cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

የደጉ ሳምራዊ መልካምነት®

ይህ ትክክለኛ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት የቴሌግራም ቻናል ነው:: (በመ/ር ሲራክ ሰሎሞን) በዚህ የቴሌግራም ቻናል:- ➮አስተማሪ እና መንፈሳዊ ፅሁፎችን ➮የቅዱሳን ገድላት ➮ መዝሙሮችን ➮መንፈሳዊ ትምህሮቶችን ያገኛሉ። የመወያያ ግሩፕ: https://t.me/+QKiTJYGJvYpmNWM0 የዚህ ግሩፕ ዓላማ ለበጎ ምግባር ቃለ እግዚአብሔርን መማማር ነዉ::

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
726
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
+430 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

"ሰላም ለኪ ኦ እግዝእትየ..." እንደሚታወቀው ስምዖን ዘዓምድ እና ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ቅዱስ አባ ያዕቆብ ዘንጽቢን ሊቀጳጳሳት እግር ስር ቁጭ ብለው እንደተማሩ አስቀድሞ በተጻፈው የቅዱስ ኤፍሬም ታሪክ ተገልጿል። ይኽ ስምዖን ዘአምድ የተባለ አባት ቅዱስ ኤፍሬምን ቅዱስ ባስልዮስ ከፍሎ በሰጠው ሃገረ ስብከት በሚያስተምርበት ጊዜ ሊጠይቀው ይመጣና ቢያይ ቅዱስ ኤፍሬም ከሉቃስ ወንጌል ጸሎተ እግዝእትነ(የእመቤታችን ጸሎት) አውጥቶ እየደገመና "ሰላም ለኪ ኦ እግዝእትየ..." እያለ ሕዝቡን ሁሉ ሲያስተምር ያገኘዋል። በዚህም ጊዜ “ኦ እግዝእትየን ከየት አመጣኸው? መምህራችን አላስተማረንም" አለው። በዚህ ጊዜ ኤፍሬምም አስተምሮናል እንጂ ብሎት እንጠይቀው ሔደን ተባባሉ። ቅዱስ ያዕቆብ ሊቀጳጳሳትም ሞቶ ነበርና ከመቃብሩ ሲደርሱ ፲ሩ ጣቶቹ እንደ ፋና እያበሩለት ተነስቶ “ሰላም ለኪ ኦ እግዝእትየ በሕይወትየ እብለኪ ሰላም ለኪ ከመ ስምዖን ዘአምድ ወድኅረ ሞትየሰ ኵሉ አዕጽምትየ ይብሉኪ ወይዌድሱኪ ሰላም ለኪ ኦ እግዝእትየ ቅድስት ድንግል ከመ ኤፍሬም ሶርያዊ” ብሎ መስክሮለታል። ይሄም ለቅዱስ ኤፍሬም ጸጋ ስለተሰጠው ነው። ከዚህ በኋላ ግን ስምዖን ዘአምድ ስለ እመቤታችን ፍቅርና ታላቅ ምስጢር አብዝቶ መጻፍና ማስተማርም ጀመረ። እንዲህም እያለ ይጸልያል:- ❝ሕፃናትን በእናታቸው ሆድ የሚሥላቸው እርሱ በሆድሽ የተሣለ የመድኃኒት እናት ሆይ እሰግድልሻለሁ❞ #ሰላም_ለኪ #ስምዖን_ዘአምድ #ውዳሴ_ማርያም ✍️መምህር ዘበነ ለማ (ዶ/ር) የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ!ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለጓደኛዎ ያጋሩ:👇🏽 https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv
نمایش همه...
የደጉ ሳምራዊ መልካምነት®

