fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
በጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ የሚስተዋለውን የኃይል መቆራረጥ ችግር ለመቀነስ የሚያስችል የመልሶ ግንባታ ስራ ተከናወነ ************* በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጣፎና የካ አባዶ የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ የሚስተዋለውን የኃይል መቆራረጥ ለመቀነስ የሚያስችል የመልሶ ግንባታ ስራ ተከናውኗል፡፡ የመልሶ ግንባታ ስራው 1 ነጥብ 5 ኪ.ሜ የሚሸፍን ሲሆን ከአባዶ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ አዲስ ኃይል ወጪ በማድረግ የተሰራ ነው፡፡ በመስመር ዝርጋታ ስራው 28 የኮንክሪት ፖሎች ተከላ እንዲሁም የአንድ ነጥብ 5 ኪሜ የኃይል አስተላላፊ ኮንዳክተር ዝርጋታ ተከናውኗል፡፡ የመልሶ ግንባታ ስራው ቀደም ሲል ለአካባቢው ኃይል ይሰጡ የነበሩ መስመሮችን ከፍተኛ የኃይል ጭነት በመቀነስ አካባቢው ላይ ያለውን የኃይል መቆራረጥ ችግር በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንስ ነው፡፡ የተዘረጋው የኃይል መስመር ለገጣፎ ኮንዶሚንየም፤የካ አያት ኮንዶሚኒየም እንዲሁም የካ አባዶ ኮንዶሚንየምን የሚሸፍን ሲሆን፤ የጋራ መኖሪያ ቤቶቹን እና አካባቢው ላይ ያሉ ነዋሪዎችን የኃይል አቅርቦት በማሻሻል ቀደም ሲል የነበረውን የኃይል መቆራረጥ ችግር ለመቀነስ የሚያስችል ነው፡፡ የኃይል መስመር ዝርጋታ ስራው አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን፤ስራውን ለማጠናቀቅ 6 ሚሊየን 301 ሺ 917 ብር ተቋሙ ወጪ አድርጓል፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ዛሬ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFPApp) አስጀምሯል። ይህ ስራ ለዜጎች መሰረታዊ አገልግሎት ለመስጠት ታልሞ የሚከናወነው የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ አካል ነው። የሁሉንም ዘርፎች ምሉዕ አቅም ለማሳካት በዲጂታል ኢትዮጵያ መደገፍ አለባቸው። ባለፉት ስድስት አመታት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከአናሎግ ወደ ዲጂታል ስርዓት ተሸጋግሯል። የህዝብ ብዛት እየጨመረ ባለበት ከተማችን ንቁ የዜጎች ተሳትፎ እጅግ አስፈላጊ ነው። ዛሬ ወደስራ የገባው መተግበሪያ በapp ስቶር እና playstore የሚገኝ ሲሆን ዜጎች ወንጀልን ለመከላከል በፎቶግራፍ፣ በቪዲዮ፣ በድምፅ፣ በሰነድ ወይም በቀጥታ በመደወል ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ያስችላል። ሁሉም ዜጋ የአካባቢያችንን እና ከተሞቻችንን ደህንነት ለማስጠበቅ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቀርባለው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

