fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید 👈

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
ዛሬ ምሽት ከራሺያ ፌደሬሽን ፌደራል ምክር ቤት አፈጉባዔ ቫለንቲና ማትቬዬንኮ እና ልዑካን ቡድናቸው ጋር ተገናኝተናል። የኢትዮጵያ እና የራሺያ ግንኙነቶችን ለመዳሰስ እና ለመወያየት ጥሩ እድል ፈጥሮልናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ለኮሚሽኑ አመራሮች ሲሰጥ የነበረዉ የግምገማዊ ስልጠና ተጠናቀቀ ። የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በሁሉም ዘርፎች ለሚገኙና ከቡድን መሪ እስከ ከፍተኛ አመራሮች በኮሚሽኑ ስልጠና ማዕከል ሲሰጥ የነበረዉ ግምገማዊ ስልጠና ዛሬ የካቲት 11ቀን 2017 ዓ.ም ተጠናቋል። የስልጠናዉን ማጠቃለያ መድረክ የመሩት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ኮማንደር አህመድ መሀመድ እንደተናገሩት በግምገማዊ ስልጠና ጊዜ አመራሩ የተነሱ የተለዩ ማነቆዎች በፍጥነት በማረም ዉጤታማ አፈጻጸም ማስመዝገብ እንደሚገባ ጠቅሰዉ አፈጻጸሙን የተሳካ እንዲሆን ሁሉም አመራር ሰራተኛ ተደጋግፎ መስራት እንዳለበት አብራርተዋል። አያይዘዉም ተልዕኮን በመፈጸም ሂደት የሚኖር የአመራር ብልሽት ቢያጋጥም የተጠያቂነት አሰራር ተግባራዊ እንደሚደረግም በማከል ኮሚሽኑ የጀመራቸዉን የሪፎርም ስራዎች ለማሳካት ሁሉም አመራርና ሰራተኛ በልዩ ትኩረት ኃላፊነቱን እንዲወጣ አቅጣጫ አስቀምጠዋል። በግምገማዊ ስልጠናዉ ላይ የተሳተፉት የኮሚሽኑ አመራሮች በበኩላቸዉ እንደተናገሩት ከግምገማዊ ስልጠናዉ ኮሚሽን መ/ቤቱ በሁሉም ዘርፎችና በሚሰጣቸዉ አገግሎቶች ለዉጤታማ ስራዎች ማነቆ የሆኑ አሰራሮችን ለመለየት እንዳስቻላቸዉ ጠቅሰዉ ስልጠናዉ የችግሮቹን መፍትሄ አብሮ ያመላከተ በመሆኑ በቀጣይ በሚኖሩ በሁሉን አቀፍ ተግባሮቻቸዉ የተሻለ ዉጤት ለማስመዝገብ ተግተዉ እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል። ለሁለት ቀናት በቆየዉ የስልጠና ጊዜ የኮሚሽኑ ማሰልጠኛ ማዕከል ስልጠናዉን እንዳስተባበረ የተገለጸ ሲሆን በግምገማዊ ስልጠናዉ ከ 315 በላይ የሆኑ በየደረጃዉ ያሉ አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን ስልጠናዉ ለኮሚሽኑ ጠቅላላ ሰራተኛ እንደሚሰጥም ተመላክቷል ። ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ ! ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት የሰባት ወራት የእቅድ የስራ አፈጻጸምን ገመገመ፡፡ የከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት የበጀት አመቱን ያለፉት ሰባት ወራት የእቅድ የአፈፃፀም ከተቋሙ ጠቅላላ ሰራተኞች ጋር በዛሬው እለት በጋራ ገምግሟል። የዉይይት መድረኩን በቢሮ ሀላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ስራ አስኪያጅ እና የጥናትና ልማት ትግበራ ዘርፍ ዋና ሀላፊ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ አስጀምረዋል። በመድረኩ ላይ ባለፉት 7 ወራት የእቅድ አፈፃፀም በአገልግሎት አሰጣጥና ክትትልና ድጋፍ፣ የቅንጅታዊ አሰራርን ከመተግበር፣ከጥናትና ትግበራ ፣ከአቅም ግንባታና ስልጠና የሚዲያና የኮሙዩኒኬሽን ስራዎችን በተመለከተ፣እንዲሁም የኘሮጀክት አፈፃፀምን ከመከታተል፣የቅድመ አደጋ መከላከል፣በከተማ ፅዳት በተለይም በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ፣ በኤሌክትሪክ አገልግሎትና እንዲሁም በሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ላይ የአገልግሎት አሰጣጡን በማሳለጥ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የተሰሩ ስራዎች የሚያሳይ ሪፖርት ቀርቦ ዉይይት ተካሂዶበታል፡፡ በቢሮ ሃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ዋና ስራ አስኪያጅ እና የጥናትና የልማት ትግበራ ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ ባለፉት 7 ወራት በፅ/ቤቱ የተከናወኑ ስራዎች አፈፃፀም ከእቅድ በላይ መከናወኑ መልካም የሚባል እንደሆነ ገልጸው ይሁን እንጅ በጥንካሬ የተቀመጡትን አጠናክሮ ማስቀጠልና በክፍተት የተመላከቱትም ላይ በቀጣይ ወራት በልዩ ትኩረት ሰጥቶ የማስተካከያ ስራዎች በፍጥነት ማከናወን እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል። አክለዉም ጽ/ ቤቱ የሚመራቸውን የተቋማት ቅንጅታዊ ስራዎች አጠናክሮ ከማስቀጠል በተጨማሪ የቅድመ አደጋ ከመከላከል፣በተጠሪ ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥን የማቀላጠፍ እና የማዘመን፣ተጠያቂነትን የማረጋገጥ፣ የግንዛቤ ስራን የማጠናከር፣ድጋፍና ክትትል ከማድረግ አንፃርም በቀሪ ወራት የተጠናከረ ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባ አመልክተዋል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የአዲስ አበባ ከተማ የሰራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ያለፉት 7 ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ በዛሬው እለት ተገምግሟል። በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ ዋ/ ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ በመሩት በዚህ መድረክ ላይ የጽ/ ቤቱ ያለፉት 7 ወራት የስራ አፈፃፀም የስትራቴጂክ እና የፕሮሰስ ካውንስል አባላት በተገኙበት ተገምግሟል። በዚሁ ወቅት ባለፉት 7ወራት በአገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ፣ በጥናትና ትግበራ፣ በኮሙዩኒኬሽንና በአስተዳደር ዘርፍ የተከናወኑ የአበይት ተግባራት አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል። አቶ ተፈራ ሞላ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት በበጀት አመቱ ያለፉት 7 ወራት ታቅደው የተከናወኑ ተግባራት አበረታች አፈፃፀም የተመዘገበባቸው መሆናቸውን ገልጸው ቀሪ የመደበኛና የሪፎርም ክትትልና ድጋፍ ስራዎችን በተያዘለት የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ የተጠናከረ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በጃፓን አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) በተዘጋጀ አለምዓቀፋዊ አጀንዳ በሆነው የጽዱ ከተሞች ኢንሼቲቭ የአካባቢ ጥበቃ አስተዳደር ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ላይ ናቸው። በጃፓን ዮካሃማ ከተማ እየተካሄደ ባለው በዚህ መድረክ ላይ አዲስ አበባን ጨምሮ የ7ት የአፍሪካ አገራት ከተሞች ማለትም የሉሳካ፣ ናይሮቢ፣ ቱኒዝያ አልጀሪያ፣ አቢጃን እና ካርቱም ከተሞች ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ ሲሆን የእውቀት፣ የምርጥ ተሞክሮ እና ልምድ ልውውጦች ፣ በደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ፣የብክለት ቁጥጥር እና ዘላቂ የከተማ ልማት ርእሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ ላይ መዲናችን አዲስ አበባን በመወከል የተገኙት ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መዲናዋን ጽዱ፣ ውብና አረንጓዴ በማድረግ ረገድ ያከናወነውን ውጤታማ ስራዎችን ለማጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው መዲናዋ የአለምዓቀፍ ምርጥ ልምዶችንም በመቀመር እያስመዘገበችው ያለውን አብነታዊ እና