1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
"ሀገር እና ጥበብ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት" በሚል መሪ ሀሳብ በተዘጋጀው ከተማ አቀፍ መድረክ ላይ ተገኝተን ከኪነጥበብ ባለሞያዎች ጋር ተወያይተናል።
ኪነጥበብ የሀገርና የትውልድ ግንባታ አምባ መሆኑን በመገንዘብ በከተማችን የምናከናውናቸው የለውጥ ስራዎች የኪነጥበብ ባለሞያዎችን ተሳትፎ ያረጋግጥ ዘንድ በትብብር ለመስራት የተዘጋጀ መድረክ ነዉ።
በዛሬው ዕለትም ከኪነጥበቡ ማህበረሰቡ ጋር ባደረግነው ውይይት በጥንካሬም ሆነ በክፍተት ባነሷቸዉን ሀሳቦች እና ጥያቄውች ላይ የተወያየን ሲሆን በቀጣይ በከተማችን ሁለንተናዊ ለውጦች ዙሪያ እጅ ለእጅ ተያይዘን ለመስራት ተግባብተናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ዛሬ ሁሉንም ክፍለ ከተማዎች ወክለው ከመጡ የአዲስ አበባ ሴቶች ጋር “የሴቶች ሚና ለሁለንተናዊ ብልፅግና “ በሚል መሪ ቃል በከተማ አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተናል።
በአዲስ አበባ የሴቶችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን አቅድን በመስራት ዉጤቶች ተመዝግበዋል።
ለአብነትም በተለያዩ ኢንቨስትመንቶች፣ በንግድና አገልግሎት ዘርፎች መሰማራት እንዲችሉ፤ ጀማሪዎችም በእንጀራና ዳቦ ፋብሪካዎች፣ በአነስተኛና ጥቃቅን፣ በአረንጓዴ ልማትና ከተማ ዉበት፣ በመጋቢ እናትነት፣ በሴፍቲኔት ፕሮግራም ከተረጂነት ወደ አምራችነት እንዲሸጋገሩ በማስቻል በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች የስራ እድልና ገቢ እንዲያገኙ እድል ተፈጥሮላቸዉ ኑሯዉን እያሻሉ ለሌሎችም የስራ እድል በመፍጠር ላይ ይገኛሉ።
በየጎዳናዉ ለብዙ ማህበራዊ ስብራት ተጋልጠው የነበሩ እህቶቻችን "ለነገዋ" የሴቶች ተሃድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ውስጥ በመገንባት የስነልቦና ህክምና እና የሞያ ስልጠና ወስደው ተጨባጭ እና ምሳሌ በሚሆኑ ስራዎች ላይ ተሰማርተዋል።
ከግል ስራቸዉ በተጨማሪም በከተማችን ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ በሰላም ሰራዊት ስር በመደራጀት እና በሎሎች በርካታ ስራዎቻችን ዉስጥ የጐላ ተሳትፎ በማድረግ ለዉጦች እንዲመዘገቡ አድርገዋል ።
በየዓመቱ ማገባደጃ ስናደርግ እንደቆየነው ሴቶችን እያወያየን ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ሀሳባቸዉን እና ጥያቄዎቻቸዉን በማዳመጥ ለሚቀጥለዉ በጀት ዓመት እቅድ ግብዓት በመዉሰድ የኢኮኖሚ ጫናዎችን ለማቃለል፣ የማህበራዊ ችግሮችን ለመቅረፍ እና ሰላማችንን ዘላቂ በማድረግ ለላቀ ወጤት በጋራ እንደምንተጋ ተግባብተናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በመዲናችን አዲስ አበባ ከፅዳት ጋር ተያይዞ ለነዋሪዎች የሚሰጡ የቤት ለቤት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በዘመናዊ ቴክኖሎጅ የተደገፈ ፈጣን፣ተደራሽ እና ቀልጣፋ የመረጃ ልውውጥ አገልግሎት እንዲኖር ለማስቻል በትናንትናው እለት ግንቦት 30/2017 ተመርቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረውን መተግበርያ ሲስተም አስመልክቶ በአዲስ ሚዲያ የተዘጋጀውን ዘገባ ይመልከቱ👉👉
