fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

የኔ' ማስታወሻ ..🧚

የኔ' ማስታወሻ ..🧚

رفتن به کانال در Telegram

በዚህ ቻናል የማይዳሰስ ጉዳይ የለም የተለያዩ አስገራሚ ታሪኮችን፣ ግጥሞችን፣ መጣጥፎችን፣ ወጎችን እንዲሁም በጥበባዊ እይታ የተቃኙ ሁሉ አይነት ጉዳዮችን እናይበታለን ሼር በማድረግ ቤተሰብ እናብዛ... እወዳችኋለሁ❤️ for any comment :- 👉 @Hamy_Hamy Subscribe 👇👇👇 https://www.youtube.com/@Yenemastawosha

نمایش بیشتر
2 071
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+137 روز
+1630 روز
آرشیو پست ها
‎ ያለፈውን ወይም የወደፊቱን ህይወቴን አልኖርም ። አሁን ብቻ ነው የሚያስደስተኝ ። ☺️☺️ ምንጊዜም በአሁን ላይ ማተኮር ከቻልክ ደስተኛ ሰው ትሆናለህ😉 @poethaymi ‎
‎
ያለፈውን ወይም የወደፊቱን ህይወቴን አልኖርም ። አሁን ብቻ ነው የሚያስደስተኝ ። ☺️☺️ ምንጊዜም በአሁን ላይ ማተኮር ከቻልክ ደስተኛ ሰው ትሆናለህ😉
@poethaymi ‎

በሰዎች ዘንድ መወደድ ጥሩ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን መከበርና መፈራት የበለጠ ዋስትና ይሰጥሃል። ሰዎች የሚወዱትን ሰው እንደ ሁኔታው በቀላሉ ሊከዱት ወይም ሊረሱት ይችላሉ፤ የሚያከብሩትንና የሚያስፈራቸውን ሰው ግን ለመካድ ሁለት ጊዜ ያስባሉ። ስለዚህ በደግነትህና በየዋህነትህ ብቻ ሰዎች እንዲጫወቱብህ አትፍቀድ፤ የራሳቸው ወሰን እንዳላቸው አሳያቸው።
📕ርዕስ፦ልዑሉ ✍️ደራሲ፦ ኒኮሎ ማኪያቬሊ @poethaymi

👉 “አንድ ሰው በእውነት እየተለወጠ መሆኑን ማወቅ ከፈለግክ… እነዚህን 3 ምልክቶች ተመልከት!” 1. #ለሁሉም_ነገር_ሰበብ_መፈለግ_ያቆማል። “እሱ ነው ያደረገው”፣ “እድሉ አልነበረኝም” ከማለት ይልቅ፣ “እኔ ምን ማድረግ እችላለሁ?” ብሎ መጠየቅ ይጀምራል። 2. #ሁሉንም_ሰው_ማስደሰት_ያቆማል። በፊት ሰዎች ምን ይላሉ ብሎ ይጨነቅ ነበር። አሁን ግን የሚያውቀውን ትክክል ለማድረግ ይሞክራል። ምክንያቱም ሁሉንም ሰው ማስደሰት የማይቻል ሥራ መሆኑን ተረድቷል። 3. #ውጤት_ላይ_ያተኩራል_ማሳየት_ላይ_አይደለም። በፊት “እኔ እየሠራሁ ነው” ይል ነበር። አሁን ግን ብዙ አይናገርም ሥራው ይናገራል። @poethaymi

አንቺ እስክታነሽው ባ'ራቱም አቅጣጫ ራሱን የሚጥል:- ደመራ ነው ልቤ በናፍቆትሽ ችቦ ነድዶ የሚቃጠል። ✍️ Solomon_sahle @poethaymi
አንቺ እስክታነሽው ባ'ራቱም አቅጣጫ ራሱን የሚጥል:- ደመራ ነው ልቤ በናፍቆትሽ ችቦ ነድዶ የሚቃጠል።
✍️ Solomon_sahle
@poethaymi