ስኬታማ ተግባር ለሌሎች የአህጉሩ ከተሞች ለማካፈል ይህ መድረክ ወርቃማ እድል የፈጠረ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል። ኢንጅነር ወንድሙ አክለውም በርካታ የመስኩ ኤክስፐርቶች እየተሳተፉበት ባለው በዚህ መድረክ ለአዲስ አበባ ከተማ ጠንካራ የአካባቢ ጥበቃ ስርአትን ለማጠናከር እና ዘላቂነቱን በማረጋገጥ ረገድ ተሻጋሪ እይታን የሚጨምሩ ጠንካራ ትስስሮችን ለመፍጠርና ከዚሁ የሚገኘውን ልምድና ተሞክሮ ለቀጣይ ስራ ለማዋል ጠቃሚ ግብአት የሚገኝበት መድረክ እንደሆነም በመልእክታቸው አስተላልፈዋል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ለኮሚሽኑ አመራሮች የግምገማዊ ስልጠና እየተሰጠ ነዉ። የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በሁሉም ዘርፎች ለሚገኙና ከቡድን መሪ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ አመራሮች የሚሳተፉበት ግምገማዊ ስልጠና በኮሚሽኑ ማሰልጠኛ ዛሬ የካቲት 10 ቀን 2017 ዓ.ም መሰጠት ተጀምሯል። ስልጠናዉ ለሁለት ቀናት እንደሚቆይ የተገለጸ ሲሆን በስልጠናዉ ላይ ከ315 በላይ አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛል። ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች በ93 ፈጥነዉ ያሳዉቁ ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳለፈ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 42ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ ውሳኔዎቹ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡- በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው የኢትዮጵያ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ አዋጁ በተቋሙ የተጀመረውን የሪፎርም ስርዓት ወደ ተግባር በመለወጥ በኢትዮጵያ የህዝቡን የእርስ በእርስ መረዳዳት ባህል የማጎልበትና ተረጂነትን በዘላቂነት በሀገር አቅም መወጣትን ማዕከል በማድረግ የአደጋ ጉዳት ሰለባ ለሆኑ ዜጎች ከሰብአዊ ድጋፍ መርሆዎች፣ ከዘላቂ የልማት ፕሮግራሞችና ከሰላም መስፈን ጋር በማስተሳሰር ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ሞራላዊ ጉዳቱን ለመቀነስ የሚያስችል ነው፡፡ ምክር ቤቱም በጉዳዩ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው በሦስት የተቋማት ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንቦች ላይ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ማቋቋሚያ ደንብ ዩኒቨርሲቲው አላማውን ለማሳካት የአደረጃጀት ማስተካከያዎችንና የአሠራር ለውጦችን ለማድረግ፤ የመከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ግሩፕ እና የመከላከያ ዲያግኖስቲክ ማዕከል ማቋቋሚያ ደንብ ተቋሙ የሀገሪቱን የልዕለ ህክምና፣ የዲያግኖስቲክ እና ተዛማጅ አገልግሎት ፍላጎትን ለማሟላት፤ እንዲሁም የተሻለ ህክምና ፍለጋ ወደ ውጭ ሀገር የሚሄዱ ታካሚዎች በሀገር ውስጥ አገልግሎቱን እንዲያገኙ ለማድረግ እንዲሁም የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ማቋቋሚያ ደንብ የተቋሙን ተግባርና ሀላፊነት በመደንገግ ለሀገር እድገት የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ለማድረግ የህግ ማዕቀፍ ሆኖ ቀርቧል። ምክር ቤቱም በቀረቡት ረቂቅ ደንቦች ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውሉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ የካቲት 10 ቀን 2017 አ.ም Office of the Prime Minister-Ethiopia

የረዳን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን 38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እጅግ ደማቅ እና ከወትሮው ለየት ባለ ሁኔታ ሲካሄድ ቆይቶ ትላንት ማምሻውን ተጠናቅቋል። የህብረቱ ጉባኤ ለከተማችን ድምቀትና የኢኮኖሚ መነቃቃት ከመፍጠሩ ባሻገር የቱሪዝም መስህቦችን እና የከተማችንን መልካም ገጽታዎችን እንዲሁም የህዝባችንን ጨዋነትና እንግዳ ተቀባይነት በማስተዋወቅ ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። በዚህ በ38ኛው የመሪዎች ጉባኤ አዲስ አበባ እንደወትሮው ሁሉ እንግዳ ተቀባይነትና ያለባትን ተደራራቢ ሃላፊነት ስራው ከሚመለከታቸው የፌደራል መስሪያ ቤቶች እና ከከተማችን ነዋሪዎችም ጋር በመሆን ላቅ ያለ የማስተናገድ ብቃትን ያሳየችበት ሲሆን ተባብረን በጋራ በሰራነዉ ስራ ለሀገራችን ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ወንድሞች እና እህቶቻችን ኩራት መሆናችንን ዳግም አሳይተናል። እንግዶቻችንም ባዩት ለዉጥ እየተደነቁ፣ በአዲስ አበባ መቆየት እየወደዱ እና ደግመው ደጋግመዉ መምጣትን እየተመኙ መሆኑን ሰምተናል። የከተማችን ነዋሪዎችም ላሳያችሁት ታላቅ እንግዳ አክባሪነትና ተቀባይነት፣ እንዲሁም እንግዶችን ለማስተናገድ ዓላማ መንገዶች ሲዘጉ ፍጹም ትዕግስት እና ጨዋነታችሁ ላቅ ያለ ምስጋናዬን ላቀርብላችሁ እወዳለሁ። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

38ኛው የአፍሪካ ኅብረት መደበኛ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቋል። ሀገራችን ኢትዮጵያም እንደ ኅብረቱ መቀመጫ ሀገር የሚጠበቅባትን አከናውናለች። አቀባበሉ፣ መስተንግዶውና መርሐ ግብሮቹ እንግዶቻችንን ያስደመመ ነበር። እንግዶቿ የማይረሳ ትውስታ፣ የማያረጅ ትዝታ እንዲኖራቸው አድርጋለች። በዚህ የተነሣ የቆይታ ጊዜያቸውን ያራዘሙ እንግዶች ብዙ ናቸው። ኢትዮጵያ ለኅብረቱ ዓላማዎች እና መርሖች መሳካት ያላትን ቁርጠኝነት በጉባኤው ዝግጅትና መስተንግዶ በተግባር አሳይታለች። የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ እንዲከናወን ብዙዎች የሚቻላቸውን ሁሉ አድርገዋል። አዘጋጅ ኮሚቴው፣ የውጭ ጉዳይ ዲፕሎማቶች፣ የፕሮቶኮል ባለሞያዎች፣ የቴሌና የመብራት ተቋማት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የጸጥታ ተቋማት፣ የትራፊክ ፖሊሶች፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች፣ ሚዲያዎች፣ የኪነ ጥበብና የሰርከስ አባላት፣ ሆቴሎች፣ የአዲስ አበባ መስተዳድር የሥራ ኃላፊዎችና ባለሞያዎች፣ የጽዳት ባለሞያዎች፣ እንደ አንድ ልብ ሰሚ፣ እንደ አንድ አካል ፈጻሚ ሆነው ተሠርተዋል። የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ ለእንግዶቹ ተገቢውን ክብርና መስተንግዶ በመስጠት፣ መንገዶች ሲዘጉ በትዕግሥት በመጠባበቅ፣ ለጉባኤው ስኬት የሚጠበቅበትን ሁሉ አድርጓል። ለሁላችሁም በኢትዮጵያ መንግሥት እና በራሴ ስም ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ። ሁላችንም በሀገር ፍቅር ስሜት በሥርዓት እና በዲሲፕሊን በመሥራታችን እንግዶቻችንን አስደምመናል። የሀገራችንን ከፍታ አሳይተናል። ከአንድ ሺ በላይ የሚሆኑት የሚዲያ ሰዎች መልካም ገጽታችንን ለዓለም አሳይተዋል። ከዐሥር ሺ ዎች የሚልቁት እንግዶች እየበለጸገች ስለምትገኘው ሀገራችን ምስክሮች ሆነዋል። ይህ ትብብራችንና ለሀገራችን ስኬት ያለን ቁርጠኝነት፣ ከጉባኤው በኋላም እንደሚቀጥል አምናለሁ። ኢትዮጵያ የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት መሆንዋ በዐለት ላይ እስኪጻፍ ድረስ ጥረታችን ይቀጥላል። በድጋሜ ሁላችሁንም አመሰግናለሁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)