1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
ከተማ አሰተዳደሩ ባለፉት 6 ወራት መሬት ዝግጅትን በተመለከተ
👉ለልማት ጥያቄዎች መሬት ከማዘጋጀት እና ወደ መሬት ባንክ በዳታ ቤዝ መመዝገብ አንጻር ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል 618.35 ሄ/ር ማዘጋጀት ተችሏል።
የለማ መሬት ከማስተላለፍ አንፃር ለመካከኛና ለከፍተኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች፣ ለጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ ለልማት ተነሺዎች፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት ለተለያዩ የሀይማኖት ተቋማት፣ ለጥቃቅንና አነስተኛ የስራ እድል ፈጠራ፣ ለጊዜያዊ መጠቀሚያ፣ ሀገራዊ ፋይዳ ላላቸው ፕሮጀክቶች የሚውል 402.64 ሄ/ር መሬት ማስተላለፍ ተችሏል። በተጨማሪም ለ3,935 በላይ የልማት ተነሺዎች ምትክ ቦታ እንዲሰጣቸው ተደርጓል።
👉በየጊዜው አዲስ የሚመጡ የይዞታ ማህደራት ሙሉ በሙሉ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ አገልግሎት ለመስጠት ማህደራት ላይ የአሰራር ጥራት ኦዲት ማድረግ በተከታታይነት እየተሰራ ነው፡፡
ለልማት ለተነሺዎች ካሳ ለመክፈል በታቀደው መሰረት ብር 9.5 ቢሊዮን መክፈል ተችሏል። አሰራርን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ የሌብነትና ብልሹ አሰራርን ለመቀነስ እየተደረገ ያለው ጥረት ውጤት እያስገኘ ነው።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ከተማ አስተዳደሩ ባለፉት 6 ወራት በመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ ያሳካቸዉ ዉጤቶች በተመለከተ፤-
የአዲስ አስፋልት መንገድ ግንባታ ከ25.7 ኪ.ሜ በላይ የአስፋልት ግንባታ ስራ የተከናወነ ሲሆን የጠጠር መንገድ ግንባታ አፈፃፀም 8.32 (38 %) ኪ.ሜ መገንባት ተችሏል።
748.90 ኪ.ሜ የመንገድ ጥገና ስራዎችም በማከናወን አፈጻጸሙን ማሳደግ ተችሏል።
በአጠቃላይ በግማሽ ዓመቱ ሁሉም ዓይነት የግንባታ በታቀደው መሰረት 87.66 ኪ.ሜ መፈጸም ተችሏል።
የውስጥ ለውስጥ በጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ እየተገነቡ ያሉ መንገዶችን በቀሪ ወራት ተገቢ ትኩረት ሰጥቷቸዉ የሚሰሩ መሆናቸዉ ተገልፃል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ከተማ አስተዳደሩ ባለፉት 6 ወራት በመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ ያሳካቸዉ ዉጤቶች በተመለከተ፤-
የአዲስ አስፋልት መንገድ ግንባታ ከ25.7 ኪ.ሜ በላይ የአስፋልት ግንባታ ስራ የተከናወነ ሲሆን የጠጠር መንገድ ግንባታ አፈፃፀም 8.32 (38 %) ኪ.ሜ መገንባት ተችሏል።
748.90 ኪ.ሜ የመንገድ ጥገና ስራዎችም በማከናወን አፈጻጸሙን ማሳደግ ተችሏል።
በአጠቃላይ በግማሽ ዓመቱ ሁሉም ዓይነት የግንባታ በታቀደው መሰረት 87.66 ኪ.ሜ መፈጸም ተችሏል።
የውስጥ ለውስጥ በጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ እየተገነቡ ያሉ መንገዶችን በቀሪ ወራት ተገቢ ትኩረት ሰጥቷቸዉ የሚሰሩ መሆናቸዉ ተገልፃል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በመዲናዋ በዝቅተኛ ኑሮ ውስጥ ለሚኖሩ ዜጎች የተደረገ ድጋፍ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ለመደገፍ በበጀት ዓመቱ ከ 12 ቢሊዬን ብር በላይ መድቦ በትኩረት እየሰራ ነው
AMN - የካቲት 12/2017 ዓ.ም
See less
ፍትሃዊ የትምህርት ሽፋንና ተደራሽነትን ከማሳደግ አኳያ የተማሪ ቅበላን 1,253,737(106%) ማድረስ ተችሏል፤ ይህም ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር አፈፃፀሙ ሲነፃፀር 89,049 ብልጫ ያለዉ ነዉ፡፡
👉 የትምህርት ፍትሀዊነትን ከማስፈንም አካያ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የልዩ ፍላጎት ትምህርትን በማስፋፋት የተማሪዎች ቁጥር 33,672(100%) ማድረስ ተችሏል።
👉 በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ በተሰራዉ ስራ በገንዘብ 3,841,682,948.15፣ በዓይነት 137,566,563.36፣ በጉልበት 19,800,640.85 እና በእውቀት 26,380,054.45 በድምሩ ብር 4,025,430,206.81 በመሰብሰብ የትምህርት ግብዓትን ማሟላት ተችሏል፡፡
👉 በዘላቂነት የተማሪዎችን የትምህርት ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችል ግብዓትን ከማቅረብ አንፃርም ለ1,037,500 (100%) ተማሪዎች ዩኒፎርም፤ለ9,125,435 (100%) ተማሮዎች ደብተር በማሰራጨት ተደራሽ ማድረግ ተችሏል።
👉 በተማሪ ምገባ አገልግሎት 835,069 (100%) ተማሪዎችን በቀን ሁለት ጊዜ መመገብ የተቻለ ሲሆን የተማሪ የቅበላ አቅም ለማሻሻልና የትምህርት ፍትሀዊነት ለማረጋጋጥ የተሰራው ስራ አበረታች ዉጤት አምጥቷል፡፡
👉በከተማችን የትምህርትና ስልጠና ጥራት ተገቢነትን ለማረጋገጥ በተሰራው ስራ በ126 ተቋማት ላይ የውጭ ኢንስፔክሽን በማካሄድ የደረጃ ምደባ እና የኢንስፔክሽን ስራዎች ተደራሽ ተደርጓል።
👉 ለትምህርትና ስልጠና የእውቅና እና የእድሳት አገልግሎት ጥያቄ ላቀረቡ 660 (94.7%) ተቋማት የእውቅና እና የእድሳት ተሰጥቷል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ከተማ አስተዳደሩ ባለፉት 6 ወራት በቱሪዝም ዘርፉ ያሳካቸዉ ዉጤቶች በተመለከተ፤-
👉ከተማችንን በባህልና በቱሪዝም ተወዳዳሪ እንድትሆን ከማድረግ አኳያ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች በማስፋፋት በከተማዋ የቱሪስት ፍሰት የማሳደግ ስራ ተሰርቷል፡፡
👉በተጨሪም 4,424,062 የሀገር ውስጥና 546,443 የውጪ ሀገር ቱሪስቶች ከተማዋን መጎብኘት ችለዋል።
👉ከሀገር ውስጥ እና ከዉጭ ቱሪስቶች ብር 96.8 ቢሊዮን ገቢ በመሰብሰብ ወደ ከተማዋ የግልና የመንግስት ገቢ /ኢኮኖሚ/ ፈሰስ እንዲሆን ማድረግ ተችሏል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ከተማ አሰተዳደሩ ባለፉት 6 ወራት ውበትና አረንጓዴ ስራዎች በተመለከተ
👉የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ከማስፋፋት አንፃር፤ በግማሽ ዓመቱ አረንጓዴ ቦታዎችን ማልማትና መንከባከብብ በተመለከተ 163.1ሄ/ር አዳዲስ የመንገድ ፓርክ እና ቁርጥራጭ ቦታዎችን ማልማት ተችሏል፡፡
👉በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ከእቅዳችን በላይ 26,720,918 ሚሊየን ችግኞችን መትከል የተቻለ ሲሆን አፈፃፀሙም ከባለፈዉ በጀት ዓመት ከተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ9.2 (52.6%) ሚለየን ችግኝ እድገት አሳይቷል፡፡
👉በዚህም የከተማችን የአረንጓዴ ሽፋን በ2010 ከነበረበት 2.8% ወደ 20% እንዲደርስ ውጤታማ ስራዎች ተከናውኗል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ከተማ አሰተዳደሩ ባለፉት 6 ወራት የቤት መሰረተ ልማትን በተመለከተ
👉ከቤቶች ልማት አንጻር በበጀት ዓመቱ የከተማዋን የቤት አቅርቦት ለማሻሻል በመንግስት አስተባባሪነት፣ በሪል ስቴት እና በግል አልሚዎች በተለያዩ መርሃ-ግብሮች 27,304 የቤቶች ተገንብተው አቅርቦት መጨመር ተችሏል፡፡
👉በልዩ ልዩ የቤት አቅርቦት አማራጮች 120,000 ( መቶ ሃያ ሺህ) ቤቶች ግንባታ ፕሮግራም የተጀመረ ሲሆን፣ ከተጠናቀቁት ውስጥ በከተማችን ለሚሰሩ የህዝብ ልማት ስራዎች (ኮሪድርን ጨምሮ) ለሚነሱ የልማት ተነሺዎች እና የተለያዩ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ታሳቢ 9ሺ 20 ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ተችሏል።
👉ህገ-ወጥነትን ከመከላከል አንፃር 113 የጋራ መኖሪያ ቤት፣ 71 የጋራ መኖሪያ ንግድ ቤት፣ 172 የቀበሌ ቤት ማስለቀቅ ተችሏል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ውሃ አቅርቦትን አና የፍሣሽ ሥራዎችን በተመለከተ
👉የውሃ አቅርቦት ሥራዎችን በተመለከተ ነባር የመጠጥ ውሃ አቅርቦት በተያዘለት መርሃ ግብር መሰረት እየተከናወነ ሲሆን፣ባሳለፍናቸው 6 ወራት የተሰሩ አዳዲስ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት በተመለከተ 15 የውሀ ጉድጓድ ቁፋሮ ተጠናቆ በቀን 25,000 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሀ አቅርቦት ተጨምሯል ተጨማሪ ቀሪ 15 ጉድጓድ በቁፈሮ ላይ ይገኛል።