እግዚአብሔር ይመስገን ።

. ኢትዮጵያ የመንግስት ወሬ ነሽ፣ ያለብሽ ሺ ብድር መቅረፍ የማትችይ፣ የህዝብ አንድ ችግር ፈሪ ሲውልብሽ፣ ማያድርብሽ ደፋር የሌቦች ጉያ ነው፣ የድንበርሽም ዳር . ወደ ፊት ወደ ፊት፣ ምን ቢሉሽ ናት ከፊት ለኔ ካልደረሰ፣ ሚደርስልሽ ትንቢት ይኖራል ያሉትን፣ ካላየሁት ኑሬ ካለፈብኝ ኋላ፣ ቢያልፍልሽ ሀገሬ እንዳትቀየሚኝ፣ እቀየምሻለሁ ትንሳኤ ሲኖርሽ፣ ትንሳኤ እንዲኖረኝ፣ ሁሌ እናፍቃለሁ። 💚💛❤️ @poethaymi

ሰዎች ስለ እኔ ምን ይላሉ ? የሚል ሃሳብ ማቆም አለብህ፤ ሁሉም ነገር መሆን ያለበት አንተ ስለ ራስህ በምታስበው ነገር ላይ ነው።😊 @Poethaymi
ሰዎች ስለ እኔ ምን ይላሉ ? የሚል ሃሳብ ማቆም አለብህ፤ ሁሉም ነገር መሆን ያለበት አንተ ስለ ራስህ በምታስበው ነገር ላይ ነው።😊 @Poethaymi

ፀሎት ማድረግ የምችል አይመስለኝም። ሁልጊዜ ለፀሎት ስቆምም ሆነ ስንበረከክ የምለው ይጠፋብኛል። ምስጋና ሳበዛ የጎደለኝ ትዝ ይለኛል።ጥያቄ ሳበዛ የተደረገልኝ በአይነ ሕሊናየ ይመጣና ውለታ ቢስ የሆን
ፀሎት ማድረግ የምችል አይመስለኝም። ሁልጊዜ ለፀሎት ስቆምም ሆነ ስንበረከክ የምለው ይጠፋብኛል። ምስጋና ሳበዛ የጎደለኝ ትዝ ይለኛል።ጥያቄ ሳበዛ የተደረገልኝ በአይነ ሕሊናየ ይመጣና ውለታ ቢስ የሆንኩ ይመስለኛል።ወዲያው ደግሞ ግሳንግስ ሐጥያቴ ትዝ ይለኝ እና የማመስገንም የመጠየቅም ሀሳቤ ይጠፋ እና ሀፋረቴ ይመጣል። ለማመጣጠን ስሞክር ደግሞ ፀሎቱን ትቼ ስራ የያዝኩ ይመስለኛል። በቃል ያጠናሁትን የተለመደ ፀሎት ባደርግ ይሻላል ብየ ስጀምር ራሴን መጨረሻው ላይ አገኘዋለሁ።በንባብም ቢሆን ያው ነው። አንዳንዴ ለራሴሠው እንዴት ከፈጣሪው ጋር መነጋገር ያቅተዋል???ከስንቱ የሰው አይነት ጋር እየተግባባሁ እንዴት ከአምላኬ ጋር መግባባት ያቅተኛል??? እያልኩ በራሴ አዝናለሁ!!!     ርዕስ:- ሚተራሊዮን ደራሲ:- ዶክተር አለማየሁ ዋሴ እሸቴ @poethaymi

( ሞክሼ ... )
======== ያ ሁሉ እግዚኦ ያ ሁሉ ቢስሚላ ያ ሁሉ ጾም ጸሎት ያ ሁሉ ምህላ ... የት ነው የሚሄደው ስሚኝ እስቲ ሀገሬ ሞክሼ አለሽ ወይ ሌላ ?? Kiyorna @poethaymi @poethaymi

