fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید 👈

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
መዲናችን አዲስ አበባ በጽዳቷ ባሳየችው እምርታዊ ለውጥ በጃፓን እየተካሄደ ባለው የጽዱ ከተሞች ኢኒሼቲቭ አድናቆት ተቸሯት! በጃፓን አለምአቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) አዘጋጅነት በጃፓኗ ከተማ ዮካሃማ እየተካሄደ ባለው የጽዱ ከተሞች ኢኒሼቲቭ አዲስ አበባን ወክለው እየተሳተፉ ያሉት በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የተመረጡ የአፍሪካ ከተሞች እየተሳተፉበት ባለው አለምዓቀፋዊ መድረክ ከተማችን በጽዳት መስክ ባከናወነችው ጠንካራ ስራ የተመዘገበው ስኬት በተሰጠው እውቅና የተሰማቸውን ደስታና ኩራት ገልፀዋል። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አክለውም በዚሁ አለምዓቀፋዊ መድረክ አዲስ አበባ አሁን በደረሰችበት የዘመናዊነትና የእድገት ደረጃ በቆሻሻ አወጋገድ እና አስተዳደር ላይ ተግባራዊ እያደረገች ያለችውን እቅድና ፖሊሲ መዲናዋን በላቀ ደረጃ ጽዱ፣ አረንጓዴ እና ለኑሮ ምቹ ለማድረግ የተቀየሰውን ጠንካራ ስትራቴጂ የሚያመላክት ሰነድ ለተሳታፊዎች ማቅረባቸውን ገልፀዋል። ሰነዱን ካቀረቡም በሁዋላ ከአፍሪካ ከተሞች ሉሳካ፣ ናይሮቢ፣ቱኒዝ፣ አልጀርስ ፣ካርቱም፣ ጁባ፣አቢጃን እና ሌሎችም የመድረኩ ተሳታፊዎች አዲስ አበባ ከተማ በጽዳቱ መስክ ያስመዘገበችው እምርታዊ ለውጥ በእጅጉ የሚደነቅ እንደሆነ በአጽንኦት ተናግረዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎች በተለይም መዲናችን አዲስ አበባ በተቀናጀ የቆሻሻ አስተዳደር ፖሊሲ በተለይም የአየር ንብረት ለውጥ ሚዛንን በሚጠብቅ መልኩ የተቀናጀ መሆኑ፣ ኡደታዊ ምጣኔ ሃብትን ለመተግበር ያለ ጠንካራ ቁርጠኝነት፣ የፕላስቲክ ውጤቶች ጋር ተያይዞ የሚመረቱ የቆሻሻ ምርት ለመቀነስ እየተደረገ ያለውን ጥረትም አድንቀዋል። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ባቀረቡት ሰነድ እ.ኤ.አ እስከ 2030 ደረቅ ቆሻሻን ወደ ኤሌክትሪክ ሃይል ምንጭነት በመቀየር እና በመልሶ መጠቀምና ኡደት ማድረግ ረገድ መዲናችን አዲስ አበባ ልትደረሰበት ያቀደችውን ከሚመነጨው ደረቅ ቆሻሻ 95 በመቶ ተደራሽነትን በማስፋት ለመሰብሰብ 70 በመቶ ደግሞ ወደ ማስወገጃ ስፍራ ( landfill) የሚሄደውን ቆሻሻ የሚቀንስ ስትራቴጂ በግልጽ በሚያሳይ ፍኖተ ካርታ በማስደገፍ አቅርበውላቸዋል። በከተማችን አዲስ አበባ የጃፓን አለምዓቀፍ የትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) ከሌሎች አጋሮች ጋር በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድና አስተዳደር ረገድ ተጨማሪ አቅም የሚሆኑ እርዳታና መሰል የቴክኒክ ድጋፎች እንደሚሰጡ እንደገለጹላቸው ኢንጅነር ወንድሙ አመልክተው ይህም አዲስ አበባ ዘመናዊ የቆሻሻ ቅብብሎሽ ጣቢያ እና የማስወገጃ ስፍራዎች እንዲሁም የዘመናዊ ከተማ የቆሻሻ አስተዳደር የሚያጎለብቱ የመልሶ መጠቀምና ኡደት ማድረግ ስራዎችን በማጠናከር፣ በሂደቱ ለዜጎች የስራ እድል መፍጠርን ጨምሮ የህብረተሰብ ተሳትፎን የሚያጎለብቱ ስራዎች እንደሚከናወንበትም አስገንዝበዋል። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በማጠቃለያቸውም ከተማችን አዲስ አበባ በጽዳቷ በአህጉርና በአለምዓቀፍ ደረጃ እያገኘችው ያለው እውቅና ለጽዱ ከተማና ለዘመናዊ የከተማ አስተዳደር መጎልበት ፈር ቀዳጅ እየሆነች መምጣቷን እንደሚያረጋግጥም አስገንዝበዋል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች በውጤታማነት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችሉ የአሰራር ስርአትን ለማጠናከር የሚያግዙ በበጀት አመቱ 6 ያህል ጥናቶችን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታወቀ። በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ ዋ/ ስራ አስኪያጅ እና የጥናትና ትግበራ ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደስ ይህን ያስታወቁት በዛሬው እለት የከተማችንን የጽዳት አጠባበቅ ስርአት ውጤታማነት በዘላቂነት ለማስጠበቅ ፋይዳ ያላቸው ሁለት የጥናት ውጤቶች ላይ ግብአት ለማሰባሰብ በተዘጋጀ የባለድርሻ አካላት መድረክ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ነው። ጽ/ቤቱ የከተማውን የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በበላይነት የመምራት፣ የማስተባበር፣ የመደገፍና የመከታተል ተልእኮውን በአግባቡ ለመወጣት በተጠሪ ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ ውጤታማነትን በጥናትና ምርምር ላይ ተመስርቶ በመፈተሽ የህብረተሰቡን እርካታ የሚያረጋግጡና የማስፈፀም አቅምን የሚያጎለብቱ ዉጤታማ አሰራሮችን ለመዘርጋት መፍትሄ አመላካች ጥናቶች ማካሄድ ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነ አስረድተዋል። በዛሬው እለት በስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የውስጥ አቅም ተጠንተው ግብአት ለማሰባሰብ የቀረቡ ጥናቶች "የደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀምና ኡደት ውጤታማነት" እና "በረጲ የሚገኙ መደበኛ ያልሆኑ የደረቅ ቆሻሻ ለቃሚዎች" ላይ የተካሄዱ ጥናቶች ናቸው። በዛሬው እለት የባለድርሻ አካላትን ግብአት ለማሰባሰብ በተጠራው መድረክ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክርቤት የመሠረተልማትና የማዘጋጃ ቤቴዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ ተቋማት ተወካዮች፣የክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጆች፣ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት በየደረጃው ያሉ አመራሮች፣ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች በውጤታማነት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችሉ የአሰራር ስርአትን ለማጠናከር የሚያግዙ በበጀት አመቱ 6 ያህል ጥናቶችን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታወቀ። በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ ዋ/ ስራ አስኪያጅ እና የጥናትና ትግበራ ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደስ ይህን ያስታወቁት በዛሬው እለት የከተማችንን የጽዳት አጠባበቅ ስርአት ውጤታማነት በዘላቂነት ለማስጠበቅ ፋይዳ ያላቸው ሁለት የጥናት ውጤቶች ላይ ግብአት ለማሰባሰብ በተዘጋጀ የባለድርሻ አካላት መድረክ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ነው። ጽ/ቤቱ የከተማውን የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በበላይነት የመምራት፣ የማስተባበር፣ የመደገፍና የመከታተል ተልእኮውን በአግባቡ ለመወጣት በተጠሪ ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ ውጤታማነትን በጥናትና ምርምር ላይ ተመስርቶ በመፈተሽ የህብረተሰቡን እርካታ የሚያረጋግጡና የማስፈፀም አቅምን የሚያጎለብቱ ዉጤታማ አሰራሮችን ለመዘርጋት መፍትሄ አመላካች ጥናቶች ማካሄድ ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነ አስረድተዋል። በዛሬው እለት በስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የውስጥ አቅም ተጠንተው ግብአት ለማሰባሰብ የቀረቡ ጥናቶች "የደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀምና ኡደት ውጤታማነት" እና "በረጲ የሚገኙ መደበኛ ያልሆኑ የደረቅ ቆሻሻ ለቃሚዎች" ላይ የተካሄዱ ጥናቶች ናቸው። በዛሬው እለት የባለድርሻ አካላትን ግብአት ለማሰባሰብ በተጠራው መድረክ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክርቤት የመሠረተልማትና የማዘጋጃ ቤቴዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ ተቋማት ተወካዮች፣የክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጆች፣ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት በየደረጃው ያሉ አመራሮች፣ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ዛሬ የነዋሪው ሉዓላዊነት መገለጫ ለሆነው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ2017 የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርታችንን አቅርበናል። ውድ የከተማችን ነዋሪዎች እናንተን በታማኝነት፣ በቅንነት እና በትህትና ለማገልገል ባደረግናቸው ጥረቶች የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተ መረጃ እንድታገኙ ሙሉ ሪፖርቱን እንድታደምጡ እጋብዛቹሃለሁ።

የምክር ቤቱ ጉባኤ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ በማሳለፍ ተጠናቋል:: የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤው የከተማ አስተዳደሩን የመጀመሪያ 6 ወራት እቅድ አፈጸጸም ሪፖርት ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩን የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ፣ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማትን እንደገና ለማቋቋም የተዘጋጀውን አዋጅ እና የምክር ቤቱን የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ሹመት በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ ተጠናቋል፡፡

በኮሪደር ልማት እና በመደበኛ ስራ ባለፈው ግማሽ ዓመት ከ210 ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ተፈጥሯል፡- አቶ ጥራቱ በየነ በግማሽ ዓመቱ በአንደኛው እና ሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ከ210 ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩን በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ እና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ ገልጸዋል፡፡ አቶ ጥራቱ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች የስራ ዕድል እንዲያገኙ በስፋት እና በንቅናቄ እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በዚህም ከተማ አስተዳደሩ ለስራ ዕድል ፈጠራ ልዩ ትኩረት በመስጠቱ ተቋም በማደራጀት' የሰው ኃይል እና በጀት በመመደብ በትኩረት እየሰራበት መሆኑን አመልክተዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ አመራርም ለዚህ ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነውም ብለዋል፡፡ ባለፉት 6 ወራት 142 ሺህ 908 ዜጎች ቋሚ የስራ ዕድል የተፈጠረላቸው መሆኑን ያወሱት አቶ ጥራቱ፣ ይህም የእቅዱ 95 በመቶ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በተለይም ለወጣቶች ልዩ ትኩረት በመስጠት ከአጠቃላዩ የስራ እድል 70 በመቶ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማድረግ ስራ እየተሰራም ነው ብለዋል፡፡ ቀደም ሲል የስራ አጥ ምዝገባ ይከናወን የነበረው በማኑዋል ነበር ያሉት ኃላፊው ይህም ትክክለኛ መረጃን ለመያዝ አስቸጋሪ በመሆኑ ከዚህ ዓመት ጀምሮ በሁሉም ወረዳዎች ስራ ፈላጊዎችን በሲስተም መመዝገብ መጀመሩን አውስተዋል፡፡ የስራ አጥ ምዝገባው በአሻራ ጭምር እየተከናወነ ነውም ብለዋል፡፡ ይህም ግልጸኝነትን እና ፍትሀዊነትን የሚያረጋግጥ መሆኑን አውስተዋል፡፡ ከዚህም ሌላ በየአንዳንዱ ብሎክ ስራ ፈላጊዎችን በመለየት የመመዝገብ ስርዓት ተዘርግቶ እየተሰራበት መሆኑን አመልክተዋል፡፡ ከዩንቨርሲቲ ተመርቀው የሚወጡ ተመራቂዎች የስራ ዕድል እንዲያገኙ በማድረግ ረገድ 20 ሺህ 299 ተመራቂዎች ከአጠቃላይ የስራ እድል ፈጠራ 14 በመቶውን ተጠቃሚ መሆናቸውንም አመልክተዋል፡፡ 13 ሺህ 731 የሚሆኑ ወጣት ስራ ፈላጊዎች በግል ድርጅቶች የስራ ልምምድ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ያወሱት አቶ ጥራቱ ከእነዚህም ውስጥ 99 በመቶ የሚሆኑት ልምምድ ባደረጉባቸው ድርጅቶች የስራ እድል ማግኘታቸውን አመልክተዋል፡፡ የመንግስት የስራ እድል ፈጠራ ብቸኛው የስራ እድል አማራጭ መሆን የለበትም ያሉት አቶ ጥራቱ የግል ድርጅቶች እና ኩባንያዎችም ይህን ስራ ሊጋሩት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ የስራ ባህልን ከመቀየር አኳያ በተለይም የኮሪደር ልማት ስራው ይህን የቆየ የስራ ባህል እንደቀየረው ተናግረዋል፡፡ የኮሪደር ልማት ስራው የስራ መነሳሳትን፣ 24 ሰዓት መስራትን እና ስራ ሳያማርጡ የመስራት ባህልን የፈጠረ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ይህ የስራ ባህል ወደ ሁሉም ሴክተሮች እንዲሰፋ እና ይህም በጥናት እነዲደገፍ እየተደረገ መሆኑን ነው የጠቀሱት፡፡ ስራ ፈጣሪ ኢንተርፕራይዞችን መፍጠር ላይ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት አቶ ጥራቱ፣ ለዚህም ምቹ ሁኔታ እየተፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ለዚህም 160 ሚሊየን ብር ተመድቦ ስራ ፈጣሪ ኢንተርፕራይዞችን የመደገፍ ስራ እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ በዚህም ከ 600 ሺ እስከ 10 ሚሊየን ብር ካፒታል የፈጠሩ 165 ጥቃቅን እና አነስተኛ ወደ ኢንተርፕራይዝነት እንዲሸጋገሩ ዝግጅት መደረጉን አውስተዋል፡፡ ይሁን እና የስራ እድል ፈጠራው በቂ ባለመሆኑ በዚህ ረገድ ተጨማሪ ስራዎችን መስራት እንደሚገባ አቶ ጥራቱ አንስተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ በማስከበር ረገድ በየደረጃዉ ያለዉ የፀጥታ መዋቅር ህዝቡን የሰላም ባለቤት ከማድረግ ባሻገር በተናበበና በተቀናጀ አግባብ በቴክኖሎጂ የታገዘ ስራ በመስራት ዉጤት መመዝገቡን ገልፀዉ፣ በከተማዋ የደረቅ ወንጀል መከላከል ከዓምናዉ ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 33 በመቶ ቀንሷል ብለዋል፡: ፖለቲካዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁሉን አካታች መመዘኛዎችን መሰረት ያደረገ ፖሊሲና እስትራቴጂ በመንደፍ በከተማዋ የመልካም አስተዳደር አሰራር እንዲሰፍን በቅንጅት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል:: የበጀት አጠቃቀምን በተመለከተም ቀድሞ 70 በመቶ ለአስተዳደር 30 በመቶ ለእድገት ተኮር የነበረዉን በጥናት በመቀየር 30 በመቶ ለአስተዳደር 70 በመቶ ለእድገት ተኮር በማድረግ ለህዝባችን በገባነዉ ቃል መሰረት ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ጀምሮ በመጨረስ፤የግዥ ስርዓታችንን ግልፀ በማድረግ ፣የክትትል አግባብን በማጠናከር እና ያለ አግባብ የሰዉ ሃይል ቅጥርን በማስቀረት በዘላቂነት የከተማዋን እድገት ማስፈፀም ችለናል ሲሉ ከንቲባዋ ተናግረዋል፡፡ ከንቲባዋ አክለዉም በ2010 የከተማዋ በጀት 30 ቢሊዮን ብር ከነበርበት ዛሬ ላይ በ6 ወራት 111.5 ቢሊዮን መሰብሰብ የተቻለዉ የግብር ምህዳሩን በማስፋት፤የታክስና የኦዲት አሰራርን በማዘመን ገቢያችንን ማሳደግ ነው ብለዋል፡: በተጨማሪም በማናቸዉም ሁለተናዊ የከተማዋ ስራዎች ህገመንግስቱ ባስቀመጠዉ አሰራር ከተማ አስተዳደሩ ከበጀት ድጎማ ጀምሮ በሌሎችም በቅንጅት እየተሰራ በርካታ የልማት ስራዎች በጥራትና በታቀደዉ ጊዜ በማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡ ከኑሮ ውድነት አኳያ አያይዘው ሲገልፁ በአራቱም የገበያ በሮች ገበሬው እና ምርት አቅራቢው በቀጥታ ምርቱን ወደ ከተማ በማምጣት አምራችና ተጠቃሚውን ምርቱን በተገቢው ዋጋ የሚገበያይበት ሰርዓት መዘርጋቱን ፣ የእሁድ ገበያዎች ስታንዳርዳቸዉን በጠበቀ መልኩ መከፈታቸው ጉልህ ሚና እያደረጉ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በትምህርት ስልጠና መምህራንን ከማብቃት አኳያ በከተማ አሰተዳደሩ የአመራር አካዳሚ እየተገነባ የሚገኝ ሲሆን ይህም ለትምህርት ጥራት ከፍተኛ አሰተዋፅኦ ያበረክታል ሲሉ ከንቲባዋ አክለዋል፡፡ የገርቢ እና ጭቆላ የውሃ ፕሮጀክት ከለውጡ በፊት በውጭ ብድር ለመስራት የታቀደ ቢሆንም በጀቱ በተያዘበት ቀነ ገደብ ባለመለቀቁ እና በአንዳንድ ምክንያቶች ግንባታው በመዘግየቱ የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር በራሱ በጀት ለመስራት አቅጣጫ ይዞ ወደ ስራ ተገብቷል፡ የቤት ግድግድ እና ጣሪያ ጋር በተያያዘ ከንቲባዋ በተጡት ምልሽ በ1968 ዓ.ም በወጣው አዋጀ መሰረት የካሬ ዋጋ ኪራይ መጠን የመቀየር ስራ እንጅ ምን አይነት የሬት ጨማሪ ያልተደረገ መሆኑን ገልፀው ለመኖሪያ ቤት 50 % ለንግድ 75% የክፍያ ሰርዓት እንዲበጀለት ተደርጓል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በህግ ደረጃ የጡረተኛ እና አቅመ ደካሞችን በተመለከተ በህግ ተፈቅዳል ቢሆንም አፈፃፀሙን በተመለከተ በየደረጃ መከታተል ስለሚያስፈልግ እየተሰራበት መሆኑን ገልፀዋል። የልማት ተነሺ የካሳ ክፍያ ሌሎች ጉዳዩች ጋር ተያይዞ በህግ አሰራር መሰረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀው ቅሬታ አሁንም ካለ በከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ፅ/ቤት በተቋቋመ ስራ ዴስክ በኩል የሚፈታ መሆኑ ከንቲባዋ ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም የአርሶ አደር ይዞታ ማረጋገጪ እና የአቃቂ ድልድይ ጀምር ስራዎችን ለማጠናቀቅ ከተማ አሰተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል፡፡

