EECSF
رفتن به کانال در Telegram
ይህ በ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ ህንፃ ኮሌጅ ወንጌል አማኞች ክርስቲያን ህብረት ነው:: #ተቀዳሚ_ዐላማ፤የምንኖርለት:- •ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት #በዚህ_ቻናል:- ☞ የክርስቶስን አካል የ ሚያንፁ ልዩ ልዩ መልዕክቶች ይቀርባሉ:: ☞ከ ህብረቱ መሪዎችና ከ [ኢቫሱ] የ ሚተላለፉ መልዕክቶችን ያገኛሉ::
نمایش بیشتر508
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
508
ዛሬም እንኳን አጎንብሼ ወይም ዘልዬ የማልሸውደው ጥሪ ቢኖር ይኸው "ናና ሙት" የሚለውን የክርስቶስ ጥሪ ነው:
ለመሞት የፈቀደና የሞተ ብቻ ነው በክርስቶስ ውስጥ ያለውን treasure የሚካፈለው: ክርስቶስ ሞተን ለእግዚአብሔር የምንኖርበት እውነት ነው - እየሞቱ መኖር::
አለመሞቴ ጎልቶ ሲታየኝና የመሞቻዬ መንገዱ ደግሞ መስቀሉ ብቻ እንደሆነ ሳስብ "አልችልም እርዳኝ" ብዬ እጮኻለሁ።
እኔ መሞት የሚገባው እንጂ ምንም በሕይወት መኖርና መገለጥ የሚገባው ነገር የለኝም፡ መገለጥ ያለበት ክርስቶስ ብቻ ነው፡ የዚህ መንገዱ ደግሞ መስቀሉ ብቻ ነው: አቋራጭ የለውም።
ከራሱ ይልቅ የክርስቶስን ሕይወት የመረጠ ብቻ የሚሄደው መንገድ ነው።
ፀጋ ይብዛልን!!
508
#PCS Part 4
ዕብራውያን 1:1-2
"ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ፥ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤.."
እግዚአብሄር አሕዛብን ሁሉ ወደ ራሱ ይጠቀልል ዘንድ እስራኤልን መረጠ ዘፀ (19:5-9)፣ ለእነርሱም በልዩልዩ ጎዳና ከተናገረ በኋላ፤ ለኛ ደግሞ በኢየሱስ ክርስቶስ ተናገረን። ክርስቶስም ከትንሳኤ በኋላ ለደቀ-መዛሙርቶቹ እንዲህ አላቸው፦
“እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”
— ማቴዎስ 28፥19-20
ይህም ለየትኛውም ክርስትያን ታላቁ ተልእኮ ነው፣ ሁሉም ክርስትያን ስራው ይህ ነው፤ ጴጥሮስ በመልዕክቱ እንዳለ፡
1ኛ ጴጥሮስ 2፡9
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤
የእግዚአብሔር ዓላማ ይህ ነው “ከዚህ በኋላ አየሁ፥ እነሆም፥ አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፤” — ራእይ 7፥9
እግዚአብሔር ዛሬም ልጁን ይዘን በዓለም ሁሉ እርሱን እንድንገልጥ ጠርቶናል፣ ዋናው መስካችን ደግሞ EIABC ግቢ ነው፤ እኛ ሁላችን በግቢ ውስጥ የእግዚአብሔር መልዕክተኞች ነን።
ታዲያ ምን እናድርግ?
-ከራሳችን ከማንነታችን እንጀምር ..... ማለትም ራሳችንን የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ለማድርግ እንቀድስ
-ከዛም ደግሞ በአጠገባችን ካሉት የተረዳነውን ከመስበክ እንጀምር ... ጓደኛ ፣ ዶርም ዉስጥ ፣ ክፍል ውስጥ ፣ ቤተሰብ ፣ ዘመድ .... ወዘተ...... ወንጌልን ስበኩ ፤ ደቀ መዝሙርም አድርጉ ።
#ወንጌል ስለልጁ ነው!
#ወንጌል ስለክብሩ ነው!
#ወንጌል ስለእግዚአብሄር መንግስት ነው!
