1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
የሐረር አቅጣጫና ተስፋ
በሐረር ከተማ የተጀመረውን የኮሪደር ልማትና አካባቢውን ለኑሮና ለቱሪዝም ምቹ የማድረግ እንቅስቃሴ ተመልክቻለሁ። በከተማዋ የተጀመረው ሥራ ዕምቅ ዐቅምን ማወቅ፤ አካባቢያዊ ጸጋዎችን ለብልጽግና መጠቀም፤ ማኅበረሰብን ማስተባበር እና የአመራር ቁርጠኝነት ሲደመሩ - ለውጥ እንዴት እንደሚመጣ ማሳያ ነው።
ሐረርን እንደ ተምሳሌት በመውሰድ አካባቢዎቻችን ለመቀየር የሚያስችሉ ሰባት ልምዶች እና አቅጣጫዎች ቀጥለው ቀርበዋል።
1. የአመራር ቁርጠኝነት፦ ሐረርን በዋናነት የቀየራት የአመራር ቁርጠኝነት ነው። ዓመታዊ ገቢያቸው ከሌሎች ያነሰ ነው። ለሥራው ያዋሉት በጀትም ዝቅተኛ ነው። ቀሪውን ያሟሉት አመራሩ ቁርጠኛ ሆኖ ቀን ከሌት በመሥራት እና ዐቅሙን አሟጥጦ በመጠቀም ነው። ሌሎች ከዚህ መማር አለብን።
2. ታሪካዊ ሀብትን ዐውቆ ማልማት፦ ሐረር እና አካባቢዋ ከሺ ዓመታት የዘለለ ታሪካዊ ሀብት አላቸው። ይሄንን ሀብት በማወቅ እና በመለየት ለጉብኝት ምቹ አድርገውታል። መንገድ ተሠርቷል፤ ሙዝየም ተገንብቷል። የአካባቢውን ንጽሕና የመጠበቅ ሥራም እየተሠራ ነው። ይሄ ለሌሎችም ትምህርት የሚሆን ነው።
3. ጥንታዊ አካባቢን አናብቦ ማዘመን፦ የሺ እና የመቶ ዓመታት ታሪክ ያላቸው የኢትዮጵያ ከተሞች እንዴት መቀየር እንዳለባቸው ሐረር ተምሳሌት ናት። ጀጎል ተለውጧል። የውስጥ ለውስጥ መንገዱ ተዘርግቷል። ግንቡን ለመጠገን የተሠራው ሥራ፣ የመብራት ሥራው፤ ጥንታዊው ከተማ የወዳደቁ ቤቶች መከማቻ እንዳይሆን እየተሠራ ያለው ሥራ፣ ጀጎልን ሁሌ አዲስ እንድትሆን አድርጓታል። ያረጁና ያፈጁ ከተሞች እንዴት እንደሚቀየሩ መማሪያ ነው።
4. አካባቢያዊ ልዩ ጸጋን ለቱሪዝም መጠቀም፦ ሐረር ሰዎችና የዱር እንስሳት ተግባብተው የሚኖሩባት ከተማ ናት። ለዚህ አንዱ ማሳያ የጅብ ትርዒት ነው። ከመቶ ዓመታት በፊት ጀምሮ ሐረርን የጎበኙ ጸሐፍት ይሄንን ትርዒት አድንቀው ጽፈዋል። ይሄንን ትርዒት ወደ ዘመናዊ የቱሪስት መዳረሻነት ለመቀየር በመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ መነሻነት የጅብ ትርዒት ማሳያ አምፊ ቴአትር በሐረር ተገንብቷል። በየአካባቢያችን ያሉትን ልዩ ጸጋዎች በዚህ መንገድ ነው ዐውቀን ማልማት ያለብን።
5. ለኮሪደር ሥራ አካባቢያዊ ዕውቀትን መጠቀማቸው፦ በአንዳንድ ከተሞች የኮሪደር ልማት በውድ ዋጋ የሚገኙትን የመንገድ መብራቶች ሐረሮች በአካባቢያቸው በማምረት በርካሽ አግኝተዋቸዋል። የመንገድ መብራትን ለመጠገን ያለውን ችግር በሚፈታ መልኩ ሐረሮች የመንገዶቻቸውን መብራቶች በርካሽና በተሻለ መንገድ ሠርተዋል። ሥራን ውድ የሚያደርገው ሀብትን እና ዕውቀትን በሚገባ አለመጠቀም ነው።
6. በአካባቢ ጸጋ አካባቢን ማስዋብ፦ ሐረር ላይ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች የተሠሩት በሐረር ድንጋይ ተጠርበው ነው። ይሄ ተግባር አዱሱ ግንባታ ከነባሩ ጋር እንዲጣጣም አድርጓል። ለአካባቢው ወጣቶችም የሥራ ዕድል ፈጥሯል፤ በጥቂት ወጪ ብዙ ሥራ ለመሥራትም አስችሏል፤ የዕውቀት ሽግግር እንዲኖር አድርጓል። ዘወር ዘወር ብለን መሬቱን እንየው። ለልማት የሚውል ብዙ ሀብት አለው።
7. አስፍቶ ማሰብ፦ ሐረር በቆዳ ስፋት ከብዙ ክልሎች ያነሰች ናት። ታሪካዊ ከተማ በመሆኗም የነዋሪዎች መጨናነቅ እና የቦታ ጥበት አለ። ጠባብን ቦታን የሚያሰፋው ሰፊ አመለካከት ነው። ሩቅን የሚያቀርበው አርቆ ተመልካችነት ነው። የሐረር የኮሪደር ልማት ሰፊ የሆነው በዚህ ዕይታ ነው። በዚህ ዕይታ የተሠሩት የእግረኛ መንገዶች፣ ፓርኮች፣ አምፊ ቴአትሮች፣ አረንጓዴ ሥፍራዎች፣ ወዘተ. አስደናቂ ናቸው። አስፍቶ ማሰብ ጥቁቱን ያበዛል፣ ሩቁን ያቀርባል።
እነዚህ ሁሉ ሥራዎች ሀብት እንዲያመነጩ ምቹ ሆቴሎች ያስፈልጋሉ። ኢንቨስተሮችን ስቦና አበረታትቶ ንግዱን ማቀላጠፍ ይገባል።
በከተማ የተሠሩ ሥራዎች ዘላቂ እንዲሆኑ በገጠሩ የሌማት ትሩፋት ይበልጥ መስፋፋት አለበት። ዘመናዊ ግብርናና የግብርና ተዋጽዖ ማቀነባበሪያዎች እንዲፈጠሩ እንትጋ። የአካባቢያችንን ገበያዎች እናነቃቃቸው።
ከዚህ ጎን ለጎን የሕዝቡን የመለወጥ ፍላጎት፣ የሰላም ፍላጎት እና ታታሪነት እንደ ሀብት በመውሰድ ሕዝብ የሚያረካ አገልግሎት እንስጥ።