አንድ ጠበቃ የውሃ ጉድጓዱን ለአንድ መምህር ሸጠለት። ከሁለት ቀን በኋላ ጠበቃው ወደ መምህሩ መጥቶ፦ "ጌታዬ! ውላችን እንደሚገልፀው የውሃ ጉድጓዱን ሸጥኩልህ እንጂ በውስጡ ያለውን ውሃ አልሸጥኩልህም
አንድ ጠበቃ የውሃ ጉድጓዱን ለአንድ መምህር ሸጠለት። ከሁለት ቀን በኋላ ጠበቃው ወደ መምህሩ መጥቶ፦ "ጌታዬ! ውላችን እንደሚገልፀው የውሃ ጉድጓዱን ሸጥኩልህ እንጂ በውስጡ ያለውን ውሃ አልሸጥኩልህም! ውሃውን መጠቀም ከፈለግክ ተጨማሪ መክፈል አለብህ!" አለው። መምህሩም ፈገግ አለና እንዲህ ሲል መለሰለት፦ "አዎ፣ እኔም ወደ አንተ ልመጣ ነበር። ልልህ የነበረውም ውሃህን ከእኔ ጉድጓድ ውስጥ እንድታወጣልኝ ነው፣ አለበለዚያ ከነገ ጀምሮ በግድጓዴ ውስጥ ለሚኖረው ውሃህ ኪራይ መክፈል ይኖርብሃል" አለው። ጠበቃው ይህን ሲሰማ ደንግጦ፦ "ኦ! እኔ እኮ እየቀለድኩ ነበር!" አለዉ። መምህሩም እየሳቀ "እንደ አንተ ያሉ ሰዎች ጠበቃ የሚሆኑት እኮ ከእኛ ዘንድ ተምረው ነው!" አለው ይባላል። ©ተዋናይ @poethaymi

ከቀጠርሽኝ ቦታ ከቀጠሮው ሰዓት ቀድሜ መጥቼ ቆሜ ብጠብቅም አጥተሽኝ እንደሄድሽ አልጠራጠርም .... ✍️ Abreham aschalew @poethaymi
ከቀጠርሽኝ ቦታ ከቀጠሮው ሰዓት ቀድሜ መጥቼ ቆሜ ብጠብቅም አጥተሽኝ እንደሄድሽ አልጠራጠርም ....
✍️ Abreham aschalew
@poethaymi

እስኪ ንገሪኝ የኔ ቀረርቶ ፥ የኔማ ዛቻ መቁረጥ አያውቅም ፥ መገዝገዝ ብቻ፡፡ የኔም ስንብት ፥ የመለየቴ ጫፍ ቢቆይ እስከ ምሽት ፥ ቢርቅ እስከ ደጃፍ! "ቻው" ስልሽ ሰምቶ ከጭፍሮቹ ጋር ፥ መንገዴ
እስኪ ንገሪኝ የኔ ቀረርቶ ፥ የኔማ ዛቻ መቁረጥ አያውቅም ፥ መገዝገዝ ብቻ፡፡ የኔም ስንብት ፥ የመለየቴ ጫፍ ቢቆይ እስከ ምሽት ፥ ቢርቅ እስከ ደጃፍ! "ቻው" ስልሽ ሰምቶ ከጭፍሮቹ ጋር ፥ መንገዴን ዘግቶ ናፍቆትሽ በሌት ፥ ይጠብቀኛል ፥ "አይኗስ?" ፥ ይለኛል "ሳቋስ?" ፥ ይለኛል "ጥርሷስ?" ፥ ይለኛል የማልችለውን ይጠይቀኛል፡፡ እስኪ ንገሪኝ … ስንቴ 'ቻው' ብልሽ ፥ ይቆርጥልኛል? ✍Habtamu Hadera @poethaymi

እምነት በመሀላ አይረጋገጥም😉 @poethaymi

ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ መተው ባለመቻላቸው ምክንያት ምንም ጥቅም የሌላቸውን አሉታዊ ስሜቶች በመያዝ ጊዜያቸውን ያባክናሉ። #Master_Your_Emotions @poethaymi
ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ መተው ባለመቻላቸው ምክንያት ምንም ጥቅም የሌላቸውን አሉታዊ ስሜቶች በመያዝ ጊዜያቸውን ያባክናሉ። #Master_Your_Emotions @poethaymi

