fa
Feedback
SMH General Construction

SMH General Construction

رفتن به کانال در Telegram

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም 👷‍♂እናማክራለን 🏢ዲዛይን እናደርጋለን 📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን 🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን 📲 0953138434(Eng sintayehu melese) tiktok https://www.tiktok.com/@ethiocons ለሃሳብ እና ኣስተያየት @Ethiocon143bot ይጠቀሙ

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام SMH General Construction

کانال SMH General Construction (@ethioengineers1) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 23 047 مشترک است و جایگاه 423 را در دسته خانه و معماری و رتبه 1 502 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 23 047 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 02 سپتامبر, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر -319 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر -22 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 18.98% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 6.73% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 4 375 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 1 552 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 20 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም 👷‍♂እናማክራለን 🏢ዲዛይን እናደርጋለን 📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን 🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን 📲 0953138434(Eng sintayehu melese) tiktok https://www.tiktok.com/@ethiocons ለሃሳብ እና ኣስተያየት @Ethiocon143bot ይጠቀሙ

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 03 سپتامبر, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته خانه و معماری تبدیل کرده‌اند.

23 047
مشترکین
-2224 ساعت
-1067 روز
-31930 روز
آرشیو پست ها
በሳይት ላይ የColumn Starter Bar Realignment Inspection! 🧐🏗️ ​በምስሉ ላይ እንደሚታየው በፋውንዴሽን/በግሬድ ቢም ላይ የተተከሉት የኮለም ስታርተር ብረቶች (Column
በሳይት ላይ የColumn Starter Bar Realignment Inspection! 🧐🏗️ ​በምስሉ ላይ እንደሚታየው በፋውንዴሽን/በግሬድ ቢም ላይ የተተከሉት የኮለም ስታርተር ብረቶች (Column Dowels) ከቦታቸው በመዛባታቸው በፓይፕ ተይዘው በሃይል ለማስተካከል እየተሞከረ ይገኛል። ​በኮለም ብረት ማስተካከል (Rebar Alignment/Cranking) ወቅት ሊዘነጉ የማይገባቸው ዋና ዋና የጥራት ቁጥጥር ነጥቦች፦ 1. ​Avoid Sharp Bends (Kinking): ብረቱን በከፍተኛ ሁኔታ በሹል መልክ ማጠፍ (Sharp Bend) በብረቱ ውስጣዊ መዋቅር ላይ ማይክሮ-ስንጥቆች (Micro-cracks) ስለሚፈጥርና የTensile Strength ስለሚቀንሰው በጽኑ የተከለከለ ነው። 2. ​Maximum Permissible Crank Ratio (1:6): የኮለም ብረትን ከቦታው ሲዛባ ማስተካከል የሚቻለው ማዘመሚያው ratio ቢያንስ 1:6 (በየ 6cm ቁመት 1cm ዝንባሌ) ሲሆን ብቻ ነው። 3. ​Cold Bending Only: በሳይት ላይ ብረቶችን ለማጠፍ በሚሞከርበት ጊዜ በጭራሽ በሙቀት/በእሳት (Heating/Torch) ማለስለስ አይፈቀድም። ​በእርስዎ ሳይት ላይ የኮለም ስታርተር ብረቶች ከቦታቸው በከፍተኛ ሁኔታ ቢዛቡ ምን ዓይነት የማስተካከያ ዘዴ (Remedial Action) ትጠቀማላችሁ? (Anchor Bolt፣ Epoxy Chemical Dowel ወይስ Offset Cranking?) ሃሳብዎን በኮሜንት ያካፍሉን! ​​

