cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ትንሳዔ ዘኢትዮጵያ ✝✝✝

📢 ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን እና ገዳማት ስርዓት ፣አሁናዊ ዜና እና ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን ፡ ቅዱሳን መካናት እና ገዳማት ታሪክ 📢 የቅዱሳን ገድላት 📢 ቅዱሳን አበው ሊቃውንት 📢 ህዝበ ክርስቲያንን ማንቃት 📢 ቅድመ ኢትዮጵያ ትንሳዔ እና የኢሉሚናቲ ኅቡእ ማኅበር ኢትዮጵያ ላይ የተሸረቡትን ሴራዎችን ማጋለጥ ለውይይት @Tinsae_ze_ethiopiaofficialgrp

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
3 851
مشترکین
-824 ساعت
-577 روز
-23030 روز
توزیع زمان ارسال

در حال بارگیری داده...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
تجزیه و تحلیل انتشار
پست هابازدید ها
به اشتراک گذاشته شده
ديناميک بازديد ها
01
በኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን፣ የምሥራቅ አውስትራሊያና ኒውዚላንድ ሀገረ ስብከት በሰጠው መግለጫ "የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ላይ ውግዘትም ሆነ በቦታቸው ሌላ አባት የመተካት ውሳኔ እንዳይተላለፍ አጥብቆ ጠየቀ። እንዲህ ያለ ውሳኔ ከተላለፈም እንደማይቀበለው አስታወቀ። ©️Adebabay media @Tinsae_ze_ethiopia
550Loading...
02
Media files
581Loading...
03
በኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን፣ የምሥራቅ አውስትራሊያና ኒውዚላንድ ሀገረ ስብከት በሰጠው መግለጫ "የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ላይ ውግዘትም ሆነ በቦታቸው ሌላ አባት የመተካት ውሳኔ እንዳይተላለፍ አጥብቆ ጠየቀ። እንዲህ ያለ ውሳኔ ከተላለፈም እንደማይቀበለው አስታወቀ። (የመግለጫውን ሙሉ ቃል አያይዘናል፤ ከቴሌግራም ገጻችን ተመልከቱት። https://t.me/AdebabayMedia2/11455)
10Loading...
04
👉በዚሁም መሰረት በመወያያ አጀንዳ አርቃቂነት በጉባኤው የተመረጡት ሰባት አበው ሊቃነ ጳጳሳት ሲኖዶሱ እንዲወያይበት 21 አጀንዳዎችን የመረጡ ሲሆን ይህም ዝርዝሩ እንደሚከተለው ይቀርባል ፦ 1.የቅዱስ ሲኖዶስ ዓመታዊ የሥራ ክንውንን በተመለከተ 2.የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሪደር ልማትን አስመልክቶ ከቤትና ሕንጻ አስተዳደርና ልማት ድርጅት የቀረበ ሪፖርት በተመለከተ 3.የሃይማኖት ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ 4.የገቢዎች ባለሥልጣን የወሰነውን የግብር አከፋፈል ሁኔታ በተመለከተ 5.አገር አቀፍ የምክክር ኮሚሽንን በተመለከተ 6.ወደ ውጭ ሀገር ለአገልግሎት የሚላኩ አገልጋዮችን በተመለከተ 7.የ2017ዓ.ም በጀት ማጽደቅን በተመለከተ 8.የስዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅን በተመለከተ 9.የምግባረ ሠናይ ጠቅላላ ሆስፒታል ረቂቅ መተዳደሪያ ደንብ በተመለከተ 10.የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን አንድነት ገዳም ኅብረት መተዳደሪያ ደንብ በተመለከተ 11. የጋሞጎፋ ሀገረ ስብከት ተብሎ የሚጠራበት ስም ቀርቶ የጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረስብከት አርባ ምንጭ ተብሎ ይጠራልኝ በማለት የቀረበውን ጥያቄ በተመለከተ 12.የጋምና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት ስለ ዚጊቲ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የቀረበውን ጥያቄ በተመለከተ 13 ኦሲኤን ቴሌቭዥን አስመልክቶ የቀረበ ጥናት በተመለከተ 14.የብፁዓን አባቶች ዝውውር ጥያቄ በተመለከተ 15. የእነ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) ማመልከቻን በተመለከት 16 ከመሪ እቅድ የሚቀርበውን ዝርዝር የመዋቅር ጥናትና ቻርት በተመለከተ 17.የመግለጫ አሰጣጥ እና የስብከት ዘዴ ትምህርት አቀራረብን በተመለከተ፣ 18.አገራዊ ሰላምን በተመለከተ 19. የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ግበረ ሰዶማዊነትን በተመለከተ ' 20 የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልናና የውስጥ አንድነትን ማጠናከር በተመለከተ 21.የቋሚ ሲኖዶስ አባላት ምርጫን በተመለከተ ©️ETHIO BETESEB MEDIA @Tinsae_ze_ethiopia
570Loading...
05
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ግንቦት ፳፩ ቀን ፳፱፲ወ፮ ዓ/ም ባደረገው የጠዋቱ የግንቦት ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ሰባት አበው ሊቃነ ጳጳሳትን በመወያያ አጀንዳ አርቃቂነት ሰየመ። በዚሁም መሰረት በመወያያ አጀንዳ አርቃቂነት የተሰየሙት ሰባት አበው ሊቃነ ጳጳሳት ሕገ ቤተ ክርስቲያን በሚያዘው መሰረት ከቋሚ ሲኖዶስ ለምልአተ ጉባኤ እንዲቀርቡ የተመሩ እና ተጨማሪ የሚባሉ አጀንዳዎችን በመቅረጽ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የማስጸደቅ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴነት የተመረጡት አበው ሊቃነ ጳጳሳት የሚከተሉት ናቸው። 1.ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ 2.ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ 3.ብፁዕ አቡነ ማርቆስ 4. ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ 5. ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል 6. ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ 7. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ኢኦቴቤ ሕዝብ ግንኙነት ©️Dewol @Tinsae_ze_ethiopia
430Loading...
06
Media files
480Loading...
07

08
መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! - ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሰሜን ጎጃምና የባሕር ዳር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ - ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት! እግዚአብሔር አምላካችን በቤተ ክርስቲያን ላይ በየጊዜው የሚደርሰውን ፈተና በማስቻል ለዚህ ሲኖዶሳዊ ምልአተ ጉባኤ እንኳን በሰላም አደረሰን! ‹‹አስተብቊዓክሙ አኃዊነ በስሙ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ትበሉ ኵልክሙ አሐደ ቃለ ወአሐደ ነገረ ወትኩኑ ፍጹማነ ወኢትትፋለጡ ወሀልዉ በአሐዱ ምክር ወበአሐዱ ልብ፤ ወንድሞች ሆይ ሁላችሁ አንድ ንግግር እንድትናገሩ፣ በአንድ ልብና በአንድ ሐሳብም የተባበራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ›› (፩ቆሮ ፩፥፲)፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን መልእክት ለቆሮንቶስ ሰዎች ለመጻፍ ሲያስብ አንድ ዓቢይ ምክንያት እንዳለው ከመልእክቱ ይዘት መረዳት ይቻላል፤ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች አንድነትንና ሰላምን ፍቅርንና መተባበርን ከምትሰብከው ወንጌለ መንግሥተ እግዚአብሔር ወጥተው ብዙ ርቀት ሂደዋል፤ አንድነቱ፣ ኅብረቱ መረዳዳቱ መተጋገዙና መተባበሩ ከመካከላቸው ጠፍቶአል፤ ሌላው ቀርቶ ቅዱስ ቊርባንን ለመቀበል በሚሰበሰቡበት ጊዜ እንኳ የሀብታምና የድሀ የሚል ክፍፍል ተፈጥሮ ቤተ ክርስቲያኗን አደጋ ላይ ጥሎአል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን እና ይህንን የመሳሰለ ፈተና በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ሥር እየሰደደ መምጣቱን በእጅጉ አሳስቦታል፤ ይህ የሰላምና የአንድነት ጠንቅ የሆነው የመለያየት አዝማሚያ በጣም ሰፍቶ ቤተ ክርስቲያንን ከማፍረሱ በፊት በትምህርት በምክርና በተግሣጽ ማረም እንዳለበት ቅዱስ ጳውሎስ ተገንዝቦአል፤ እሱ ራሱም በአካል በመካከላቸው ተገኝቶ ሊያስተካክላቸው ፈቃደኛ ነበረ፤ ነገር ግን እሱ በዚህ ጊዜ በሮም ውስጥ እስር ቤት ላይ ስለነበረ አልቻለም፤ የነበረው አማራጭ በጽሑፍ ማስተማርና መምከር ነውና፤ ይህንን መልእክት ጽፎላቸዋል፡፡ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት! ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዘላቂው የቤተ ክርስቲያን ፈተና ሲነግረን ‹‹ወበዓለምሰ ሀለወክሙ ትርከቡ ሕማመ፤ በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ›› እንዳለው ቤተ ክርስቲያን ከፈተና ተለይታ አታውቅም፤ ፈተናውም ከተወሰነ አቅጣጫ ብቻ የሚመጣ ሳይሆን ከብዙ አቅጣጫ ይከባታል፤ የቤተ ክርስቲያን መከራ ከውጭ ብቻም አይደለም ከውስጥም እንጂ፤ ከባዕድ ብቻም አይደለም ከወዳጅም እንጂ፣ የወዳጅ ፈታኝ እንደሚብስም ታውቆ ያደረ ነገር ነው፤ ባዕዳውያን አይሁድ ጌታን ይዘው የገደሉ የውስጥ ሰው የሆነው ይሁዳ በሰጣቸው ምልክት ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ በከባድ ፈተና ውስጥ እያለፈች ትገኛለች፤ እንደተነገረው የውጭው ፈተና ባይቀርላትም ከሱ በላይ ግን በውስጧ የሚነሡ ፈተናዎች ተልእኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ ዕንቅፋት ሆነውባታል፤ ከጥንት ጀምሮ የነበረ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ፣ የጸሊአ ሢመትና የጸሊአ ንዋይ መንፈሳዊ ባህሏ ተዘንግቶአል፤ በምትኩም ፍቅረ ሢመትና ፍቅረ ንዋይ ነግሦአል፤ መለያየትና መነቃቀፍ እየሰፉ መጥተዋል፣ ሃይማኖታችንንና ባህላችንን የማይወክሉ ኃይለ ቃላት፣ ኃላፊነት በጐደለው አገላለጽ እየተሰነዘሩ በጎቻችንን አስበርግገዋል፤ ድርጊቶቹ በበጎቻችን ዘንድ የነበረንን ተሰሚነትና ተደማጭነት ሊቀንሱብን እየተንደረደሩ ነው፡፡ እነዚህና እነዚህ የመሳሰሉ ክሥተቶች በውስጣችን ሥር በሰደዱ ቁጥር ጉዳትን እያስከተሉ ነው፤ ሰዎች ከኦርቶዶክሳዊ ቀኖና እና ሥርዓት ባፈነገጠ መልኩ ራስን በራስ የመሾም አባዜ እየተለማመዱ ነው፤ እሽቅድምድሙም በዚህ ዙሪያ አይሎአል፤ በአጠቃላይ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖችን የፈተነ መለያየት በቤተ ክርስቲያናችንም ብቅ ጥልቅ እያለ እየፈተነን ነው፤ የፈተናው መንሥኤ ውጫዊ ሳንካ ባይጠፋበትም የውስጣችን ሰዎች