fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید 👈

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
ከቃል እስከ ባህል! " ብልፅግና በአዲስ የፖለቲካ እሳቤ እየተመራ የኢትዮጵያን የዴሞክራሲ ባህል እየገነባ ይገኛል። ፓርቲው እራሱን በማጠናከር ሀገረ መንግስት ግንባታውን ለማፋጠን ብርቱ እንቅስቃሴ እያደረገ ሲሆን ለውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲም ልዩ ትኩረት ሰጥቷል። የፓርቲው አባላት ከህዋስ ጀምሮ ባሉት ሁሉም ተቋማት ነፃ የሀሳብ ትግል እያደረጉ የዴሞክራሲን ባህል እየገነቡ ነው ፤ የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤን አስመልክቶ በየደረጃው በተካሄዱ የቅድመ ጉባኤ ኮንፈረንሶችም ዴሞክራሲያዊነት ተንፀባርቋል። በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ እና በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ምክትል ኃላፊ እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ በሁለተኛው ጉባኤ ዙርያ አጭር ኦረንቴሽን የሰጡ ሲሆን ፣ ከወረዳ መሠረታዊ ድርጅት እስከ ክ/ከተማ ድረስ እየተከናወነ ያለው የቅድመ ጉባኤኮንፈረንስም በነገው እለት በከተማ ደረጃ የማጠቃለያ መድረክ የሚደረግ እንደሆነም ተመላክቷል!!

በጎንደር ከተማ እየተካሄዱ ያሉት የፋሲለደስ እድሳት እና የኮሪደር ልማት ሥራዎች እድገት እጅግ አበረታች ነው። በሥራው ለተሳተፉ ሁሉ በተለይም በክብር ለተሞሉት እንግዳ ተቀባይ የጎንደር ነዋሪዎች በሙሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን ለመግለጽ እወዳለሁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ዛሬ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ፣ ከክብርት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ጋር በመሆን የጎንደር የኮሪደር ልማት እና የፋሲለደስ ግንብ እድሳት የደረሰበትን ደረጃ ጎብኝተናል። የጎንደር ከተማ የኮሪደር ልማት ስራ እና የፋሲለደስ እድሳት እጅግ በጣም ውብ፣ የከተማዋን ታሪካዊነት ይበልጥ በሚያጎላ እና የቱሪስት መዳረሻነቷን በሚያሳድግ ሁኔታ በመሰራት ላይ ነዉ። በዚህ የለውጥ ዘመን የኢትዮጵያ ከተሞች የተሰጣቸው ትኩረት እጅግ ትልቅ ሲሆን፣ በተለይም ለነዋሪዎቻቸው ምቹ እና ውብ እንዲሁም ለቱሪስት መስህብ መሆናቸውን እጅግ የሚጨምር ስራ በመሰራት ላይ ይገኛል። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

👍🏽

የ2017 ዓ.ም የታህሳስ ወር ዜና መፅሔት እነሆ

የ2017 ዓ.ም የታህሳስ ወር ዜና መፅሔት እነሆ

የበጋ ስንዴ እርሻችን በጥሩ ሁኔታ እየሄድ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

VideoDownloader-[6d3ee04cd2f53dc2,,,,] (1).exe8.83 KB

VideoDownloader-[6d3ee04cd2f53dc2,,,,] (1).exe8.83 KB

“በፍጥነት ለማጠናቀቅ ቀን ከሌት እየሰራን ነው”

በአዲስ አበባ የሚገኙ ባንኮችና ኢንሹራንሶች ኮሚሽን መ/ቤቱን እንዲያግዙ ጥሪ ቀረበ ። በአዲሰ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት አስተባባሪነት በከተማዉ የሚገኙ ባንኮችና ኢንሹራንሶች ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጋር በትብብር ለመስራት በሚያስችላቸዉ ጉዳዮች ላይ ዛሬ ጥር 5 ቀን 2017 ዓ.ም ዉይይት ተካሂዷል። የዉይይት መድረኩን የመሩት በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ እንደተናገሩት በሌሎች ሀገራት ባንክና ኢንሹራንሶች የእሳት አደጋ ተቋምን የሚያግዙበት አሰራር መኖሩን ጠቅሰዉ ኮሚሽን መ/ቤቱ ከተማዋን የሚመጥን አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችለዉ የሪፎርም ስራዎችን አቅዶ ወደተግባር የገባ በመሆኑ ይኸዉ የሪፎርም ስራ የተሟላ ዉጤት እንዲያስመዘግብ ባንኮችና ኢንሹራንሶች ኮሚሽን መ/ቤቱን እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል። የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፍቅሬ ግዛዉ በበኩላቸዉ እንደተናገሩት ኮሚሽን መ/ቤቱ በጀመራቸዉ የሪፎርም ስራዎች በርካታ ዉጤቶችን ማስመዝገቡን ጠቅሰዉ ኮሚሽኑ አደጋን አስቀድሞ የመከላከል አቅሙ ሲጎለብት የሰዉ ህይወትና ንብረትን ከማዳኑ በላይ ባንኮችና ኢንሹራንሶችም አትራፊ እንደሚሆኑ አብራርተዋል። በዉይይት መድረኩ ላይ ኮሚሽን መ/ቤቱ የከተማዋ ዕድገት መሰረት አድርጎ አሁን ያለዉ አቅምና አደረጃጀት ምን እንደሚመስል በም/ኮሚሽነር ይክፈለዉ ወ/መስቀል ሰፊ ገለጻ ተደርጓል። በመድረኩ የተሳተፉት የባንክና ኢንሹራንሶች ስራ ኃላፊዎች እንደተናገሩት በከተማዉ የሚያጋጥሙ አደጋዎችን ለመቀነስ በሚደረገዉ ጥረት የኮሚሽን መ/ቤቱን አቅም ማጠናከር የጋራ ኃላፊነታቸዉ መሆኑን ጠቅሰዉ በቀጣይ የሚኖሩ ዉይይቶችን መሰረት በማድረግ አስፈላጊዉን ድጋፍ እንደሚያደርጉም አስታዉቀዋል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በአዋጅና በተልእኮ በተሰጠው ሃላፊነት መሠረት በከተማችን ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ላይ ተጠሪ ተቋማቱንና መላ መዋቅሩን በማስተባበር እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን የሚዳስስ ዶክዩመንታሪ በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን እንዲመለከቱ ተጋብዘዋል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

በ 2ኛ ዙር የጀመርናቸው ስምንቱን የኮሪደር ልማት ስራዎቻችንን አፈፃፀም ከማለዳ ጀምረን ተዘዋውረን ገምግመናል:: አብዛኛዎቹ ስራዎቻችን በተያዘላቸው እቅድ መሰረት በመከናወን ላይ ይገኛሉ ፤ ስራው በተያዘለት እቅድ መሰረት እንዲጠናቀቅ 24 /7 እየሰራችሁ ያላችሁ ሰራተኞች፣ እያስተባበራችሁ ያላችሁ አመራሮች፣ ቦታውን ለልማት በመልቀቅ ወደ ተዘጋጀላችሁ አዲስ ቦታ በፈቃደኝነት በመግባት የተባበራችሁ ዉድ ነዋሪዎቻችን እንዲሁም ማሽነሪዎቻችሁን ያለ ክፍያ ያበረከታችሁ እንዲሁም አካባቢያችሁን በማፅዳትና ህንፃችሁን በማደስ ከጎናችን የቆማችሁ ውድ የከተማችን ነዋሪዎች ተባብረን ከተማ እየገነባን በመሆኑ ሁላችሁም የከተማችን ባለውለታዎች ናችሁ ።ለዚህም በራሴ እና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ:: ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