በምክር ቤት አባላት በኩል የተነሱ ጥያቄና ሀሳቦች በሙሉ በቀሪ ግዜያት ዕቅዳችን አካተን ተደማሪ አቅም በሚፈጥርልን አኳሃን የምንሰራባቸው ይሆናል "ምክትል ከንቲባና የአዲስ አበባ የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ምክትል ከንቲባው ይህንን ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕዝብ ምክር ቤት የ2017 ዓ.ም አራተኛ የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ባለበት ወቅት ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው። በምክር ቤት አባላት የተነሱ ጥያቄዎችና ሀሳቦችን ተደማሪ አቅም በሚፈጥርልን አኳሃን በቀሪ ግዜያት በልማትና በመልካም አስተዳደር ዕቅዶቻችን ሁሉ አካተን በልዩ ትኩረት ለላቀ የዕቅድ አፈጻጸም ተቀናጅተን የምንሰራባቸው ይሆናል ብለዋል ። በበጀት ዓመቱ ግማሽ አፈጻጸም እንዳደረግነው ሁሉ በቀጣይ ግዚያት የልማት ዕቅዶቻችን በሙሉ የነዋሪዎችን ሕይወትና የኑሮ ጫና በሚያቃልል አኳሃን እስከ ወረዳ ድረስ በየደረጃው ያለን አመራሮች በላቀ ቅንጅት በየዘርፉ ያሉን ዕቅዶች አፈጻጸም እየመዘንን መንቀሳቀስ የሁላችንም የጋራና የተናጠል ኃላፊነት ነውም ሲሉ በአጽንኦት ሲናገሩ ተደምጠዋል ። በጋራ ተጠቃሚነት መርህ በውይይት ከመኖሪያ አካባቢያቸው ለተነሱ ነዋሪዎች በመሬት መስተንግዶ፤በግንባታ ፈቃድ መስተንግዶና በካሳ መስተንግዶ ወቅቱን ያገናዘብ አገልግሎት በሚገባ ሰጥተናል በቀጣይም መንጠባጠቦች እንዳይኖሩ በዚሁ አግባብ እየተናበብን ምላሽ የምንሰጥ መሆናችንን ሁሉም ሊያውቅ ይገባልም ብለዋል ምክትል ከንቲባው። ከአርሶ አደሮች መፍት ጋር በተገናኘ የሚነሱ ጥያቄዎችን የህግ ማዕቀፍ አበጅተን በዘላቂነት እየፈተን እንገኛለን ያሉት ም/ከንቲባው በከተማው የሚስተዋለውን የኑሮ ውድነት ለማርገብ እንዲቻለን የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች ያለውን ፍላጎት በሚያረካ አግባብ ለማቅረብ የሚያስችሉ ተግባራትን አከናውነናል በቀጣይም ምርትና ምርታማነትን ጨምሮ አስፈላጊ ተግባራትን በዚሁ ልክ የምንፈጽም ይሆናል ሲሉ አብራርተዋል። ለከተማችን ዘላቂ ዕድገት በምናከናውናቸው የልማት ስራዎች ፣የህንጻ ግንባታና የስራ ዕድል ፈጠራ ተግባራት ሁሉ አካል ጉዳተኛ የሕብረተሰብ ክፍሎች ታሳቢ እንዲሆኑ ከማስቻል ባለፈ ተጠቃሚ የሚሆኑበት አግባብ እንዲፈጠር ም አበክረን እንሰራለንም ሲሉ በአንክሮ ተናግረዋል ።

ዛሬ የነዋሪው ሉዓላዊነት መገለጫ ለሆነው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ2017 የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርታችንን አቅርበናል። ውድ የከተማችን ነዋሪዎች እናንተን በታማኝነት፣ በቅንነት እና በትህትና ለማገልገል ባደረግናቸው ጥረቶች የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተ መረጃ እንድታገኙ ሙሉ ሪፖርቱን እንድታደምጡ እጋብዛቹሃለሁ። Har'a ibsituu birmadummaa jiraattotaa kan ta'e mana maree magaalaa Finfinneef riippoortii raawwii hojii ji'a ja'aa bara 2017 dhiheessineerra. Qaaliiwwan jiraattota magaalaa keenyaa haqummaa, gaaruummaa fi naamusaan isin tajaajiluuuf tattaaffiiwwan taasisneen milkaa'inoota argaman ilaalchisuun odeeffannoo akka argattan guutuu riippoortichaa akka dhaggeeffattan isin affeera. See less

