fa
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
2017 የግንቦት ወር ዜና መጽሄት እነሆ.pdf3.87 MB

የረዳን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን ! ዛሬ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር በመሆን ከአንበሳ ጋራዥ ጃክሮስ እና የጎሮ አደባባይ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ጎብኝተን ለህዝብ አገልግሎት ክፍት አድርገናቸዋል ። ይህ መስመር የትራፊክ ፍሰቱ መጨናነቅ የሚታይበት እና ለአደጋ የተጋለጠ ነበር አስቸጋሪ መስመር ነበር። አሁን ደረጃውን የጠበቀ አስፖልት ፣ የእግርኛ መንገድ እና የብስክሌት መስመር ፣ የህፃናት መጫዎቻ ፤ የመኪና ፓርኪንግ ፣ታክሲ እና አዉቶቢስ መጫኛና ማዉረጃ ፣የህዝብ ማረፊያ ክፍት ቦታዎች፣የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች እና የንግድ ቤቶች ከመንገድ ዳር ያላቸው ርቀት ታሳቢ ተደርጎ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚነት ታሳቢ ያደረገ አካታች መሰረተ ልማት ያካተቱ ናቸዉ። ከጎሮ ዋና መስመር ለሚመጡ ተሸከርካሪዎች እና ከቦሌ አለም አቀፍ የበረራ ጣቢያ በኩል የሚመጡ ተሸከርካሪዎችን በማስተንፈስ የከተማዋን የትራፊክ መጨናነቅ መፍትሔ ይሰጣል። በተጨማሪም ሰፊ የንግድ የስራዎች እንዲፈጠሩ በማስቻል በሺዎች ለሚቆጠሩ ነዋሪዎች ቋሚ የስራ እድል የፈጠረ ነዉ። ሁሌም ህዝብን መሠረት ያደረገ ልማት መስራታችን ብቻ ሳይሆን ለትውልዱ የምናስረክባት አዲስ አበባ ንፁህ ፣ ፅዱ፣ ውብ አበባ እና ለመኖር ምቹ ለጐብኝዎች ተመራጭ እስከምትሆን ሌት ተቀን መትጋታችንን አጠናክረና እንቀጥላለን። በኮሪደር ልማቱ መስመር የተካተቱ ስራዎች ፦ 4ኪሎ ሜትር የሳይክል መንገድ ፤ ከ8 ኪሎ ሜትር በላይ ደረጀውን የጠበቀ የእግረኛ መንገድ ፤ 3 የመኪና ማቆሚያ ፓርኪንግ ቦታዎች ፣ የህፃናት መጫዎቻዎች ፣ 7 ፕላዛዎች ፣ 6 የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች ፣ ፋውንቴኖች 13 ታክሲ መጫኛና ማዉረጃ ፣ እና 872 ሱቆች ይገኙበታል :: ዉድ የከተማችን ነዋሪዎች ይህን የልማት ስራ አጠናቀን እነሆ ስንላችሁ የናንተ መሆኑን በመረዳት እየጠበቃችሁት እንድትጠቀሙበት እያልኩ ለነበራችሁ ድጋፍ ፣ ላደረጋችሁት ትብብር እና ተሳትፎ ምስጋናዬን በከተማ አስተዳደሩ ስም ላቀርብ እወዳለሁ ። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአንበሳ ጋራዥ-ጃክሮስ-ጎሮ አደባባይ የኮሪደር ሥራ ከፍተኛ የፍሰት ጭንቅንቅ የነበረበትን ከባቢ ቀይሮታል። የእግረኛ መንገዶች፣ የብስክሌት መንገዶች ፣ የመኪና ማቆሚያዎች፣ የሕፃናት መጫወቻዎች፣ ሱቆች፣ የሕዝብ ማረፊያ ፕላዛዎች፣ የሕዝብ መጸዳጃዎች፣ የተለዩ የታክሲ እና የአውቶቡስ ቤዮች መሠራት አካባቢውን የበለጠ ተደራሽ፣ አካታች እና ለመኖር ምቹ አድርጎ እንደገና የገነባ ተግባር ነው። የከተማም ሆነ የገጠር ኮሪደር ሥራዎች የከበረ የሰውልጅ የአኗኗር ዘይቤን ያስስተዋወቀ እና ፍትኃዊ የሕዝባዊ ስፍራዎች አጠቃቀምን በመፍጠርም ማኅበረሰቦችን ከፍ ያደረገ ነው። በተለይም በቅርቡ የጀመርናቸው የገጠር ኮሪደር ሥራዎች የገጠር የመኖሪያ ከባቢዎችን እንደገና በማደስ የነዋሪዎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ያለሙ ናቸው። የኮሪደር ልማት ሥራ ወደ ከተማው ጫፎች እንዲደርስ ሀብት በማሰባሰብ የከወኑትን የአዲስ አበባ አስተዳደር እና የክፍለ ከተማ አመራሮችን ከልብ ለማመስገን እፈልጋለሁ። በከተማችን የሚገኙ ሌሎች ክፍለ ከተሞች እና በመላው ሀገራችን የሚገኙ ከተሞችም የከተማ አኗኗርን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ በአዲስ ምናብ እና የሀሳብ ውቅር ለመሥራት በተነሳንበት በአሁኑ ወቅት ዜጋ ተኮር የሆኑ ተግባራትን ቅድሚያ ሰጥተው መሥራታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቀርባለሁ። The development of the Anbesa