ሐረሮች በርቱ። ግን ገና ብዙ ይቀረናልና ረክታችሁ እንዳትቆሙ። ሕዝብን እያወያያችሁና እያስተባበራችሁ ሐረርን ከዓለም ጋር ለማወዳደር እስክትችሉ ትጉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ (ዶ/ር)
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ሰራተኞች "ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል" በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 😎 በተለያዩ ዝግጅቶች አክብረዋል።
በአለም ዓቀፍ ደረጃ ለ114ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ49ኛ ጊዜ እየተከበረ ያለውን ይህን ቀን እንደ ጽ/ቤት በፓናል ውይይት፣ የነገዋ ሴት ፕሮጀክትን በመጎበኘት በዛሬው ዕለት የጽ/ ቤቱ ሰራተኞች አክብረዋል።
የጽ/ቤቱ ሰራተኞች እለቱን አስመልክቶ የጎበኙት የነገዋ የሴቶች የተሀድሶ እና የክህሎት ማበልፀጊያ ማእከል ለተለያዩ ጥቃት የተጋለጡ እንዲሁም የጎዳና ተዳዳሪ የነበሩና ወደ ማእከሉ የገቡ ሴቶች በዘላቂነት እንዲቋቋሙ፣ ገቢ እያገኙ ራሳቸውን እንዲችሉ የክህሎት ማበልፀጊያ የማሰልጠኛ ማዕከላት፣ የስነ ልቦና እና ምክር አገልግሎት፣ የሕክምና ማዕከል፣ ዶርሚተሪ፣ መመገቢያ አዳራሾች እንዲሁም የስፖርት ማዘውተሪያ እና የመዝናኛ ስፍራዎች የተካተቱበት ነው ።
አለም አቀፍ የሴቶች ቀን/ማርች8/ በማስመልከት በተዘጋጀው በዚህ የጉብኝት መርሀ ግብር የተሳተፉ የአዲስ አበባ ከተማ ሰራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ሰራተኞች አዲስ አበባን ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት ለሁሉም የምትመች ከተማ ለማድረግ የከተማ አስተዳደሩ እውን ያደረገው ይህ ትልቅ ፕሮጀክት የሚደነቅ እያንዳንዱ ዜጋም ለሌላው የሚተርፍ ማህበራዊ ሀላፊነት እንዲወጣ የሚያነሳሳ እንደሆነ ገልፀው ፕሮጀክቱ ቀጣይነት እንዲኖረው ሁሉም ሊረባረብ እንደሚገባና ሠራተኞችም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከትም ቃል የገቡበት ነው።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የየካቲት ወር የስራ እንቅስቃሴን የሚያስቃኝ ዜና መጽሄት ከታች በተቀመጠው ሊንክ እንዲያነቡ ተጋብዘዋል።
https://t.me/aacitymanager/17738
የአደጋ ጊዜ ቅድመ ልምምድ ( Sumilation) ማካሄድ እዉነተኛ አደጋ ባጋጠመ ጊዜ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እንደሚያስችል ተገለጸ።
በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከጳዉሎስ ሆስፒታል ጋር በመተባበር በእሳት አደጋና በሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ጊዜ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የአደጋ ጊዜ ቅድመ ልምምድ ዛሬ መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም በሆስፒታሉ ቅጥር ጊቢ አካሄዷል ።
በልምምዱም በአደጋ ጊዜ ሰዎች ካሉበት ህንጻ እንዴትና ወዴት መዉጣት እንዳለባቸዉ እንደዚሁም የደረሰዉን አደጋ በፍጥነት በመቆጣጠር ለተጎጂዎች ስለሚሰጥ የህክምና አገልግሎት ላይ ያተኮረ ነዉ።
በልምምድ መርሀ ግብሩ ላይ ም/ኮሚሽነርና የአደጋ ምላሽ ዘርፍ ኃላፊ ኮማንደር መስፍን አያሌዉ እንደተናገሩት አደጋ ከማጋጠሙ በፊት አስቀድሞ የአደጋ ጊዜ ልምምዶችን ማካሄድ እዉነተኛ አደጋ በአጋጠመ ጊዜ ህይወትና ንብረትን በማዳን ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እንደሚያስችል አብራርተዋል።
በአደጋ ጊዜ ልምምዱ ላይ የጳዉሎስ ሆስፒታል ጤና ባለሞያዎችና የአስተዳደር ሰራተኞች ተሳትፈዋል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም በአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት ተጠሪ በሆኑ ተቋማት ለሚሰጡ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች የሚከተሉትን አድራሻዎች ይጠቀሙ!
1.የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ
ዋና ቢሮ አድራሻ፡- በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 1 በተለምዶ ፒያሳ እሪ በከንቱ ዮናታን ቢቲ ህንጻ ከ7ኛ ፎቅ ጀምሮ
ነጻ የስልክ መስመር - 6199
ቴሌግራም፡- https://t.me/CGAACMA
ዩቲዩብ ፡- https://www.youtube.com/@aacma-bu4zt
ዌብሳይት፡- www.aacma.gov.et
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/profile.php?id=100064800963883
2.የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ
ዋና ቢሮ አድራሻ :- አዲሱ ገበያ ቱኒዝያ መንገድ ሸገር መናፈሻ ግቢ ውስጥ
ነጻ የስልክ መስመር - 7533
ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et
የፌስቡክ (facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686
ቴሌግራም (telegram): https://t.me/addisvaitalpress
ፖስታ ሳ.ቁ (Box No)፡ 20320
3. የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን
ዋና ቢሮ አድራሻ ;-አራዳ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 10 አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፊትለፊት
ነጻ የስልክ መስመር :- 939
fdrmc1926@addisfire.gov.et
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/AADRMC1
4. የአዲስ አበባ ከተማ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን
የቢሮ አድራሻ:- አራዳ ክ/ ከተማ ወረዳ 1 በተለምዶ ፒያሳ እሪ በከንቱ አካባቢ ኤንሪኮ ኬክ ቤት ዝቅ ብሎ ዋስትና ንግድ ማዕከል 17ኛ ፎቅ
ስ.ቁ 0111127775
ፌስቡክ ገፅ:-https://www.facebook.com/profile.php?id=61565439308107
EMail; AAESAA@aaca.gov.et
Website:-https://aaesa.gov.et
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
https://www.facebook.com/EEUOfficial
ማምሻውን የአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ግንባታ ከጅማሮው አንስቶ በስኬት እስኪጠናቀቅ ድረስ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላትን አመስግነናል::
ስንተባበርና በአንድነት ስንሰራ ስራዎቻችን ጥራት ያለዉ እና ዉጤታማ ይሆናል። ተግዳሮቶችን በመሻገር የጎደለውን እየሞላን ሀገራችንን ከፍ የሚያደርጉ ትላልቅ ስራዎች ለመስራት አቅም እየፈጠርን ሁላችንም ለስኬት እንደምንበቃ አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ትልቅ ማሳያ ነው::
ማዕከሉ ዓለምአቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እና ለሀገር ያለውን ጠቀሜታ በመገንዘብ ለስኬት እንዲበቃ አስተዋጽዖ ያበረከቱ የማዕከሉ የቦርድ እና የማኔጅመንት አባላት፣የስራ ተቋራጩ እና አማካሪ ድርጅቱ፣ ባለአክሲዮኖች፣ ለልማት ከአካባቢው የተነሱ ነዋሪዎችን እንዲሁም ስራውን ያስተባበሩ የከተማችን አመራሮች እና ሰራተኞችን በሙሉ በራሴና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።
በዛሬው እለት ቅዳሜ የካቲት 29 ቀን አሁን ምሽት 1ሰአት ከ15 ላይ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ቡልቡላ 1ኛ ደረጃ አጠገብ ባለዉ ድልድይ ጋ የደረሰ የትራፊክ አደጋ ነዉ።
በአደጋዉ በሰው ህይወት ላይ ምንም ጉዳት አልደረሰም።
በትራፊክ አደጋ ምክንያት በሰዉና በንብረት ላይ እያጋጠሙ ያሉ አደጋዎችን ለመከላከል በተለይም አሽከርካሪዎች አስፈላጊዉን የደህንነት መስፈርቶችን ጠብቆ ማሽከርከር እንደሚገባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳስቧል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የሰላም ሰራዊት አባላት የአካባቢያቸውን ሰላምና ጸጥታ ከማስጠበቅ ባለፈ የአደጋ ስጋትን ላይ ያላቸውን ግንዛቤ በማስፋት መኖሪያ አካባቢያቸውንና ብሎኮቻቸውን ከአደጋ የጸዳ ማድረግ እንዳለባቸው ተገለጸ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የጉለሌ ቅርንጫፍና ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ጋር በጋራ ከ10ሩም ወረዳ ለተወጣጡ የሰላም ሰራዊት አባላት በአደጋ ስጋት ቅነሳ ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል።
በስልጠናው ላይ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ደረጀ እንደተናገሩት የክፍለ ከተማውን ሁለንተናዊ ሰላም በማረጋገጥ የሰላም ሰራዊቱ ሚና የጎላ መሆኑን ገልጸው አሁንም የሰላም ሰራዊቱ የአካባቢውን ሰላምና ጸጥታ የሰላም ሰራዊቱ የአካባቢውን ሰላምና ጸጥታ በማስጠበቅ ባለፈ በየአካባቢው የሚደርሱ ድንገተኛ አደጋዎች በወሰዱት ግንዛቤ የአደጋዎችን ምንነትና ግንዛቤ በበቂ ሁኔታ በመጨበጥ መከላከል ይገባል ብለዋል።
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ጥላሁን ቶላ በበኩላቸው በከተማችን ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመከላከል በየደረጃው ከሚገኙ ነዋሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እየተሰራ ይገኛል በዛሬው ለጉለሌ ሰላም ሰራዊት አካል የተሰጠው የግንዛቤ የዚሁ አካል ነው ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ኒቆዲሞስ ቡቼ በበኩላቸው በእሳት አደጋ ቅድመ መከላከል፣ በአደጋ ጊዜ እና ድህረ መከላከል ዙሪያ በክፍለ ከተማ ደረጃ በርካታ ተግባራት መከናወኑን ገልፀው የአደጋ ቅነሳው በመንግስት ብቻ የሚከናወን ሳይሆን በህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ በመሆኑ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መስጠት ከስጋት ነፃ የሆነች ከተማን መፍጠር ነው ብለዋል።
የሰላም ሰራዊት አባላት ግንዛቤውን በመጨበጥ በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን የአደጋ ስጋት የመቀነስ ተልዕኮአቸውን መወጣት አለባቸው ሲሉ ገልፀዋል።
ጉለሌ ኮሚኒኬሽን
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!
የአዲስ አበባ አበባ ከተማ አሰተዳደር ካቢኔ በዛሬው 4ኛ አመት 8ኛ መደበኛ ስብሰባ በሚከተሉት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል::
1ኛ አገራዊ እና ማህበራዊ ፋይዳ ላላቸው የማኑፋክቸሪንግ እና ሌሎች ፕሮጀክቶች የሚውል የቦታ ጥያቄን መርምሮ አፅድቋል::
2ኛ መደበኛ ያልሆነ የጎዳና ላይ ንግድን ሥርዓት ለማስያዝ ይረዳ ዘንድ የተዘጋጀ ረቂቅ ደንብን ተወያይቶ አፅድቋል::
3ኛ በምሽት የንግድ ቤቶች እና የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ለማራዘም በወጣው ደንብ ዝርዝር ላይ ተወያይቶ አፅድቋል::
4ኛ የተርሚናል አገልግሎት አሠራር እና ቁጥጥር ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል::
5ኛ የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ አደረጃጀት እና አሠራርን ለመወሰን የተዘጋጀ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል::
6ኛ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለሥልጣን ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 166 / 2016 ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል::
7ኛ የገርቢ የመጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክት ለመተግበር የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ ውሳኔ አሳልፏል::