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ፣የአቃቂ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና እና የከተማ እና ክፍለ ከተማ አመራሮች የተሳተፉበት በአቃቂ ክፍለ ከተማ በዛሬው እለት የተካሄደው ሳምንታዊ ከተማ አቀፍ የፅዳት ንቅናቄ፣ የመልሶ መጠቀም ኤግዚቪሽን እና የቤት ለቤት የፅዳት ግንዛቤ መተግበሪያ ሲስተም ምረቃ ስነስርአት በፎቶ ሲቃኝ:-
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ72ኛው የዓለም ቁንጅና ውድድር ላይ በማሸነፍ የኢትዮጵያ ስም በዓለም መድረክ ከፍ ብሎ እንዲጠራ ላደረገችው የዓለም ቁንጅና አሸናፊ (Miss World) ሀሴት ደረጀ ሽልማት አበረከቱ።
ከንቲባዋ ይህንን ሽልማት ያበረከቱት "ሀገር እና ጥበብ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት" በሚል መሪ ሀሳብ በተዘጋጀው ከተማ አቀፍ የኪነጥበብ ባለሞያዎች ውይይት መድረክ ላይ ስሆን፣ ኢትዮጵያ በሁሉም መስክ በዓለም መድረክ ላይ አሸናፊ መሆን እንደምትችል የሀሴት ደረጀ ድል ምስክር ነው ብለዋል።
ሀሴት ዉጫዊ ብቻ ሳይሆን በርካታ ዉስጣዊ ቁንጅና እና ብቃት ስላሳየችን ለብዙ ወጣቶች እና ልጆች የእንችላለን ምሳሌት ነች ብለዋል።
በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ቱሪዝም እና ባህል አምባደር ሆና እድትሰራ ተልእኮ ሰጥተዋታል።
የዓለም ቁንጅና አሸናፊ (Miss World) ሀሴት ደረጀም ለተደረገላት ሽልማት እና ተልእኮ አመስግናለች።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዛሬው እለት በየክፍለ ከተሞች እየተከናወኑ ያሉ ሞዴል የማዘጋጃ ቤታዊ ስራዎች ላይ ከከተማና እና የክፍለ ከተማ አመራሮች ጋር በመሆን የመስክ ምልከታና ጉብኝት አካሂደዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ ቤት ባዘጋጀው በዚህ የመስክ ምልከታ በ4 ክፍለ ከተሞች ባሉ 7 ወረዳዎች ላይ የሞዴል ፅዳት ሥራዎች፣የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪዎች አገልግሎት እና የቅድመ አደጋ መከላከል ስራዎች በመስክ ተጎብኝተዋል።
በዚሁ ጉብኝት ላይ በአቃቂ/ቃሊቲ፣ በነፋስ ስልክ/ላፍቶ፣ በቦሌ እና በየካ ክፍለ ከተማ እየተሰጡ ያሉ ሞዴል የማዘጋጃ ቤታዊ ስራዎች ተጎብኝተዋል።
በዛሬው እለት የዚሁ የመስክ ጉብኝት አካል የሆነ በነፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የሞዴል የፅዳት ብሎኮች እና የእሳት አደጋና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት ህንፃ ግንባታ ያለበት ደረጃ ተጎበኝቷል።
በጉብኝቱ የከተማ ስራ አስኪያጅ አመራሮች፣ የተጠራ ተቋማት አመራሮች እና የ11ዱም ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጆች እንዲሁም የነፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ድላየው ታምሬን ጨምሮ ሌሎች የክፍለ ከተማው አመራሮች ተገኝተዋል።
በጉብኝቱ ወቅት በክፍለ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት በወረዳ ለቡ እና በወረዳ 10 ሞዴል የተደረጉ ብሎኮችን እንዲሁም ለእሳት አደጋ እና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ፅ/ቤትነት የተገነባ የህንፃ ግንባታ ያለበት ደረጃ ተጎብኝቷል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት ሞዴል የተደረጉ ብሎኮች አከባቢውን ፅዱና ምቹ ከማድረግ ባሻገር ለሌሎችም ትምህርት የሚሰጡ አብነታዊ ስራዎች ናቸው ብለዋል።