ኢትዮጵያ በወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና በዲጂታል ማንነት ላይ ያተኮረውን የ2025 አህጉራዊው 11ኛ የ ID4Africa ጉባኤ እንድታዘጋጅ ተመረጠች በደቡብ አፍሪካ አስተናጋጅነት በኬፕታዎን ከተማ በመካሄ
+3
ኢትዮጵያ በወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና በዲጂታል ማንነት ላይ ያተኮረውን የ2025 አህጉራዊው 11ኛ የ ID4Africa ጉባኤ እንድታዘጋጅ ተመረጠች በደቡብ አፍሪካ አስተናጋጅነት በኬፕታዎን ከተማ በመካሄድ ላይ ያለው የID4Africa 10ኛ ጠቅላላ ዓመታዊ ጉባኤ Digital Identity As DPI Fostering Trust Inclusion and Adoption በሚል መርህ ቃል እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ አህጉሪቱ በሲቪል ምዝገባ እና በዲጂታል ማንነት ምዝገባ ላይ ያለውን ሁኔታ ከልማት እና መስል ጉዳዮች ጋር በመያያዝ ትኩረት እየተደረገበት ሲገኝ አዲስ አበባ ከተማ ከ6 ተወዳዳሪ ከተሞች ጋር በመወዳደር አሸንፋ የ2025 የጉባኤው አስተናገጅ ሆና ተመርጣለች። በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶ/ር ሙክታር ከድር እንዲሁም የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ኡቶ ዮዳሄ አርዕያ ስላሴ አስተናጋጅነቱን ተቀብለዋል። ይህ አዘጋጅነት በዘርፉ ያለውን የኢትዮጵያ እንቅስቃሴ ያነቃቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ዛሬ ሚያዚያ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ከረፋዱ 3:45 ሰዓት ላይ በቦሌ ክፍለ-ከተማ ወረዳ ሰባት የረር እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ህንጻ ለመገንባት የመሰረት ስራ ላይ ከነበሩ ሰራተኞች መካከል የአንድ
+7
ዛሬ ሚያዚያ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ከረፋዱ 3:45 ሰዓት ላይ በቦሌ ክፍለ-ከተማ ወረዳ ሰባት የረር እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ህንጻ ለመገንባት የመሰረት ስራ ላይ ከነበሩ ሰራተኞች መካከል የአንድ ሰዉ ህይወት አልፏአል። አደጋዉ የደረሰዉ ሰራተኞቹ በስራ ላይ እንዳሉ ስራዉ ከሚከናወንበት አጠገብ የነበረና አፋፍ ላይ ያለ የግለሰብ መኖሪያ ቤት ዉሀ ልክና አፈር በሰራተኞቹ ላይ በመናዱ የደረሰ ነዉ። የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የግለሰቡን አስከሬን ከተጫነበት አፈርና ድንጋይ ስር አዉጥተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል። በማናቸዉም የግንባታ ስራዎች የአደጋ ደህንነት መስፈርትን ጠብቆ አለመስራት መሰል አደጋዎችን የሚያስከትል በመሆኑ አሰሪዎችና የዘርፉ ባለሙያዎች እና የሚመለከታቸው የግንባታ ፈቃድ ሰጪ አካላትም ተገቢዉን ክትትል ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባቸዉ ኮሚሽን መ/ቤቱ አሳስቧል።

"ዛሬ በአዋሬ አካባቢ ከስድስት አመታት በፊት በጀመርነው የዝቅተኛ ወጪ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ እንቅስቃሴ ምናልባትም የመጨረሻው ስፍራውን ለግንባታ ዝግጁ የማድረግ ስራ ተሰርቷል። የመኖሪያ ሁኔታዎቹ ችግር የበዛባቸው ነበሩ። እጅግ ያረጁ፣ የተጠባበቁ፣ መፀዳጃ የሌላቸው መኖሪያዎች ነበሩ። ምቹ የመኖሪያ እና አረንጓዴ አካባቢ የሚያካትተው አዲሱን የመኖሪያ ህንፃ ግንባታ በመጪው መስከረም ወር ለማጠናቀቅ ዛሬ አስጀምረናል። ይህ ስራ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉትን ወገኖቻችንን ህይወት ብቻ ሳይሆን የሪል ስቴት አልሚዎችንም የጠቀመ ነው። በዚህ ፕሮጀክት የቀጣይነት መንፈስ አይተንበታል። አፅንተንበታልም። አዋሬ ቀጣይነት ያለው ያላሰለሰ ጥረት የመኖሪያ አካባቢዎችን ሊለውጥ የነዋሪዎችን የኑሮ ዘይቤ እና ተስፋ ከፍ ሊያደርግ እንደሚችል ማሳያ ምልክት ነው። የዚህ አመቱ የዝቅተኛ ቤቶች ግንባታ ወጪ በከፊል በቪዛ ፋውንዴሽን (VISA Foundation) ተሸፍኗል። ሌሎች ተመሳሳይ ድርጅቶች እና በጎ አድራጊዎች ለዜጎች ህይወት እና ከባቢ መለወጥ ያለመታከት ልግስናቸውን እንዲዘረጉ ጥሪዬን አቀርባለው" ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ

ማሳሰቢያ ዛሬ ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ በ9፡30 ሰዓት ገደማ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም-አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ የዕሳት አደጋ ተከስቶ ነበር። እሳቱ የተፈጠረው ከአውሮፕላን ማ
ማሳሰቢያ ዛሬ ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ በ9፡30 ሰዓት ገደማ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም-አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ የዕሳት አደጋ ተከስቶ ነበር። እሳቱ የተፈጠረው ከአውሮፕላን ማረፊያው አጥር ውጭ ባሉ የመኖሪያ ቤቶች ውስጥ እንደነበረና አሁን ላይ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተረድተናል። በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዕለታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ምንም ዓይነት መስተጓጎል እንዳልነበረ ለመግለጽ እንወዳለን።

አየር መንገድ አካባቢ የተነሳው የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል”፦ የአዲስ አበባ ከተማ እሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት አካባቢ ዛሬ ከቀኑ 9፡41 ላይ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል። የእሳት አደጋው በኮሚሽን ባለሞያዎች፣ በአየር መንገዱ የእሳት አደጋ ሰራተኞች እና ሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ባደረጉት ርብርብ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉን ኮሚሽኑ ገልጿል። አደጋው ከአየር መንገድ ግቢው ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ኮሚሽኑ አስታውቆ በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች እና ሚዲያዎች የእሳት አደጋው በአየር መንገዱ ውስጥ እንደተከሰተ ተድርገጎ የሚያሰራጩት ዘገባ ፍፁም ከእውነት የራቀ ነው ሲል ኮሚሽኑ አረጋግጧል። አደጋው በአንድ የድንገተኛ እሳት አደጋ ባለሞያ ላይ ቀላል ጉዳት ማድረሱን እና የእሳት አደጋው መነሻ ምክንያት እና ያስከተለው የጉዳት መጠን የማጣራት ስራው ሲጠናቀቅ ለህብረተሰቡ ይፋ እንደሚደረግም ኮሚሽኑ አስታውቋል። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

" አዲስን እንደ አዲስ" https://linktr.ee/AddisMediaNetwork AMN - ግንቦት 13/2016 ዓ.ም

በዘጠና ቀናት ታቅደው የተከናወኑ ተግባራት በመስክ ጉብኝት ተደረገ። በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በርካታ ስራዎች ባለፉት ሶስት ወረተረት ታቅደው ሲከናወኑ እንደነበር ይታዘቃል። ከእነዚህ ተግባራት መካከል በዛሬው እለት ✍️በአርሶ አደርና በከተማ ግብርና የተከናወኑ ተግባራት ✍️ በECD/የቀዳማይ ልጅነት የህፃናት መጫወቻ እና መዋያ ✍️ መሪ ህዳሴ ሞዴል ትምህርት ተቋም ለተማሪዎች የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ እና ሌሎችንም ተግባራት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲንና የከተማ ደጋፊ አመራሮች ፥ የክፍለ ከተማ አጠቃላይ አመራሮች ወረዳ ኮር አመራሮች በወረዳ 13 የተከናወኑትን ተግባራት የመስክ ምልከታ አድርገዋል። ውጤታማ ስራ መሰራቱንም ገልፀዋል። Lemi Kura Communication ለሚ ኩራ

የ90 ቀናት የንቅናቄ ዕቅድ የተግባር አፈፃፀም የማጠቃለያ ግምገማ ተከናወነ። የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ባለፉት በዘጠና ቀናት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ የከተማ ደጋፊ አመራሮች ፥ አጠቃላይ የክፍለ ከተማ አመራሮች፥የ10ሩም ወረዳ ኮር አመራሮችና የሚመለከታቸው የወረዳ አመራሮች ጋር ግምገማ አካሂዷል። ትኩረት የተደረገባቸው ነጥቦች 👉የሌማት ትሩፋት የከተማ ግብርና ስራዎች 👉የስራ እድል ፈጠራ ከምዝገባ እስከ ተጠቃሚነት 👉የንግድ ስርዓቱን ማዘመንና ኑሮ ውድነትን መቆጣጠር እና የዋጋ ንረትን ከመከላከል አንፃር 👉የገቢ አሠባሠብ በተመለከተ 👉 የህብረት ተሳትፎ የሰው ተኮር ስራዎች 👉የአርሶ አደርና የከተማ ግብርና ስራዎች 👉 በአረንጓዴ ልማት የመንገድ አካፋይ ስራዎች 👉የቀዳማዊ ልጅነትና መጫወቻ ቦታዎችን ሌሎች ክፍለ ከተማ ትኩረት ተሠጥቶባቸው እየሠራባቸው የሚገኙ ተግባራት ናቸው። መድረኩን የመሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን ባሳለፍነው የ90 ቀን ስራችን እንደ ክፍለ ከተማ በርካታ ተግባራት በውጤት ተከናውነዋል።ለዚህ ደግሞ የተሰጠው የአመራር ስምሪት እና ተግባራትን በምልከታ ወርዶ በማየት መገምገምና አቅጣጫ በማስቀመጥ ሂደቱ በየደረጃው ያለው የአመራር ተግባር ነውና ሊበረታታ ይገባል። በዚህ ውጤት ቢታጀብም ውስን ትኩረት የሚሹ ተግባራት ላይ በልዩ ትኩረት መስራት ያሻል ብለዋል። የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ገመቹ በበኩላቸው እቅድ አቅደን የጋራ በማድረግ ወደ ስራ ከገባን ጊዜ ጀምሮ ተግባራትን ተከፋፍለን በየክላስተር የተሰሩትን በየሁለት ቀን በመገምገም በመናበብ የሰራናቸው ተግባራት አሁን ላይ ውጤት እንድናስመዘግብ እረድቶናል።በቀጣይ በ100% ያላጠናቀቅናቸው አንዳንድ ተግባራት በቀሪ ጊዜ በመስራት ውጤት ማስመዝገብ ከእያንዳንዱ አመራር ይጠበቃል ብለዋል። የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድርና አክለው ብልፅግና ያቀደውን በውጤት የሚፈፅም የተናገረውን የሚተገብር ፖርቲ ነው ስንል አመራሩ በርብርብ ያስመዘገባቸው ውጤቶች ማሳያ ናቸው። በቀጣይም በመናበብና በመቀናጀተት ቀሪ ተግባራትን በውጤት በመቀየር የአመት እቅዳችንን እናሳካለን ብለዋል። በመጨረሻም ያሳለፍነው የሶስት ወር/90 ቀን የተግባር አፈፃፀማችን 👉 አመራሩ በቁርጠኝነት ተግባር ቆጥሮ ከወሰደ መስራት እንደሚችል ያየንበት 👉 ህብረተሰቡን አሳትፈን የሰራናቸው ሰው ተኮር ስራችን የህ/ሰባችንን ተባባሪነትና ልማት ፈላጊነት ያየንበት 👉 አዲስ የስራ ባህል ያየንበትና ያዳበርንበት 👉 ፀጋዎቻችንን ለይተን በአግባቡ እንድንጠቀም የሚያስችል አተያይ የወሰድንበት እና ሌሎችንም ልምዶች ያካበትንበት እንደሆነ ተነስቷል። በመጨረሻም በቀጣይ ቀሪ 47 ቀናት/ አንድ ወር ከ17 ቀን ምን መሰራት እንዳለብን የሚያመላክት አጭር ዕቅድ ቀርቦ በመወያየት ተጠናቋል። Lemi Kura Communication ለሚ ኩራ