EECSF
رفتن به کانال در Telegram
ይህ በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ ህንፃ ኮሌጅ ወንጌል አማኞች ክርስቲያን ህብረት ነው:: #ተቀዳሚ_ዐላማ፤የምንኖርለት:- •ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት #በዚህ_ቻናል:- ☞ የክርስቶስን አካል የ ሚያንፁ ልዩ ልዩ መልዕክቶች ይቀርባሉ:: ☞ከ ህብረቱ መሪዎችና ከ [ኢቫሱ] የ ሚተላለፉ መልዕክቶችን ያገኛሉ::
نمایش بیشتر508
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
508
እግዚአብሔር ሰውን በመልኩና በምሳሌው ለራሱ(ለእግዚአብሔር) ሥለፈጠረው ሰው ከፈጣሪው ጋር መገናኘትን ይፈልጋል።የሚገናኘውም በፀሎት ነው።ፀሎት በእግዚአብሔር ላይ ጥገኛ መሆናችንን፣በራሣችን ብቃት ምንም ማድረግ እንደማንችል ያሣያል።መፅሀፍ ቅዱሥ በማንኛውም ሁኔታ እና በየትኛውም ግዜ እንድንፀልይ ያሣሥበናል።ክርሥቶሥም በምድር ሣለ በቃል እና በተግባር ይህንኑ አሥተምሮናል።ዘወትር መፀለይ ብቻ ሣይሆን ሣንሠለች ደሞ ልንፀልይ ይገባል።እግዚአብሔር ፀሎታችንን እንደሚሠማ እና እንደሚመልሥ ቃሉ ያረጋግጥልናል።እንግዲህ እንድንፀልይ ሚያበረታቱ እነዚህ ምክንያቶች ካሉን በእምነት በክርሥቶስ ኢየሱስ ወደ አባታችን እና ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ።
(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 34)
----------
3፤ እግዚአብሔርን ከእኔ ጋር ታላቅ አድርጉት፥ በአንድነትም ስሙን ከፍ ከፍ እናድርግ።
4፤ እግዚአብሔርን ፈለግሁት መለሰልኝም፥ ከመከራዬም ሁሉ አዳነኝ።
5፤ ወደ እርሱ ቅረቡ ያበራላችሁማል፥ ፊታችሁም አያፍርም።
508
🎶በፀሎት
መልስ ይመለሳል በፀሎት
ልብ ይጠበቃል በፀሎት
በፀሎት በመንበርከክ🎶
(ሃና ተክሌ)
መዝሙር 32
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ ኃጢአቴን ለአንተ አስታወቅሁ፥ በደሌንም አልሸፈንሁም፤ ለእግዚአብሔር መተላለፌን እነግራለሁ አልሁ፤ አንተም የልቤን ኃጢአት ተውህልኝ።
⁶ ስለዚህ ቅዱስ ሁሉ በምቹ ጊዜ ወደ አንተ ይለምናል፤ ብዙ የጥፋት ውኃም ወደ እርሱ አይቀርብም።
📌PRAYER is the first thing we need to put always first!
508
📌prayer is Father and son r/ship that need to be done without ceasing!
👉ሐዋርያት 10 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በቂሳርያ፣ ‘የኢጣሊያ ክፍለ ጦር’ በሚባለው ሰራዊት ውስጥ የመቶ አለቃ የሆነ ቆርኔሌዎስ የተባለ አንድ ሰው ነበረ።
² እርሱም ከመላው ቤተ ሰቡ ጋር በመንፈሳዊ ነገር የተጋና እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ ለሰዎች እጅግ ምጽዋት የሚሰጥ፣ አዘውትሮ ወደ እግዚአብሔር የሚጸልይ ነበር።
📌“ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።”
— 1ኛ ተሰሎንቄ 5፥17-18
📌“በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፤”
— ኤፌሶን 6፥18
👉Here, the scripture tells us
👉አዘውትሮ ወደ እግዚአብሔር የሚጸልይ ነበር።👈
👉ሳታቋርጡ ጸልዩ👈
👉ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ👈
📌Prayer is not something we do when we only want it, but it is something we need do consistently(ሳታቋርጡ;ዘወትር)
📌📌This is b/ce, prayer is:
1.relationship b/n son and father
2.we are in continuous fighting with the devil
❤❤pray without ceasing❤️❤️
Stay blessed and safe!!
508
Grace and peace to you from God our Father and the Lord Jesus Christ.