እናም
#ወንገል ኃላፊነታችን ነው!!!
ተባረኩ!
#activate_action
#PCS
508
“ክብሩን ለአሕዛብ ተኣምራቱንም ለወገኖች ሁሉ ንገሩ፤”
— መዝሙር 96፥3
ምድር ሁሉ ከክብርህ ትሞላ ዘንድ፣ ህዝብም ሁሉ ማዳንህን ያይ ዘንድ ይገባሃል!
እንጸልይ!
ተባረኩ!
508
📢📢 Hi 👋👋👋beloved how are u doing....
💥this is from worship team leaders, we are glad to see you with as and we are thankful.
✨✨✨As your request to join our team entrance exam will be on Friday @9:30LT come on time❗️❗️❗️❗️
Stay blessed❤️❤️❤️❤️
🎺🎺 FROM WORSHIP TEAM
🎷🎷🎹🪗🎸🪕🎻🥁🪘🎼
508
አለመፀለይ #Normal አይደለም‼️
━━━━━⊱✿⊰━━━━━
🌑እንደ አለመፀለይ(ከኢየሱስ ጋር እንደ አለማውራት) በክርስትያኖች ህይወት ትልቅ #ኪሳራ የለም!
🌑መንፈሳዊ ህይወቴ #ደክሟል ስለዚህ መፀለይ አልቻልኩም ስትሉ ለበለጠ ድካም ራሳችሁን አሳልፋችሁ እየሰጣችሁ እንደሆነ አትርሱ!
🌒መበርታት እፈልጋለሁ ግን መፀለይ አልችልም ወይም ይሰለቸኛል ማለት መዳን እፈልጋለሁ መድሀኒቱን ግን አልወስድም እንደማለት ነው (ብትደክሙ እንኳን #ፈውሳችሁ ያለው እዛው ነው)
🌓ስለዚህ መፀለይ ሲያቅታችሁ ጌታ ሆይ መፀለይ እንድችል እርዳኝ ብላችሁ #ፀልዩ!!
🌔#ፀሎት መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን እንዲቃትት በመፍቀድ ከጌታ ከራሱ ጋር ህብረት ማድረግ እንጂ የተመረጡ ቃላትን እየተጠቀሙ ምሬትን መግለጫ መንገድ አይደለም!!
🌕እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤
ሮሜ 8 : 26
🌕ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።
1ተሰ5 : 17-18
🌕ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች ሥጋ ግን ደካማ ነው አለው።
ማቴ 26 : 41
#MENTENA
508
PCS: part 3
የሰው ልጅ ባለመታዘዙና በበደሉ ምክንያት ከእግዚአብሔር መገኘት ራቀ፡፡ ሰው ወደቀ፡፡ ...... ነገር ግን እግዚአብሔር አለምን ሁሉ ያድን ዘንድ ለአብርሃም ኪዳን ገባለት፣ባረከዉም።
ዘፍ 12፡1- 3
ዘፍ 13: 15
ዘፍ 15፡5
ዘፍ 26: 3-5
ዘፍጥረት 22
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁷ በእውነት በረከትን እባርክሃለሁ፥ ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብትና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘርህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳል፤
¹⁸ የምድር አሕዛብ ሁሉም በዘርህ ይባረካሉ፥ ቃሌን ሰምተሃልና።
~በዚህ ሁሉ ድግግሞሽ ውስጥ እግዚአብሔር የሚገባለት ቃል "በዘርህ አለም ይባረካል" እያለ ነው።
~በአሁኑ ጊዜ በአለም ላይ ወደ 16,000 የሕዝብ ነገዶች አሉ። ከእነዚህ ዉስጥ 6,000 ያክሉ ነገዶች እግዚአብሔርን በፍጹም አያውቁም።
“ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፤ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።”
— መዝሙር 46፥10
~እግዚአብሔር የእስራኤል አምላክ ብቻ ሳይሆን የምድር ሁሉ አምላክ ነው፤ በእነርሱም ዘንድ ራሱን ይፈልጋል።
~እግዚአብሔር በአህዛብ መካከል ከፍ ከፍ ማለት ይፈልጋል።
“እርሱም፦ የያዕቆብን ነገዶች እንድታስነሣ ከእስራኤልም የዳኑትን እንድትመስል ባሪያዬ ትሆን ዘንድ እጅግ ቀላል ነገር ነውና እስከ ምድር ዳር ድረስ መድኃኒት ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌ ሰጥቼሃለሁ ይላል።”
— ኢሳይያስ 49፥6
~እግዚአብሔር ለኢሳያስ ፡ የእስራኤል ነገድ ብቻ ሳይሆን የምድር ነገድ ሁሉ ብርሃን እንድትሆን ነው' ።
~የበረከቱም ሚስጥር ይሄ ነው። በአብርሃምና በዘሩ አለም ሁሉ ይባረክ ዘንድ ነው።
በዛሬዋ እለት በአለማችን ላይ ፡
*ሃይማኖት የለሾች = 101,000,000 ሰዎች
*ሙስሊም = 1,300,000,000 ሰዎች
*የጎሳ እምነት = 161,000,000 ሰዎች
*ቡድሂዝም = 275,000,000 ሰዎች
*ሂንዱይዝም = 860,000,000 ሰዎች
በአጠቃላይ ወደ 3,000,000,000 (3 ቢሊዮን) ሰው አለም ላይ ወንጌልን አልሰማም።
~ውድ ወገኖቼ ይሄ ጉዳይ የእግዚአብሄር ዋና ዋናና ዋነኛው ጉዳይ ነው። የተጠራንበትም አላማ ለዚህ ነው...... ደቀ መዝሙር እንድናደርግ !!
~ግን እያንዳንዱ አማኝ የተጠራበትን ጥሪ እየኖረው ነውን? .... በፍጹም በፍጹም አይደለም።
ታዲያ ምን እናድርግ?
-ከራሳችን ከማንነታችን እንጀምር ..... ማለትም ራሳችንን ለራሱ ለእግዚአብሄር ከመስጠት
-ከዛም ደግሞ በአጠገባችን ካሉት የተረዳነውን ከመስበክ እንጀምር ... ጓደኛ ፣ ዶርም ዉስጥ ፣ ክፍል ውስጥ ፣ ቤተሰብ ፣ ዘመድ .... ወዘተ...... ወንጌልን ስበኩ ፤ ደቀ መዝሙርም አድርጉ ።
#ወንጌል ስለልጁ ነው!
#ወንጌል ስለክብሩ ነው!
#ወንጌል ስለእግዚአብሄር መንግስት ነው!
#FELLOSHIP_IS_NOT_AN_ORGANIZATION_BUT_ITS_A_MOVEMENT_______SO_MOVEEEEE!!
ተባረኩ!
#activate_action 💪💪💪
#PCS
508
ሰላም እንዴት ናችሁ ውድ የEiABC ክርስቲያን ተማሪዎች፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም እና ፀጋ ለእናንተ ይሁን ።
Team ያልመረጣችሁ የህብረታችን ልጆች ከታች👇👇 በምታዩት Google Form በመመዝገብ እግዚአብሔር በሰጣቹ ፀጋ እንድታገለግሉ እናንተም ደግሞ እንድትገለገሉ ስንል በትልቅ ፍቅር እንጋብዛችኋለን🙏🙏🙏🙏።
https://forms.gle/2ca9DVPLADKmVBLFA
@EiABC fellowship
508
#PCS 2
ባለ ተልዕኮው እግዚአብሔር (The Missionary GOD)
ከዘፍጥረት - ራዕይ
ክፍል-1: የእስራኤል ጥሪ
እግዚአብሔር የሰውን ልጅ በራሱ መልክ እና ምሳሌ የፈጠረው ቢሆንም፤ የሰው ልጅ ግን አለመታዘዝን መረጠ፣ በዚህም ምክንያት ከእግዚአብሔር መገኘት ራቀ።
እግዚአብሔር ግን ከሰው ልጅ ጋር ለመታረቅ አንድን ሰው ተመለከተ በእርሱም ውስጥ በክርስቶስ ኢየሱስ የተዋጀ ህዝብን አየ፤ ለበረከትም ጠራው