በሳይት ላይ የPad Footing PVC Sleeves Inspection! 🧐🏗️ ​በምስሉ ላይ እንደሚታየው የፓድ ፉቲንግ ኮንክሪት ከተፈሰሰ በኋላ በስታርተር ብረቱ ዙሪያ የPVC ቱቦዎች (Sleeve
በሳይት ላይ የPad Footing PVC Sleeves Inspection! 🧐🏗️ ​በምስሉ ላይ እንደሚታየው የፓድ ፉቲንግ ኮንክሪት ከተፈሰሰ በኋላ በስታርተር ብረቱ ዙሪያ የPVC ቱቦዎች (Sleeves) ተተክለው ይገኛሉ። ይህ አሰራር በስራ ቦታዎች ላይ ለተለያዩ ኢንጂነሪንግ ዓላማዎች ይውላል። ​በፉቲንግ ላይ PVC Sleeves የሚተከሉበት ዋና ዋና ምክንያቶች፦ 1. ​Anchor Bolt Pocket Creation: ለብረት ስትራክቸር (Steel Columns) የሚያገለግሉ Anchor Bolts ኮንክሪቱ ከደረቀ በኋላ በትክክለኛው Alignement ለመትከል እና Grouting ለማድረግ ቦታ ለማዘጋጀት። 2. ​Post-tensioning / Ground Anchors: ፋውንዴሽኑ ከስር ካለው አፈር ወይም ድንጋይ ጋር በጥብቅ እንዲያያዝ ለጂኦቴክኒካል አሬንጅመንት (Ground Anchors/Micro-piles) ማስገቢያ ቀዳዳ ለማዘጋጀት። 3. ​Plumbing/Utility Penetrations: አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የውሃ እና የፍሳሽ መስመሮች በኮንክሪት አካል ውስጥ ማለፍ እንዲችሉ አስቀድሞ ቦታ ለማዘጋጀት (Sleeving)። ​

በግንባታ ስራ ላይ የብረት (Rebar) ዋና ጥቅም ምንድን ነው? 🧐🏗️ ​ብዙ ጊዜ "ኮንክሪት ጠንካራ ከሆነ ብረት ለምን ያስፈልገዋል?" የሚል ጥያቄ ይነሳል። መልሱ የኮንክሪት እና የብረት ተፈጥሮአዊ ባህሪ ይለያያል! ​ብረት በመዋቅር ውስጥ የሚሰጣቸው 3 ወሳኝ ጥቅሞች፦ 1. ​የመወጠር ኃይልን መሸከም (High Tensile Strength)፦ ኮንክሪት የመጫን ኃይልን (Compressive Force) የመቋቋም ከፍተኛ አቅም ቢኖረውም፣ የመወጠር ኃይልን (Tensile Force) ግን መቋቋም አይችልም። ብረት በኮንክሪት ውስጥ ሲገባ ይህንን የመወጠር ኃይል በመሸከም ቢም እና ሰላብ እንዳይሰነጠቁ ያደርጋል። 2. ​የመተጣጠፍ እና የመለጠጥ ባህሪ (Ductility)፦ የመሬት መንቀጥቀጥ ወይም ከፍተኛ የጎንዮሽ ኃይል በሚመጣበት ጊዜ መዋቅሩ ሳይፈርስ ወይም ሳይቆረጥ በቂ የመታጠፍ ዕድል (Deformation) እንዲኖረው በማድረግ ድንገተኛ የመፍረስ አደጋን ይከላከላል። 3. ​የስንጥቅ ቁጥጥር እና የሙቀት መጣጣን (Crack Control & Thermal Expansion)፦ በኮንክሪት ድርቀት (Shrinkage) የሚፈጠሩ ስንጥቆችን ይይዛል። በተጨማሪም የብረት እና የኮንክሪት የሙቀት መስፋፋት መጠን (12 * 10^-6 /°C}) እጅግ ተቀራራቢ በመሆኑ፣ በሙቀትና በብርድ ወቅት ሁለቱም አካላት አብረው በመስፋፋትና በመኮማተር ሳይላቀቁ በጥሩ ትስስር (Bond) ይሰጣሉ። ​የእርስዎ ሳይት ላይ በብረት ፍተሻ ወቅት ትኩረት የሚሰጡት ዋና ነጥብ ምንድን ነው? (ዲያሜትር፣ የካሬ እጥፋት፣ ወይስ ላፕ ርዝመት?)

🏗️ ስለ ጠጣር (Aggregate) ይህን ያውቃሉ? ​በማንኛውም ግንባታ ውስጥ ከ 60% እስከ 75% የሚሆነውን የኮንክሪት አካል የሚሸፍነው (ጠጠር እና አሸዋ) መሆኑን ያውቃሉ? ጠጣሩ ለህንጻዎ ጥንካሬ እና ዘላቂነት ዋናው መሠረት ነው! ​ዋና ዋና የጠጣር ዓይነቶች፡ 1. ​ደቅቅ ጠጣር (Fine Aggregate)፡ መጠናቸው ከ 4.75 ሚ.ሜ በታች የሆኑ (እንደ አሸዋ ያሉ) ሲሆኑ፤ በትልልቅ ጠጠሮች መካከል ያለውን ክፍተት ይሞላሉ። 2. ​ግዙፍ ጠጣር (Coarse Aggregate)፡ መጠናቸው ከ 4.75 ሚ.ሜ በላይ የሆኑ ጠጠሮች ሲሆኑ፤ ለኮንክሪት ዋናውን የመሸከም አቅም ይሰጣሉ። ​ጥራት ያለው አግሪጌት መጠቀም ያለው ጥቅም፡- .​የኮንክሪት የመሸከም አቅምን ይጨምራል። . ​ሲሚንቶ ሲደርቅ የሚፈጠርን መሰነጣጠቅ ይከላከላል። . ​አላስፈላጊ የሲሚንቶ ብክነትን በመቀነስ ወጪን ይቆጥባል።

⚡️አንድ የግንባታ ፕሮጀክት ጨረታ ሲሞላ ከEngineer’s Estimate (EE) ምን ያህል በታች ወይም በላይ መሆን አለበት? የሚለው በቀጥታ “ይህን ፐርሰንት መሆን አለበት” የሚል አንድ ዓለም-አቀፍ ደንብ የለውም። ✤ግን በተግባር ለመገመት ይህን መመሪያ መጠቀም ትችላለህ፦ 🌶0%–5% በታች/በላይ → በአጠቃላይ ከEE ጋር በጣም ቅርብ ነው። 🌶5%–10% በታች → ተወዳዳሪ ዋጋ ነው፣ ግን cost breakdown በጥንቃቄ መፈተሽ ይገባል። 🌶10%–20% በታች → በጣም ዝቅተኛ ዋጋ መሆን ስለሚችል የተጫራቹን financial capacity, resource cost, material/labour rates, overhead & profit በጥንቃቄ ማየት ያስፈልጋል። 🌶20% በላይ በታች → እጅግ ዝቅተኛ ዋጋ ነው፤ በተለይ ከሌሎች ተጫራቾችም በጣም ከተለየ እንደ Abnormally Low Bid ሊመረመር ይችላል። 🌶10%–20% በላይ → ዋጋው ከEE ከፍ ያለ ነው፤ የጨረታው ህግ/የግዥ ሰነዱ ካልከለከለ በስተቀር በራሱ ምክንያት ብቻ ውድቅ አይሆንም። 👉 በጣም ጠቃሚው ነጥብ ✤ጨረታ ለመሙላት “ከEngineer’s Estimate 10% በታች እንድሆን አደርጋለሁ” ብሎ መወሰን ብቻ ትክክለኛ አይደለም። 👉 የሚመረጠው ዋጋ ከሚከተሉት መሠረት መውጣት አለበት፦ ✤Bid Price = Direct Cost + Indirect Cost + Risk + Overhead + Profit ለምሳሌ፣ Engineer’s Estimate = 100,000,000 ብር ከሆነ፦ 95M → 5% በታች 90M → 10% በታች 80M → 20% በታች 110M → 10% በላይ ነገር ግን የተጫራቾች ዋጋ ከEE ጋር ማነፃፀር ብቻ አይበቃም፤ የሁሉም ተጫራቾች average bid እና የEE ግንኙነትም አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ እንግዲህ Engineer’s Estimate (EE) = 100,000,000 ብር እንበል። የራስህን የጨረታ ዋጋ እንዴት እንደምታወጣ ደረጃ በደረጃ እንይ። 1. በመጀመሪያ Direct Cost አስላ ለምሳሌ፦ Material = 55,000,000 Labour = 12,000,000 Equipment = 8,000,000 ስለዚህ፦ Direct Cost = 55M + 12M + 8M = 75,000,000 ብር 2. Indirect Cost / Site Overhead ጨምር ለምሳሌ፦ ✤Site office ✤Site engineer/staff ✤Camp ✤Electricity & water ✤Transportation ✤Communication ✤Insurance ✤Safety ✤Temporary works እነዚህ በአጠቃላይ 5% ብንወስድ፦ 75M × 5% = 3.75M ስለዚህ፦ Cost = 75M + 3.75M = 78.75M 3. Risk/Contingency አስብ የግንባታ ፕሮጀክት ላይ የmaterial price fluctuation፣ productivity፣ transportation፣ unforeseen site condition ወዘተ ሊኖሩ ይችላሉ። ለምሳሌ 3% እንውሰድ፦ 78.75M × 3% = 2.3625M እንግዲህ፦ 78.75M + 2.3625M = 81.1125M 4. Profit ጨምር ለምሳሌ የምትፈልገው profit 8% ከሆነ፦ 81.1125M × 8% = 6.489M ስለዚህ የመጨረሻ Bid Price፦ 81.1125M + 6.489M = 87.6015M ማለትም በግምት፦ Bid Price = 87.60 Million Birr 5. ከEngineer’s Estimate ጋር አነፃፅር EE = 100M Bid = 87.60M የሚሆነው፦ ስለዚህ የአንተ Bid Price ከEngineer’s Estimate 12.4% በታች ነው። #ይቀጥላል ......

