضي..
ثم تزوجت برجل (كبير سن) لتكون الزوجة الثالثة!!!
.
بعض النساء هداهن الله ترفض التعدد وتطلب الطلاق، فإذا طلقت إذا بها بعد سنة من جلوسها عند أهلها، تقبل برجل متزوج!..
.
وأخرى:
رفضت الزواج عليها وتطلقت، ثم قبلت أن تتزوج رجلا متزوجًا، وبالسر.. (مسيار)!!
منقول
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
እምነታችንን ለመማር ጊዜ ይኑረን
~
ሑዘይፈቱ ብኑል የማን - ረዲየላሁ ዐንሁ - እንዲህ ይላሉ፦
لاتضرك الفتنة ما عرفت دينك، انما الفتنة اذا اشتبه عليك الحق والباطل فلم تدرِ ايهما تتبع، فتلك الفتنة.
"ሃይማኖትህን እስካወቅክ ድረስ ፈተና አይጎዳህም። ፈተና የሚሆነው እውነትና ሃሰት ሲምታታብህና የቱን መከተል እንዳለብህ ካላወቅክ ነው። እሱ ነው ፈተና ማለት!"
[ሙሶነፉ ኢብኒ አቢ ሸይባህ፡ 15/70]
Ibnu Munewor
=
* የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
* የዋትሳፕ ቻናል፦
https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M
* ፌስቡክ
https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
በዐቂዳ ጉዳይ በዚህ ዘመን የሚነሱ ንትርኮችን አይቶ መደናገር አይገባም። ቀደም ባለው ዘመን የተዘጋጁ ከሶሐቦች ጀምሮ የመልካም ቀደምቶችን አቋም በማወቅ መገላገል ይቻላል። ይህንን ጉዳይ አጉልተው የሚያሳዩ የቀደምት ከታቦች ብዙ ናቸው። ጥቂቱን ለመጠቆም እነዚህን ኪታቦች መመልከት ይቻላል:-
١ — «الرد على الجهمية والزنادقة» لأحمد بن حنبل (٢٤١ هـ) رحمه الله.
٢ — «خلق أفعال العباد» للبخاري (٢٥٦ هـ) رحمه الله.
٣ — «الرد على الجهمية» لعثمان الدارميّ (٢٨٠ هـ) رحمه الله.
٤ — «النقض على بشر المَريسي» للدارمي (٢٨٠ هـ) رحمه الله.
٥ — «الاختلاف في اللفظ والرد على الجهمية والمشبهة» لابن قتيبة (٢٧٦ هـ) رحمه الله.
٦ — «شرح السنة» لإسماعيل المزني المصري تلميذ الشافعي (٢٦٤ هـ) رحمهما الله.
٧ — «التوحيد» لابن خزيمة (٣١١ هـ) رحمه الله.
٨ — «حائية ابن أبي داود» لابن أبي داود (٣١٦ هـ) رحمه الله.
٩ — «الشريعة» لأبي بكر الآجري (٣٦٠ هـ) رحمه الله.
١٠ — «الإبانة عن شريعة الفرقة الناجية ومجانبة الفرق المذمومة» لابن بطة العكبري (٣٨٧ هـ) رحمه الله.
١١ — «الرد على الجهمية» لمحمد بن إسحاق بن منده (٣٩٥ هـ) رحمه الله.
١٢ — «التوحيد ومعرفة الأسماء والصفات» لابن منده رحمه الله.
١٣ — «شرح السنة» لابن أبي زمنين (٣٩٩ هـ) رحمه الله.
١٤ — «شرح أصول اعتقاد أهل السنة» اللالكائي (٤١٢ هـ) رحمه الله.
١٥ — «عقيدة أصحاب الحديث» لأبي عثمان الصابوني (٤٤٩ هـ) رحمه الله.
١٦ — «ذم الكلام وأهله» لأبي إسماعيل الأنصاري الهروي (٤٨١ هـ) رحمه الله.
