fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

📚منهج السلف طريقنا الى الله 📚

📚منهج السلف طريقنا الى الله 📚

رفتن به کانال در Telegram

↘️በዚህ ቻናል የሚተላለፉት ↘️በሱና ኡስታዞች የተቀሩ ደርሶች ↘️የሱና ኡስታዞች ሙሀደራዎች ↘️በመቀጠል አስተማሪ ፁሁፎች ➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴ https://t.me/htt_asselfya

نمایش بیشتر
3 819
مشترکین
-524 ساؚت
+1617 عوز
+15530 عوز
آرشیو پست ها
የሚጮሁትን የማይኖሩ ጉዶች! ክፍል - 1 ~ ወንድማችን ሳዳት ከማል የነዚህን ከራሳቸው ጋር እንኳ የማይግባቡ ጉዶች የተሳከረ አካሄድ ሲነቅፍ ጊዜ "በጀርሕ እና ተዕዲል ዒልም ላይ ተሳለቀ" ብለው ላንቃቸው እስኪበጠስ ሲጮሁ ነበር። የተቸው የነሱን ቅጣንባሩ የጠፋው አካሄድ እንደሆነ ጠፍቷቸው አይደለም። ሆነ ብለው ጩኸታቸው እንዲደምቅላቸው እና ቂላቂሎችን ለመጥለፍ አላማ ነው በዚያ መልኩ ያቀረቡት። ይሄው የራሳቸው ሰው በነብዩ ﷺ ሐዲሥ ላይ ሲሳለቅ ስሙት። (ሂሳቡ የራሳችሁ ነው።) ደግሞ አያፍሩም ይስቁለታል! = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor

የሚጮሁትን የማይኖሩ ጉዶች! ክፍል - 2 ~ ሰለፎች ሙብተዲዕ ጋር አብሮ ከመቀማመጥ የከለከሉባቸው መረጃዎች በተጨባጭ አሉ። በርግጥ ከሰለፎች ከዚህ የተለየ ይዘት ያላቸው መረጃዎችም በተጨባጭ አሉ። ይ
+1
የሚጮሁትን የማይኖሩ ጉዶች! ክፍል - 2 ~ ሰለፎች ሙብተዲዕ ጋር አብሮ ከመቀማመጥ የከለከሉባቸው መረጃዎች በተጨባጭ አሉ። በርግጥ ከሰለፎች ከዚህ የተለየ ይዘት ያላቸው መረጃዎችም በተጨባጭ አሉ። ይህም ጉዳዩ 2 ሲደመር 2 ይሆናል አራት አይነት በጥሬው የሚያዝ እንዳልሆነ ይጠቁማል። (ራሱን ችሎ እመለስበታለሁ ኢንሻአላህ። እስከዚያ እንደለመዱት ይጩሁ።) ለጊዜው ግን አንድ ነገር ላቅርብ። ያያዝኳቸውን ምስሎች ተመልከቱ። የመጀመሪያው ምስል ላይ በሰማያዊ የተጠቆመው፣ 2ኛው ላይ ደግሞ በቀይ የተጠቆመው የነሱ ሰዎች ናቸው። ሙብተዲዕ ጋር ስለ መቀማመጥ ሰርክ የሚጮሁ ሰዎች የራሳቸው መስለሐ ያለበት ቦታ ግን እንዲህ ይጣዳሉ። የመጀመሪያው የባለፈው ረመዷን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በቅርቡ የተደገመ ነው። ምስሉ ሲሰራጭ ጊዜ "ሸይኽ ፉላን ሰርግ ላይ መገኘት ይቻላል ብለዋል" የሚል ማመሀኛ አምጥተዋል። 1ኛ ነገር ይሄ ሰርግ አይደለም አታምታቱ። 2ኛ ነገር ሰርግስ ቢሆን ሴቶች ጋር ተቀላቅሎ መቀመጥ ይቻላል? (በቀይ የሸፈንኩት ሴቶች ናቸው። ቪዲየዎቹ ላይ ደግሞ በሰፊው ማየት ይቻላል።) ደግሞ አያፍሩም ይህንን ዘገባ ግድግዳቸው ላይ ይለጥፋሉ። በተጨማሪም ዩሱፍ አሕመድም (ባህር ዳር) ከሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ዘህረዲን ጋር ተቃቅፎ ሞቅ አድርጎ ሰላምታ ሲለዋወጥ ነበር። ቀደም ብሎም ከላይ ከሚታዩት ጋር ባንድ ላይ ፎቶ ተነስቷል። በነገራችን ላይ ክፍለ ሃገር ላይ የመጅሊስ መዋቅር ውስጥ የገቡ አሉ። እሱን የምመጣበት ጊዜ አለኝ ፣ ኢንሻአላህ። እና ቀመራችሁ እንዴት ነው? መለኪያችሁ ስሜት ብቻ ነው። የሰለፎች ንግግሮች የሚጠቀሱት እንዲሁ ለሽፋን ያህል ነው። = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor

የሚጮሁትን የማይኖሩ ጉዶች! ክፍል - 1 ~ ወንድማችን ሳዳት ከማል የነዚህን ከራሳቸው ጋር እንኳ የማይግባቡ ጉዶች የተሳከረ አካሄድ ሲነቅፍ ጊዜ "በጀርሕ እና ተዕዲል ዒልም ላይ ተሳለቀ" ብለው ላንቃቸው እስኪበጠስ ሲጮሁ ነበር። የተቸው የነሱን ቅጣንባሩ የጠፋው አካሄድ እንደሆነ ጠፍቷቸው አይደለም። ሆነ ብለው ጩኸታቸው እንዲደምቅላቸው እና ቂላቂሎችን ለመጥለፍ አላማ ነው በዚያ መልኩ ያቀረቡት። ይሄው የራሳቸው ሰው በነብዩ ﷺ ሐዲሥ ላይ ሲሳለቅ ስሙት። (ሂሳቡ የራሳችሁ ነው።) ደግሞ አያፍሩም ይስቁለታል! = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor

የሚጮሁትን የማይኖሩ ጉዶች! ክፍል - 1 ~ ወንድማችን ሳዳት ከማል የነዚህን ከራሳቸው ጋር እንኳ የማይግባቡ ጉዶች የተሳከረ አካሄድ ሲነቅፍ ጊዜ "በጀርሕ እና ተዕዲል ዒልም ላይ ተሳለቀ" ብለው ላንቃቸው እስኪበጠስ ሲጮሁ ነበር። የተቸው የነሱን ቅጣንባሩ የጠፋው አካሄድ እንደሆነ ጠፍቷቸው አይደለም። ሆነ ብለው ጩኸታቸው እንዲደምቅላቸው እና ቂላቂሎችን ለመጥለፍ አላማ ነው በዚያ መልኩ ያቀረቡት። ይሄው የራሳቸው ሰው በነብዩ ﷺ ሐዲሥ ላይ ሲሳለቅ ስሙት። (ሂሳቡ የራሳችሁ ነው።) ደግሞ አያፍሩም ይስቁለታል! = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor

የሚጮሁትን የማይኖሩ ጉዶች! ክፍል - 1 ~ ወንድማችን ሳዳት ከማል የነዚህን ከራሳቸው ጋር እንኳ የማይግባቡ ጉዶች የተሳከረ አካሄድ ሲነቅፍ ጊዜ "በጀርሕ እና ተዕዲል ዒልም ላይ ተሳለቀ" ብለው ላንቃቸው እስኪበጠስ ሲጮሁ ነበር። የተቸው የነሱን ቅጣንባሩ የጠፋው አካሄድ እንደሆነ ጠፍቷቸው አይደለም። ሆነ ብለው ጩኸታቸው እንዲደምቅላቸው እና ቂላቂሎችን ለመጥለፍ አላማ ነው በዚያ መልኩ ያቀረቡት። ይሄው የራሳቸው ሰው በነብዩ ﷺ ሐዲሥ ላይ ሲሳለቅ ስሙት። (ሂሳቡ የራሳችሁ ነው።) ደግሞ አያፍሩም ይስቁለታል! = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor

የሚጮሁትን የማይኖሩ ጉዶች! ክፍል - 4 ~ ያያያዝኩት የባህሩ ተካ ንግግር ነው። የውሸት እርከኑን በዚህ መጠን ከፍ አድርጎታል። ውሸቱን ሲለማመደው ጊዜ "አንባቢ ይታዘበኛል" የሚለውንም ትቶታል። እንዲያው አንድ ሰው መስሎት ተሳስቶ ቢናገር ይሁን። ይሄ ሐያእ የቀለለው ፍጡር ግን በምን መልኩ ሰው ላይ እንደሚዋሽ ተመልከቱ። ሳዳት ነው ወደነዚህ አካላት የሚጣራው? በሐዲሥ እንደመጣው ከሙናፊቅ ምልክቶች ውስጥ ሁለቱ ሲያወሩ መዋሸት እና በሙግት ላይ አመፀኝነት ወይም ገልብጦ መወንጀል ነው። በነዚህ አጥፊዎች ላይ ረድ መስጠት ነው ወደነሱ መጣራት ተብሎ የሚገለፀው? ጥላቻ አናቱ ላይ ወጥቶ በትክክል ማየት እንዳይችል ጋርዶታል። በረድ ስም እየዋሸ መለጠፍ ጣፋጭ ምግብ ሆኖለታል። እጅ እጅ የሚል ፅሁፉን ውሸት ጣል ሲያደርግበት ውበትና ጥንካሬ የሚጨምር ይመስለው እንደሁ አላውቅም። "የሰካራም ግጥም ሁሌ ቅዳ ቅዳ" እንዲሉ ወጥሮ የውሸት አውቶማቲክ መተኮሱን ተያይዞታል። ረድ ማለት የጠሉት ሰው ላይ የፈለጉትን መለጠፍ ሆኗል ባህሩ ዘንድ። ሰው እንዴት በዚህ ደረጃ ውሸትን ስራዬ ብሎ አጥብቆ ይይዛል? ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ وإِيَّاكُمْ والْكَذِبَ، فَإِنَّ الْكَذِبَ يَهْدِي إِلَى الْفُجُورِ، وإِنَّ الْفُجُورَ يَهْدِي إِلَى النَّارِ، ومَا يَزَالُ الرَّجُلُ يَكْذِبُ ويَتَحَرَّى الْكَذِبَ حَتَّى يُكْتَبَ عِنْدَ اللَّهِ كَذَّابًا “አደራ ውሸትን ተጠንቀቁ! ውሸት ወደ ጥመት ይመራል፤ ጥመት ደግሞ ወደ እሳት ይመራል፡፡ አንድ ሰው ሲዋሽና ውሸትም ላይ ሲያተኩር አላህ ዘንድ ውሸታም ተብሎ ይመዘገባል።” [ቡኻሪይ እና ሙስሊም] ሳዳትን በማጠልሸት ላይ እንቅልፍ ከምታጡ ራሳችሁን ከዚህ የውሸት ሱስ አውጡ። ሳዳት እናንተን ከነ ንዝንዛችሁ እርግፍ አድርጎ ትቶ አነሰም በዛም የራሱ ስራ ላይ ነው ያለው። ደግሞም በተለይ ተራውን ህዝብ በማንቃት ላይ ባለው አስተዋፅኦ አንዳችሁ እንኳ የሚስተካከል ቀርቶ የሚቀርብ ነገር የለውም። የራሳችሁን ድርሻ ባግባቡ እንደመወጣት ሰዎች የሱን ትምህርት እንዳይከታተሉ ጥላሸት መቀባትን ጂሃድ አድርጋችሁታል። ይሄ ነው የናንተ ስኬት። ባህሩ ተካ እንደምታዩት ወንድማችን ሳዳትን ወደ "ቲክ – ቶክ መንደር ወርዶ ወጣቱን ወደ ዮኒ ማኛና ኢክራም አውቶሞቲቭ" ይጣራል እያለ ነው። * ሳዳት ከአጥፊዎች ነው ያስጠነቀቀው። ባህሩ ደግሞ አጥፊዎቹን ጥሎ ሳዳትን መዝለፍ ላይ ነው የተጠመደው። ከአጥፊዎች ማስጠንቀቅ ወደነሱ መጣራት ከሆነ እንዳበደ ውሻ ሁሉን የምትናከሱት እናንተ አጥፊዎች ወደምትሏቸው እየተጣራችሁ ኖሯል ለካ? መቼም በራሳችሁ ጩኸት ስለደነቆራችሁ ሂሳባችሁ ምን እንደሚሰጥ አይገባችሁም። * ምናልባት አጥፊዎቹን ፊት ለፊት ተገኝቶ መምከሩን ከሆነ ወደነሱ መጣራት የምትለው ይሄ ምን ያህል በልብህ ያረገዝከው ጥላቻ ነገሮችን የመረዳት አቅምህንም እንዳሽመደመደው ነው የሚያሳየው። እንዲያው አቀራረቡ ላይ ሂስ አለኝ ብትል እንኳ እንዳንተ አይነቱ በቆሻሻ የብሄር ካባ ተጀቡኖ የጉራጌ ካፊ'ሮች ጋር አንድነት ስለማድረግ የሚሰብክ ሰው ሂስ የመሰንዘሩን ድፍረት እንዴት ነው የሚያገኘው? የጥላቻ ብቅል ይህን ያክል ያሰክራል ለካ! የሚገርመው በዚህ መልኩ አይኑን በጨው አጥቦ እየዋሸ "ውሸታም" ተባልኩ ብሎ ሲብሰው ማየት ነው። የእውነት ህሊና ካለህ ከመባልህ ይልቅ መሆንህ ያስጨንቅህ። ያለበለዚያ ነገሮችን እየገለበጥክ ማየትህን ትቀጥላለህ። ጠቢቡ ኢብኑል ቀዪም ረሒመሁላህ ምን እንደሚሉ ተመልከት:- إياك وَالْكذب فَإِنَّهُ يفْسد عَلَيْك تصور المعلومات على مَا هِيَ عَلَيْهِ وَيفْسد عَلَيْك تصورها وَتَعْلِيمهَا للنَّاس فَإِن الْكَاذِب يصور الْمَعْدُوم مَوْجُودا وَالْمَوْجُود مَعْدُوما وَالْحق بَاطِلا وَالْبَاطِل حَقًا وَالْخَيْر شرا وَالشَّر خيرا فَيفْسد عَلَيْهِ تصَوره وَعلمه عُقُوبَة لَهُ. "ውሸትን ተጠንቀቅ። እሱ መረጃዎችን ባሉበት ሁኔታ (በትክክለኛ ቅርፃቸው) የመረዳት አቅምህን ይበክልብሃል። በተጨባጭ መሳልና ማሳወቅንም እንዲሁ ያበላሽብሃል። ውሸታም የሌለውን እንዳለ፣ ያለውን እንደሌለ፣ እውነቱን ሃሰት፣ ሃሰቱን እውነት፣ ኸይሩን ሸር፣ ሸሩን ደግሞ ኸይር አድርጎ ገልብጦ ያቀርባል። በውሸቱ ይቅቀጣ ዘንድ የመረዳት አቅሙም እውቀቱም ይበላሽበታል።" [አልፈዋኢድ፡ 135] ውሸትን እንደ ፅድቅ ማየት የሚመጣው በዚህ ምክንያት ነው። "የማይበስል ጭንቅላት መብሰሉ ላይቀር የሰው ማገዶ ያስጨርሳል።" = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor

አሁን ሊፍት ይላል

የለተሞ መንጋ ~ እኛ በሸይኽ ረቢዕ ላይ ድንበር ማለፍ አይገባም እንላለን፣ ለካስ ሰዎቹ ሌላ ዓለም ነው ያሉት። ጭራሽ በሑሴን ሙሐመድ ላይ ድንበር እያለፉ ኖሯል። "የሐበሻው ኢብኑ ባዝ" ተብሏል ለካ
የለተሞ መንጋ ~ እኛ በሸይኽ ረቢዕ ላይ ድንበር ማለፍ አይገባም እንላለን፣ ለካስ ሰዎቹ ሌላ ዓለም ነው ያሉት። ጭራሽ በሑሴን ሙሐመድ ላይ ድንበር እያለፉ ኖሯል። "የሐበሻው ኢብኑ ባዝ" ተብሏል ለካ! ምናልባትም እንዲህ ዓይነቱ ቡድንተኝነት የወለደው ከንቱ ሙገሳ ይሆናል ልባቸውን አሳብጦ ገደል እየከተታቸው ያለው። አንደኛውንም "ሸይኹል ኢስላም" እያሉት እንደሆነ ሰምቼ ነበር። እውነት ይሆን? ከቅጥፈቱ በላይ የገረመኝ ጠሀ ኸዲር ይህንን አሳፋሪ ወሬ ቁም ነገር አድርጎ መለጠፉ ነው። ሰዎቹ ግን እኛ ከምንገምታቸውም በጣም የራቁ ናቸው። = * የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor

የለተሞ መንጋ ~ እኛ በሸይኽ ረቢዕ ላይ ድንበር ማለፍ አይገባም እንላለን፣ ለካስ ሰዎቹ ሌላ ዓለም ነው ያሉት። ጭራሽ በሑሴን ሙሐመድ ላይ ድንበር እያለፉ ኖሯል። "የሐበሻው ኢብኑ ባዝ" ተብሏል ለካ
የለተሞ መንጋ ~ እኛ በሸይኽ ረቢዕ ላይ ድንበር ማለፍ አይገባም እንላለን፣ ለካስ ሰዎቹ ሌላ ዓለም ነው ያሉት። ጭራሽ በሑሴን ሙሐመድ ላይ ድንበር እያለፉ ኖሯል። "የሐበሻው ኢብኑ ባዝ" ተብሏል ለካ! ምናልባትም እንዲህ ዓይነቱ ቡድንተኝነት የወለደው ከንቱ ሙገሳ ይሆናል ልባቸውን አሳብጦ ገደል እየከተታቸው ያለው። አንደኛውንም "ሸይኹል ኢስላም" እያሉት እንደሆነ ሰምቼ ነበር። እውነት ይሆን? ከቅጥፈቱ በላይ የገረመኝ ጠሀ ኸዲር ይህንን አሳፋሪ ወሬ ቁም ነገር አድርጎ መለጠፉ ነው። ሰዎቹ ግን እኛ ከምንገምታቸውም በጣም የራቁ ናቸው። = * የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor

አንድ ነጥብ ~ የትግራይ ህዝብ በጦርነቱ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት የሚታወቅ ነው። ሰሞኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳይ ሰዎች ከ67 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው እርዳታ ማድረጋቸው ጥሩ የድጋፍ ስራ መሆኑን አውስቼ "አላህ ጀዛቸውን ይክፈላቸው" ብል ይሄ ስሜት ያሰከረው መንጋ ሲንጫጫ ነበር። ከዚህ በፊት የመስጂድ ቦታ ለሰጡን አካላት ምስጋና ስገልፅ ምንም ያላሉት እነዚያ ሙስሊሞች ስላልሆኑ ነው። አንዳንድ ሰዎች ዘንድ "እናመሰግናለን፣ አላህ ይስጥልን" ማለት ለሙስሊሞች ሲሆን የቢድዐን አካል ማወደስ፣ የመንሀጅ መንሸራተት ሲሆን ለካፊሮች ሲሆን ግን ችግር የለውም። እንዲያውም እንደ ንቃት ነው የሚቆጠረው። ነገሮች እንዴት እየተያዙ እንደሆነ ቆም ብለን እናስተውል። በተረፈ የመጅሊስ ሰዎች አካሄድ እንከን የለሽ ነው የሚል አቋም የለኝም። ባደባባይ ከሚታዩ ችግሮቻቸው ውስጥ በአንድ ሁለቱ ላይ ከዚህ ቀደም በግልፅ ፅፌያለሁ። ለማንኛውም አንድ አካል ችግር ቢኖርበት እንኳ በመልካም ስራው ላይ "ጀዛሁላሁ ኸይራ" ማለት አቧራ የሚያስነሳ አይደለም። 1- ኢብኑ ባዝ - ረሒመሁላህ - ከሙሐመድ አልገዛሊ "መዐ'ላህ" ኪታብ በረጅሙ ከወሰዱ በኋላ መጨረሻ ላይ "ጀዛሁላሁ ኸይራ" ይላሉ። [ነቅዱል ቀውሚየቲል ዐረቢያ] [መጅሙዑ ፈታዋ፡1/317] 2- ሸይኹል አልባኒይም - ረሒመሁላህ - አሕመድ ዲዳትን ትልቅ ጂሃድ ላይ እንዳሉ በመግለፅ "ጀዛሁላሁ ኸይራ" ይላሉ። [ሲልሲለቱል ሁዳ ወኑር] 3- ሸይኽ ሙሐመድ ዐሊ ኣደምም እንዲሁ ከዩሱፍ አልቀርዳዊ "ፊቅሁ ዘካ" ኪታቡ ረዘም ያለ ክፍል ከወሰዱ በኋላ "ጀዛሁላሁ ኸይራ" ይላሉ። [ዘኺራ፡ 22/168] አለፍ ብለውም እንዲህ ሲሉ ስራውን ከማድነቅ ጋር ዱዓእ ያደርጋሉ:- انتهى ما كتبه الدكتور القرضاويّ شكر اللَّه سعيه، وهو بحثٌ نفيسٌ جدًا. የቀርዷዊ ማንነት የሚታወቅ ነው። አሁንም ሸይኹል አልባኒይ ለሙሐመድ አልገዛሊይ እና ዩሱፍ አልቀርዷዊይ አድናቆታቸውን ከገለፁ በኋላ ለቀርዷዊ "አላህ ይጠብቀው። ሙስሊሞችንም ይጥቀምበት" ብለዋል። [ጋየቱል መራም፡ 7] አልባኒይ የነዚህን አካላት ብልሹ አካሄድ በመተቸት የታወቁ ናቸው። ከመሆኑም ጋር "በመልካም ስራቸው" ላይ አላህ እንዲመነዳቸው ዱዓእ ሲያደርጉ እናያለን። መሰል አካሄድ ብንፈልግ ሌሎችም ጋር እናገኛለን። "ሙብተዲዕን ማድነቅ ይቻላል" እያልኩ አይደለም። ይልቁንም ነገሮችን መለየትና በልክ መያዝ እንልመድ እያልኩ ነው። ያያያዝኩት በሕሩ ተካ በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ላይ የነበረን ሁከት ተከትሎ የነበረውን ሂደት አስመልክቶ ርስቱ ይርዳውን፣ የፍትህ ሚኒስቴርን፣ አስተዋይና ሚዛናዊ ብሎ የገለፃቸውን ክርስቲያኖችን፣ የጉንችሬና የእነሞር አመራሮችን ያደነቀበትና ያመሰገነበት ነው። ለሽፋን ከሚቀርቡ ሰሞንኛ ግርግር ውጭ እነዚህ የተጠቀሱት አካላት ለአካባቢው ችግር ወይ ጠንሳሽ ናቸው። ወይ አፍራሽ ሚና የነበራቸው ናቸው። ወይ ደግሞ ኃላፊነታቸውን ባለመወጣት ችግሩ እንዲቀጥል ያደረጉ ናቸው። (የተነሳውን ነጥብ ጥለው በማስቀየስ ላይ እንደሚጠመዱ እጠብቃለሁ።) = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor

ደርስ ~ * ሪያዱ ሷሊሒን * ክፍል:- 1️⃣4️⃣4️⃣ * የኪታቡን ሶፍት ኮፒ (በ pdf ) በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ https://t.me/IbnuMunewor/3505 * የለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 426፣ باب استحباب قيام رمضان * የሚሰጥበት ቦታ፦ አሸዋ ሜዳ፣ መስጂደል ዋሊደይን * የሚሰጥበት ጊዜ:- ሐሙስ እና ጁሙዐ = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor

ኢስራእ እና ሚዕራጅ መቼ ተካሄደ? ~ ብዙ ሰዎች በተለይም ሱፍዮች አካባቢ ኢስራእ እና ሚዕራጅ ረጀብ 27 እንደተካሄደ ያምናሉ። ግና ይህን የሚያስረዳ ሶሒሕ ማስረጃ ማቅረብ አይችሉም ። ክስተቱ በምን ቀን፣ በምን ወር፣ በየትኛው አመት እንደተፈፀመ በውል አይታወቅም። በዚህም ሳቢያ የዑለማዎች ሐሳብ ተለያይቷል። ጊዜውን የሚጠቁም አንድም ሶሒሕ ማስረጃ በሌለበት ረጀብን እየጠበቁ የሚያከብሩ ሰዎች የሚገርሙ ናቸው። ረጀብ ነው የሚለውን "ግልፅ የሆነ ውሸት ነው" ብለው የገለፁት አሉ። አመቱን በተመለከተ ① ከሂጅራ በፊት ስድስት ወር ቀደም ብሎ፣ ② ከሂጅራ አንድ አመት በፊት ③ ከሂጅራ ከ 3 አመት በፊት፣ ④ ከሂጅራ ከ5 አመት በፊት፣ ⑤ ከመላካቸው በፊት፣ ወዘተ የሚሉ አሉ። ከሂጅራ ከ8 ወር በፊት፣ ከሂጅራ ከ11 ወር በፊት፣ ከሂጅራ ከ15 ወር በፊት፣ ከሂጅራ ከ17 ወር በፊት፣ ከሂጅራ ከ18 ወር በፊት፣ ከሂጅራ ከ20 ወር በፊት እና ሌሎችም። ወሩን በተመለከተነው ① ረቢዑል አወል ወር ነው የሚል ዘገባ አለ። [ጦበቃት ኢብኒ ሰዕድ: 1/213–214] ② ዙል ቂዕዳ ወር ያሉ አሉ። [አልቢዳያ ወኒሃያህ: 3/109] ③ ረጀብ ወር ነው ያሉ አሉ። ④ ረመዳን ነው ያሉም አሉ። ⑤ ረቢዑል ኣኺር ያሉም አሉ። ⑥ ሸዋል ወር ያሉም አሉ። ከነዚህ ውስጥ አመቱንም ወሩንም የሚጠቁም አንድም ሶሒሕ ማስረጃ የለም። ያሉት ማስረጃዎች በሙሉ ደካማ ናቸው። ስለዚህ ኢስራእና ሚዕራጅ አላህ ለነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የዋለው ትልቅ ተአምር ቢሆንም ጊዜው በትክክል አይታወቅም። ይህም በሱፍዮች እንደሚደረገው አመት እየጠበቁ ክስተቱን ማክበር ቀደምቶች ዘንድ እንዳልነበር በቂ ማስረጃ ነው። ሰለፎች ዘንድ ቢከበር ኖሮ ጊዜው በውል ይታወቅ ነበርና። (ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 16/2009) = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor

ሙሓደራ ክፍል 189 አዲስ ሙሓደራ ክፍል 01 ረድ በ ወሰን ተላላፊዎች ላይ የ ሚዳሰሱ ነጥቦች ለ አብነት 👇 ““የ አብዱል ሀሚድ አልለተሚይ እና  ሁሰይን ሙሀመድ ስህተቶች እና ግጭጭቶች…““ 🎤 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ሐቲም) https://t.me/UstazKedirAhmed

ደርስ ~ * ሪያዱ ሷሊሒን * ክፍል:- 1️⃣4️⃣3️⃣ * የኪታቡን ሶፍት ኮፒ (በ pdf ) በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ https://t.me/IbnuMunewor/3505 * የለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 421፣ ሐዲሥ ቁ. 1158 * የሚሰጥበት ቦታ፦ አሸዋ ሜዳ፣ መስጂደል ዋሊደይን * የሚሰጥበት ጊዜ:- ሐሙስ እና ጁሙዐ = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor

ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:- من أحبَّ أن يلحق بدرجة الأبرار ، فلينو في كل يوم نفع الخلق فيما يسر الله من مصالحهم على يديه. "የደጋጎች ደረጃ ላይ መድረስ የሚወድ በያንዳንዷ ቀን አላህ በሱ ሰበብ ባገራለት መጠን ፍጡራንን ለመጥቀም ያስብ።" [አልኢማኑል አውሰጥ: 1/609] = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor

ከየትኛውም አካል፣ በየትኛውም መልኩ የሚቀርብን እርምት በጥሩ ኒያ ባይሆን እንኳ ለኔ እስከጠቀመኝ ድረስ - ከምስጋና ጋር - ለመቀበል ዝግጁ ነኝ ኢንሻአላህ። የአቋም ስህተት ከሆነ እማርበታለሁ ፣ አቋሜንም አስተካክላለሁ። በቅጡ ያልታሰበበት የቃላት ስህተት ከሆነም አስፈላጊ በምለው መጠን አስተካክለሁ፣ ወይም አስወግደዋለሁ። በዚህም መሰረት ጠቅላዩ የመጣ ሰሞን ስለሱ ያኔ በደጋፊም በነቃፊም በኩል ሲራገብ በነበረው ጉዳይ ላይ በልክ እንድንሆን የፃፍኩት ፅሁፍ ፋይዳ-ቢስ እና አላስፈላጊ ቃል የያዘ በመሆኑ አስወግጀዋለሁ። رحم الله امرأ أهدى إلي عيوبي = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor

የሚጮሁትን የማይኖሩ ጉዶች! ክፍል - 6 {ረይስና ሱለይማን አሩሐይሊ ከመንሀጅ ውጭ ናቸው!} ~ ረይስን "እሱን ተወው" ፤ "ሙአኸዛ አለበት"፣ "የሱ ኢጅቲሃድ ነው ማለት፣ የሱለይማን አሩሐይሊ ኢጅቲሃድ ነው ማለት፣ .. ውድቅ ነው፣ ኤክስ ነው። ሙዕተበር የሆኑ ዓሊሞችን አምጣ። ... የነዚህ የነዚህን ተዋቸው። ከመንሀጅ ውጭ ናቸው።" ረይስ "ሚስኪን ነው።" ከዚህም በተጨማሪ ከውስጣቸው ረይስን በኢርጃእ የሚከሱት እንዳሉ በተጨባጭ አውቃለሁ። "የቢድዐ ሰዎች ምልክት የሱና ሰዎችን መንካት ነው" የሚለውን በመያዝ ሌሎች ላይ በተብዲዕ የሚዘምቱ ሰዎች ራሳቸው እንዳሻቸው ከመናገር አይመለሱም። ያያያዝኩት ድምፅ የለተሞ ድምፅ ነው። ያለቦታው ሰቃቅለው የጀርሕና ተዕዲል ዓሊም አድርገውት በዚህ መልኩ በድፍረት ይፈርዳል። ነጥቤ ረይስና ሱለይማን አሩሐይሊን አለመቀበሉ አይደለም። ረይስም፣ ሩሐይሊም፣ ረቢዕም፣ ፈውዛንም፣ ... ከነዚህ የበለጠም፣ ያነሰም ቢሆነ በጭፍን አንቀበልም። ታዲያ ርእስ እየመረጡ ሳይሆን አንድ ዓሊም ሌላውን ስላጎደፈ ራሱ በጭፍን ልንወስድ አይገባም። ማንም ቢሆን ያ ዓሊም። ረቢዕ ጋር ሲሆን የሚቀየር ነገር የለም። ረይስ ወይም ሌላ ሰው አንድ ዓሊም ላይ ያላግባብ ቢናገሩ እንደማንቀበለው ረቢዕ ወይም ሙሐመድ ብኑ ሃዲ አንድ ሰው ላይ ስለተናገሩም በጭፍን አንወስድም። የትኛውንም በሰለፊያ ካባ ተጠቅልሎ የሚቀርብ ቡድንተኝነት አሽቀንጥሮ መጣል ይገባል። የነዚህ ሰዎች ሁኔታ የሚገርመው ግን መንሀጁ ችግር አለበት ከሚሉት ረይስ ጋር እነ ጠሀ ኸዲር ጥብቅ ትስስር ያላቸው መሆኑ ነው። ቻናሉም ላይ ደጋግሞ ያሰራጭለታል። የመንሀጅ ችግር ካለበት ለምንድነው ከሱ ጋር የምትተባበሩት? ለናንተ ሲሆን ከሰለፊያ መንሀጅ ውጭ ካለ አካል ጋር መተባበር ይቻላል ማለት ነው? = https://t.me/IbnuMunewor