ይህ ትክክለኛ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት የቴሌግራም ቻናል ነው:: (በመ/ር ሲራክ ሰሎሞን) በዚህ የቴሌግራም ቻናል:- ➮አስተማሪ እና መንፈሳዊ ፅሁፎችን ➮የቅዱሳን ገድላት ➮ መዝሙሮችን ➮መንፈሳዊ ትምህሮቶችን ያገኛሉ። የመወያያ ግሩፕ:

https://t.me/+QKiTJYGJvYpmNWM0

የዚህ ግሩፕ ዓላማ ለበጎ ምግባር ቃለ እግዚአብሔርን መማማር ነዉ::

Photo unavailableShow in Telegram
ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ በነገው ዕለት 172 ደቀ መዛሙርትን ሊያስመርቅ ነው ! የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሐ ግብራት ሲያስተምራቸው የቆዩ 172 ተማሪዎች በነገው ዕለት ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም በዩነቨርሲቲው አዳራሽ ውስጥ ያስመርቃል። በነገው ዕለት የሚመረቁት ደቀ መዛሙርት በሰርተፊኬት ፣ በመጀመሪያ ዲግሪና  በሁለተኛ ዲግሪ በቀንና በማታ መርሐ ግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ መሆናቸውን ለማወቅ ችለናል። የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ!ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለጓደኛዎ ያጋሩ:👇🏽 https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv
نمایش همه...
✝️#በጾም_ጥገቡ ✝️ ✍️አጽዋማት በመጡ ጊዜ እየደጋገምን ከምንሰማቸው ነገሮች አንዱ "ጾም መከልከል ነው" የሚል ነው። ከምን ቢሉ በአእምሮ ከክፉ አሳብ፣ በዓይን ከመጥፎ እይታ፣ በጆሮ ከከንቱ ወሬ፣ በእጅና በእግር ከክፉ ተግባር መከልከል ነው። ጾም ከክፉ ሥራ መከልከል እንደሆነ ሁሉ ለበጎ ሥራ ደግሞ መዘርጋት ነው። በጾም ውስጥ በርካታ መንፈሳዊ ድርጊቶች ይከወኑበታል። ጸሎት፣ ምጽዋትና ንስሐ ዋነኞቹ ቢሆኑም አርምሞና ሌሎችም ሰናይ ምግባራት የምንማርባት ጾም የሕይወት ሰሌዳ ናት፡ ሊቃውንት አባቶቻችን ጾምን ሲገልጿት «እማ ለጸሎት፣ ወእኅታ ለአርምሞ፣ ወነቅዓ ለአንብዕ፣ ወጥንተ ኩሉ ገድለ ሰናይት» ይሏታል። አዎ እንደሚባለው ጾም የረሀብ አድማ አይደለም። ቁርስና ምሳ የዘለልነውንም ማምሻውን የምናካክስበት አይደለም። ይልቁንስ ቀን የባሳቸውና ወረት ያነሳቸውን ወገኖች የምናይበት መንፈሳዊ ጉብኝት ነው በጾም ወቅት ቁርስና ምሳን ስንዘል ለቁርስና ለምሳ የምንጠቀመውን ለወገኖቻችን የምናጋራበትም የቸርነት እጅ ነው። በሌላ በኩልም ለተወሰኑ ጊዜያት በጾም የምንራበው እድሜ ዘመናቸውን በረሃብ የሚያሳልፉ ወገኖቻችንን ለማሰብም ጭምር ነው ስቃያቸው ይገባን ዘንድ፣ ረሃባቸውንም እንረዳው ዘንድ እንጾማለን። ጾም የምግባርና የትሩፋት ማዕድ ናት። በምግብ ስንራብ በጽድቅ የምንጠግብባት፣ የታረዙትን ስናለብስ ጸጋ እግዚአብሔርን የምንለብስባት፣ በውኃ ስንጠማ በምሕረቱ ጠል የምንረካባት ድንቅ የጽድቅ መንገድ ናት፡፡ ነቢያት አባቶቻችን የጌታችንን መምጣት አበክረው ይጠባበቁ ነበር። ጠዋት ከተኙበት ሲነቁ፣ ማታ ወደ መኝታቸው ሲገቡ አቤቱ ክንድህን ላክልን፣ ብርሃንህን ላክልን፣ ኃይልህንና ቀኝህን ላክልን አድነንም እያሉ ይማጸኑ ነበር። የጌታችንን መምጣት በትንቢት መነጽርነት ቢያዮም ጌታ መጥቶ ከፍዳ ዘመን፣ መርገምና ኩነኔ ካጠላበት ሰውነት እስኪያድናቸው ይናፍቁ ነበር። እሊህ አባቶቻችን ሊያዮት የናፈቁትን ሳያዮ የጌታችንን የመምጣት ቀን እየተሳለሙ አለፉ።(ዕብ ፲፩፥፲፫) ይህን ሲያስረግጥ ጌታችን ነቢያት የምታዮትን ለማየት የምትሰሙትን ለመስማት ተመኝተው አልሰሙም አላዮምም የናንተ አይኖች ግን ብፁዐን ናቸው አለ። ለዚህ ነው ቅድስት ቤተክርስቲያናችን አባተቆቻችን በትንቢት የዘሩትን አዝመራ እኛ በላን፣ በእንባ ያፈለቁትን ውኃ ጠጣን፣ በትንቢት የፈተሉትን ሸማ /አዲሱን ሰው/ እኛ በጥምቀት ለበስን የምትለን። ታዲያ አበው ያለሙትን፣ ነቢያት የናፈቁትን ጌታ ሐዋርያት በዘመናቸው አገኙት የእርሱ ደቀ መዛሙርትም ለመሆን በቁ። (ማቴ ፬፥፲፱) ጌታ ፴ ዘመን ተጠምቆ ፫ ዓመት ከ ፫ ወር አስተምሮ ቤዛነትና አርዓያነቱን ፈጽሞ በእልልታ ድምጽ ወደ ሰማይ ዐረገ ሐዋርያት ቆመው ያዮት ስለነበር አእምሯቸውም ከእርሱ ጋር ዐረገ። (ሐዋ ፩፥፲፩) ከ ፲ ቀናት በኋላም በጽርሀ ጽዮን መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ ኃይልን ብርታትን አገኙ። (ሐዋ ፪፥፩–፬) እነሆ አሁን ዓለምን በእርፈ መስቀል የሚያርሱበት ጊዜ ደርሷልና ወደየ ሀገረ ስብከታቸው ከመሄዳቸው በፊት ይህን «የሐዋርያት ጾም» ብለን የምንጠራውን ጾም ጾሙ፤ አሳ አጥማጆች ሰውን እያጠመዱ የክርስቶስ አካል አደረጉ። ይህ ጾም ከሐዋርያት ለእኛ የተላለፈ ጾም በመሆኑ እኛም እንጾመዋለን። በተለይ በርካታ ሰዎች ከቤተክርስቲያን ኅብረት አንድነት በተለዮበት በዚህ ወቅት አብዝተን መጾም ይገባናል። ጅማሬውን ፍጻሜ፣ እፍኙን ኩንታል የሚያደርግ አምላካችን እግዚአብሔር ጾሙን የበረከት፣ የንስሐ ፣ ደዌን ማራቂያ፣ የኃጢአት መደምሰሻ፣ የዲያብሎስ ድል መንሻ የመንግሥተ ሰማያት መውረሻ ያድርግልን አሜን!!! መልካም የጾም ጊዜ የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ!ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለጓደኛዎ ያጋሩ:👇🏽 https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv
نمایش همه...
የደጉ ሳምራዊ መልካምነት®

ይህ ትክክለኛ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት የቴሌግራም ቻናል ነው:: (በመ/ር ሲራክ ሰሎሞን) በዚህ የቴሌግራም ቻናል:- ➮አስተማሪ እና መንፈሳዊ ፅሁፎችን ➮የቅዱሳን ገድላት ➮ መዝሙሮችን ➮መንፈሳዊ ትምህሮቶችን ያገኛሉ። የመወያያ ግሩፕ:

https://t.me/+QKiTJYGJvYpmNWM0

የዚህ ግሩፕ ዓላማ ለበጎ ምግባር ቃለ እግዚአብሔርን መማማር ነዉ::

በቡስካ ደብረ ጽዮን አቡነ ሙሴ ገዳም በአመክሮ ለነበሩ መናንያንና መናንያት ሥርዓተ ምንኩስና ተፈጸመላቸው፡፡ በደቡብ ኦሞ አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት በቡስካ ደብረ ጽዮን አቡነ ሙሴ ገዳም በአመክሮ ለነበሩ መናንያንና መናንያት ሥርዐተ ምንኩስና ሰኔ 27 ቀን 2016 ዓ.ም ተፈጸመላቸው፡፡ የማዕረገ ምንኩስናውን ክብር ያገኙት 6 ወንድሞች እና 10 እኅቶች መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን ሥርዓተ ምንኩስናውን የፈጸሙት በብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ሥርጭድት ድርጀት የበላይ ኃላፊና የምሥራቅና ሰሜን አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንትና የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ነው፡፡ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳቱ በሀገረ ስብከቱ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎችንም ተዘዋውረው መጎብኘታቸው የተጠቆመ ሲሆን፣ ጠብ አጫሪ ግለሰቦች በዳሰነች ወረዳ ሕፃናትን አስኮብልለው ማኅተብ ለማስበጠስ ሲጥሩ መያዛቸውን ተከትሎ ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸውንና አባታዊ ማሳሰቢያ ማስተላለፋቸውንም ሀገረ ስብከቱ ያደረሰን መረጃ ያመላክታል፡፡ የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ!ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለጓደኛዎ ያጋሩ:👇🏽 https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv
نمایش همه...
👏 1
"የሃይማኖት ተቋሞቻችን ለዘላቂ ሰላማችን" በሚል ርዕስ በሸራተን አዲስ ላሊበላ አዳራሽ ሀገር አቀፍ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ይገኛል ! "የሃይማኖት ተቋሞቻችን ለዘላቂ ሰላማችን"በሚል ርዕስ በሸራተን አዲስ ላሊበላ አዳራሽ ሀገር አቀፍ ኮንፈረንስ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በተገኙበት ሰኔ 26 ቀን2016 ዓ.ም በመካሄድ ላይ ይገኛል። በኮንፈረንሱ ላይ ቅዱስነታቸውን ጨምሮ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ የባሕር ዳርና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ፣ አቶ ብናልፍ አንዷለም የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያው ኃላፊዎች ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የየክፍሉ ኃላፊዎች ፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ፣ የልዩ ልዩ ሃይማኖት ተቋማት መሪዎች ተገኝተዋል። የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ!ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለጓደኛዎ ያጋሩ: 👇🏽👇🏽👇🏽 https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv
نمایش همه...
" ነገን ዛሬ እንሥራ " በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው " ማዕዶት ለኢትዮጵያ " ኦርቶዶክሳዊ የኪነጥበብ መርሐግብር በሚሊንየም አዳራሽ በመካሄድ ላይ ነው። ገቢው በከፋ ሸካ ቤንች ማጂ ሀገረ ስብከት በቦንጋ ከተማ ለሚገነባው የአብነት ትምሕርት ቤት የሚውል ነው። መርሐ ግብሩን በጸሎተ ወንጌል የከፈቱት ብፁዕ አቡነ ማርቆስ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የስብከተወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ሲሆኑ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ከፋ ሸካ ቤንች ማጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሰዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ፣የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ኦርቶዶክሳውያን ታድመዋል። ©eotc tv ++++++++++++++++++++++++++++++++++++ #ቅድስት በምትሆን በጽርሐ ጽዮን በሐዋርያት ላይ የወረደ የአብ በረከት የወልድ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ አንድነት በሁላችን ላይ ይውረድ ዕፅፍ ድርብ ይሁን" ሥርዓተ ቅዳሴ ቁ.፻፴፮
نمایش همه...