⚡️R.C. መሠረታዊ ግንዛቤ 1. Reinforced Concrete ምንድነው? Reinforced Concrete (R.C.) ማለት Concrete እና Steel Reinforcement በአንድነት የሚሰሩ የመዋቅር አባላት ናቸው። Concrete በተለይ Compression ለመቋቋም ጥሩ ነው። Steel ደግሞ Tension ለመቋቋም ጥሩ ነው። ስለዚህ፦ Concrete + Steel = Reinforced Concrete 2. Concrete እና Steel ለምን አብረው ይሰራሉ? አንድ Beam እንደምሳሌ እንውሰድ። ጭነት ሲጫንበት Beam ወደታች ይታጠፋል። በአጠቃላይ፦ የላይኛው ክፍል → Compression የታችኛው ክፍል → Tension ስለዚህ በBeam የታችኛው ክፍል Steel Reinforcement በመጨመር Tension እንቋቋማለን። 3. ዋና የR.C. Structural Members በአንድ ህንፃ ውስጥ ዋናዎቹ፦ 1. Slab የFloor እና Roof ጭነት የሚሸከም አባል። 2. Beam የSlab እና ሌሎች ጭነቶችን ተቀብሎ ወደ Column የሚያስተላልፍ። 3. Column የBeam እና Slab ጭነትን ወደ Foundation የሚያስተላልፍ። 4. Footing የColumn ጭነትን ወደ Soil የሚያስተላልፍ። 5. Shear Wall በተለይ የLateral Load እንደ Wind እና Earthquake ኃይል ለመቋቋም የሚያገለግል።

በብሎኬት ግንባታ ወቅት የቱምቢ (Plumb Bob) ትክክለኛ አጠቃቀም እና የሳይት ቁጥጥር! 🧐🏗️ ​በምስሉ ላይ እንደምናየው የብሎኬት ግንባታው በትክክል ወደ ላይ ቀጥተኛ (Plumb / Vertic
በብሎኬት ግንባታ ወቅት የቱምቢ (Plumb Bob) ትክክለኛ አጠቃቀም እና የሳይት ቁጥጥር! 🧐🏗️ ​በምስሉ ላይ እንደምናየው የብሎኬት ግንባታው በትክክል ወደ ላይ ቀጥተኛ (Plumb / Vertical) መሆኑን ለማረጋገጥ የቱምቢ(Plumb Bob) ልኬት እየተወሰደ ይገኛል። ​በቱቢ ልኬት ወቅት ትኩረት የሚሹ ቁልፍ ነጥቦች፦ 1.​ The Gap Requirement: በቱምቢው የታችኛው ነጥብ (Bob) እና በብሎኬቱ መካከል ትንሽ ክፍተት (ከ 1mm እስከ 2mm) መኖር አለበት — ቱምቢው ከብሎኬቱ ጋር ሙሉ በሙሉ ከተነካካ ልኬቱ ትክክል አይደለም። 2. ​Checking Top Block vs. Base: የቱምቢው የእንጨት/የላይኛው መደገፊያ ብሎኬቱ ላይ ሲያዝ፣ የታችኛው ተንጠልጣይ ነጥብ ከመሰረቱ (Base Course) ጋር የነበረውን አሰላለፍ መፈተሽ አለበት። 3. ​Regular Check: የቱምቢ ቁጥጥር ግንባታው አልቆ ሳይሆን በየተደረደረው የብሎኬት መስመር (In every course) መከናወን አለበት። ​በእርስዎ ሳይት ላይ ለብሎኬት አሰላለፍ Spirit Level ወይስ Plumb Bob (ቱምቢ) ይመርጣሉ? ሃሳብዎን በኮሜንት ያካፍሉን!👇 ​

DEFLECTION ምንድነው? 👉አንድ Beam ላይ Load ሲጫን Beam ቀድሞ ከነበረበት ቀጥተኛ ቅርጽ ይወጣና ይጎበጣል። ይህ የBeam ከOriginal Position የሚያደርገው የVertical Displacement Deflection ይባላል። Before Loading A ───────────────────── B After Loading A ────────╲____╱──────── B ↓ Deflection በተለምዶ δ ወይም y እንጠቀማለን። Units mm m በBuilding Design ብዙ ጊዜ mm ይጠቀማል።

የኮንክሪት የውሃ ማፍሰሻ ቦይ (Concrete Roof Gutter) ውሃ እንዳያስተላልፍ የሚደረጉ ዋና ዋና ጥንቃቄዎች! 🧐🌧️ ​በምስሉ ላይ እንደምናየው በቆርቆሮው እና በፓራፔት ግንቡ መካከል የኮ
የኮንክሪት የውሃ ማፍሰሻ ቦይ (Concrete Roof Gutter) ውሃ እንዳያስተላልፍ የሚደረጉ ዋና ዋና ጥንቃቄዎች! 🧐🌧️ ​በምስሉ ላይ እንደምናየው በቆርቆሮው እና በፓራፔት ግንቡ መካከል የኮንክሪት ቦይ (Concrete Gutter) ተሰርቷል። ይህ ቦታ በህንፃዎች ላይ ከፍተኛ የውሃ ሰርጎ የመግባት (Water Leakage) አደጋ ከሚፈጠርባቸው ቦታዎች አንዱ ነው። ​በኮንክሪት ጋተር ስራ ወቅት ሊረሱ የማይገባቸው ነጥቦች፦ 1. ​Proper Slope/Fall: ኮንክሪቱ ውሃ እንዳያቁር ቢያንስ 1% እስከ 2% ተዳፋትነት (Slope towards downspout) ሊኖረው ይገባል። 2. ​Waterproofing Membrane: በኮንክሪት ቦዩ ላይ ጥራት ያለው የውሃ መከላከያ (App Waterproofing Membrane / Elastomeric Coating) መቀባት/መንጠፍ። 3. ​Flashing & Overlap: በቆርቆሮው እና በጋተሩ መካከል ያለው መጋጠሚያ ላይ ብረታዊ ፍላሽንግ (Metal Flashing) ገብቶ በቂ Overlap መኖሩን ማረጋገጥ። ​በእርስዎ ሳይት ላይ ለኮንክሪት ጋተር ውሃ መከላከያ Crystalline Coating ይመርጣሉ ወይስ Bituminous Membrane?