በክፍለ ከተማው የቅድመ አደጋ መከላከልን ተግባርን ለማጠናከር የተገነባው ህንፃ አደጋን አስቀድሞ ለመከላከል ከተከሰተም ፈጣን ምላሽ ሰጪነትን ለማጠናከር የሚያግዝ እና ለዘመናዊ ከተማ ወሳኝ የሆነ ተግባር እንደሆነ ገልፀዋል።
የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ድላየሁ ታምሬ በክፍለ ከተማ ደረጃ ሞዴል ብሎኮችን በመፍጠር ረገድ ውጤታማ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው በተለይም የህንፃ ቀለም ስታንደርድ በማስጠበቅና ብሎኮችን ውብ፣ ምቹና አረንጓዴ ከማድረግ አንፃር በርካታ ተግባራት የተከናወኑ መሆኑን ገልፀዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
ብቃት ያለዉ ሲቪል ሰርቫንት ለኢትዮጵያ ብልፅግና መሰረት ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት "ብቃት ያለዉ ሲቪል ሰርቫንት ለኢትዮጵያ ብልጽግና መሠረት ነው "በሚል መሪ ቃል የፅ/ቤቱ አመራሮች የመሩት እና ከባለሙያዎች ጋር የጋራ የዉይይት መድረክ ተካሂዷል። በውይይቱ በመዲናችን እየተሰሩ ያሉ ተግባራትን እንዲሁም ወቅታዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ ሲቪል ሰርቫንቱ ሊኖረው በሚገባ ሚና ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።
በመድረኩ ለውይይቱ መነሻ የሚሆን ሰነድ የቀረበ ሲሆን እንደ ሀገር ባለፉት አመታት ሀገሪቱ በፖለቲካ፣በኢኮኖሚና በዲፕሎማሲው መድረክ ያገኘቻቸው ውጤቶች፣የኮሪደር የልማት ስራዎች፣ በቴክኖሎጂው ዘርፍ የታዩ ለዉጦች፣የአገልግሎት አሰጣጥን ከማሻሻል፣የስራ እድል ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ፣ከተረጅነት ወደ አምራችነት በማሻገር ሂደት የተሰሩ ስራዎች በሰነድ ቀርቧል።
የሪፎርም ስራዎችን ከማከናወን ፣በጤና፣በትምህርት ዘርፍ የተሰሩ ስራዎች፣የተገለፀ ሲሆን ሲቪል ሰርቫንቱ ከዚህ ጋር ተያይዞ ሊኖረው የሚገባ ሚናም ተመላክቷል።
በቢሮ ሀላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ስራ አስኪያጅና የጥናትና ልማት ትግበራ ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ እንደገለፁት ሲቪል ሰርቫንቱ ለመጡት ለዉጦች እና ለሀገራችን ብልጽግና ያለዉ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው አሁን እያካሄድን ያለው ዉይይትም የጋራ መግባባት በመፍጠር የተገኙ ውጤቶችን ለማፅናትና፣ችግሮችን ለመሻገር የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን ለመወሰን የሚጠቅምና አቅም የሚሆን ነዉ ሲሉ ጠቅሰዋል።
አክለዉም ለመጣዉ ለዉጥ የሁሉም ዜጋ ድርሻ የላቀ መሆኑን ገልፀዉ በተለይም የሲቪል ሰርቫንቱ ሚና ከፍተኛ ነዉ ብለዉ በቀጣይ በተለያዩ ምክንያቶች ማነቆ የሆኑብንን ችግሮች ለመፍታት እና ያሉብንን ክፍቶች ሞልተን ለመሻገር ሁሉም እዚህ የሚገኘው ሲቪል ሰርቫንት ሀላፊነቱን በሚገባ በትኩረት በመስራት የተጀመረዉን የብልፅግና ጉዞ መደገፍና ማስቀጠል ይገባል ሲሉ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