በተለያዩ ተቋማት እየተሰጡ ያሉ አገልግሎቶች መሻሻሎች ታይቶባቸዋል - ጀማሉ ጀንበር (ዶ/ር) በ2017 በበጀት አመት አጋማሽ በመዲናዋ በተለያዩ ተቋማት እየተሰጡ ያሉ አገልግሎቶች መሻሻሎች እንደተስተዋሉባቸው በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ጀማሉ ጀንበር ዶ/ር ገለጹ፡፡ የቢሮ ሀላፊው ይህን ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀሙን በገመገመበት ወቅት ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር የሚስተዋልባቸውን ተቋማት በመለየት እና የሪፎርም ስራዎች በመሰራታቸው እንዲሁም አስፈላጊው ድጋፍ እና ክትትል በመደረጉ ለውጦች ሊመጡ መቻላቸውን ነው ዶክተር ጀማሉ የተናገሩት፡፡ በመሬት ልማት፣ በትራንስፖርት አሰጣጥ፣ በቤቶች ኮርፖሬሽን፣ በቤቶች ልማት፣ በሲቪል ምዝገባ እና በነዋሪዎች አገልግሎት እንዲሁም በሌሎችም ተቋማት ከዚህ በፊት ከነበረው አኳያ መሻሻሎች ቢኖሩም ከሚጠበቀው ውጤት አንፃር አሁንም ቀሪ ስራዎች እንዳሉ ገልጸዋል፡፡ በየተቋማቱ የሚነሱ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመቅረፍ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስራ ለመስራት ጥረት እየተደረገ እንደሆነም አመላክተዋል፡፡ ሌብነትና ብልሹ አሰራሮችን ለማስቀረት በተደረገ ክትትል፣ ባለፉት 6 ወራት ወደ 2 ሺህ 124 የሚደርሱ ሰራተኞችን እና አመራሮች ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረጋቸውንም ገልጸዋል፡፡ በቀጣይም ይህ አሰራር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በማመላከት፣ ህዝቡም መብቱን በገንዘብ መሸጥ እንደማይገባው እና ችግሮች ሲያጋጥሙትም ለሚመለከታቸው አካላት ማሳወቅ እንደሚኖርበት አስገንዝበዋል፡፡ የሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎችን የማጣራት ሂደቱም በከተማና በፌዴራል ደረጃ ተጠናክሮ እንደሚካሄድ እና ስራዎችም እንደተጀመሩ አመላክተዋል፡፡ በሲቪል ምዝገባ እና በነዋሪዎች አገልግሎት በኩል ተጨባጭ የሆኑ ለውጦች መምጣታቸውን የገለጹት ዶክተር ጀማሉ፣ በሲስተም መቆራረጥ ምክንያት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ በገቢ አሰባሰብ በኩልም ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሎች መታየታቸውን ያመላከቱት የቢሮ ኃላፊው፣ በበጀት ዓመቱ 6 ወራትም ተከታታይነት ያላቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል፡፡ በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ 6 ወራት በቅንጅት በተሰሩ ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሻሻሎች እንደታዩባቸው ነው ዶክተር ጀማሉ የተናገሩት፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም 4ኛ የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን በዛሬው ዕለት እያካሄደ ይገኛል:: ምክር ቤቱ በጉባኤው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአስፈጻሚ አካላት የ2017 የስድስት ወራት አፈጻጸም ሪፖርት ገምግሞ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል::