EECSF
رفتن به کانال در Telegram
ይህ በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ ህንፃ ኮሌጅ ወንጌል አማኞች ክርስቲያን ህብረት ነው:: #ተቀዳሚ_ዐላማ፤የምንኖርለት:- •ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት #በዚህ_ቻናል:- ☞ የክርስቶስን አካል የ ሚያንፁ ልዩ ልዩ መልዕክቶች ይቀርባሉ:: ☞ከ ህብረቱ መሪዎችና ከ [ኢቫሱ] የ ሚተላለፉ መልዕክቶችን ያገኛሉ::
نمایش بیشتر508
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
508
መዝሙር 98
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
² እግዚአብሔር ማዳኑን አስታወቀ፥ በአሕዛብም ፊት ጽድቁን ገለጠ።
³ ለያዕቆብ ምሕረቱን ለእስራኤልም ቤት እውነቱን አሰበ፤ የምድር ዳርቻዎች ሁሉ የአምላካችንን ማዳን አዩ።
የእግዚአብሔርን ማዳን እንዲያዩ ለሱዳን አረብ ህዝብ እንፀልያለን!
ማለዳዬን ለጌታ!!
508
#PCS Part 5
ወንጌልን በ PCS በኩል ለማካፈል ማስተዋል ካሉብን ነገሮች መካከል፡
1. የግል ቅድስና (ምልልስ)
የክርስቶስን መልክ ለማያውቁት መግልጥ የሚወድ ቢኖር እርሱ መጀመሪያ ክርስቶስን መምሰል አለበት፣ ዮሐንስ በመልዕክቱ በብርሃን ተመላለሱ ያለው ይህንን ነው፤ እኛ በብርሃን ተመላልሰን ለሌላው ብርሃን እንድንሆን!
2. ግኑኝነትን ማጠናከር
የእግዚአብሔርን ወንገል በግቢ ውስጥ ለመስራት ግኑኝነት/ጓደኝነት በጣም ወሳኝ ነው፤ ነገር ግን ይህ ሲባል በጓደኝነት አጥር ውስጥ በመታጠር ክርስቶስን ለነሱ ከማካፈል ይልቅ ጓደኝነታችን እንዳይበላሽ መጥንቀቅን ሳይሆን ለነሱ ግድ እንደሚለን በማሳየት፣ በመንከባከብ፣ በምግብ ቢሆን በስራ አብረናቸው በመሆን ግኑኝነታችንን ማጠናቀቅ።
-ለእነርሱ መጸለይ
-ካለን ነገር ማካፈል
-ስለሚያምኑት እምነት በቂ እውቀት ማዳበር እና ማክበር
-ስለ እነርሱ ማወቅ
እና ልብ ማለት ያለብን ነገር እኛ በተወደድንበት ፍቅር ነው ለሎችን መውደድ ያለብን!
3. ወንጌልን ስንናገር
-ወንጌልን ለመመስከር ከየዕለት ምልልሳችን በመነሳት በዛ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ጥያቄ እንዲነሳ ማድረግ፣
-እነሱ ከሚያነሱት ጉዳይ በመነሳት ጥያቀዎችን መፍጠር
-ስለ ህይወት ምልልስ ማውራት፣
-የራስን ልምምድ ወይም የሌሎችን ልምምድ ማካፈል
-ወንጌልን ስንናግር በአስተምሮ (Doctrinal) ጉዳዮች ላይ በተቻለ አቅም አለመከራከር፣ ክርክር ልዩነትን ያሰፋል! ግን በተረጋጋ መንፈስ የእግዚአብሔርን ቃል ማስረዳት
-ከልዩነት ይልቅ በሚያግባባን ነገር ላይ መሰረት በማድረግ መጀመር
-መጽሐፍ ቅዱስ በጋራ ማጥናት
-መጽሐፍትን እና መዝሙራትን ማካፈል
4. የእርሱን ሃይል መመልከት (The Power Behind You)
ማቴዎስ 28
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁸ ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ።
¹⁹-²⁰ እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።
ታላቁን ተልዕኮ ከመናገሩ በፊት ክርስቶስ ይህንን ማረጋገጫ ሰጥቶናል ይህም ስልጣን ሁሉ የጌታ እንደሆነ እና ሲዘጋውም እስከ አለም ፍጻሜ ድረስ አብሮን እንደሆነ ማረጋገጫ ሰጥቶናል። ይህንንም ተልዕኮ ሲሰጠን እርሱ ራሱን ተማምኖ እንጂ በኛ ኃይል እንዳልሆነ እናውቃለን፤ እኛ ብንተክል፣ ውሃ ብናጠጣ አልያም ብዙ ነገር ብናደርግ የሚያሳድግ እርሱ እንደሆነ አውቀን ከኛ ሚጠበቀውን ሁሉ እናድርግ። እኛ ከምናደርገው በላይ የስራው ባለቤት እንደሚሰራ አውቀን፣ በእርሱ ላይ ታምነን የየድርሻችንን እንወጣ።
“እንግዲያስ የሚያሳድግ እግዚአብሔር እንጂ የሚተክል ቢሆን ወይም የሚያጠጣ ቢሆን አንዳች አይደለም።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 3፥7
ታዲያ ምን እናድርግ?
-ከራሳችን ከማንነታችን እንጀምር ..... ማለትም ራሳችንን እግዚአብሔርን ለመምሰል እናስለምድ ያለንንም ግኑኝነት እናጠናክር
-ከዛም ደግሞ በአጠገባችን ካሉት የተረዳነውን ከመስበክ እንጀምር ... ጓደኛ ፣ ዶርም ዉስጥ ፣ ክፍል ውስጥ .... ወዘተ...... ወንጌልን ስበኩ ፤ ደቀ መዝሙርም አድርጉ ።
#ወንጌል ስለልጁ ነው!
#ወንጌል ስለክብሩ ነው!
#ወንጌል ስለእግዚአብሄር መንግስት ነው!
እናም
#ወንጌል ኃላፊነታችን ነው!!!
ተባረኩ!
#activate_action
#PCS
508
TEUSDAY SERVICE
"ከእነርሱም ጋር አብሮ ሳለ ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡ አዘዛቸው፥ ነገር ግን፦ ከእኔ የሰማችሁትን አብ የሰጠውን የተስፋ ቃል ጠብቁ፤
ዮሐንስ በውኃ አጥምቆ ነበርና፥ እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኃላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ አለ።"
ሐዋርያት 1:4-5
💥የፀሎት ጊዜ
💥የአምልኮ ጊዜ
💥የቃል ጊዜ
ቦታ - Lideta Assemble of God church
ሰዓት- 11:30
🔥🔥በፍፁም አይቀርም❗️❗️
ሁላችሁም ኑ የእግዚአብሔርንም ድንቅ ስራ እዩ።
#EiABCFelloship
508
“እንግዲህ ያላመኑበትን እንዴት አድርገው ይጠሩታል? ባልሰሙትስ እንዴት ያምናሉ? ያለ ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ?”
— ሮሜ 10፥14
የሚጸለይለት የህዝብ ክፍል-አገው!
በጸሎት እንትጋ!🙏