١٧ — «الأربعين في دلائل التوحيد» للأنصاري الهروي رحمه الله.
١٩ — «الانتصار لأهل الحديث» لأبي المظفر السمعاني (٤٨٩ هـ) رحمه الله.
٢٠ — «الحجة في بيان المحجة» لأبي القاسم التيمي (٥٣٥ هـ) رحمه الله.
Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ማህበራዊ መገናኛዎችን ትርጉም ባለው መልኩ ለበጎ ተግባር እናውላቸው። እንማማር፣ እንመካከር፣ የደርስና የደዕዋ መድረኮችን እንለዋወጥ፣ እናስተዋውቅ፣ የታመመን እናሳክም፣ የተቸገረን እንርዳ፣ የጠፋን እናፋልግ፣ የስራ አቅጣጫዎችን፣ የቢዝነስ ሃሳቦችን፣ የጤና መረጃዎችን፣ በሌሎችም የዱንያም ይሁን የዲን ጉዳይ ላይ አስተዋፅዖ ባላቸው ጉዳዮች ላይ ድርሻ ይኑረን። ይህ ሲሆን ቆይታችን ትርጉም ይኖረዋል። ተሳትፏችንም ቢያንስ እንኳ በረካ ይኖረዋል። አላህ ያግዘን።
ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
خيرُ الناسِ أنفعُهم للناسِ
"ከሰው ሁሉ በላጭ ማለት ይበልጥ ለሰው ጠቃሚ የሆነው ነው።"
አልባኒይ "ሐሰን" ብለውታል።
Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ይድረስ ለአቶ "እንድሪስ" ባሉበት
~
ይህ መልእክት ከደረሰዎ ጊዜ ጀምሮ ስምዎት ኢድሪስ እንጂ እንድሪስ እንዳልሆነ አውቀው እንዲያስተካክሉ ይሁን። ከአክብሮት ጋር።
ስምዎት ማንን ተምሳሌት እንዳደረገ ያውቁ ዘንድም ይህቺን ቁርኣናዊ አንቀፅ እንዲያስተውሉ ተጋብዘዋል።
(وَاذْكُرْ فِي الْكِتَابِ إِدْرِيسَ ۚ إِنَّهُ كَانَ صِدِّيقًا نَبِيًّا)
"በመፅሐፉም ኢድሪስን አውሳ፡፡ እርሱ እጅግ እውነተኛ የሆነ ነቢይ ነበርና፡፡" [መርየም: 56]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የነሕው ደርስ ጥቆማ
~
በነሕው ርእስ ላይ ደጋግሜ የተከታተልኳቸውና እየተከታተልኳቸው ያሉ ምርጥ ትምህርቶችን ልጠቁማችሁ።
1. መትኑል ኣጁሩሚያህ - ዓዲል አልመሹሪ
2. አነሕው ሶጊር - ሱለይማን አልዑዩኒ
3. ሙተሚመቱል ኣጁሩሚያህ - ዓዲል አልመሹሪ
4. ቀጥሩ ነዳ - ሱለይማን አል ዑዩኒ
ማሳሰቢያ፦
1. አጁሩሚያን ስትማሩ የሙሐመድ ሙሕዩዲን ዐብዱል ሐሚድን “ቱሕፈቱ ሰኒያህ” ወይም የማሊክ አልመህዘሪን “አልሙምቲዕ ፊ ሸርሒል ኣጁሩሚያ” ኪታቦች ጎን በጎን ብታዩ ትጠቀማላችሁ።
2. የዓዲል አልመሹሪ ዱሩሶች የሰዓት ርዝማኔያቸው አጫጭር፣ ቁጥራቸው ግን ብዙ ነው። ነገር ግን አቀራረቡ ተማሪው ራሱን እንዲገመግም የሚያሳይ ነው። ጠያቂ አቀራረቡ የገባን መስሎን እንዳንሸወድ ያግዛል። በዚያ ላይ ከፍ ባለ ቁጥር ኢዕራቡንም እያለማመደ ነው የሚሄደው። የሸይኽ ሱለይማን አልዑዩኒ ደርሶችም እጅግ ምርጥ ናቸው። “አነሕው ሶጊር” ራሱ ያዘጋጃት አጭር ሪሳላ ስትሆን በጥሩ ሁኔታ ደጋግሞ አስተምሯታል። ኪታቧም፣ ደርሶቹም እጅግ ድንቅ ናቸው። ጀርቧቸው።