ዘፍጥረት 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እግዚአብሔርም አብራምን አለው፦ ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ።
² ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም አከብረዋለሁ፤ ለበረከትም ሁን፤
ከአብርሃምም የዘር ሀረግ እስራኤል ህዝብ ሆኖ ወጣ። እስራኤልም ከግብፅ በእግዚአብሔር በፀናች እና በተዘረጋ ክንድ ከወጡ በኃላ በሲና ተራራ ከእግዚአብሔር ቃል ኪዳንን ተቀበሉ፣ አግዚአብሔርም በተራራው እንዲህ አላቸው
ዘጸአት 19
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ አሁንም ቃሌን በእውነት ብትሰሙ ኪዳኔንም ብትጠብቁ፥ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአሕዛብ ሁሉ የተመረጠ ርስት ትሆኑልኛላችሁ፤
⁶ እናንተም የካህናት መንግሥት የተቀደሰም ሕዝብ ትሆኑልኛላችሁ። ለእስራኤል ልጆች የምትነግራቸው ቃል ይህ ነው።
አግዚአብሔር እስራኤልን
-የተመረጠ ርስት
-የካህናት መንግሥት
-የተቀደሰም ሕዝብ
ሲል በእነርሱ በኩል በዓለም ሁሉ ራሱን ሊያስቃውቅ እንጂ እነርሱን የተለየ አድርጎ በማየት አልነበረም! እርሱ የሰማይና የምድር ፈጣሪ የሁሉ አምላክ ነውና፤ ግን በእስራኤል በኩል ራሱን ለአሕዛብ ይገልጥ ነበር።
ፀሎት፦ አቤቱ እምላኬ እና ጌታዬ ሆይ ስምህ በሰማይና በምድር ብሩክ ይሁን፤ እነሆ በዚህ ዘመን ልጅህን በዓለም ሁሉ ለማሳወቅ እኔን
-የተመረጠ ርስት
-የካህናት መንግሥት
-የተቀደሰም ሕዝብ
አርገህ መርጠኸኛል ግን ልዩ ሆኜ ሳይሆን በኔ በኩል ልጅህን ልትገልጥ ነውና፤ እኔም ይህን ተረድቼ ወንጌልን ለዓለም ሁሉ እሰብካለሁ፤ በዙሪያዬ ባሉት ሁሉ አንተን ልገልጥ ከፊት ይልቅ እተጋለሁ፣ ይህም በመንፈስህ እንጂ በኔ ኃይል አይደለምና ፀጋህ ያበርታኝ!🙏🙏
-አሜን!!!
ተባረኩ!
#activate_action
#PCS
508
“በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና።”
— ሮሜ 1፥16
አቤቱ የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ ወንጌል እኔ የዳንኩበት መሠረት፣ ደግሞም በአለም ላይ ለሉ ሁሉ በስምህ ላመኑ ያንተ የማዳን ኃይል ነውና! አይሁድ ሳልል የግሪክ ሰው፤ ይህም ማለት ዘርን ሳልመርጥ፣ በጓደኝነት አጥር ውስጥ ሳልታጠር የዳንኩበትን ያንተን ኃይል (ወንጌልህን) ለህዝብ ሁሉ እንድናገር አንተ እርዳኝ🙏🙏 በወንጌል አላፍርምና!...... አሜን!!
Action team!
#activate_action
#PCS
508
#የእግዚአብሔርቃል_ሙላት_ይኑርባችሁ፡፡
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ዕቅድ
ቅደም ተከተላዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
ከJanuary 1 እስከ December 31 2023
በ ACTION TEAM ተዘጋጅቶ የቀረበላችሁ ፡፡
#activate_action
508
"ከዋና ዋና የፌስቡክና የትዊተር ጠቀሜታዎች መካከል አንዱ በመጨረሻው ቀን ጸሎት አልባነት ከጊዜ እጥረት የተነሳ እንዳልሆነ ማረጋገጥ ነው።"
~ዮሐንስ ፓይፐር~
ወዳጆቼ፣ የማንጸልየው ጊዜ አጥተን አይደለም ሰንፈን ነው።