ለሱ ምቹ ሆነው መገኘታቸው አልቀረም፤ በመሆኑም ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ፈተና የማይናቅ ጉዳት እየደረሰባት ነው፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ ሰላምዋና አንድነቷ ጥያቄ ላይ ወድቆአል፡፡ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት! በሀብተ መንፈስ ቅዱስ ወልደን፣ በሀብተ ክህነት ሹመን፣ በመዐርገ ምንኩስና አልቀን በቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት ያስቀመጥናቸው ሰዎች በውኑ ‹‹እርስ በርስዋ የምትለያይ ቤት… የሚለውን አምላካዊ አስተምህሮ እንዴት ዘነጉት? ወይስ ድሮውንም ሳያውቁት ነው ኃላፊነቱ የተሰጣቸው? ወይስ ደግሞ ሆን ብለው ቃሉን ቸል ብለውታል? ሁሉም ውሉደ ክህነት ለዚህ መልስ መስጠት ይጠበቅበታል፤ በመልካም አስተዳደርና በቂም በቀል እያሳበቡ ቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም ብሎም ለማፍረስ መሮጥ በማናቸውም መመዘኛ ሚዛን አይደፋም፤ ውሃም አያነሣም፡፡ ችግር ሲኖር በመወያየት በጥበብና በሕግ ማረም እንጂ የጋራ ችግርን ለተወሰነ አካል በመለጠፍና እሱን ብቻ ተጠያቂ በማድረግ ንጹህ መሆን አይቻልም፤ ሁሉም ጓዳው ቢፈተሽ ከዚህ የተለየ ነገር አይገኝም፤ አንድነትንና ሰላምን ግቡ ያደረገ ግምገማን መገምገም፣ መወያየትና መመካከር፣ ሕግንና ሥርዓትን ማእከል አድርጎ መሥራት ተመራጭ መፍትሔ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ባለፉት ዓመታት አስከፊ በደል ተፈጽሞአል አሁንም አልቆመም፤ ይሁን እንጂ በደል ዛሬ ብቻ የተጀመረ አድርገን አናስብ፤ ይብዛም ይነስ በደል ፊትም ነበረ፤ ዛሬም አለ፤ ነገም የተለየ ነገር ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ በደልን በካሣና በዕርቅ በይቅርታና በምሕረት መዝጋት፣ ተመሳሳይ በደል እንዳይፈጸም አስተማማኝ የሆነ ተቅዋማዊ ሥርዓትን ማበጀት መልካም ፈሊጥ ይሆናል፤ በደልንና ጥፋትን ምክንያት አድርገን እስከ ዘለቄታው መለያየትን መምረጥ ግን ራስን በራስ መጉዳት ይሆናል፤ ስለዚህ ይህ ቅዱስ ጉባኤ በዚህ ዙሪያ በስፋትና በጥልቀት በመወያየት ሁሉንም ሊያስማማ በሚችል መልኩ ወደ ሰላምና ዕርቅ ሊያደርስ የሚችል ስራ መስራት ይኖርበታል፡፡ ብፀዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖስ አባላት! የማኅበረ ሰባችን ችግር በቤተ ክርስቲያን ብቻ የተወሰነ አይደለም፤ በሀገር ደረጃ እየቀጠለ ያለው አለመግባባትም ለጠቅላላ ማኅበረ ሰባችን ፈተና ከሆነ ውሎ አድሮአል፤ የቤተ ክርስቲያናችን ፈተና ምንጭ ከሆኑትም አንዱና ዕድል ሰጩ ይህ ሀገራዊ አለመግባባት ነው፤ በዚህ አለመግባባት ምክንያት ገዳማውያን መነኮሳት፤ መምህራን ካህናት ምእመናን አብያተ ክርስቲያናት ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ በሰላም ወጥቶ መግባትም አጠራጣሪ ሆኖአል፤ ይህንን ችግር ለመፍታት የሚደረግ ጥረትም ጎልቶ አይታይም፡፡ በመሆኑም ይህ ክሥተት እውን ኢትዮጵያውያን የራሳችንን ችግር በራሳችን መፍታት የማንችል ሰዎች ነን ወይ? ለኛስ ከኛ የበለጠ ማን ይመጣልናል? የሚለውን ጥያቄ ልናነሣ ግድ ነው፤ ስለዚህ ለሀገር ህልውናና ድኅነት የሚበጅ ነገር እንዲመጣ ቤተ ክርስቲያን ባላት ሃይማኖታዊና ሰብአዊ ኃላፊነት ጠንክራ መስራት ይጠበቅባታል፤ ከዚህ በተረፈ ይህ ዓቢይ ጉባኤ ወሳኝና ወቅታዊ እንዲሁም ሐዋርያዊና ቀኖናዊ በሆኑ የቤተ ክርስቲያናችን ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ለቤተ ክርስቲያንና ለሀገር የሚበጁ ነገሮችን በማየት ጠቃሚ ውሳኔዎችን እንዲያሳልፍ በዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ በመጨረሻም
500Loading...
09
ዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በእግዚአብሔር ፈቃድ የተጀመረ መሆኑን በመንፈስ ቅዱስ ስም እናበስራለን ፡፡ መልካም ጉባኤ ያደርግልን! እግዚአብሔር አምላካችን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!! ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!! አሜን፡፡ አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ግንቦት ፳፩ ቀን !፻0፮ ዓ.ም. አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ©️DEWOLደወል ሚዲያ @Tinsae_ze_ethiopia
560Loading...
10
Media files
370Loading...
11
✏የደረሰን ጥብቅ መረጃ (ግንቦት 20/ 2016 ዓ.ም ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ) 👉ሲኖዶሱ በመንታ መንገድ ፦ ✍️ እነ አቡነ ገብርኤል፣አቡነ ሳዊሮስ፣አቡነ ኤዎስጣቴዎስ፣አቡነ ሩፋኤል፣ወዘተ..አቡነ ሉቃስ ተወግዘውና አቶ ተብለው ከቤተክርስቲያን እንዲለዩ፣ሲኖዶሱ ነገሩን ቀለል ለማድረግ የሚሞክር ከሆነ ወይም አቡነ ሉቃስን በተግሳጽ ሊያልፋቸው ከሞከረ በጽኑ እንደሚታገሉና በአቋማቸው ጸንተው በልዩነት እስከ መውጣት የሚደርስ አቋም በመያዝ ሲኖዶሱን ለሁለት እስከመክፈል ድረስ ለመታገል በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ። ✍️ ይህንን ዓላማቸውን ለማስፈጸም አቡነ ፋኑኤል፣አቡነ ቀሌምንጦስና አቡነ ኤርምያስን በአጋዥነት ለመጠቀም አቅደው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። በተጨማሪም ዓላማቸውን ለማስፈጸም ይረዳቸው ዘንድ አጀንዳ አርቃቂ ውስጥ አቡነ ሳዊሮስን ወይም አቡነ ሩፋኤልን ወይም አቡነ ኤዎስጣቴዎስን ወይም አቡነ ገብርኤልን ለማስገባት አቅደው እየሰሩ እንደሚገኙ ። ✍️ የሲኖዶስ ጸሐፊውን አቡነ ጴጥሮስን በተመለከተ በምትካቸው በሕጉ መሰረት ሁለተኛ የወጡትን ጳጳስ መተካት ይገባል በሚል አቡነ ሩፋኤል አቡነ ጴጥሮስን እንዲተኩ በማድረግ በቀሪ የሥራ ዘመናቸው አቡነ አብርሃምን በቅርበት በመከታተል መግለጫ እንዳይሰጡ፣ሕዝበ ክርስቲያኑን በተለይም ወጣቱን ትውልድ እንዳያስተባብሩና እንዳይመሩ እጆቻቸውን አስሮ ማቆየትና ፓትርያርኩ ላይ ጥቃት የሚፈጠርበትን ሁኔታ በመፍጠር የኦሮሞ ፓትርያርክነትን እውን የማድረግ ተልእኳቸውን በአጭር ጊዜ ተፈጻሚ ለማድረግ አቡነ ሩፋኤል ተልዕኮ ወስደው እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ፦ ✍️ ሌላኛው ቡድን ወይም ከእነ አቡነ ሩፋኤል በተቃራኒው የሚገኙት ጳጳሳት ደግሞ በአቡነ ጴጥሮስ ምትክ ጳጳስ ከመመደብ ይልቅ ተወካዩ ወይም ምክትል ጸሐፊው ሥራውን እየሰሩ እንዲቆዩ የቅዱስ ሲኖዶስ አጀንዳ አጭርና ውዝግብ የሌለበት በማድረግ ጉባኤው በአጭር ጊዜ ሊቋጭ ይገባል ብለው የሚንቀሳቀሱ ሲሆኑ ፦ ✍️ እነዚህ ጳጳሳት ማንንም ማውገዝ አያስፈልግም የሚል ዓላማ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ሲሆኑ አቡነ ሉቃስ ተወግዘው መለየት አለባቸው የሚል ጠንካራ አቋምና የመንግስት ተልዕኮ የተቀበሉ ጳጳሳት ደግሞ አቡነ ሉቃስን ለማውገዝ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን የከዚህ ቀደም ንግግርና የአቡነ ዮሴፍን የፓትርያርኩ ንግግር የግላቸው እንጂ የሲኖዶስ አቋም አይደለም ያሉትን መግለጫ በመጥቀስ መርጦ አልቃሽ አትሁኑ የሚል አቋም ይዘው ውግዘቱን ለመተግበር በቆራጥነት እየተንቀሳቀሱ ናቸው። ✍️ በአጠቃላይ የዘንድሮ ሲኖዶስ አቡነ ጴጥሮስን አጀንዳ ያለማድረግ፣አቡነ ሉቃስን በጽኑ ማውገዝ፣ከውጭ ወደ አገር ውስጥ መግባት የተከለከሉ አባቶች ጉዳይ አጀንዳ የማይሆንበት ፣አገዛዙም አቡነ ሉቃስ እንዳይወገዙ የሚጥሩ አባቶች ማንነት ተለይቶ ዝርዝራቸው እንዲደርሰው አቅጣጫ ያስቀመጠበት ፣አብላጫው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አቡነ ሉቃስ እንዳይወገዙ ውሳኔ ካስተላለፈ የሥርዓቱ ደጋፊዎች በልዩነት ወጥተው የሥርዓቱ አቀንቃኝነታቸውን በይፋ ለማረጋገጥ ቃል ኪዳን የገቡበት በአይነትና በይዘቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ ልዩ የሆነ መንፈሳዊ ይዘት የሌለው ጉባኤ እንደሚሆን የውስጥ የመረጃ ምንጮቻችን ለኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ አጋርተውናል ፦ ©️ Ethio beteseb media
530Loading...
12
Media files
480Loading...
13

14
ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ግንቦት 21/2016 ዓ/ም የመክፈቻ ፀሎት ይደረጋ:: በየዓመቱ ትንሣኤ በዋለ በ25ኛ ቀን የሚካሔደው ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ነገ ከሰዓት በኋላ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ መሪነት የመክፈቻ ሥርዓተ ጸሎቱ ይከናወናል።
600Loading...
15
ቅዱስ ሲኖዶስ የዋና ጸሐፊውን ጉዳይ እልባት ሳያደርስ ጉባኤውን ማካሔድ የለበትም ባይ ነኝ። ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በሌሉበት ጉባኤውን ካካሔደ ልዕልናውን እንዳስደፈረ ይቆጠራል። ዳኝነት የሚፈልግ ጉዳይ እንኳ ቢኖር በአካል መገኘት ይገባቸዋል። ራሱን በራሱ እንዳያስበላ መላልሶ ማሰብ ይፈልጋል። ጸሎት አድርሶ ወደ የሀገረስብከቱ ከመመለስ በቀር የሚታሰብ ስብሰባ አደጋው በቀላሉ አይመለስም። በቁርጠኝነት እንጅ በመልመጥመጥ የሚወጣ ጋኔን ኖሮ አያውቅም። ©ዓባይነህ ካሴ ቅዱስ ሲኖዶስ የዋና ጸሐፊውን ጉዳይ እልባት ሳያደርስ ጉባኤውን ማካሔድ የለበትም ባይ ነኝ። ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በሌሉበት ጉባኤውን ካካሔደ ልዕልናውን እንዳስደፈረ ይቆጠራል። ዳኝነት የሚፈልግ ጉዳይ እንኳ ቢኖር በአካል መገኘት ይገባቸዋል። ራሱን በራሱ እንዳያስበላ መላልሶ ማሰብ ይፈልጋል። ጸሎት አድርሶ ወደ የሀገረስብከቱ ከመመለስ በቀር የሚታሰብ ስብሰባ አደጋው በቀላሉ አይመለስም። በቁርጠኝነት እንጅ በመልመጥመጥ የሚወጣ ጋኔን ኖሮ አያውቅም። ©ዓባይነህ ካሴ @Tinsae_ze_ethiopia
580Loading...
16
ርክበ ካህናት ========= ግንቦት ፳፩ ይህቺ ዕለት በቤተ ክርስቲያን "ርክበ ካህናት" : "ዕለተ ጥብርያዶስ" በመባል ትታወቃለች:: "ዳግሚት ዕለተ አግብኦተ ግብር" የሚሏትም አሉ:: ርክበ ካህናት በቁሙ "የካህናት ኖሎት (እረኞች) መገናኘትን" የሚመለከት ቃል ነው:: የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጐ ከተነሳ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ በየጸጋቸው መጠን እየተገለጠ ያጽናናቸው ያጸናቸው ፣ያስተምራቸው ፣ ይባርካቸውም ነበር:: እስከ ዕርገቱ ባሉ ፵ ቀናትም መጽሐፈ ኪዳንን ፣ ትምህርተ ኅቡዓትን ፣ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያንን አስተምሯቸዋል:: በልቡናቸውም አሳድሮባቸዋል:: በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተጻፈ ደግሞ ከዕርገቱ አስቀድሞ ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ ፫ ጊዜ በጉባኤ ተገልጧል:: ፩.የትንሳኤ (ዮሐ ፳:፲፱) ፪.የአግብኦተ ግብር /ዳግም ትንሳኤ(ዮሐ፳:፳፮) ፫.ዕለተ ጥብርያዶስ  (ዮሐ. ፳፩፣፩-፯) በተረፈው ግን ለድንግል ማርያም ሁሉን ዕለታት መገለጡን አበው ያስተምራሉ:: በዚህች ዕለት በቅዱስ ዼጥሮስ መሪነት ሐዋርያቱ ወደ ጥብርያዶስ ሔዱ:: አሶችን ሊያጠምዱም በብዙ ደከሙ:: ነገር ግን ጌታችን በረድኤት አብሯቸው አልነበረምና አንዳች አሣ በመረባቸው ሊገባ አልቻለም:: ማጥመድ (አስተምሮ ከክህደት ወደ ሃይማኖት : ከኃጢአት ወደ ጽድቅ መመለስ) የሚቻለው በረድኤተ እግዚአብሔር እንጂ በእውቀት ብዛት ወይም በአንደበተ ርቱዕነት ብቻ አይደለምና:: ሐዋርያት ሌሊቱን ሙሉ ዓሣ ለማጥመድ ሲለፋ አድረው ፣ሲነጋ ግን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቅዱሳን ደቀ መዛሙርቱ መጣ:: በጥብርያዶስ ባሕር ዳርቻም ቆሞ ታያቸው:: ከሚወደው ደቀ መዝሙሩ ከዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ በቀር ያወቀው ግን አልነበረም:: ቸሩ አባት "ልጆቼ! አንዳች የሚበላ ነገር አላችሁ?" ሲል ጠየቀ:: "ጌታ ሆይ! የለም" አሉት:: "የለንም" ብሎ የሌለንን ነገር በጌታ ፊት ማመኑ እጅግ መልካም ነው:: ምክንያቱም ያጣነውን ነገር ያን ጊዜ ሊጠቁመን ቸርነቱ ብዙ ነውና:: ያን ጊዜ ሐዋርያቱን መረባቸውን በመርከብ ቀኝ እንዲጥሉ አዘዛቸው:: እነርሱም በደስታ ጣሉ:: በአግራሞት እስኪሞሉ ድረስ : መረባቸውም ሊቀደድ እስኪደርስ ድረስ ፻፶፫ ዓሦች ተያዙላቸው:: ያን ጊዜም የሚወደው ደቀ መዝሙሩ ቅዱስ ዮሐንስ ምስጢር አወጣ:: ለቅዱስ ዼጥሮስ "ጌታ እኮ ነው" አለው:: ሽማግሌው ቅዱስ ግን ራቁቱን ነበርና ወደ ባሕሩ ተወረወረ:: ከአፍታ በሁዋላም ጌታችን ከሐዋርያቱ ጋር በድጋሚ (ለ2ኛ ጊዜ) ለምሳ ተቀመጠ:: ባርኮ ሰጥቶ : ልባቸውን ሊያጸና አብሯቸው በላ:: በዚያች ሰዓት ቅዱስ ዼጥሮስን ፫ ጊዜ "ትወደኛለህን?" ሲል ጠየቀው:: ቅዱሱ አረጋዊም እየደጋገመ "ለሊከ ተአምር ከመ አነ አፈቅረከ (እንድወድህ አንተ ታውቃለህ)" ሲል መለሰ:: ጌታም በበጐች ሐዋርያት (ካህናት) : በጠቦቶች አርድእት (ዲያቆናት) : በአባግዕት ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት (ምዕመናን ወምዕመናት) ላይ ሁሉ እረኛ እንዲሆን ሾመው:: ቀጥሎም የሰማዕትነቱን ምስጢር ገልጦለት "ተከተለኝ" (ለጊዜው በእግር : በሁዋላ ግን በግብር ምሰለኝ) ብሎታል:: ወልደ ነጐድጉዋድ ወፍቁረ እግዚእ ቅዱስ ዮሐንስም ሞትን እንደማይቀምስ እንዲሁ ተናግሮለታል:: ይህች ዕለትም እነዚህ ሁሉ ተግባራት የተከናወኑባት ናትና በእጅጉ ትከበራለች:: ቤተክርስቲያናችንም ይህንን አብነት አድርጋ ሁሌ የጳጳሳትን ጉባዔ(ቅዱስ ሲኖዶስ) ከትንሳኤ በ፳፬ኛው ቀን ጀምሮ ታደርጋለች፡፡አባቶቻችን ዻዻሳትም ከጌታና ከደቀ መዛሙርቱ አብነትን ነስተው በዚህች ቀን ፪ኛውን ታላቅ ሲኖዶስ ያደርጋሉ:: መንፈስ ቅዱስ እየተራዳቸው ለቤተ ክርስቲያንና ለኛ ለልጆቿ የሚጠቅም መመሪያን ያወጣሉ ብለን እንጠብቃለን:: በተለይ ደግሞ በአምናው ርክበ ካህናት ስለ ፳፰ ቱ ኢትዮጵያውያን ሰማዕታት የሚባለውን ሁሉ ተስፋ አድርገን ነበር፣ ከቅዱሳን ሰማዕታት ጋር ዜናቸውን ለመደመር (ለመመስከር) እጅጉን ናፍቀንም ነበር:: ዘንድሮም አዲስ ነገር ካለ ብንሰማ ደስ ይለናል:: በተለይ በዚህ ዓመት ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን የወረራት የጠላትን ጦር የሚሰብር ፣ምክራቸውን የሚመክት ፣ ክፋታቸውን የሚያኮላሽ የሲኖዶስ ውሳኔ ከአባቶቻችን እንጠብቃለን። መንጋው ባዝኗልና፣ እረኝነት የተሰጣቸው አባቶቻችን እንዲነቁልንም ከተስፋ ጋር እንማጸናለን። የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ መንፈሱ ከአባቶቻችንና ከእኛ ከኃጥአኑ ጋር በረድኤት ይኑር:: @Tinsae_ze_ethiopia
560Loading...
17
ዓለም አቀፍ የመነኮሳት ማኅበር ወቅታዊ ሀገራዊ እና ቤተ ክርስቲያናዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ጠንከር ጠንከር ያሉ አቋሞቹን በመዘርዘር መግለጫ አወጣ። ማኅበሩ በመግለጫው ቅዱስ ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያን የገጠማትን ፈተና ለመመከት በሚመጥን ካልተራመደ ሓላፊነቱን ለሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እስከማስረከብ መሔድ አለበት ብሏል። ብፁዕ አቡነ ሉቃስንም በብርቱ ተከላክሏል። ተግሣጻቸው ነቢዩ ኤልያስ ኤልዛቤልና አክዓብን እንደገሰጸበት ያለ ነው ብሏል። © ዐባይነህ ካሴ
1270Loading...
18
በመንግስት አፋኞት ከተወሰደ በኃላ እስከ አሁን ያለበት ሁኔታ በቤተሰብም ሆነ በህግ ባለሙያ አልተጎበኘም ሁላችንም የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ድምፅ ልንሆነው ያስፈልጋል
1620Loading...
19
በቅድስት ቤትክርስቲያን ሥርዓተ አስተምህሮ ውስጥ በጊዜ ቅዳሴ ከወንጌል በኋላ ዲያቆኑ “ፃኡ ንዑሰ ክርስቲያን “ በማለት ያዛል። ይኸውም ፍሬ ቅዳሴ ህብስት እና ወይኑ ወደ ከበረ ስጋ ወደሙ ሚለወጥበት ጊዜ ስልሆን ይህም ለንዑሰ ክርስቲያን ማለትም በማህተመ መንፈስ ቅዱስ ላልታተሙ ላልተጠመቁ ክርስትና ላልተነሱ የተፈገደ የተገባ ስልይድለ ነው። በዚህ ላይ አስተያየት ስጡበት …
3551Loading...
20
ከእለታት አንድ ቀን አንድ አባት ወደ አባታችን አባ መቃርዮስ በኣት ሄደና "አባቴ ሆይ ድኅነትን አገኝ ዘንድ ምን ላድርግ?" ሲል ጥያቄ አቀረበላቸው። አባታችንም እንዲህ በማለት አሉት። "ወደ መቃብር ሂድና ሙታንን ሰድበሃቸው ና" አሉት። ይህ አባትም የተባለውን አድርጎ ተመለሰ። አባታችንም "ምን አሉህ?" ሲሉ ጠየቁት። ሰውየዉም "ምንም አልመለሱልኝም" ሲል መለሰ። አባ መቃርዮስም "አሁን ደግሞ ሂድና ሙታንን አመስግናቸው" አሉት። ሄዶም አመሰገናቸው። "አሁንስ ምን አሉህ" ሲል በድጋሚ ጠየቁት። ሰውዬም "ምንም አልመለሱልኝም" ሲል መለሰ። አባታችን አባ መቃርዮስም: "ስትሰድባቸው ፤ስታመሰግናቸው እና  ስታወድሳቸው ምንም አልመለሱም፤ አንተም ለነፍስህ ድህነትን ከፈለግህ እንደሞተ ሰው ሆነህ ኑር። ሰዎች ክፉ ቢያደርጉብህም፣ ቢያመሰግኑህም ምንም አይሰማህ" አሉት። @Tinsae_ze_ethiopia
1680Loading...