3. ሙተሚማን ስትማሩ ከመሹሪ ዱሩስ ጎን ለጎን በአሕመድ ብኑ ሣቢት አልወሷቢ የተዘጋጀችዋን “አዱረቱል በሂያህ” ሸርሕ በደንብ ተጠቀሙ። በጣም ምርጥ ምጥን ስራ ነች። የpdf ፋይል ከፈለጋችሁ በዚህ ታገኛላችሁ፦ https://t.me/c/1269314107/166871
4. የፈጀውን ጊዜ ቢወስድ ሳታቋርጡ በተከታታይ ደርሶቹን አዳምጡ፣ ሸርሖቹንም አንብቡ። ረዘም ላለ ጊዜ በመሃል ማቋረጥ ከባድ ተፅእኖ እንዳለው ከዓሊሞቹ ጥቆማ ባሻገር ከራሴ ድክመትና ገጠመኝ ያረጋገጥኩት ነው። ስለዚህ በሆነ ምክንያት ካቋረጣችሁ ከመነሻው ተመልሳችሁ ጀምሩ።
5. ጥሩ ማጫወቻ (player) አውርዱና በምትሄዱበት ቦታ ሁሉ ሆናችሁ አዳምጡ። እኔ MX Player ነው የምጠቀመው። የተለያዩ ደርሶችን ብትከፍቱ፣ አቋርጣችሁ ስትመለሱ ሁሉንም ከቆማችሁበት ታገኙታላችሁ። የመረዳት መጠናችሁን እያያችሁ የድምፁን ፍጥነት መጨመር መቀነስ ትችላላችሁ። ማውረድ ከፈለጋችሁ ይሄውና፦
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.mxtech.videoplayer.ad
6. ዱሩሶቹን ስትከታተሉ ገብቶናል ብላችሁ እንዳትዘናጉ። በደንብ ያልሰረፀ ከሆነ ለጊዜው ብትይዙትም የተወሰነ ርቃችሁ ስትመለሱ ብዙውን ጥላችሁት ልታገኙት ትችላላችሁ።
7. ከተጠቀሱት ኪታቦች ውጭም በሁለቱ ሸይኾች የተሰጡ ሌሎች የነሕው ዱሩሶች በቴሌግራም ቻነሎቻቸው ታገኛላችሁ። አቀራረባቸውም ምርጥ ነው። ከጀማሪ ከፍ የምትሉ እራሱ ከስር ጀምራችሁ አንዴ ብትሄዱባቸው ከአቀራረባቸው ሁነኛ የማስተማርን ስልት ትማሩባቸዋላችሁ።
8. የሸይኽ ሱለይማን ቻናል ይሄ ነው ፦ https://t.me/sboh3
የመሹሪን ከፈለጋችሁ ለብቻ ለብቻ ሰብሰብ ስለ ደረግኳቸው በዚህ ማግኘት ትችላላችሁ
- ኣጁሩሚያህ :- https://t.me/+2Z9s36PUUGE2MmY0
- ሙተሚማህ :- https://t.me/+najxxdrSRr4xZjJk
Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
قال العلامة ابن الجوزي:
"لَيْسَ الْعجب أَمر الْخَلِيل بِذبح وَلَده؛
وَإِنَّمَا الْعجب مُبَاشرَة الذّبْح بِيَدِهِ!".
.
📖: المدهش: (٨٧).
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
🔴قال سعيد بن جبير:
"أشهد أني سمعت ابن عباس يقول : إن القنوت في صلاةالصبح بدعة"
📚الدارقطني ١٧٠٤
