fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید 👈

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
ለሀገራቸው እና ህዝባቸው በትልቅ ብቃት ፣በታማኝነት፣ በሀቀኝነት ፣ በላቀ ስብዕና ያገለገሉ የሀገር ባለውለታ የሆኑትን የአቶ ቡልቻ ደመቅሳን የአስክሬን ሽኝት ስነ-ስርዓት ፈፅመናል:: ፈጣሪ ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ሁሉ መፅናናትን እንዲሰጥ እመኛለሁ! ፈጣሪ ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑርልን ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በይፋዊ ጉብኝታቸው ወቅት የሁለትዮሽ ግንኙነቶቻችንን ለማጠናከር ውጤታማ ውይይቶች ካደረግን በኋላ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድን ሸኝቻለው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ ር አቢይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድን በብሔራዊ ቤተመንግሥት ያደረጉላቸው አቅባበል - በምስል።

ከመገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ እስከ አዲሱ ቤተ መንግስት የከተማዋን ከፍታ ለማረጋገጥ በጥራትና በፍጥነት እየተገነባ በሚገኘውን የመንገድ ኮሪደር ልማት ተረፈ ምርት የማንሳትና የጽዳት ንቅናቄ ተካሄደ። በጽዳት ንቅናቄው ላይ የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ምርክነህ ያዕቆብ፣ የክፍለ ከተማው የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ከበደ እና የክፍለ ከተማው ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከፍያለው ተሾመ እንዲሁም የወረዳ አመራሮች፣ የክፍለ ከተማና ወረዳ የተጠሪ ተቋማት ባለሙያዎች፣ የመንገድ ፅዳት ሰራተኞች፣ የደንብ ኦፊሰሮችና ነዋሪዎች ተሳትፈዋል። በንቅናቄው የግንባታ ተረፈ ምርቶችን የማንሳትና የፅዳት ሥራ ተከናውኗል። በጽዳትና በግንባታ ተረፈ ምርት ማንሳት ንቅናቄው ላይ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ምርክነህ ያዕቆብ እንደገለፁት ፅዳት የሁልጊዜ ተግባር ሊሆን እንደሚገባና ከተማችን አዲስ አበባን ፅዱና ውብ በማድረግ ተወዳዳሪ ዓለም አቀፍ ከተማ ለማድረግ የሁሉም ህብረተሰብ ድርሻ የጎላ መሆኑን አስገንዝበዋል። አክለውም ከተማችን አዲስ አበባን ፅዱና ውብ በማድረግ ተወዳዳሪ ዓለም አቀፍ ከተማ ለማድረግ የሁሉም ህብረተሰብ ድርሻ የጎላ እንደሆነም አመልክተዋል። የክፍለ ከተማው ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከፍያለው ተሾመ በበኩላቸው የከተማዋን ከፍታ የሚያረጋግጠውን የኮሪደር ልማት የግንባታ ተረፈ ምርት ማንሳት እና ማጽዳት የዕለት ተዕለት ተግባር መሆኑንና በቀጣይም ልማቱ እስኪጠናቀቅ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። Yeka Communication-የካ ኮሙኒኬሽን ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የኢትዮጵያ መንግስት እና የሶማሊያ መንግስት ያወጡት የጋራ የአቋም መግለጫ

የሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ እንኳን ወደ ኢትዮዽያ መጡ እላለሁ።" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ኤጀንሲው የፀሃይ ብርሃንን በመጠቀም በሚመነጭ የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት እንዳይቋረጥ የሚያስችል አማራጭ ቴክኖሎጂ በወረዳ ጽ/ቤቶች በሙከራ ማስጀመሩን አስታወቀ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ እያደረገ ባለው የተቋም ግንባታ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ወደ ቴክኖሎጂ ማሸጋገሩ ይታወሳል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ በሚገጥምበት ወቅት አገልግሎት ላይ ጫና እየፈጠረ መሆኑ በህብረተሰቡ በስፋት የሚነሳ ቅሬታ ሲሆን ምንም እንኳን 2/3 በሚሆኑት የተቋሙ የወረዳ ጽ/ቤቶች የጄኔሬተር አቅርቦት ቢኖርም ከአዋጭነት እና ከቀጣይነት አኳያ ክፍተት ያለው መሆኑ ታይቷል። ይህንኑ መነሻ በማድረግ አማራጭ ታዳሽ የፀሃይ ብርሃን ሃይል ተጠቅሞ አገልግሎት በወረዳዎች እንዳይቋረጥ ማድረግ የሚያስችል ሙከራ ከፍተኛ የተገልጋይ ፍሰት ካለባቸው ወረዳዎች አንዱ በሆነው የቦሌ ወረዳ 12 ጽ/ቤት ዛሬ ተግባራዊ ተደርጓል። በድምሩ 18 ፓናል ገጠማ የተደረገ ሲሆን እስከ 20ሺ KW ሃይል ማመንጨት የሚያስችል አቅም ተፈጥሮለታል። ኤጀንሲው የፀሃይ ሃይልን በመጠቀም አገልግሎት ሳይቋረጥ መስጠት የሚያስችለውን የሶላር ቴክኖሎጂ ከCorner Stone Investment Group የሚባል የአሜሪካ ድርጅት በድጋፍ ያገኘ ሲሆን የBIZET PLC ስራውን በማስተባበር የሙከራ ትገበራው ዛሬ ተከናውኗል። በዕለቱ መርሃ-ግብር የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ፣ የቦሌ ክ/ከተማ ዋና ስራ-አስፈፃሚ ወ/ሮ አለምፀሃይ ሽፈራው እንዲሁም የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ የማነ ደሳለኝ ተገኝተዋል። አቶ ዮናስ በዕለቱ ባስተላለፉት መልዕክት ኤጀንሲው በህዝብ ቅሬታ የሚቀርብባቸውን ችግሮች ለይቶ አንድም ሳይቀር ለመፍታት ጥረት እንደሚያደርግ ገልፀው በተያዘው በጀት ዓመት የሃይል አማራጭ ስራውን በሁሉም ክ/ከተሞች የተመረጡ ወረዳዎች ለማዳረስ ጥረት እንደሚደረግ ጠቁመዋል። ሃላፊው አክለውም ከተማችን ታዳሽ ሃይልን የመጠቀም አማራጮችን በመከተል አዲስ አባባን ስማርት የማድረግ ውጥኗን ማሳካት የሚቻለው በእንዲህ ዓይነት አማራጮች እንደሆነ አምስተዋል። ለበለጠ መረጃ በነፃ መስመር 7533 ይደውሉ ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

በ29ኛው ዙር ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ 874 መደበኛ የፖሊስ አባላትን አስመርቀን ወደ ስራ አስገብተናል። ከተማችንን ከማንኛዉም የፀጥታ ስጋት ነጻ ለማድረግ በብቁ የሰው ሃይል፣ በሎጂስቲክ እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለመገንባት የተጀመረዉ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ዛሬ የተመረቃችሁ የ29ኛ ዙር መደበኛ የፖሊስ አባላት ወደ ስራ ስትገቡ ከህዝባችሁ ጋር በቅርበት በመስራት ወንጀለኞችን በጀግንነት የምትመክቱ እና ህዝቡን በሰብዓዊነት የምታገለግሉ በመሆን የተሰጣችሁን ኃላፊነት በብቃት እንድትወጡ፣ ህዝባችሁን በታማኝነት እንድታገለግሉ ለማሳሰብ እወዳለሁ። "በጀግንነት መጠበቅ፣ በሰብዓዊነት ማገልገል" ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