21
እንኳን ለዳግም ትንሣኤ አደረሳችሁ በዋናው ትንሣኤ ሳምንት የምትመጣዋ ዕለተ እሑድ ‹ዳግም ትንሣኤ› ተብላ ትዘከራለች፡፡ ጌታችን በትንሣኤው ዕለት ማታ በዝግ በር ገብቶ፣ በቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ተገኝቶ ‹‹ሰላም ለዅላችሁ ይኹን!›› በማለት ትንሣኤውን ሲገልጽላቸው ሐዋርያው ቶማስ አልተገኘም ነበር፡፡ በኋላ ከሔደበት ሲመጣ ጌታችን እንደ ተነሣ እና እንደ ተገለጸላቸው ሐዋርያት በደስታ ሲነግሩት ‹‹ እናንተ ‹አየን› ብላችሁ ስትመሰክሩ፤ ስታስተምሩ፤ እኔ ግን ‹ሰምቼአለሁ› ብዬ ልመሰክር፤ ላስተምር? አይኾንም፡፡ እኔም ካላየሁ አላምንም›› አለ፡፡ ስለዚህም የሰውን ዅሉ፤ ይልቁንም የመረጣቸው የወዳጆቹን የልብ ዐሳብ የሚያውቀው፣ ቸርነቱ ወሰን የሌለው የባሕርይ አምላክ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ልክ እንደ መጀመሪያው ትንሣኤ ዕለት አበው ሐዋርያት በተዘጋ ቤት በአንድነት ተሰባስበው እንዳሉ በሩን ሳይከፍት ገብቶ ‹‹ሰላም ለዅላችሁ ይኹን!›› በማለት በመካከላቸው ቆመ፡፡ ቶማስንም ‹‹ያመንህ እንጂ ተጠራጣሪ አትኹን፤ እነሆ የተቸነከሩ እጆቼንና እግሮቼን፣ የተወጋ ጐኔንም ናና እይ፤›› ብሎ አሳየው፡፡ እርሱም ምልክቱን በማየቱ፣ በመዳሰሱ ትንሣኤውንና አምላክነቱን እንደ ፍላጎቱ በመረዳቱ ‹‹ጌታዬ፣ አምላኬ ብሎ መስክሮ›› የክርስቶስን ትንሣኤ አመነ፡፡ የሳምንቷ ዕለተ ሰንበት፣ የትንሣኤው ምሥጢር ለሁለተኛ ጊዜ ለሐዋርያት የተገለጠበት ዕለት በመኾኑ የትንሣኤው ሳምንት እሑድ ‹ዳግም ትንሣኤ› ተብሎ ይጠራል፤ ይከበራል (ዮሐ. ፳፥፳፬-፴)፡፡ ብርሃነ ትንሣኤውን የገለጸልን አምላካችን ለብርሃነ ዕርገቱም በሰላም ያድርሰን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
1560Loading...
22
✏የድንግል ማርያም ልደት (መወለድ) "The Nativity of the blessed Virgin Mary” 👉የፈጣሪያችን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደችበትን ግንቦት አንድን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ልደታ_ለማርያም በማለት ከጥንት ጀምሮ በታላቅ መንፈሳዊ ሐሤት በቅዳሴ፣ በማሕሌት የምታከብርላት ሲኾን፤ በተለያዩ ክፍላተ ዓለማት ያሉ ክርስቲያኖችም ይኽነን በዓል “The Nativity of the blessed Virgin Mary” (የተባረከችው የድንግል ማርያም ልደት (መወለድ) በማለት ያስባሉ። 👉ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደቷ ቀን ሊቁ ዮሐንስ ዘደማስቆ እንዲህ ብሏል፦ "'The day of the Nativity of the Mother of God is a day of Universal joy, because through the Mother of God, the entire Human race was renewed. " 🙏ትርጉም (የአምላክ እናት የልደቷ ቀን ለዓለም ሁሉ የደስታ ቀን ነው፥ ምክኒያቱም በአምላክ እናት የሰው ሁሉ ዘር ባሕርይ ታድሷልና) ይህ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ሲገናዘብ ሊቀ መልአክ ቅ/ገብርኤል ካህኑ ዘካርያስን ልጅ እንደሚወልድ ባበሠረው ጊዜ “•••ደስታ ተድላም ይሆንልሃል፥ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።”ሉቃስ 1፥14 በማለት ነግሮታል። የጌታ መልእክተኛ የሆነ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ በመወለድ ብዙዎች ደስ ይለቸዋል ከተባለ የአምላክ እናት ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም በመወለዷ ምን ያህል ሰውን ሊያስደስት እንደሚችል ማወቅ ይቻላል። 👉አባ ሕርያቆስም የእመቤታችን መጸነስና መወለድ ሲገልጽ:- “ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለሽም በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ!” ቅዳሴ ማርያም 🙏(ቅዱስ ኤፍሬም ) 👉ፍህም የተሸከመች የወርቅ ማዕጠንት ድንግል ሆይ ቡሩክ ከቤተ መቅደስ ይዞሽ የወጣ እሳትነት ያለውን ፍህም የተሸከምሽ የወርቅ ማዕጠንት አንቺ ነሽ ። ፍህም የተባለውም ኃጢአትን የሚያስተሠርይና በደልን የሚደመስስ ነው፤ ይኸውም ካንቺ ሰው የሆነና ራሱን የተወደደ መስዋዕት አድርጎ ያሳረገ የእግዚአብሔር ቃል ነው 🙏የእመቤታችን በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን ‼ ©️Ethio beteseb media @Tinsae_ze_ethiopia
2000Loading...
23
ልደታ ለማርያም በግንቦት አንድ ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች። እርሷም ለሰው ሁሉ ወገን ድኅነት የሆነባት ናት፡፡ ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷም ስሙ ኢያቄም ከሴቶች ወገን የከበረች ሚስቱ ሐና ይባላሉ፡፡ ሁለቱም ልጅ በማጣት ሲያዝኑ ኖሩ። በዚያ ወራት የመካኖች መብዓ ካህናቱ አይቀበሉም ነበርና፡፡ እነርሱም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኅዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር፡፡ ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ሐሳባቸውን ተመለከተ፡፡ ክቡር ኢያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኅነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው፡፡ በፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው ወረደ፤ ለተመሰገነች ሚስቱ ለሐናም ከእግዚአብሔር መልአክ የሰማውን ያንን ራእይ ነገራት። ቃሉ እውነት እንደሆነ እርሷም አመነች። ልዑል እግዚአብሔርንም አመሰገነች። የተመሰገነች ቅድስት ሐናም ከእርሷ የሚወለደውን በዘመኑ ሁሉ ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ታደርገው ዘንድ ለእግዚአብሔር ስለትን ተሳለች፡፡ ከዚህም በኋላ ይህችን የከበረች ሕፃን ፀንሳ ወለደች። ስሟንም ‹ማርያም› ብላ ሰየመቻት። ትርጓሜውም ‹እመቤት› ነው። ‹ደግሞም ሀብታና ስጦታ› ማለት ነው፡፡ በእውነት የዓለሙ ሁሉ እመቤት ሁላችን በእርሷ ሰማያዊ ሀብት ልጅነትን ያገኘንባት ናትና። የሥጋና የነፍስ መድኃኒት የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ለዘለዓለሙ ይኑር፤ አሜን፡፡ ከመጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ግንቦት @Tinsae_ze_ethiopia
2031Loading...
24
"ከውሸት ፣ ከክፋት ፣ ከመወነጃጀል ነጽተን ትንሣኤውን በእውነትና በፍቅር እናክብር " ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሚያዝያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በዓለ ትንሣኤን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። ትንሣኤ ማለት ሕዝበ ክርስቲያኑ በጠቅላላ አምኖ የሕይወትን ትንሣኤ ስናከብር ነው በማለት የገለጹ ሲሆን አያይዘውም በዓለማችን ላይ የ ትንሣኤ ሕይወትን የሚለማመድ እና በሞት ጥላ ስር የሚኖሩ አሉ በመሆኑም በሞት ጥላ ለሚኖሩት ትንሣኤ የሚባል ነገር የለም ነገር ግን በሕይወት ትንሣኤ ስንኖር ዛሬ ብቻ ሳይሆን ሁሌም ትንሣኤ ነው በማለት ምክራቸውን ለግሰውናል። ምድራችን ሁል ጊዜ በበሽታ ላይ ነው ያለችዉ በሕመም ላይ ነው ያለችው ስለዚህ ትንሣኤ ዛሬ ነው ካልን ከውሸት ፣ ከክፋት ፣ ከመወነጃጀል ነጽተን ትንሣኤውን በእውነትና በፍቅር እናክብር በዓሉም የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ እና የአንድነት ይሁንልን በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። ©️ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል @Tinsae_ze_ethiopia
1970Loading...
25

26
በትንሣኤ እና በጠቅላላው በሐምሳው ቀናት ክርስቲያናዊ ሰላምታችን በረዥሙ እንዲሁም በአጭሩ (ሐሳብ መስጠት ይቻላል!!!) +++ Orthodox Greetings at Easter & the 50 days: ++++ ሀ/ በረዥሙ ካህን: ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን Priest:- Christ is risen from the dead ሕዝብ፦ በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን People:- With great strength and authority ካህን: ዓሠሮ ለሰይጣን Priest:- He chained Satan ሕዝብ፦ አግዓዞ ለአዳም People:- He freed Adam ካህን:- ሰላም Priest:- Peace ሕዝብ፦ እምይእዜሰ People:- Henceforth ካህን:- ኮነ Priest:- Became … ሕዝብ፦ ፍሥሐ ወሰላም People:- Joy and peace ++++++ ለ/ በአጭሩ፤ + Short greeting form (as in the Other Orthodox Churches) in our day to day encounters could be:- ** ሰላምታ አቅራቢ:- "ክርስቶስ ተንሥአ [እሙታን]" = (ክርስቶስ ተነሥቷል) ++ Greeter:- Christ is risen [from the dead.] ** ሰላምታ ተቀባይ:- "በአማን ተንሥአ እሙታን!!" = (በእውነት ተነሥቷል) ++ Person receiving the greeting:- "Truly He is risen [from the dead.]" + በሌሎች ክርስቲያኖች ዘንድ ያለው ሰላምታ!!!! ** “Christ is Risen!”, ** “Truly, He is Risen”. (This is used in almost all Christian nations, each translating it to its own language.) A/ Greek: ** “Χριστός ἀνέστη! Ἀληθῶς ανέστη! ** (Khristós Anésti! Alithós Anésti!)”, B/ Latin: ** “Christus resurrexit! Resurrexit vere!”, C/ Aramaic Syriac: “ܡܫܝܚܐ ܩܡ! ܫܪܝܪܐܝܬ ܩܡ!‎ (Mshiḥa qām! sharīrāīth qām! ; Mshiḥo Qom! Shariroith Qom!)”, D/ Hebrew: “המשיח קם! באמת קם!‎ (Hameshiach qam! Be’emet qam!)”, E/ Arabic: “المسيح قام! حقا قام!‎ (al-Masīḥ qām! Ḥaqqan qām!); المسيح قام! بالحقيقة قام!‎ (al-Masīḥ qām! Belḥāqiqāti qām!)”. F/ Coptic, the Paschal greeting is: ** Neo-Bohairic as “Pikhristos Aftonf! Khen oumethmi aftonf!” and in Old Bohairic as “pikhristos afdonf! khen oumetmei afdonf!”. ++++ ©️ TMC @Tinsae_ze_ethiopia
3473Loading...
በኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን፣ የምሥራቅ አውስትራሊያና ኒውዚላንድ ሀገረ ስብከት በሰጠው መግለጫ "የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ላይ ውግዘትም ሆነ በቦታቸው ሌላ አባት የመተካት ውሳኔ እንዳይተላለፍ አጥብቆ ጠየቀ። እንዲህ ያለ ውሳኔ ከተላለፈም እንደማይቀበለው አስታወቀ። ©️Adebabay media @Tinsae_ze_ethiopia
نمایش همه...