How are you doing beloved brothers and sisters in Christ?
I hope You are doing great! Be strong God is with us all the time!
በዚህ ሳምንት ሰኞ እንደጀመርነው (ስለ እግዚአብሔር ፍቅር እየተማማርን እንደ ነበር ይታወቃል) ከዚህ በኃላ በየሣምንቱ በተመራረጡ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ከእግዚአብሔር ቃል ስለምንማማር በትጋት እንድትከታተሉና እንድትሳተፉ በጌታ ፍቅር አሳስባችሁለው!!
God bless you for your obedience !!
508
❤️❤️❤️የእግዚአብሔር ፍቅር❤️❤️
ስለ ፍቅር ለመግለጽ መሞከር እጅጉን በጣም ከባድ ነው ምክንያቱም ስለ ፍቅር ለመግለጽ መሞከር ማለት እግዚአብሔርን ለመግለጽ መሞከር ነው። It is impossible! ምክንያቱ ደግሞ "ፍቅር እግዚአብሔር ነው"!
ለጌታ ምን ያህል እንደምንወደው ከመንገራችን በፊት በመጀመሪያ ፍቅሩ ከመረዳት ቢያልፍም እርሱ ምን ያህል እንደወደደን እናም ስለወደደን ምን እንዳደረገልን ማወቅ እና መረዳት የእርሱን ያህል ባንችልም ለእርሱ ባይመጥንም ትክክለኛ ምላሽ እንድንሰጥ ይረዳናል። ፍቅርንም እራሱ ያወቅነው በእርሱ ነውና። “እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤” 1ኛዮሐ 3፥16
የእግዚአብሔር ፍቅር:-
❤️ የእግዚአብሔር ፍቅር ትልቅ ነው፤ ምንም ያህል በደላችን እና ኃጢያታችን እጅግ ብዛቱ ሚዛኑ ቢከብድም የእግዚአብሔር ፍቅሩ ሚዛኑን ደፍቶ ተቀበለን የማይገባንን ህይወት ከክርስቶስ ጋር ሰጠን።
ኤፌ 2፥5 “ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥”
❤️ የእግዚአብሔር ፍቅር ከመታወቅ በላይ ነው፤ “ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል፥ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፥”
ኤፌ 3፥18-19
❤️ እግዚአብሔር አባት እኛን የወደደን አንድያ ልጁን ኢየሱስን በወደደበት መጠን ነው። ልኩ መጠኑ እጅግ ከአእምሮአችን በላይ ነው። What an amazing Love it is???
ዮሐንስ 17
²³ እንዲሁም ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ያውቃል።
²⁶ እኔንም የወደድህባት ፍቅር በእነርሱ እንድትሆን እኔም በእነርሱ፥ ስምህን አስታወቅኋቸው አስታውቃቸውማለሁ።
❤️ እግዚአብሔር ፍቅር ሁሉን ወዷል፡- ወንዱን ሴቷን ፆታ አይለይም፤ ጥቁሩን ቀዩን ዘር አይለይ ብሔር አይለይ፣ ድኃውን ሐብታሙን፣ አለሙን ሁሉ ነው የወደደው ለዚህም ይህ ፍቅር ለእኛም የደረሰን።
“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
ዮሐንስ 3፥16
❤️ it is Unconditional:
"ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
❤️ ይህ ፍቅር የዘላለም ህይወት ሰጥቶናል።
እጅግ በጣም ከሚወደን ውዳችን ጋር ችግር ሀዘን መከራ መከፋት ለቅሶ በሌለበት ዘላለም ከእርሱ ልንኖር ስፍራን ሊያዘጋጅልን ሄዷል ሊውስደን እንዲህ የወደደን ጌታ ኢየሱስ ተመልሶ በክብር ይመጣል።
“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
ዮሐ 3፥16
❤️ በፍቅሩ የራሱ ልጆች እድርጎናል፤ እሁን የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ፣ ልጅ ነሽ አንተም ልጁ ነህ ሃሌሉያ!!!
“የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን።” 1ኛዮሐ 3፥1
❤️ ፍቅሩ ዘላለም ነው። አንዴ ላይጠላን በማይለዋወጠው ሁኔታዎች ላይ ባልተመሠረተው በማይወጣና በማይወርደው በዘላለማዊ ፍቅሩ ወዶናል
“...የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው።”
ዮሐንስ 13፥1
“ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።”
1ኛ ዮሐንስ 4፥10
No one able to separate us from this so wonderful Love!!!