👉በተጨማሪ በቀን 100,000 ሜትር ኪዩብ የማምረት አቅም ያለው በኦሮሚያ ቡሾፍቱ አካባቢ የሚገኘው የጩቋላ ከርሠ ምድር የውሀ ልማት ፕሮጃክት 13 ጉድጓድ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ በቀን 80,000 ሜትር ኪዩብ ውሀ ተገኝቷል።
👉7 ተጨማሪ ጉድጓድ በቁፈሮ ላይ ይገኛል እንዲሁም በቀን 73,000 ሜትር ኪዩብ የማምረት አቅም ያለው የገርቢ የውሃ ግድብ ፕሮጀክትን በከተማው በጀት ለመገንባት ወስነን ሂደት ላይ ይገኛል።
👉መሰረታዊ የአቅርቦት ችግር ለመፍታት ሁሉን አቀፍ የከርሠ ምድር ውሃ አጠቃቀምና አስተዳደር ጥናት (Comprensive ground water management project) በአለም አቀፍ አማካሪ ድርጅትእያስጠናን እንገኛለን፡፡
👉በቀን 30,000 ሜትር ኪዩብ ማጣራት የሚችል የቦሌ አራብሳ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ተጠናቋል በቀን 104,000 ሜትር ኪዩብ ማጣራት የሚችል የምስራቅ ተፋሰስ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ተጀምሯል።
👉በቀን 20,000 ሜትር ኪዩብ ማጣራት የሚችል የኮዪ ፈጬ 1 እና 2 የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ተጀምሯል፡፡ ለረጅም ዘመናት ብክለትን በማስከተል እና የጤና ጠንቅ በመሆኑ ሲያስቸግሩ የኖሩ የወንዝና ወንዝ ዳርቻ 23.6 ኪ. ሜትር የማጽዳትና የመንከባከብ ስራ ተሰርቷል።
👉 ከዚህ በተጨማሪ ፍሳሽን ወደ ወንዞች በመልቀቅ ብክለት ማስከተልን የሚከላከል ደንብ በካቢኔዎች ፀድቆ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ከተማ አስተዳደሩ በበጀት ዓመቱ በ 6 ወራት በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ያሳካቸዉ ዉጤቶች በተመለከተ፤-
የመረጃ ጥራት እና ተደራሽነትን ለማሳድግ የሚያስችል ስርዓት በመዘርጋት በከተማችን በተከናወኑ የልማት ስራዎች፤ በመልካም አስተዳደርና በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ የግንዛቤ ስራዎችን ተሰርተዋል፡፡
በሰው ተኮር የልማት ስራዎች፤ በከተማ ግብርና የልማት ትሩፋት እና በስራ እድል ፈጠራ የተገኙ ውጤቶችን እንዲሁም በፕሮጀክቶች ግንባታ አፈፃጸም ለሚዲያ አካላት ግልፀኝነትን በመፍጠር የመረጃ ተደራሽነትን ማስፋት ተችሏል፡፡
በተለያዩ ወቅታዊና ከተማ አቀፍ ጉዳዮች ላይ የጥቆማ፣የምርመራ እና የትናታኔ ዜና በማዘጋጀት፤በማሰራጨት እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮች በማጋለጥ አመራሩ በህዝብ ተጠያቂና ግልጽ እንዲሆን የማድረግ ስራ ተሰርቷል።
በከተማ አስተዳደሩ የተከናወኑና እየተከናወኑ ባሉ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ግዙፍ የልማት ስራዎች እና ሰው ተኮር ተግባራት ዙሪያ የተለያዩ መልዕክቶችን በምስልና በድምፅ በማቀናበር ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ለህዝብ እንዲደርስ ተደርጓል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ዛሬ የካቲት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ላይ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ-ከተማ ወረዳ አንድ ሞቢል እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በእንጨትና በብረታ ብረት ዉጤቶች ማምረቻና በሌሎች ድርጅቶች ላይ ተከስቶ የነበረዉ የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ዉሏል።
የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ፣ የጸጥታ አካላት ፣ የደንብ ማስከበርና የአካባቢዉ ማህበረሰብ ባደረጉት ከፍተኛ ርብርብና ቅንጅት እሳቱን በመቆጣጠር በአቅራቢያዉ ወዳሉ ሌሎች ማምረቻና ተቋማት ተዛምቶ የከፋ ዉድመት ሳያስከትል እሳቱን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ተችሏል።
የእሳት አደጋዉን መንስዔ ፖሊስ ምርመራ እያደረገ ሲሆን በአደጋዉ በሰዉ ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።
በማምረቻና በንግድ ስፍራዎች አካባቢ በጥንቃቄ ጉድለትና ቸልተኝነት ምክንያት የሚያጋጥሙ አደጋዎችን ለመከላከል ለጥንቃቄ ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ኮሚሽን መ/ቤቱ አሳስቧል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