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ከሀገረ ስብከቱና ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሠራተኞች ጋር በዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ዙሪያ ተወያዩ። ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና የተዋሕዶ ሚዲያ የበላይ ጠባቂ ሊቀ ጳጳስ ከሀገረ ስብከቱና ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሠራተኞች ጋር በዓመታዊ ሥራ አፈጻጸም ዙሪያ ተወያዩ። በውይይት መርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕነታቸውን ጨምሮ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የሀገረ ስብከቱ የዋና ክፍል ሐላፊዎችና ሠራተኞች፣የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጆችና ሠራተኞች ተገኝተዋል። ውይይቱ በዓመቱ የነበረውን አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸምና አሠራር በተመለከተ ሰፋ ያለ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ከተሳታፊዎች በርካታ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ተነስዋል። አስተያየት ሰጪዎቹ የጋራ ውይይት መደረጉን አመስግነው ሀገረ ስብከቱ እያከናወናቸውን ያሉ መልካምና በጎ ጅምሮችን እንደሚያደንቁ ገልጸዋል። ከተነሱት ጉዳዮች መካከል ሀገረ ስብከቱና ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ተናቦ መሥራት ፣ የቅጥር ጉዳይ አፈጻጸም፣ በፍርድ ቤት የተያዙ ጉዳዮች፣ የሰበካ ጉባኤ ምርጫ ክፍተቶችና ክትትሎች፣ የአዳዲስ አብያተ ክርስቲያናት ምሥረታን በተመለከተ፣ ወደ ሸገር ሀገረ ስብከት የተካለሉ አብያተ ክርስቲያናት ደረሰኞች፣ መዝገቦችና ካርዶች ፣ በክብረ ክህነት ያጋጠሙ ተግዳሮቾች ፣ የስብከተ ወንጌል ጉዳይ የሚሉት ይጠቀሳሉ። የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ በተነሱ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በማብራሪያቸው ላይ ሀገረ ስብከቱ ያከናወናቸውን ተግባራት በዝርዝር ገልጸው በተለይም ችግሮችን ቤተ ክርስቲያንን ማእከል በማድረግ በምክክር እንዲፈቱ መደረጋቸውን አብራርተዋል ፤ አክለውም ሀገረ ስብከቱ ከግለሰብ ይልቅ የተቋማዊ ልዕልናን ማስቀደም ሥራዎችን በጥናት ሁነኛ ለውጥ ለማምጣት እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም ገልጸዋል። ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ በሀገረ ስብከትና በክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት እስከ አሁን ያጋጠሙትን ችግሮች ሥራዎች በማእከል መብዛታቸው፣ የመረጃ አሰጣጥና ተደራሽነት ጉዳይ እንዲሁም የግብረ መልስ ሪፖረት ክፍተቶች መሆናቸውን ተቁመዋል። ይሁን እንጂ ሀገረ ስብከቱ ከቅጥር ውጭ ያሉ ሥራዎች በክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት መዋቅር በኩል እንደሚፈጸሙ ገልጸዋል ፤ አክውም በቀጣይ ከአስተዳዳሪዎች ጀምሮ ሁሉን አቀፍ የጋራና የተናጥል ስልጠናና እንደሚሰጥ ተናግረዋል። ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የማጠቃለያ ሐሳብና መመሪያ ያስተላለፉ ሲሆን ሀገረ ስብከቱ መሠረታዊ ከሚባሉ ተልእኮዎች ስብከተ ወንጌል የራስ አገዝ ልማትና ለትውልዱ ቅርብ ከመሆን ይልቅ በግለሰቦች ቅጥርና ዝውውር ጊዜውን እያባከነ መምጣቱን ገልጸዋል። ብፁዕነታቸው የሀገረ ስብከቱ ሁሉን አቀፍ ችግሮች በቅርብ ጊዜያት ሳይሆኑ ከ20 ዓመታት በላይ በሆኑ ተደራራቢ የአሠራር ግድፈቶለችና ክፍተቶች የመጡ እንደሆኑ መሆናቸውን አስተውሰዋል። በተጨማሪም የበለጠውን ዋጋ የሚያሰጠውን ቅን አገልግሎት ለማገልገል እንዳይቻል እንቅፋት ከሆኑት ጉዳዮች መካከል ከሀገረ ስብከቱ ጀምሮ እስከ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ተናቦና የመዋቅር ልዕልና ጠብቆ ያለመሥራት ችግር እንዳሉም ተጠቁመዋል። በክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት የሚከናወኑ ሥራዎች በተለይ የማጣራት ተግባራት ፍትሕ ርትዕን በማስፈን ዙሪያ የሚስተዋሉ ክፍተቶች እንዳሉ ገልጸው ችግሮችን በጥናት ቀመለየት በዘመነ አሠራር ማስተካከል ይገባናል ብለዋል። ከሀገረ ስብከቱ የሚስተዋሉ የአሠራር ክፍተቶችና የተናብቦት ችግር ለመቅረፍ ይቻል ዘንድ ጥናትን መሠረት ያደረገ የመፍትሔ ሐሳብ መቅረብ እንደሚኖርበትም መመሪያ አስተላልፈዋል። እስካሁን በአሠራር ችግር፣በደቦና በከንቱን የኔባይነት እንዲሁም በቡድተኝነት የአብያተ ክርስቲያናት የሥራ ቢሮዎች ይታሸጉ እንደነበረ ተጠቁመው አሁን ጊዜ ሀገረ ስብከቱ በሚያከናውነው የመፍትሔ አቅጣጫ ምክንያት ይህ ዓይነቱ ድርጊት መቅረቱ ሀገረ ስብከቱ የሠራቸው መልካም ሥራዎች ማሳያዎች ናቸው ብለዋል። በመጨረሻም ብፁዕነታቸው ከትንሹ ጉዳይ ወጥተን ትልቁን አሻጋሪ ሐሳብ በመያዝ ከሀገረ ስብከት እስከ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ድረስ የራስ አገዝ ልማቶችን በማጠናከር ነገን ያሰበ ቤተ ክርስቲያናዊና ትውልዳዊ ሥራ ልንሠራ ይገባል ለዚህም ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት ይኖርበታል ብለዋል። ዘገባው:- የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ነው የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ!ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለጓደኛዎ ያጋሩ: 👇🏽👇🏽👇🏽 https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv
نمایش همه...
የደጉ ሳምራዊ መልካምነት®

ይህ ትክክለኛ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት የቴሌግራም ቻናል ነው:: (በመ/ር ሲራክ ሰሎሞን) በዚህ የቴሌግራም ቻናል:- ➮አስተማሪ እና መንፈሳዊ ፅሁፎችን ➮የቅዱሳን ገድላት ➮ መዝሙሮችን ➮መንፈሳዊ ትምህሮቶችን ያገኛሉ። የመወያያ ግሩፕ:

https://t.me/+QKiTJYGJvYpmNWM0

የዚህ ግሩፕ ዓላማ ለበጎ ምግባር ቃለ እግዚአብሔርን መማማር ነዉ::

Photo unavailableShow in Telegram
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ከሀገረ ስብከቱና ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሠራተኞች ጋር በዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ዙሪያ ተወያዩ። የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ!ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለጓደኛዎ ያጋሩ: 👇🏽👇🏽👇🏽 https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv
نمایش همه...
01:56
Video unavailableShow in Telegram
"24 ሰዓት ለሰጠን እግዚአብሔር 1 ሰዓት ለጸሎት መስጠት ጭንቅ ነውን ?" የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ!ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለጓደኛዎ ያጋሩ: 👇🏽👇🏽👇🏽 https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv
نمایش همه...
24_ሰዓት_ለሰጠን_እግዚአብሔር_1_ሰዓት_ለጸሎት_መስጠት_ጭንቅ_ነውን.mp46.22 MB
1
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.