በራፍት ፋውንዴሽን (Raft Foundation) ብረት ዝርጋታ ላይ ትኩረት የሚሹ ዋና ዋና ነጥቦች! 🧐🏗️ ​በምስሉ ላይ እንደሚታየው ወፍራም የታችኛ እና የላይኛ የብረት ንብርብሮች (Top & Bo
በራፍት ፋውንዴሽን (Raft Foundation) ብረት ዝርጋታ ላይ ትኩረት የሚሹ ዋና ዋና ነጥቦች! 🧐🏗️በምስሉ ላይ እንደሚታየው ወፍራም የታችኛ እና የላይኛ የብረት ንብርብሮች (Top & Bottom Rebar Mesh) በከፍተኛ ጥንቃቄ ተዘርግተው በማሰሪያ ሽቦ (Binding wire) ተጣብቀዋል። ​በራፍት መሰረት ስራ ወቅት በሳይት ቁጥጥር ወቅት ሊረሱ የማይገባቸው ነጥቦች፦ 1. ​Chair Supports (የብረት ወንበሮች): በTop እና Bottom Mesh መካከል ያለውን ክፍተት በትክክል ለመጠበቅ በቂ የብረት ወንበሮች (Chairs) መጠቀም። 2. ​Concrete Covers (ስፔሰሮች): የከባድ መሰረት ስለሆነ ከታች እና ከጎን በቂ የኮንክሪት ከቨር (50mm - 75mm) መስጠት። 3. ​Rebar Spacing & Lapping: በብረቶች መካከል ያለው ክፍተት ለትልቅ ጠጠር/ኮንክሪት ማልፈያ በቂ መሆኑን እና የላፕ (Lapping) ቦታዎችን ማረጋገጥ።

⚡️Cube Test (Compressive Strength Test) 1. Cube Test ምንድን ነው? ✅Cube Test ማለት የተጠናከረ ኮንክሪት የግፊት ጥንካሬ (Compressive Strength) ለመለካት የሚደረግ የላብራቶሪ ሙከራ ነው። 👉 Slump Test የሥራ ቀላልነትን ይለካል፤ 👉Cube Test ደግሞ የኮንክሪቱን ጥንካሬ ይለካል።

#Rate #Analysis ምንድን ነው?Rate Analysis ማለት የአንድ የግንባታ ሥራ (1 m³ Concrete፣ 1 m² Plastering፣ 1 m³ Masonry...) አንድ ዩኒት ለመስራት የሚያስፈልገውን ቁሳቁስ፣ የሰራተኛ፣ የማሽን እና ሌሎች ወጪዎች በዝርዝር ማስላት ነው። #Rate Analysis የሚመልሰው ጥያቄ፦ "1 m³ Concrete ለመስራት ስንት ብር ያስፈልጋል?"

Project Management Triangle የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት በ3 ዋና ነገሮች ላይ ይመሰረታል፦ ✅Time (ጊዜ) ✅Cost (ወጪ) ✅Quality / Scope (ጥራት / የሥራ መጠን) 🙏ከእነዚህ አንዱ ከተቀየረ ሌሎቹም ይጎዳሉ። ለምሳሌ፦ ✅ጊዜን ብታሳጥር ወጪ ሊጨምር ይችላል። ✅ወጪን ብትቀንስ ጥራት ሊቀንስ ይችላል።

🙏Stress ዓይነቶች 1. Tensile Stress (የመዘርጋት ውጥረት) ✅ቁሱ ሲጎተት የሚፈጠር ውጥረት ነው። ምሳሌ፦ ✅የSteel Reinforcement ✅Steel Tie Rod 2. Compressive Stress (የመጨመቅ ውጥረት) ✅ቁሱ ሲጨመቅ የሚፈጠር ውጥረት ነው። ምሳሌ፦ ✅Column ✅Concrete Block ✅ኮንክሪት በCompression ውስጥ በጣም ጠንካራ ነው። 3. Shear Stress (የመንሸራተት ውጥረት) በሁለት ተቃራኒ ኃይሎች ምክንያት ቁሱ ሊንሸራተት ሲሞክር የሚፈጠር ውጥረት ነው። ምሳሌ፦ ✅Beam በSupport አቅራቢያ ✅✅Bolts Rivets