Garage - Jukrose - Goro Square corridor has brought transformative changes to a once congested area. The addition of walkways, parking facilities, children’s playgrounds, shops, public plazas, public toilets, and designated taxi and bus bays has revitalized the neighborhood, making it more accessible, inclusive, and livable for all. Corridor development projects across both urban and rural settings continue to introduce dignified, equitable public spaces that uplift communities. In particular, our recent rural corridor initiatives aim to rejuvenate rural areas and improve the quality of life for their residents. I extend my sincere appreciation to the Addis Ababa City Administration and the subcities that have mobilized resources to expand the corridor initiative into the city’s peripheral areas. I encourage other subcities and cities across the country to keep prioritizing citizen-centered approaches as we reimagine and reconfigure urban life for the better.

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋር በመሆን የተጠናቀቀውን የአንበሳ ጋራዥ-ጃክሮስ-ጎሮ አደባባይ የኮሪደር ልማት ሥራ ዛሬ ተመልክተዋል። የኮሪደር ልማት ሥራው 8 ኪሎሜትር የእግረኛ መንገድ፣ 4 ኪሎሜትር የብስክሌት መጋለቢያ፣ የሕዝብ መጸዳጃዎች፣ ደረጃቸውን የጠበቁ ሱቆች፣ በመላው ከተማዋ እንደተገነቡት ያሉ የተለያዩ ዘመናዊ የሕዝብ መገልገያዎች ግንባታን አካትቷል። ይኽ ለውጥ በከፍተኛ የፍሰት መጨናነቅ በሚታወቀው ከባቢ በእጅጉ ሲፈለግ የነበረውን የፍሰት መሻሻል እና የኑሮ ደረጃ ከፍታ የሰጠ ሆኗል። Prime Minister Abiy Ahmed, together with Addis Ababa Mayor Adanech Abebe, reviewed the completed Anbesa Garage - Jukrose - Goro Square corridor development earlier today. The developed corridor features an 8-kilometer pedestrian walkway, a 4-kilometer cycle lane, public toilets, standardized shops, and a range of modern amenities consistent with other corridor projects across the city. This transformation brings much-needed structure and relief to an area previously known for frequent congestion. #PMOEthiopia

ዛሬ ሁሉንም ክፍለ ከተማዎች ወክለው ከመጡ የአዲስ አበባ ሴቶች ጋር “የሴቶች ሚና ለሁለንተናዊ ብልፅግና “ በሚል መሪ ቃል በከተማ አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተናል። በአዲስ አበባ የሴቶችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን አቅድን በመስራት ዉጤቶች ተመዝግበዋል። ለአብነትም በተለያዩ ኢንቨስትመንቶች፣ በንግድና አገልግሎት ዘርፎች መሰማራት እንዲችሉ፤ ጀማሪዎችም በእንጀራና ዳቦ ፋብሪካዎች፣ በአነስተኛና ጥቃቅን፣ በአረንጓዴ ልማትና ከተማ ዉበት፣ በመጋቢ እናትነት፣ በሴፍቲኔት ፕሮግራም ከተረጂነት ወደ አምራችነት እንዲሸጋገሩ በማስቻል በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች የስራ እድልና ገቢ እንዲያገኙ እድል ተፈጥሮላቸዉ ኑሯዉን እያሻሉ ለሌሎችም የስራ እድል በመፍጠር ላይ ይገኛሉ። በየጎዳናዉ ለብዙ ማህበራዊ ስብራት ተጋልጠው የነበሩ እህቶቻችን "ለነገዋ" የሴቶች ተሃድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ውስጥ በመገንባት የስነልቦና ህክምና እና የሞያ ስልጠና ወስደው ተጨባጭ እና ምሳሌ በሚሆኑ ስራዎች ላይ ተሰማርተዋል። ከግል ስራቸዉ በተጨማሪም በከተማችን ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ በሰላም ሰራዊት ስር በመደራጀት እና በሎሎች በርካታ ስራዎቻችን ዉስጥ የጐላ ተሳትፎ በማድረግ ለዉጦች እንዲመዘገቡ አድርገዋል ። በየዓመቱ ማገባደጃ ስናደርግ እንደቆየነው ሴቶችን እያወያየን ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ሀሳባቸዉን እና ጥያቄዎቻቸዉን በማዳመጥ ለሚቀጥለዉ በጀት ዓመት እቅድ ግብዓት በመዉሰድ የኢኮኖሚ ጫናዎችን ለማቃለል፣ የማህበራዊ ችግሮችን ለመቅረፍ እና ሰላማችንን ዘላቂ በማድረግ ለላቀ ወጤት በጋራ እንደምንተጋ ተግባብተናል። ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

በስልጠና የተገኘን ዕዉቀትና መረጃ በራስ አቅም በማሳደግ ብቁ አመራርና ባለሙያ መሆን እንደሚገባ ተገለጸ። በአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት አስተባባሪት ለእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አመራርና ባለሙያዎች በልዩ ልዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለአምስት ቀናት ሲሰጥ የቆየዉ ስልጠና ዛሬ ሰኔ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ተጠናቋል። በስልጠናዉ ማጠቃለያ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አህመድ መሀመድ እንደተናገሩት ስልጠናዉ ኮሚሽን መ/ቤቱ የሚሰጣቸዉን አገልግሎቶች በተሻለ አቅምና አሰራር ለመፈጸም ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና እንደሆነ አስታዉሰዉ በስልጠናዉ የተሳተፉ አመራርና ባለሙያዎች ከስልጠናዉ ያገኙትን እዉቀትና መረጃ በማሳደግ ሙያዉ የሚጠይቀዉን የተሟላ አቅም እንዲፈጥሩ አሳስበዋል። ኮሚሽነሩ አያይዘዉም ስልጠናዉን በማስተባበርና ለስልጠናዉ የሚጠይቀዉን ወጪ በመሸፈን ከፍተኛ አስተዋጾኦ ላደረገዉ የከተማዉ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት እና እንደዚሁም በዘርፉ ልምድ ያላቸዉን አሰልጣኞችን በመመደብ ድጋፍ ላደረጉት ለፌደራል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ምስጋና አቅርበዋል። የስልጠናዉ ተሳታፊዎች በበኩላቸዉ በአምስቱ ቀናት የስልጠና ቆይታቸዉ የወሰዱት ሰልጠና ለቀጣይ ስራዎቻቸዉ ከፍተኛ ዕገዛ እንደሚያደርግላቸዉ ጠቅሰዉ ቀደም ሲል የሚሰሩበትን የተለምዶ አሰራር በማስቀረት ተግባሮቻቸዉን በዘመናዊና በተቀላጠፈ መንገድ መፈጸም እንደሚያስችላቸዉ ተናግረዋል። ሰልጣኞች በስልጠና ቆይታቸዉ ስለሎጂስቲክና የቁጥጥር ምንነት፣ ስለአደጋ ዝግጁነትና የሀብት አሰባሰብ ፣ ስለ አደጋ ተጎጂዎች ኘሮጀክት ዝግጅት ፣ ለአደጋ ተጎጂዎች የስነ ልቦና ድጋፍ አሰጣጥ፣ ስለድህረ አደጋ አገልግሎት፣ GPS/Geographical positing system and Remo sensing፣ ስለ SPSS እና በሌሎች ተያያዥ ርዕሶች ላይ ስልጠናዉ እንደተጣቸዉ ተመላክቷል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

