1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
እንኳን ለዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን አደረሳችሁ፣ አደረሰን!
ዘንድሮ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ስናከብር የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ከሚያስችሉ ስራዎች ምን ያህል አሳካን፣ ምን ያህል ሴቶችን ህይወት የቀየሩ ፕሮጀክቶችን አጠናቅቀን፣ ምን ያህል ሴቶችን ተጠቃሚ አደረግን እንዲሁም ምን ያህል ቅድሚያ ለሚገባቸው ሴቶች ቅድሚያ መስጠታችንን በተግባር አረጋገጥን በማለት እና ለሌሎች ተደማሪ ድሎች ራሳችንን በማዘጋጀት ነው።
ከዚህ አንፃር ለከተማችን ሴቶች ተጠቃሚነት የሰራናቸው ስራዎች ፍሬ አፍርተዋል ፤ ግን በቂ ስላልሆኑ የሴቶችን አቅም ይበልጥ እያጎለበትን፣ እስካሁን ያገኘናቸውን ስኬቶች አጠናክረን ለበለጠ ተጠቃሚነት በትጋት መስራታችንን እንቀጥል እላለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
"አካባቢያችንን እናፀዳለን የከተማችንን ሰላም እንጠብቃለን" በሚል መሪ ሀሳብ የጽዳት ዘመቻ ተካሂዷል።
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር "አካባቢያችንን እናፀዳለን የከተማችንን ሰላም እንጠብቃለን" በሚል መሪ ሀሳብ የጽዳት ዘመቻ ተካሂዷል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ አመራሮች፣የሰላም ሰራዊት፣የደንብ ኦፊሰሮችና የፖሊስ አካላት ተገኝተዋል።
የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ በቀለ እንዳሉት የፀጥታ መዋቅሩ የከተማዋን ሰላምና ልማት በመጠቅ፣ ማህበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት የላቀ ተሳትፎ እያሳየ ነው ብለዋል።
አቶ ባህሩ አክለውም ጽዳቷ የተጠበቀ፣ ውብና ምቹ ከተማን ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት በማገዝ የድርሻችንን እንወጣለን።
የክፍለ ከተማው ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ አለሚቱ አበራ በበኩላቸው የጽዳት ዘመቻው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው፤ ከኮሪደር ልማቱ ጋር የሚዛመድ ገጽታን ለመፍጠር፤ ቆሻሻን በአይነቱ በማስቀመጥና ወደ ሀብት በመቀየር፣ የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ በቅንጅት እንሰራለን ብለዋል።
Lafto Communication- ላፍቶ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
"ለከተማዬ ሰላም ዘብ እቆማለሁ!ፅዳቷንም እጠብቃለሁ " በሚል የጽዳት ንቅናቄ ተካሄደ።
የአራዳ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ ሮ ጸጋ ነሽ ታምራት እንደገለጹት የከተማችንን ጽዳት በማስጠበቅ ለነዋሪዎቿ ምቹ የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
አክለውም ዛሬ የተጀመረው ለሶስት ወራት የሚቆይ የጽዳት መርሐ ግብር መሆኑን አስታውሰው ሁሉም የክ/ከተማው ነዋረዎች ፅዳትን ባህል በማድረግ ፅዱ አካባቢን መፍጠር እንዳለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በጽዳት ንቅናቄው የጸጥታ አካላትና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆነዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የጸጥታ አካላት ሰላምና ጸጥታ ከማስጠበቅ ባሻገር በከተማዋ የጽዳት አምባሳደር መሆን እንዳለባቸው ተገለጸ።
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 "የከተማዬን ሰላም አስጠብቃለሁ ፅዳቷንም እጠብቃለሁ" በሚል መሪ ቃል የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ::
"የከተማዬን ሰላም አስጠብቃለሁ ፅዳቷንም እጠብቃለሁ" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የጽዳት ዘመቻ ላይ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ፣የፌዴራል ፖሊስ አባላት፣ የአዲስ አባባ ፖሊስ አባላት፣ የሰላም ሰራዊት አባላት እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል ።
በፅዳት ዘመቻው ተገኝተው መልዕክት ያሰተላለፉት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ደረጀ እንደተናገሩት ፅዳትን ባህሉ ያደረገ ዜጋን ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት ተስፋ ሰጭ ውጤት እየተመዘገበበት መሆኑን ገልፀው የፀጥታ ሀይሉም የልማትና የከተማ ማስዋብ ላይ ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ሀላፊነቱን እየተወጣ ነው ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ዋና አማካሪ ወ/ሮ ሀዳስ ኪዱ በበኩላቸው መዲናችን አዲስ አበባን ውብ፣ ፅዱና ማራኪ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ ጠቅሰው ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል የፅዳት ስራን ባህል በማድረግ ያለማንም ቀስቃሽ አካባቢውን ሊያፀዳ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል::
ቆሻሻ ሀብት ነው በመልሶ መጠቀም በርካታ የስራ እድል እየፈጠረ በመሆኑ በአግባቡ ሊወገድ ይገባል ብለዋል።
Gullele communication-ጉለሌ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ጆሀንስበርግ እንደ አዲስ አበባ እንድትሆን እንሰራለን- ሲሪሊ ራማፎሳ
አዲስ አበባ ፀድታ÷ ተውባ እና ደምቃ ምቹ ከተማ ሆናለች ሲሉ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ተናገሩ::
ጆሃንስበርግም እንደ አዲስ አበባ ሆና ማየት እንፈልጋለን ሲሉም ገልፀዋል::
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ይህንን የተናገሩት በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የጆሀንስበርግ ከተማ የምታስተናግደውን የጂ 20 የመሪዎች ስብሰባ ቅድመ ዝግጅትን አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር ላይ ነው::
በንግግራቸውም በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት መደነቃቸውን አንስተዋል::
በአዲስ አበባ ነዋሪዎች በቀን እና በምሽት በምቹ ጎዳናዎች ላይ እንደልባቸው መንቀሳቀስ እንደሚችሉም ገልፀዋል::
ፕሬዝዳንቱ በቅርቡ ለአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ አዲስ አበባ በተገኙበት ወቅት ከተማዋን ተዘዋውረው መጎብኘታቸው ይታወሳል::
FBC
ቢሊ ግራሃም ኢቫጀሊካል አሶሴሽን ፕሬዚዳንት ከሆኑት ሬቨረንድ ፍራንክሊን ግራሃምን በቢሮዬ ተቀብያቸዉ እንኳን ደህና መጡ ብለናቸዋል።
ፍራንክሊን ግራሃም እንደ አባታቸው ሁሉ ለኢትዮጲያ ጥልቅ ፍቅር ያላቸው መሆኑን ፣ ሁሌ እንደሚፀልዩ እና ላለፉት 40 ዓመታት ኢትዮጵያን በተደጋጋሚ የጎበኙ ሲሆን በከተማችን አዲስ አበባ ባዩት ፈጣን ለውጥ መደነቃቸውንም ገልጸውልናል::
ለኢትዮጵያ እና ህዝቦቿ ያላሳዩት ፍቅር እና መልካም ምኞት እናመሰግናለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ቢሊ ግራሃም ኢቫጀሊካል አሶሴሽን ፕሬዚዳንት ከሆኑት ሬቨረንድ ፍራንክሊን ግራሃምን በቢሮዬ ተቀብያቸዉ እንኳን ደህና መጡ ብለናቸዋል።
ፍራንክሊን ግራሃም እንደ አባታቸው ሁሉ ለኢትዮጲያ ጥልቅ ፍቅር ያላቸው መሆኑን ፣ ሁሌ እንደሚፀልዩ እና ላለፉት 40 ዓመታት ኢትዮጵያን በተደጋጋሚ የጎበኙ ሲሆን በከተማችን አዲስ አበባ ባዩት ፈጣን ለውጥ መደነቃቸውንም ገልጸውልናል::
ለኢትዮጵያ እና ህዝቦቿ ያላሳዩት ፍቅር እና መልካም ምኞት እናመሰግናለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
"በህይወት ማትረፍ ተችሏል"
ዛሬ የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም በአራዳ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 7 ቤለር እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በደረሰ የኮንስትራክሽን የስራ ላይ አደጋ ሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።
አደጋዉ የደረሰዉ የመንገድ ፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦ ለመቅበር በቁፋሮ ስራ ላይ በነበሩ ሁለት ሰራተኞች ላይ ከፍተኛ መጠን ያለዉ አፈር ተንዶባቸዉ ነዉ።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ባለሞያዎች አምስት ሜትር ገደማ ጥልቀት ካለዉ ጠባብ ጉድጓድ ዉስጥ አፈር ተጭኗቸዉ የነበሩትን ሁለቱን ሰራተኞች 1:20 ሰዓት በፈጀ ጥረት በኋላ በህይወት ማዉጣት ችለዋል።
በህይወት የወጡት ሁለቱ ወጣቶች እድሜያቸው 27 እና 29 ዓመት የተገመተ ሲሆን በአደጋው ምክኒያት ጉዳት የደረሰባቸው በመሆኑ በኮሚሽኑ አምቡላንስ እየተረዱ ወደ ዳግማዊ ሚኒልክ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡
በአዲስ አበባ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ተገቢዉን የአደጋ ደህንነት መስፈርትን ጠብቆ ባለመስራት መሰል አደጋዎች በተደጋጋሚ እያጋጠሙ በመሆኑ በተለይም አሰሪዎች የሰራተኞቻቸዉን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታቸዉን እንዲወጡም ኮሚሽን መ/ቤቱ ያሳስባል።
ለእሳትና ለሌሎች ድነገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነው ያሳውቁ
በሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ የመንግስት ዋና ዋና አጀንዳዎችን ከማስረጽ አንጻር ውጤታማ ስራዎች ተሰርተዋል-መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
በበጀት አመቱ ግማሽ አመት እቅድ በሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ የመንግስት ዋና ዋና አጀንዳዎችን ከማስረጽ አንጻር ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ የግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ "ዓላማ ተኮር፤ የተናበበ እና የተቀናጀ የተግባቦት ስርዓት ለእመርታዊ እድገት" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ፥ በግማሽ ዓመቱ ዘርፉ መንግስታዊ አጀንዳዎችን ከማስረጽ አንጻር ውጤታማ ስራዎች ሰርቷል።
ዘርፉ ህዝብን በልማት ከማሳተፍ እና ከማነቃቃት አንጻርም አበረታች ስራዎች መከናወኑን ገልጸዋል።
በተለይም የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር፣እንዲሁም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተሳካ መልኩ እንዲከናወን ዘርፉ በጎ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አንስተዋል።
በተጨማሪም እንደ አገር በትኩረት እየተከናወነ በሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ በህዝብ ተሳትፎ እንዲታገዝ ዘርፉ ትልቅ ሚና መጫወቱን ተናግረዋል።
በተመሳሳይ እንደ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን እና የሰንደቅ ዓላማ ቀን የመሳሰሉ አገራዊ ሁነቶች ከተገቢው መልዕክት ጋር መሸፈናቸውን ጠቅሰዋል።
እነዚህ ሁነቶችም ለሰላም ግንባታ እና ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በመገንባት ሂደት ትልቅ ውጤት ነበራቸው ብለዋል።
በሌላ በኩል የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ከዘላቂ ሰላም ግንባታ እንዲሁም አፍራሽ መረጃዎችን ከመከላከል አንጻር አሁንም ብዙ ስራዎች እንደሚቀሩ ማውሳታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በመድረኩ ላይ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ሀላፊዎች፣ የኮሙኒኬሽን ዘርፍ ሃላፊዎች እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
#GCSEthiopia
ስማርት ሲቲ እየሆነች የመጣችውን መዲናችን አዲስ አበባን የሚመጥን ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር በቴክኖሎጅ የዘመነ፣ ቀልጣፋና ስሉጥ አገልግሎት እውን በማድረግ ረገድ ውጤታማ ተግባራት እየተከናወነ ነው።
See less