Flexible Pavement Layers (1) Wearing Course 👉ይህ ተሽከርካሪዎች በቀጥታ የሚጓዙበት ንብርብር ነው። ስራው 👉መንሸራተትን መቀነስ 👉ውሃን መከላከል 👉ለስላሳ የመንገድ ገጽ መስጠት (2) Binder Course 👉Wearing Courseን ይደግፋል 👉የትራፊክ ጭነትን ወደ Base Course ያስተላልፋል (3) Base Course 👉የመንገዱ ዋና ጭነት ተሸካሚ ንብርብር 👉ከተመረጠ ድንጋይ (Crushed Aggregate) ይሠራል (4) Sub-base 👉Base Courseን ይደግፋል 👉ውሃን ያስወግዳል (Drainage) 👉የጭነት ስርጭትን ያሻሽላል (5) Subgrade 👉Subgrade የመንገዱ የተፈጥሮ አፈር ወይም የተጠናከረ አፈር ነው። 👉የSubgrade ጥራት የመንገዱን ዕድሜ በጣም ይወስናል።

⚡️የጨረታ መክፈቻ ቃለ-ጉባኤ (Minutes of Bid Opening) ለተጫራቾች መላክ እንዳለበት ያውቃሉ? - የመንግሥት የግዥ መመሪያዎችም ሆኑ የዓለም አቀፍ አበዳሪዎች (እንደ የዓለም ባንክ ያሉ) ሕጎች የጨረታ መክፈቻ ቃለ-ጉባኤ (Minutes) ወዲያውኑ ለተጫራቾች መላክ እንዳለበት በግልፅ ያስገድዳሉ። ይሁን እንጂ በተግባር ግን ይህ ሲደረግ ብዙም አይታይም። -  በመክፈቻው ላይ የተነበቡ ዋጋዎች፣ ቅናሾች እና የሲፒኦ ዝርዝሮች ተጫራቾች እንዲያውቁት በማድረግ ተጫራቾች የግዥ ሂደቱ ፍትሃዊ እና በሕግ መሠረት እየተመራ መሆኑን እንዲያምኑ ያደርጋል፤ ይህም ለወደፊቱ ተቋሙ የተሻሉና ተወዳዳሪ ዋጋዎችን እንዲያገኝ ይረዳል። - ግዥውን የሚፈፅመው ተቋም ይህን ካላደረገ ተጫራቾች የጨረታ መክፈቻ ቃለ-ጉባኤ (Minutes of Bid Opening) እንዲላክላቸው መጠየቅ ይችላሉ

⚡️በTender Evaluation የሚመረመሩ ነገሮች ✅የኮንትራክተሩ ልምድ ✅የፋይናንስ አቅም ✅የቴክኒክ ብቃት ✅የመሳሪያ አቅም ✅የባለሙያ ቡድን ✅የሥራ ፕሮግራም ✅የቀረበው ዋጋ

Setting Out (ማስቀመጫ መስመሮች) ይህ በSurvey Engineer የሚሰራ ሥራ ነው። የሚደረጉ ሥራዎችBenchmark ማረጋገጥ ✅Grid Line ማስቀመጥ ✅Building Corners ማስቀመጥ ✅Foundation Center Line ማስቀመጥ መሣሪያዎች ✅Total Station ✅Level Machine ✅GPS (እንደ ፕሮጀክቱ አይነት) 🙏🙏 በSetting Out የሚፈጠር ስህተት በሙሉ ፕሮጀክቱ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል፤ ስለዚህ በConsultant መረጋገጥ አለበት።

Shrinkage እና Swellበተፈጥሮ አፈር ላይ እነዚህ ለውጦች ይከሰታሉ። 1.Swell 👉አፈር ሲቆፈር መጠኑ ይጨምራል። ምሳሌ 100 m³ የነበረ አፈር ከተቆፈረ በኋላ 120 m³ ሊሆን ይችላል። 2.Shrinkage 👉አፈሩ ተመልሶ ሲጠናከር መጠኑ ይቀንሳል።

🙏Method Statement ምንድን ነው? ⚡️Method Statement (MS) ማለት አንድ ሥራ እንዴት፣ በምን መሣሪያ፣ በማን፣ በምን የጥራት እና የደህንነት ሂደት እንደሚሰራ የሚገልጽ የጽሑፍ ሰነድ ነው። ዓላማው ✅ሥራው በአንድ ወጥ ዘዴ እንዲሰራ ✅ጥራት (Quality) እንዲጠበቅ ✅ደህንነት (Safety) እንዲረጋገጥ ✅የውል መስፈርቶች እንዲከበሩ