በመዲናችን አዲስ አበባ ከፅዳት ጋር ተያይዞ ለነዋሪዎች የሚሰጡ የቤት ለቤት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በዘመናዊ ቴክኖሎጅ የተደገፈ ፈጣን፣ተደራሽ እና ቀልጣፋ የመረጃ ልውውጥ አገልግሎት እንዲኖር ለማስቻል በትናንትናው እለት ግንቦት 30/2017 ተመርቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረውን መተግበርያ ሲስተም አስመልክቶ በአዲስ ሚዲያ የተዘጋጀውን ዘገባ ይመልከቱ👉👉 ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 በፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት የተዘጋጁ 41 ሞዴል ብሎኮች አስመርቀው ለወረዳው ነዋሪዎች አስረክበዋል። በምረቃና በርክክብ መረሀ ግብሩ ላይ የከተማና የክፍለ ከተማ እንዲሁም የወረዳ አስተዳደሩ አመራሮች ተገኝተዋል። በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት መልእክት መዲናችን አዲስ አበባ በጽዳቷ፣ ሳቢ እና ውብ እየሆነች ዘመናዊነቷን እና ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነቷን እያጎለበተች ትገኛለች ሲሉ ተናግረዋል። በከተማችን ጽዳት ላይ እምርታዊ ለውጥ ማምጣት የተቻለው ሌት ከቀን በሚተጉ አመራሮች፣ በነዋሪዎቿ እና በባለድርሻ አካላት ያላሰለሰ ጥረት ነው ሲሉ ተናግረዋል። አክለውም የከተማችን ፅዳት በዘላቂነት እንዲጠበቅ እና ሁሉም ነዋሪ ፅዳትን ባህል እስኪያደርግ ድረስ ብሎኮችን፣ ቀጠናዎችን እና፣ ወረዳዎችን ንፁህ በማድረግ የተጀመረውን የከተማችንን ፅዳት የማስጠበቅ ስራ አጋዥ የመሆን ሃላፊነታችንን ሁላችንም በብቃት መወጣት ይኖርብናል ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ኢንጅነር ወንድሙ በዚሁ ወቅት የቤት ለቤት እና የብሎኮች የመስክ ምልከታ በማድረግ 41ዱን ብሎኮች ሞዴልነታቸውን በማረጋገጥ ለህዝብ አስረክበዋል ። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ለመዲናችን ነዋሪዎች በየወረዳዎች እየተሰጠ ያለውን የሲቪል ምዝገባ እና ነዋሪዎች አገልግሎት አሰጣጥ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የመስክ ምልከታ አደረጉ። በአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት አዘጋጅነት በተለያዩ ክፍለከተሞች እና ወረዳዎች ላይ በተካሄደው የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ስራዎች የመስክ ምልከታ እና ጉብኝት ላይ ከሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ጋር ተያይዞ ለከተማችን ነዋሪዎች እየተሰጠ ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በተለይም በነፋስ ስልክ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 11 እና በቦሌ ክ/ ከተማ ወረዳ 12 ፅ/ቤት በአካል ተገኝተው ነዋሪዎች እያገኙት ስላለው አገልግሎት ሃሳብ እና አስተያዬታቸውን ተቀብለዋቸዋል። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ወቅት በየደረጃው ካለው የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አመራሮች ጋር ባካሄዱት በዚሁ የመስክ ምልከታ ላይ በየወረዳዎች እየተሰጠ ያለው አገልግሎት አሰጣጥ እና የስራ በህል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተቀየረ ያለ እና የህዝቡን የአገልግሎት እርካታ የጨመረ፣ በቴክኖሎጅ የተደገፈ፣ በዚህም ብልሹ አሰራርን ለመከላከል እየተደረገ ያለው ጥረትም አበረታች መሆኑን ተናግረዋል። አክለውም በተመለከቷቸው ወረዳዎች ዜጎች የሁነት አገልግሎቶችን ምቹ በሆነ ሰፍራ በዲጂታል ታግዘው እያገኙ መሆኑ በመዲናችን እየተተገበረ የሚገኘው የዘመነ የስማርትሲቲ አገልግሎት በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ትግበራ ተጨባጭ መገለጫ መሆኑን አመልክተዋል። ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በመስክ ምልከታቸው ወቅት በነፋስ ስልከ/ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ፅ/ ቤት በተዘጋጀው የሙሽራ ክፍል ጋብቻቸውን እየፈፅሙ ላገኟቸው ጥንዶች "የእንኳን ደስ ያላችሁ" የመልካም ምኞት መልእክታቸውን በማስተላለፍ የጋብቻ ሰርተፊኬታቸውንም አበርክተውላቸዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager