fa
Feedback
EECSF

EECSF

رفتن به کانال در Telegram

ይህ በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ ህንፃ ኮሌጅ ወንጌል አማኞች ክርስቲያን ህብረት ነው:: #ተቀዳሚ_ዐላማ፤የምንኖርለት:- •ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት #በዚህ_ቻናል:- ☞ የክርስቶስን አካል የ ሚያንፁ ልዩ ልዩ መልዕክቶች ይቀርባሉ:: ☞ከ ህብረቱ መሪዎችና ከ [ኢቫሱ] የ ሚተላለፉ መልዕክቶችን ያገኛሉ::

نمایش بیشتر
508
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
ስለ ቃሉ ጊዜ ጌታችን የተመሰገነ ይሁን!! በሕያው ቃሉ መሰረት የምንኖር እና የምናድግ እንድንሆን ጌታ ይርዳን፤ አሜን። መልዕክቱን ያካፈለችንን እህት ቢታንያ እግዚአብሔር ይባርክልን፣ያሳድግልን!!

"እግዚአብሔርን በእኛ አይን አንየው" ( በእህት ቢታንያ ) ⭕️ እግዚአብሔርን አውቀን አንጨርሰውም። አዳዲስ ነገር ሲያስተምረን፣ ሲገልጥልን ከሌሎች የበለጥን፣ አውቀንም የጨረስን አይምሰለን ✔️ ገና ብዙ አለ። " እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ የእምነትን መጠን እንዳካፈለው፥ እንደ ባለ አእምሮ እንዲያስብ እንጂ ማሰብ ከሚገባው አልፎ በትዕቢት እንዳያስብ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ በተሰጠኝ ጸጋ እናገራለሁ።" (ወደ ሮሜ ሰዎች 12: 3) ⭕️ በጌታ ቤት ስንመላለስ ሁሌ አዳዲስ ነገር ጌታ ያስተምረናል። ስለዚህ እግዚያብሄር በገለጠልን ልክ ✔️ በትህትና ✔️ ያወቅነውን በህይወት እየኖርበነው ✔️ በፍቅር ለሌሎች እያካፈልን መኖር ይጠበቅብናል 📌 እንጂ ይህንን እግዚያብሄር ገልጦልኛል ብለን ከሁሉ በለይ አዋቂዎች ወይም አዉቀን የጨረስን አድርገን አናስብ ይህ ትዕቢት ነው 📌 ጌታንም በቃ አውቄዋለሁ የሚል ስሜት ሊሰማን አይገባም። ገና ብዙ አለ 📌በዚህ አለም ሰንመላለስ ምሳሌ ሊሆን የሚገባው እየሱስ ነው። ኢየሱስ ጌታ ሆኖ ሳለ እኛን ለማዳን፣ ክብሩን፣ ሰልጣኑን ሁሉ ትቶ መጣ... እኛ ከዕውቀት ሁሉ ትንሿን አውቀን እንዴት እንታበያለን " ከእውቀት ከፍለን እናውቃለንና፥ ከትንቢትም ከፍለን እንናገራለንና፤" (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13: 9) (1 ቆሮ 1: 21) (1ቆሮ 1:25) 📌 በገለጠልን ልክ በትህትና እንመላለስ። 📌 ይሄ ሲባል ጀግሞ የበለጠ አንወቅ ባለንበት እንቁም ማለት አይደለም ነገር ግን ለማወቅ ወደእርሱ አንቅረብ። እንጠይቅ አርሱ ያስተምረናል ሆሴዕ 6: 3 📌 ሰው ስለሆንን ብዙ ጥያቄ ሊኖሩን ይችላሉ። እነዚህን ጥያቄ ይዘን ወደ ጌታ እንቅረብ እስኪመልስልንም ድረስ በቤት ሆነን እንጠብቀው። አጉረምርመን ከቤቱ አንውጣ 📌በዛ ውስጥ የበለጠ እናውቀዋለን፤ በአዲስ መንገድ ደግሞ እንመለከተዋለን ( 1ነገ 19 ) ( ሮሜ 11:4 )

1.20 MB

1.24 MB

አሁን የእግዚአብሔርን ቃል የምንከፋፈልበት ጊዜ ይሆናል። ዛሬ ቃሉን የምታካፍለን እህት ቢታንያ ናት። አብረን እንካፈል እስቲ😊

ስለ ዝማሬው እግዚአብሔር ይመስገን! 🙌🙌 ያገለገለን ወንድማችንን ጌታ ይባርከው!! በዝማሬው እንደታነፃችሁበት እናምናለን

ዝማሬ፡ ዮሴፍ የማክሰኞ ሕብረት

አሜን!! ስለነበረን የፀሎት ጊዜ ጌታ ይመስገን፡፡ ቦንቱ ተባረኪ አሁን የዝማሬ ጊዜ ይሆናል😊

5.35 KB

እስኪ ጥቂት ደቂቃ ከእህት ቦንቱ ጋር እንፀልያለን።

ሰላም የክርስቶስ ኢየሱስ ለሆናችሁ ለእናንተ ይሁን!! ፕሮግራማችንን በጌታ በኢየሱስ ስም እንጀምራለን። እንግዲህ ጌታ በምህረቱ ደግፎናልና ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን፤ አሜን። ዛሬ ደግሞ አጠር አድ
ሰላም የክርስቶስ ኢየሱስ ለሆናችሁ ለእናንተ ይሁን!! ፕሮግራማችንን በጌታ በኢየሱስ ስም እንጀምራለን። እንግዲህ ጌታ በምህረቱ ደግፎናልና ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን፤ አሜን። ዛሬ ደግሞ አጠር አድርገን የምንተናነጽባቸውን ፍሬ ነገሮች እንከፋፈላለን፤ አብራችሁን ቆዩ።

Diligence combines a willingness to work hard with a discerning focus, a sense of urgency, au vigilant carefulness, and faithful perseverance. And one of the clearest biblical calls to diligence is Paul’s exhortation: Look carefully then how you walk, not as unwise but as wise, making the best use of the time, because the days are evil. Therefore do not be foolish, but understand what the will of the Lord is. (Ephesians 5:15–17) >“A diligent person must learn to strategically neglect lesser priorities.” >A diligent person feels urgency over the brief time he has on earth and seeks to wisely use his brief number of days on the few things he discerns to be the most important for him (Psalm 90:12). >And finally, diligent people faithfully persevere in cultivating and applying a discerning focus, a sense of urgency, and a vigilant care over how they live. Article by Jon Bloom

ሰላም የክርስቶስ ኢየሱስ ለሆናችሁ ለእናንተ ይሁን!! ዛሬ ልንጀምር ያሰብነውን የ online ፕሮግራማችንን በአንዳንድ ምክንያቶች ዛሬ አናከናውንም። ስለዚህም ይቅርታ እንድታደርጉልን ከልብ እንጠይቃለ
ሰላም የክርስቶስ ኢየሱስ ለሆናችሁ ለእናንተ ይሁን!! ዛሬ ልንጀምር ያሰብነውን የ online ፕሮግራማችንን በአንዳንድ ምክንያቶች ዛሬ አናከናውንም። ስለዚህም ይቅርታ እንድታደርጉልን ከልብ እንጠይቃለን። ጌታ ቢፈቅድና ብንኖር ነገ ዕለተ ዕሮብ 12:00 ላይ እንገናኛለን። የጌታ ጸጋና ምህረት ሰላምም ይብዛልን🙏

EECSF_GRAPHICS Join and share : @EECSF
EECSF_GRAPHICS Join and share : @EECSF

🎵ወደ ትጋት ሀገር ይደረግ መብረር የሥንፍናዬ እድሜ አይለፍ ከዛሬ🎶 ታካች ሰው አንሁን፦ የሠራተኛ አምላክ ልጆች ነንና ምሳሌ 6 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁶ አንተ ታካች፥ ወደ ገብረ ጕንዳን ሂድ፥ መንገድዋንም ተመልክተህ ጠቢብ ሁን። ⁷ አለቃና አዛዥ ገዢም ሳይኖራት፤ ⁸ መብልዋን በበጋ ታሰናዳለች፥ መኖዋንም በመከር ትሰበስባለች። ⁹ አንተ ታካች፥ እስከ መቼ ትተኛለህ? ከእንቅልፍህስ መቼ ትነሣለህ? ¹⁰ ጥቂት ትተኛለህ፥ ጥቂት ታንቀላፋለህ፥ ትተኛም ዘንድ ጥቂት እጅህን ታጥፋለህ፤ ¹¹ እንግዲህ ድህነትህ እንደ ወንበዴ፥ ችጋርህም ሰይፍ እንደ ታጠቀ ሰው ይመጣብሃል። “ታካች ሰው፦ አንበሳ በመንገድ አለ፤ አንበሳ በጎዳና አለ ይላል።” — ምሳሌ 26፥13 👉👉ከታይ ዘመናችን በነገር ሁሉ ምንተጋበት ዓመት ይሁንልን👈👈 ❤️stay safe❤️