ሮሜ 8:35 &
ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን?…
ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥
ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።"
DEAR GOD WE LOVE U
SO MUCH!!!❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
508
❤❤❤The Love of God❤️❤️
“ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን?”
— ሮሜ 8፥35
ሮሜ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁶ ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።
³⁷ በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።
³⁸ ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥
³⁹ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።
508
God loves his children...It is seen through his continuous forgiveness and kindness
⭕️God never🙅♂says " you are unwelcome or looks at us in a different way because we have sinned" just as people does...
🕐 He always wants our repentance and return to him, he is willing to accept us again
" እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል።"
(የሉቃስ ወንጌል 15: 7)
" ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና ደግሞም ሕያው ሆኖአል፤ ጠፍቶም ነበር ተገኝቶአልም። ደስም ይላቸው ጀመር።"
(የሉቃስ ወንጌል 15: 24)
Even if we do wrong he doesn't have evil intentions toward us. He is always good for us.
If he punishs us for our wrong doing, it's not with bad intentions. His plans for us is always good...never to harm us.
😊His kindness is beyond measure
Even when we don't know him, love him back and when we were still in sin, his response was not as it should have been, instead
👉He provide way for our salvation " በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።"
(የዮሐንስ ወንጌል 3: 16)
👉He provide way for us to have relationship and peace with him
" እንግዲህ በእምነት ከጸደቅን በእግዚአብሔር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እንያዝ፤"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 5: 1)
508
" ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥" ኤፌ 2:5
እግዚአብሔር የወደደን የሚወደድ ነገር ሳይኖረን ነው።ስለዚህ እሡን በድርጊታችን ለማስደሠት አንሞክር።አሁንም የሚወደን ሥራችን አይቶ አይደለም።
508
❝... በእኔ ላይ ያለው ዓላማውም ፍቅር ነው።❞ —መኃልየ. 2: 4
🎶 ሰው ሁሉ ንፁህ ሆኖ እኔ ግን ብቆሽሽ
በምድር ላይ እኔ ብቻ በኃጢአት ብበላሽ
መሞት የሚገባኝ እኔ ብቻ ብሆን
ኢየሱስ ለብቻዬ ይመጣልኝ ነበር
❤️❤️ የወደደን በፍቅሩ እንድንኖር ነው - ሁልጊዜ ሊወደን
508
------------📖-------------
❝እርሱ በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል፥ ስለዚህም እኛ ራሳችን በእግዚአብሔር በምንጽናናበት መጽናናት በመከራ ሁሉ ያሉትን ማጽናናት እንችላለን።❞
2ኛ ቆሮ 1: 4
------------📖-------------
508
ፆም ነው የሚፈቱት ወይስ ለሀጢያት ነው የሚፈቱት?
ወንድም እህቶቼ ይህን ፅሁፍ የፃፍኩት ሰሞኑን ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ወጣቶች ፆም ሲፈቱ ስለሚያደርጉት አሳፋሪ ነገሮች ያለ ሀፍረት ሲናገሩ አይቼ በማዘኔ ነው።
በእውነት ልናነቃቸው ይገባል!
ፆም ከፀሎት ጋር ካልሆነ ድህነትን ማሰቢያ እንጂ እግዚአብሔርን ማሰቢያ አይሆንም። እንደዛ ቢሆንማ እንደታረዙ ሰዎች ቅዱስ አይኖርም ነበር።
ብርቱ ሰው ግን በፆም ውስጥ ይፀልያል በፀሎቱ ውስጥ ስጋውን ጎስሞ እግዚአብሔርን ይፈልጋል ደግሞም ያያል።
ፆም ከፀሎት ጋር ከሆነ ከሀጢያት ይፈታል!
ፆም ብቻውን ግን ለሀጢያት ይፈታል።
"በአምላካችን ፊት ራሳችንን እናዋርድ ዘንድ፥ ከእርሱም የቀናውን መንገድ ለእኛና ለልጆቻችን ለንብረታችንም ሁሉ እንለምን ዘንድ በዚያ በአኅዋ ወንዝ አጠገብ ጾም አወጅሁ።
ስለዚህም ነገር ጾምን፥ ወደ እግዚአብሔርም ለመንን፤ እርሱም ተለመነን።"
መጽሐፈ ዕዝራ 8 : 21 እና 23
508
------------📖------------
❝በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም።❞
ዮሐንስ 15: 4
------------📖------------