ጅል ሰው ትኩሳት ነው ..🙅
@poethaymu

አንዴ ብቻ ...m4a8.46 KB

አንዴ ብቻ ይድላኝ ፣ አንዴ ብቻ ልረፍ፣ አንዴ ብቻ ልኑር ፣ አንዴ ብቻ ልትረፍ ፣ ፋታ ብቻ ላግኝ እንደምፈልገዉ፣ እንዴት እንደማለቅስ እኔ ነኝ የማቀዉ ። ሀብታሙ ሀደራ ✍️ @poethaymi @po
አንዴ ብቻ ይድላኝ ፣ አንዴ ብቻ ልረፍ፣ አንዴ ብቻ ልኑር ፣ አንዴ ብቻ ልትረፍ ፣ ፋታ ብቻ ላግኝ እንደምፈልገዉ፣ እንዴት እንደማለቅስ እኔ ነኝ የማቀዉ ። ሀብታሙ ሀደራ ✍️ @poethaymi @poethaymi

#መሳቅ_ግን_እንዴት_ነው? በጊዜ ቅብብል መሆን አለመሆን በሚታገሉበት መምሰል ከመሆን ጋር በሚወዳጅበት በዚህ በክረምቱ፦ በዝናብ ጠብታ አካሌ እየራሰ ልቤ እየተናጠ ይህን አስባለሁ... በታጠፈ አንጀቴ
#መሳቅ_ግን_እንዴት_ነው? በጊዜ ቅብብል መሆን አለመሆን በሚታገሉበት መምሰል ከመሆን ጋር በሚወዳጅበት በዚህ በክረምቱ፦ በዝናብ ጠብታ አካሌ እየራሰ ልቤ እየተናጠ ይህን አስባለሁ... በታጠፈ አንጀቴ ብርድ በጀቦነው ልክ እንደጐርፍ እድሜ ታይቶ በሚጠፋው በዚ አቅም ሰባሪ በበረዶ ዘመን ማመን ተሸርሽሮ ቃል የትም ተጥሎ ሲመሽ እየነጋ ሲነጋ ቢመሽም ሳቅ ከተባለ የማያልፉት የለም... #መሳቅ_ግን_እንዴት_ነው? እንባ ከአይን ዘልቆ... ልብ ከሀሴት ርቆ ዝም ብሎ ብቻውን ተጉዞ.... ተጉዞ.. ያሰቡት ሲጐድል ስህተት ልክ ሲሆን ትክክል ሲሳሳት ጐደሎ ተሟጦ የሞላ ሲጐድል... ሁሉም መሆን ትቶ መምሰልን ሲመስል.. በዳይ እየሳቀ ተበዳይ ሲያነባ.... #መሳቅ_ግን_እንዴት_ነው? በተወዛገበ በጭንቅንቅ ስሜት የማይቻል ችሎ ከራስ ጋር መታገል.. ፈገግ ለማለት ልብ ውስጥ ሀዘን መቅበር.... በዝምታ ብሩሽ በፀጥታ ቀለም በራስ ልክ ሰው መሳል ሁልጊዜ መኮለም.....? #መሳቅ_ግን_እንዴት_ነው? ተፃፈ ፦ በሀይሚ ሀምሌ 19/2012..ሲዘንብ የተፃፈ @poethaymi @poethaymi @poethaymi

. . . በእርግማኖች መሐል " የአባቴ አምላክ ካለ ..." ሲሉ ሰማሁ ልበል? ታድያ ምነው ... " ካለ " ብለውታል መኖሩን ማወቅ ነው .. ፀሎቱ ይቀድማል? 🤔🤔🤔🤔🤔 👇👇👇 @poethaymi @poethaymi @poethaymi