fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
መንግስታችን ለዛሬ ሳይሆን ለመጪው ትውልድ የሚሠራ መንግስት በመሆኑ በቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ ላይ በስፋት እየሠራን እንገኛለን" በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ክብርት ሂክማ ከይረዲን በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በዛሬው እለት ለምርቃት የበቃው በወረዳ 14 የአባዶ ጤና ጣቢያ የልማት ኘሮጀክቶች የማስፋፊያ ግንባታዎችን ጨምሮ ከወረቀት ንክኪ ነፃ የአገልግሎት መስጫ እና የካርድ ክፍሎች እንዲሁም የህፃናት ማቆያ ግንባታዎች ተመርቀው ለህዝብ አገልግሎት ክፍት መሆናቸው ተገለፀ። በምረቃው ስነ-ስርዓት በክብር እንግድነት የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ወ/ሮ ሂክማ ኸይረዲን እንዳሉት የከተማ አስተዳደሩ በልዩ ሁኔታ ትኩረት ሠጥቶ እየሠራባቸው ከሚገኙ ተግባራት መካከል አገልግሎትን በቴክኖሎጂ የተደገፈና ለማህበረሰቡ ጥራት እና ፍጥረት ያለው አገልግሎት መስጠት ነው ። በዚህም ከዚህ በፊት በሆስፒታሎች የነበረውን ተግባር ወደ ጤና ጣቢያዎች የማውረድና የመተግበር ስራዎች እየተሠሩ ይገኛሉ ያሉት ወ/ሮ ሂክማ በከተማም በ39 ጤና ጣቢያዎችም አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ የተደገፈና ከወረቀት ንክኪ በፀዳ መልኩ እየተሠጠ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል። በሌላ በኩል መንግስታችን ለዛሬ ሳይሆን ለመጪው ትውልድ የሚሠራ መንግስት በመሆኑ በከተማው በቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ በዚህ አመት 1,500 የሚሆኑ የህፃናት መጫወቻና መዋያ ለመስራት ታቅዶ በዘጠኝ ወራት ውስጥ 534 የቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ ተግባራት መፈፀማቸውን ገልፀዋል። የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ም/ኃላፊ ዶ/ር ሙሉጌታ እንዳለ በበኩላቸው በጤና ተቋማት የሚሠጡ አገልግሎቶችን ማዘመን ተገልጋዩ ህብረተሰብ ወደ ጤና ተቋማት ሲመጡ መረጃዎችን እንዲሁም የሚፈልጉት አገልግሎት በፍጥነት እንዲያገኙ ይረዳል ብለዋል። የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው ባሉ ዘጠኝ ጤና ጣቢያዎች ዛሬን ጨምሮ በአምስቱ ጤና ጣቢያዎች ላይ የቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ ተግባር እየተከናወነ እንዳለ ገልፀው በ23 የትምህርህ ተቋማትም ላይ የቀዳማይ ልጅነት ተግባር ለማስጀመር ታቅዶ በ15 ላይ እንደተጀመረና ቀሪዎቹ በቀጣይ ሳምታት እንደሚመረቁ በንግግራቸው ገልፀዋል። የለሚ ኩራ ኮሚኒኬሽን ግንቦት 13/2016 ዓ.ም

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የምክር ቤት አባላትና አመራሮች በፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት የተሰሩ ሞዴል ብሎኮችን ተዘዋውረው ጎበኙ፡፡ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ምክር ቤት አባላትና አመራሮች በክፍለ ከተማው
+5
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የምክር ቤት አባላትና አመራሮች በፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት የተሰሩ ሞዴል ብሎኮችን ተዘዋውረው ጎበኙ፡፡ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ምክር ቤት አባላትና አመራሮች በክፍለ ከተማው የተፈጠሩ ሞዴል ብሎኮችን፣ ሞዴል ተቋማትን፣ የፕላስቲክ መልሶ መጠቀም ማዕከልን፣ እንዲሁም የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ቅብብሎሽ ጣቢያ ግንባታ ያለበትን ደረጃ ጎብኝተዋል፡፡ ፅዱ፣ ውብና ምቹ አካባቢን ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት በእውነትም ተጨባጭ ውጤት እያሳየ መሆኑን ባደረግነው ምልከታ አረጋግጠናል ያሉት የክፍለ ከተማው ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ በቀለ ጉታ በዘርፉ የታየው መነቃቃት የሚደነቅ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡ የምክር ቤቱ ማዘጋጃ ቤታዊ ዘርፍ ሰብሳቢ አቶ አቦነህ ሳህሌ በበኩላቸው የፅዳትና ውበት ዘርፉ ስኬታማ እንዲሆን በተደጋጋሚ ሲከታተሉና ሲጠይቁ እንደነበር ገልፀው ዛሬ መሬት ላይ ወርደን የተመለከትነው ነገር ግን ለጥያቄዎቻችን ምላሽ የሰጠና ሁላችንንም ያስደሰተ ነገር ተመልክተናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አዲሱ ጎንፋ በበኩላቸው የምክር ቤቱ አባላትና አመራሮች የተሰሩ ተግባራትን ተዘዋውረው መጎብኘታቸው ለቀጣይ ስራችን የሚያግዝ በመሆኑ የሚያደርጉልን ድጋፍና ክትትል እናመሰግናለን ብለዋል፡፡

ትላንት እና ዛሬ ከከተማችን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የኮሪደር ልማት ስራዎቻችንን ተዘዋውረን ገምግመናል። በኮሪደር ልማት ስራዎቻችን ከ48 ኪ.ሜ በላይ የተሽከርካሪ የመንገድ ልማት፣ 4 የመሬት ውስጥ የእግረኛ መንገዶች፣ 96 ኪ.ሜ ሰፋፊ የእግረኛና 100 ኪ.ሜ የብስክሌት መንገዶች፣ 5 ኪ.ሜ የመሮጫ ትራክ፣ 48 የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡን የሚያሳልጡ የአውቶቡስ እና የታክሲ ተርሚናሎችንና መጫኛ ማውረጃ ስፍራዎች፣ በጥቅሉ ከ 240 ኪ.ሜ በላይ የሚሆን የመንገድ እና ተያያዥ መሰረተ ልማት፤ 70 የከተማን ውበት የሚጨምሩ የህዝብ መናፈሻ ስፍራዎች፣ ፋውንቴኖችና የአረንጏዴ ስፍራዎች፣ የመዝናኛና የመናፈሻ ስፍራዎች፣ የልጆች መጫዎቻና የህዝብ ፕላዛዎች፣ 120 የሚሆኑ የመጸዳጃ ቤቶች፣ የከተማዋን ማዘጋጃዊ አገልግሎቶችን ደረጃ ከፍ የሚያደርጉ የፍሳሽ ማስተላለፊያዎች፣ ከተማችንን የሚመጥኑ የደህንነት ካሜራዎች፣ የኬብል ትራንስፖርት ስርዓት ( intelligent transport system) በመሬት ውስጥ የመዘርጋት ስራ ፣ ከ400 በላይ ህንጻዎች እንዲታደሱ የማድረግ እንዲሁም የከተማዋን ደረጃ የሚመጥኑ የቀለምና የመብራት ስራዎች እና ሌሎች በርካታ ግንባታዎችን በመከናወን ላይ የምንገኝ ሲሆን በግንባታ ላይ የሚገኙት ስራዎች ሲጠናቀቁ አዲስ አበባችን እንደ ስሟ ውብ፣ አበባ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ እንዲሁም እየጨመረ የመጣውን የመዲናችንን ዓለምአቀፍ የስበት ማዕከልነት በማሳደግ ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የሰነቅነውን ራዕይ በማሳካት ረገድ የላቀ ሚና የሚጫወቱ ይሆናል። ቃል በገባነው መሰረት የተወሰኑ መንገዶች ( ከጥቃቅን ስራዎች በስተቀር) አጠናቅቀን ለአገልግሎት ክፍት ያደረግን ሲሆን፣ (ለአብነት ያክል ከቴዎድሮስ አደባባይ እስክ አድዋ ድል መታሰቢያ ከደጎል እስከ ቀይ ባህር ኮንደሚኒየም ከአራት ኪሎ እስከ ቅ/ ማርያም መገንጠያ፣ ከሜክሲኮ አደባባይ እስከ ሳርቤት) ቀሪዎቹንም በገነባነው አዲስ የስራ ባሕል ዓመታት ይፈጅ የነበረውን ስራ በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ሳምንቱን ሙሉ 24/7 እየሰራን እንገኛለን። በዚህ የኮሪደር ስራ ላይ እየተሳተፋችሁ ያላችሁ ኮንትራክተሮች፣ አማካሪዎች፣ በየደረጃው ያላችሁ አመራሮች፣ መሃንዲሶች፣ ባለሙያዎች ፣ መላው የፕሮጀክቶቹ ሠራተኞች፣ የጸጥታ አካላት እንዲሁም የከተማችን ነዋሪዎች ስለትጋታችሁና በቅን ልቦና እየሰጣችሁት ላለው አገልግሎት እና ትብብር በከተማ አስተዳደሩ እና በነዋሪዎቻችን ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ኤፍ ኤም 97.1 ጋር በመተባበር የሚያቀርቡላችሁ ሳምንታዊ የሬድዮ ፕሮግራም በክፍል 9 ዝግጅቱ ትኩረቱን በመዲናችን የአደጋ መከላከልና የመቆጣጠር ተግባር ላይ አድርጓል። ህይወትና ንብረትን ከአደጋ የመታደግ ክቡር አገልግሎት ፈጻሚዎች የየእለት ውሎ ምን ይመስላል የሚለውን ይቃኛል። እንድትከታተሉት ተጋብዛችኋል።

በመዲናችን ዘወትር በየሳምንቱ ቅዳሜ ማለዳ የሚካሄደው የጽዳት ንቅናቄ የከተማዋን አመራሮች ጨምሮ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች እያሳተፈ በተጠናከረ መንገድ ቀጥሏል። በዚህ ሳምንትም የከተማችን ምክር ቤት አመራሮችና አባላት ያካሄዱት የጽዳት ንቅናቄ ድንቅ አርአያነት የታየበት ተግባር ነበር።

ወርሃ ክረምቱ ከመግባቱ በፊት የፍሳሽ መስመሮችን ማስተካልና በጎርፍ ሳቢያ የሚደርሱ ጉዳቶችን ቀድሞ መከላከል እንደሚገባ ተጠቆመ! በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤትና በጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ አዘጋጅነት "የመረጠኝን ህዝብ በፅዳት አገለግላለሁ!" በሚል መሪ ቃል የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት የተሳተፉበት የጽዳት ንቅናቄ መርሃ ግብር ዛሬ ግንቦት 10/ 2016 አ.ም በቂርቆስ ክ/ከተማ ስቴድየም ዙሪያ ተካሂዷል። በጽዳት መርሐ ግብሩ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ክብርት ሂክማ ከይረዲን፣ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ ቤት ም/ አፈ ጉባኤ ወ/ ሪት ፋኢዛ መሃመድና ፣ የምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና አባላት፣ የከተማ አስተዳደሩና የቂርቆስ ክ/ ከተማ አመራሮች፣ የጽዳት አምባሳደሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ባለድርሻ አካላትም ተሳትፈዋል። ንቅናቄውን በንግግር ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ምክርቤት ም/አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሪት ፋኢዛ መሀመድ ወርሃ ክረምቱ ከመግባቱ በፊት የፍሳሽ መስመሮችን ማስተካልና በጎርፍ ሳቢያ የሚደርሱ ጉዳቶችን አስቀድሞ መከላከል እንደሚገባ አሳስበዋል። ም/አፈ ጉባኤዋ አክለው እንደገለፁት በአረንጓዴ አሻራ ስራችን ሁሉንም አካባቢዎች አረንጓዴ ለማድረግ እየተሰራ ያለውን ስራ በተጀመረው ፍጥነት ሳይቆራረጥ ከማስቀጠል ጎን ለጎን የክረምቱን ወራት ታሳቢ ያደረጉ ስራዎችን የሚመለከታችሁ ተቋማት በቅንጅት መስራት እንዳለባችሁ ማሳሰብ እወዳለሁ ብለዋል። በመጨረሻም ይህ የጽዳት ንቅናቄ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ባሳተፈ መልኩ መካሄዱን አድንቀው በቀጣይም በተመሳሳይ ግለት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል። በተለይ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር የተጀመረው "የጽዱ ኢትዮጵያ" ኢንሼቲቭ ግቡን እንዲመታ የህዝብ እንደራሴዎች ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። ግንቦት 10/2016 ዓ.ም ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ማህበረሰቡ ፅዳትን ባህል በማድረግና ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ አረንጓዴና ለኑሮ ምቹ የሆነች ከተማ መፍጠር የሚያደርገው ጥረት ምን ይመስላል ሲል ኢዜአ የተወሰኑ የከተማዋ ነዋሪዎችን አነጋግሯል። አቶ ሽፈራው ወርቁና ዋና ሳጅን ተሾመ ይመር የተባሉ የመዲናዋ ነዋሪዎች ፅዳት የስልጣኔና የጤንነት ምልክት በመሆኑ ቆሻሻን ከቤትና ከአካባቢ በአግባቡ ለማስወገድ በጋራ እየሰራን ነው ብለዋል። ደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ላይ ያለው ግንዛቤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ በመምጣቱ ቆሻሻን የሚጠየፍ ትውልድ ለመፍጠር መንገድ መክፈቱን ተናግረዋል። በቀጣይም የግንዛቤ ስራውን የተለያዩ የብዙሃን ትራንስፖርቶችን በመጠቀም መስራት ለለውጥ ያግዛል ብለዋል፡፡ የጽዳትን ጠቀሜታ ከቤት በመጀመር ለልጆች ማስተማር ይህንኑ ልማድ አድርገው እንዲያድጉ እንደሚረዳቸው የተናገሩት ደግሞ ወይዘሮ ብርሃኔ መለሰ ናቸው፡፡ እንደ ሀገር የተጀመሩ ስራዎች በቀጣይ በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥሉ ተሳትፏቸውን እንደሚያሳድጉ የተናገሩት ወይዘሮ ሃና ዮሃንስ ናቸው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሙላቱ ተገኝ በበኩላቸው ከተማዋን በማይመጥን ሁኔታ በህገ ወጥ መንገድ ቆሻሻ የሚያስወግዱ ጥቂት ሰዎች በመኖራቸው ከተግባራቸው እንዲቆጠቡ የሚረዳ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን መናገራቸውን ኢ.ዜ.አ ዘግቧል፡፡ ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ላይ ያለው ግንዛቤ እየተሻሻለ በመምጣቱ ቆሻሻን የሚጠየፍ ትውልድ ለመፍጠር መንገድ የሚከፍት ነው በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ላይ ያለው ግንዛቤ እየተሻሻለ በመምጣቱ ቆሻሻን የሚጠየፍ ትውልድ ለመፍጠር መንገድ የሚከፍት መሆኑን አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ገልፀዋል። ከ135 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያላት አዲስ አበባ፣ በስፋት እንጂ በፅዳትና ውበት ብዙም እንዳላደገች የሚያነሱ በርካታ አስተያየት ሰጪዎች እንደነበሩ አይዘነጋም፡፡ ከተማዋ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችን የምታስተናግድና የአፍሪካ መዲና ብትሆንም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በቂ መናፈሻዎችና አረንጓዴ ሥፍራዎች አልነበሯትም፡፡ ከዚህ ባለፈ የፅዳት አጠባበቋ ዝቅተኛ መሆኑን ተከትሎ ስሟን፣ ዝናዋንና የዕድሜ ርዝማኔዋን የሚመጥን ውበት ሳትላበስ ቆይታለች፡፡ አሁን ላይ ይህ አስተሳሰብ በተግባር እየተቀየረ በመምጣቱ ነዋሪዎቿ ከተማዋንና ስሟን የሚመጥን የጽዳት አወጋገድ እንዲኖር የበኩላቸውን ሃላፊነት መወጣት ጀምረዋል፡፡ ማህበረሰቡ ፅዳትን ባህል በማድረግና ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ አረንጓዴና ለኑሮ ምቹ የሆነች ከተማ መፍጠር የሚያደርገው ጥረት ምን ይመስላል ሲል ኢዜአ የተወሰኑ የከተማዋ ነዋሪዎችን አነጋግሯል። አቶ ሽፈራው ወርቁና ዋና ሳጅን ተሾመ ይመር የተባሉ የመዲናዋ ነዋሪዎች ፅዳት የስልጣኔና የጤንነት ምልክት በመሆኑ ቆሻሻን ከቤትና ከአካባቢ በአግባቡ ለማስወገድ በጋራ እየሰራን ነው ብለዋል። ደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ላይ ያለው ግንዛቤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ በመምጣቱ ቆሻሻን የሚጠየፍ ትውልድ ለመፍጠር መንገድ መክፈቱን ተናግረዋል። በቀጣይም የግንዛቤ ስራውን የተለያዩ የብዙሃን ትራንስፖርቶችን በመጠቀም መስራት ለለውጥ ያግዛል ብለዋል፡፡ የጽዳትን ጠቀሜታ ከቤት በመጀመር ለልጆች ማስተማር ይህንኑ ልማድ አድርገው እንዲያድጉ እንደሚረዳቸው የተናገሩት ደግሞ ወይዘሮ ብርሃኔ መለሰ ናቸው፡፡ እንደ ሀገር የተጀመሩ ስራዎች በቀጣይ በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥሉ ተሳትፏቸውን እንደሚያሳድጉ የተናገሩት ወይዘሮ ሃና ዮሃንስ ናቸው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሙላቱ ተገኝ በበኩላቸው ከተማዋን በማይመጥን ሁኔታ በህገ ወጥ መንገድ ቆሻሻ የሚያስወግዱ ጥቂት ሰዎች በመኖራቸው ከተግባራቸው እንዲቆጠቡ የሚረዳ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን መናገራቸውን ኢ.ዜ.አ ዘግቧል፡፡ ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ላይ ያለው ግንዛቤ እየተሻሻለ በመምጣቱ ቆሻሻን የሚጠየፍ ትውልድ ለመፍጠር መንገድ የሚከፍት ነው በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ላይ ያለው ግንዛቤ እየተሻሻለ በመምጣቱ ቆሻሻን የሚጠየፍ ትውልድ ለመፍጠር መንገድ የሚከፍት መሆኑን አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ገልፀዋል። ከ135 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያላት አዲስ አበባ፣ በስፋት እንጂ በፅዳትና ውበት ብዙም እንዳላደገች የሚያነሱ በርካታ አስተያየት ሰጪዎች እንደነበሩ አይዘነጋም፡፡ ከተማዋ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችን የምታስተናግድና የአፍሪካ መዲና ብትሆንም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በቂ መናፈሻዎችና አረንጓዴ ሥፍራዎች አልነበሯትም፡፡ ከዚህ ባለፈ የፅዳት አጠባበቋ ዝቅተኛ መሆኑን ተከትሎ ስሟን፣ ዝናዋንና የዕድሜ ርዝማኔዋን የሚመጥን ውበት ሳትላበስ ቆይታለች፡፡ አሁን ላይ ይህ አስተሳሰብ በተግባር እየተቀየረ በመምጣቱ ነዋሪዎቿ ከተማዋንና ስሟን የሚመጥን የጽዳት አወጋገድ እንዲኖር የበኩላቸውን ሃላፊነት መወጣት ጀምረዋል፡፡ ማህበረሰቡ ፅዳትን ባህል በማድረግና ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ አረንጓዴና ለኑሮ ምቹ የሆነች ከተማ መፍጠር የሚያደርገው ጥረት ምን ይመስላል ሲል ኢዜአ የተወሰኑ የከተማዋ ነዋሪዎችን አነጋግሯል። አቶ ሽፈራው ወርቁና ዋና ሳጅን ተሾመ ይመር የተባሉ የመዲናዋ ነዋሪዎች ፅዳት የስልጣኔና የጤንነት ምልክት በመሆኑ ቆሻሻን ከቤትና ከአካባቢ በአግባቡ ለማስወገድ በጋራ እየሰራን ነው ብለዋል። ደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ላይ ያለው ግንዛቤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ በመምጣቱ ቆሻሻን የሚጠየፍ ትውልድ ለመፍጠር መንገድ መክፈቱን ተናግረዋል። በቀጣይም የግንዛቤ ስራውን የተለያዩ የብዙሃን ትራንስፖርቶችን በመጠቀም መስራት ለለውጥ ያግዛል ብለዋል፡፡ የጽዳትን ጠቀሜታ ከቤት በመጀመር ለልጆች ማስተማር ይህንኑ ልማድ አድርገው እንዲያድጉ እንደሚረዳቸው የተናገሩት ደግሞ ወይዘሮ ብርሃኔ መለሰ ናቸው፡፡ እንደ ሀገር የተጀመሩ ስራዎች በቀጣይ በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥሉ ተሳትፏቸውን እንደሚያሳድጉ የተናገሩት ወይዘሮ ሃና ዮሃንስ ናቸው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሙላቱ ተገኝ በበኩላቸው ከተማዋን በማይመጥን ሁኔታ በህገ ወጥ መንገድ ቆሻሻ የሚያስወግዱ ጥቂት ሰዎች በመኖራቸው ከተግባራቸው እንዲቆጠቡ የሚረዳ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን መናገራቸውን ኢ.ዜ.አ ዘግቧል፡፡ ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ላይ ያለው ግንዛቤ እየተሻሻለ በመምጣቱ ቆሻሻን የሚጠየፍ ትውልድ ለመፍጠር መንገድ የሚከፍት ነው በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ላይ ያለው ግንዛቤ እየተሻሻለ በመምጣቱ ቆሻሻን የሚጠየፍ ትውልድ ለመፍጠር መንገድ የሚከፍት መሆኑን አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ገልፀዋል። ከ135 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያላት አዲስ አበባ፣ በስፋት እንጂ በፅዳትና ውበት ብዙም እንዳላደገች የሚያነሱ በርካታ አስተያየት ሰጪዎች እንደነበሩ አይዘነጋም፡፡ ከተማዋ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችን የምታስተናግድና የአፍሪካ መዲና ብትሆንም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በቂ መናፈሻዎችና አረንጓዴ ሥፍራዎች አልነበሯትም፡፡ ከዚህ ባለፈ የፅዳት አጠባበቋ ዝቅተኛ መሆኑን ተከትሎ ስሟን፣ ዝናዋንና የዕድሜ ርዝማኔዋን የሚመጥን ውበት ሳትላበስ ቆይታለች፡፡ አሁን ላይ ይህ አስተሳሰብ በተግባር እየተቀየረ በመምጣቱ ነዋሪዎቿ ከተማዋንና ስሟን የሚመጥን የጽዳት አወጋገድ እንዲኖር የበኩላቸውን ሃላፊነት መወጣት ጀምረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ "የመረጠኝን ህዝብ በፅዳት አገለግላለሁ!" በሚል መሪ ቃል በነገው እለት ቅዳሜ ግንቦት 10/ 2016 አ.ም በአይነቱ ልዩ የሆነ የፅዳት ንቅናቄ ይካሄዳል። የጽዳት ንቅናቄው የአዲ
+1
በአዲስ አበባ ከተማ "የመረጠኝን ህዝብ በፅዳት አገለግላለሁ!" በሚል መሪ ቃል በነገው እለት ቅዳሜ ግንቦት 10/ 2016 አ.ም በአይነቱ ልዩ የሆነ የፅዳት ንቅናቄ ይካሄዳል። የጽዳት ንቅናቄው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላትና የፌደራል ፓርላማ አባላት የሚሳተፉበትና በከተማው በሁሉም ክ/ ከተሞች የሚካሄድ ነው። "የመረጠኝን ህዝብ በፅዳት አገለግላለሁ!" በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ይህ የጽዳት ንቅናቄ እንደ ከተማ በማእከል በተመረጠው ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ስታዲየም ዙሪያ አካባቢ ነገ ቅዳሜ ግንቦት 10/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰአት 30 ጀምሮ ይካሄዳል። ከተማችን አዲስ አበባ ፅዱ ፣ ውብ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ እንድትሆን ለማድረግ ከተማ አስተዳደሩ በየደረጃው የሚገኙ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮችን ጨምሮ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ፣ የፅዳት አምባሳደሮች ፣ የፀጥታ አካላት ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ ባለድርሻ አካላትንና አጠቃላይ የከተማዋ ነዋሪ ህብረተሰብን ያሳተፈ ሳምንታዊ የፅዳት ንቅናቄ እያካሄደ ይገኛል። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የመዲናዋ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በአገልግሎት አሰጣጥ የሚያጋጥሙትን ችግሮች ለመፍታት በቅንጅት መሥራት አለበት አዲስ አበባ፤ ግንቦት 9/2016(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በአገልግሎት አሰጣጥ የሚያጋጥሙትን ችግሮች ለመከላከል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት መሥራት እንዳለበት ተመላከተ። ኤጀንሲው ለከተማዋ ነዋሪ በሚሰጠው አገልግሎት ወቅት በሚያጋጥሙ ችግሮች ዙሪያ ከባለድርሻ አካለት ጋር ውይይት አካሂዷል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሂክማ ኸይረዲን በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፤ ኤጀንሲው አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የሚያከናውናቸው ተግባራት የሚበረታቱ ናቸው። ተቋሙ እየዘረጋ ያለው ዲጂታል ሥርዓት የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠትና የተገልጋዮችን ጊዜ በመቆጠብ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ መሆኑንም ነው ያመላከቱት። ይሁን እንጂ ሃሰተኛ ሰነድና ሕገ-ወጥ ድለላን በመከላከል እንዲሁም በሠራተኛ እርምት አወሳሰድና የወንጀል ሕግ ተጠያቂነት ላይ አሁንም ክፍተቶች እንዳሉ ተናግረዋል። ሕትመት ቤቶች ለሃሰተኛ ሰነድ ዝግጅት ያላቸውን ሚና በመገንዘብ ተቆጣጣሪ አካልና ፍቃድ ሰጪ አካላት በሕትመት ቤቶች ላይ ቁጥጥራቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል። በተለይም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እነዚህን ችግሮች መከላከል እንደሚገባ ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዮናስ አለማየሁ በበኩላቸው የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት የሪፎርም ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል። ተቋሙ ካከናወናቸው የሪፎርም ሥራዎች የአገልግሎት አሰጣጥ፣ ጥራትና ተደራሽነት ያማከለ የዲጂታል አሰራር ተግባራዊ ማድረጉን ጠቁመው ይህም ብልሹ አሰራርን በመታገልና ተጠያቂነትን በማስፈን ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ጠቅሰዋል። ይሁን እንጂ በአንዳንድ ሕትመት ቤቶች አማካይኝነት የሚዘጋጁ ሕገ-ወጥ ሰነዶች አሁንም ተግዳሮት ሆነው መቀጠላቸውን ተናግረው ይህንን ለመከላከል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

የሃስተኛ ሰነድ ወንጀልን መከላከል ላይ ያተኮረ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ተካሄደ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ
+7
የሃስተኛ ሰነድ ወንጀልን መከላከል ላይ ያተኮረ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ተካሄደ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አማካኝነት ለከተማው ነዋሪ በሚሰጠው አገልግሎት ሂደት በሃሰተኛ ሰነድ ፣ በህገ-ወጥ ድለላ ፣ በሰራተኛ እርምት አወሳሰድ እና የወንጀል የህገ ተጠያቂነት ዙርያ ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች እና እየገጠሙ ያሉ ተግዳሮቶች ዙሪያ ከከተማ አስተዳደሩ እና ከፌደራል ባለድርሻ ተቋማት ጋር የጋራ የምክክር መድሰክ አካሂዷል። በዚሁ የምክክር መድረክ ወቅት በሲቪል ምዝገባ እና በነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በተለይም በሀሰተኛ ሰነዶች ህትመትና ዝግጅትን የተመለከተ የህግ ተጠያቂነት፣በቀጣይ የሚጠበቁ የመፍትሄ አቅጣጫ፣አለም አቀፋዊ ልምዶች እና አሰራሮችና እስካሁን በህገወጦች ላይ የተወሰዱ እርምጃዎችን የሚዳስስ የጥናት ሰነዶች ቀርበዋል። በመድረኩ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ክብርት ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን እንደገለፁት በሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አሰራሩንና አገልግሎት አሰጣጡን የሚያሻሽል ሰፊና ቀጣይነት ያለው የሪፎርም ስራ እየተከናወነ መሆኑን አውስተው ለህገ ወጥነትና ብልሹ አሰራር የሚዳርጉ የሃሰተኛ ሰነድና ተያያዥ ወንጀሎችን ለመቅረፍ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ባለቤት በመሆን እና ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ወንጀሉን መከላከል እንደሚባም አስገንዝበዋል። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ!

የግል መፀዳጃና የንፅህና መጠበቂያ ክፍሎች በሌሉበትና ህዝብ በከፍተኛ ጥግግት በሚኖርባቸው የከተማ አካባቢዎች ህዝባዊ መፀዳጃ ቤቶች የንፅህና አጠባበቅ ደረጃን ለመጠበቅ ብሎም የበሽታዎች መስፋፋትን ለ
የግል መፀዳጃና የንፅህና መጠበቂያ ክፍሎች በሌሉበትና ህዝብ በከፍተኛ ጥግግት በሚኖርባቸው የከተማ አካባቢዎች ህዝባዊ መፀዳጃ ቤቶች የንፅህና አጠባበቅ ደረጃን ለመጠበቅ ብሎም የበሽታዎች መስፋፋትን ለመግታት እጅግ አስፈላጊ ናቸው። በቂ የመፀዳጃ ቤቶችን ማዘጋጀት የንፅህናን ደረጃ ከማሻሻሉም ባሻገር ለሁሉም የማኅበረሰብ አባላት ከዚህ ጋር የተያያዙ የሰብዕና እና የሰዋዊ ክብር ጉዳዮችን በምቹ ሁኔታ ምላሽ በመስጠት ለአጠቃላይ ህዝባዊ ጤናና ደኅንነት አስተዋፅዖ ያደርጋል። #ጽዱኢትዮጵያ ተቀላቅለዋል? #PMOEthiopia ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

photo content
+2