ጸሎት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር የምናደርገው የጠለቀ ግንኙነት ነው ቃሉ ምን ይለናል፡ 1.በትጋት ጸልዩ እንግዲህ ሊመጣ ካለው ከዚህ ሁሉ ለማምለጥ ፥በሰው ልጅም ፡ፊት ለመቆም እንድትችሉ ስትጸልዩ ሁል ጊዜ ትጉ።"ሉቃ 21:36" “በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፤”— ኤፌሶን 6፥18 2.ሳታቋርጡ፣ ሁል ጊዜ ጸልዩ፣ ሳትሰለቹ ፀልዩ “ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።” ---1ኛ ተሰ5፥17-18 3.ለመጸለይ ሰበብ አያስፈል፣ ቢመቸንም ባይመቸንም መጸለይ አለብን፡ መጽሐፍ ቅዱስ በማናቸውም ሁኔታ እና በየትኛውም ጊዜ እንድንፀልይ ያሳስበናል። ማርቆስ 6 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁴⁵ ወዲያውም ሕዝቡን ሲያሰናብት ሳለ ደቀ መዛሙርቱ በታንኳ ገብተው ወደ ማዶ ወደ ቤተ ሳይዳ እንዲቀድሙት ግድ አላቸው። ⁴⁶ ካሰናበታቸውም በኋላ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ። “ዳንኤልም ጽሕፈቱ እንደ ተጻፈ ባወቀ ጊዜ ወደ ቤቱ ገባ፤ የእልፍኙም መስኮቶች ወደ ኢየሩሳሌም አንጻር ተከፍተው ነበር፤ ቀድሞም ያደርግ እንደ ነበረ በየዕለቱ ሦስት ጊዜ በጕልበቱ ተንበርክኮ በአምላኩ ፊት ጸለየ አመሰገነም።”— ዳንኤል 6፥10 4.ለምን እንጸልያለን? ሰሚ አምላክ ስላለን መዝሙር 34 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁴ እግዚአብሔርን ፈለግሁት መለሰልኝም፥ ከመከራዬም ሁሉ አዳነኝ። ⁵ ወደ እርሱ ቅረቡ ያበራላችሁማል፥ ፊታችሁም አያፍርም። 👉👉👉Pray hard👈👈👈

# Prayer is important as it is a place where we receive vision, strength, solution, Peace...but it's also a place where we listen to God. We as humans, we have so many inabilities. 👉 We need someone who can lead us in life, seeing what's before us 👉 We need someone who can encourage us, who gives true hope 👉 We need someone that can shape us, we know that God wants to see the image of his son through us, so we need someone who can shape us... 👉 We need someone who tells us that we are ok, because we are in good hands 👉 We need someone who tells us that we are not defined by the mistakes that we have made once or by our failed issues or by somebody else but by the one in control of our life and all the other things. That someone can't certainly be a person but God himself So in prayer we came before God knowing he listens and answers, showing all our inabilities and asking God for help, guidance, strength, Thanksgiving and all other... " ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።" (ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4: 6)

እንግዲህ ሊመጣ ካለው ከዚህ ሁሉ ለማምለጥ ፥በሰው ልጅም ፡ፊት ለመቆም እንድትችሉ ስትጸልዩ ሁል ጊዜ ትጉ። "ሉቃ 21:36"

በቅርብ ቀን! Get ready EECSF_ Join and share : @EECSF
በቅርብ ቀን! Get ready EECSF_ Join and share : @EECSF

EECSF_GRAPHICS Join and share : @EECSF
EECSF_GRAPHICS Join and share : @EECSF