1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
የዩኤንዲፒ ረዳት ዋና ፀሃፊ እና የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር አሁና ኤዚያኮንዋ እና የኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር ሳም ዱዎ ገላን ጉራ መኖርያና የተቀናጀ የልማት መንደርን ጎበኙ።
በጉብኝታቸዉ ለልማት ተነሺዎች የተፈጠረዉን የመሰረተ ልማት ምቹ ሁኔታ የስፖርት ማዘዉተርያ ስፍራ፣ የህፃናት መጫወቻ ሜዳዎች ከተሟላ መጫወቻ ጋር፣ ከቅድመ መደበኛ እስከ 2ኛ ደረጃ ያሉ ግንባታቸዉ በ57 ቀናት ዉስጥ ተጠናቆ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ት/ቤቶች እንዲሁም ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶችን የጎበኙ ሲሆን የልማት ተነሺዎች አሁን ያሉበት የኑሮ ሁኔታ በመኖርያ ቤታቸዉ በመገኘት ተዘዋዉረዉ ለማየት ችለዋል።
የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተርዋ አሁና ኤዚያኮንዋ በተመለከቱት ሰዉ ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች ደስተኛ መሆናቸዉን እና መንግስት ከማህበረሰቡ ጋር ቀርቦ የሚሰራበት መንገድ የሚደነቅ መሆኑን ገልፀዋል።
ነዋሪዎች በበኩላቸዉ ከዚህ ቀደም የነበራቸዉ የአኗኗር ዘይቤና ይኖሩበት የነበረዉ ስፍራ ለሰዉ ልጅ ክብር የማይመጥን፣ ለጤናም ከፍተኛ ስጋት የነበረዉ መሆኑን በማስታወስ አሁን ላይ በተመቻቸላቸዉ የተሟላ መሰረተ ልማት እና ሰዉ ተኮር የልማት ስራዎች ደስተኞች መሆናቸዉን አብራርተዉ ገልፀዋል።
ህይወቱን ማትረፍ ተችሏል!
ዛሬ እሁድ የካቲት 9 ቀን 2017 ዓ.ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ሐምሌ 19 ትምህርት ቤት አለፍ ብሎ ለህንጻ ግንባታ የመሰረት ቁፋሮ ስራ ላይ የነበረ የቀን ሰራተኛ አፈር ተንዶበት ህይወቱ አደጋ ዉስጥ የነበረ ቢሆንም የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን Fire and Disaster Risk Management Commission የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በቦታዉ ላይ በፍጥነት ደርሰዉ ህይወቱን ማትረፍ ችለዋል።
መጠነኛ ጉዳት የደረሰበትን ተጎጂ በኮሚሽኑ የቅድመ ሆስፒታል አገልግሎት አምቡላንስ ዉስጥ የህክምና እርዳታ ተደርጎለታል ።
በአዲስ አበባ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የአደጋ ደህንነት መስፈርት ጠብቆ ባለመስራት መሰል አደጋዎች እያጋጠሙ በመሆኑ አደጋዉን አስቀድሞ ለመከላከል በተለይም አሰሪዎች ስራዉ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊዉን የደህንነት መስፈርት ማሟላት እንደሚገባቸዉ ኮሚሽኑ ያሳስባል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager?is_from_webapp=1&sender_device=pc
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ የመጀመሪያ ቀን ከተለያዩ መሪዎች ጋር በቁልፍ ቀጠናዊ፣ አኅጉራዊ እና የልማት ቀዳሚ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደረግንበት ውጤታማ ቀን ነበር። ከኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዝዳንት ቴዮዶር ኦቢያንግ ንጉዬ ማምባሶንጎ፣ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ብሎም የቦትስዋና ፕሬዝዳንት ዱማ ቦኮ ጋር ትብብሮቻችንን በምናጠናክርባቸው መንገዶች ላይ ቁርጠኝነታችንን አረጋግጠናል። ከሩዋንዳ ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ እና ከታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉህ ሀሰን ጋርም የአፍሪካን እድገት ለማፋጠን የጋራ ጥረቶቻችንን ለማጠናከር ተወያይተናል።
ከመንግሥታትም ባሻገር ከግሎባል ፈንድ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ፒተር ሳንድስ እና ከጂኤቪአይ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳኒያ ኒሽታር ጋር የጤናውን ዘርፍ በማጠናከር ሥራ ላይ ተወያይተናል። ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት አኪንዊሚ አዲሴና እና አይኤፍኤዲ ፕሬዝዳንት አልቫሮ ላሪዮ ጋርም የኢትዮጵያን የግብርና ዘርፍ የሚያጎለብቱ ጉዳዮችን አንስተን ተነጋግረናል። ከንግዱ ዘርፍም ከአሊኮ ዳንጎቴ እና ቶኒ ኢሉሜሉ ጋርም የግሉ ዘርፍ የአፍሪካን እድገት በመምራት ረገድ ስላለው ሚና ውይይት አድርገናል።
በነዚህ ውይይቶች ላይ በመመሥረትም የጋራ ብልፅግናን ለማሳካት እንሠራለን።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ዘላቂ ፍትህ፣ ሰላም እና ብልፅግናን ለማረጋገጥ በቅኝ ግዛት ድንበሮች ከተጣሉብን መልክዓ ምድራዊና ፖለቲካዊ ውጥረቶች እና ታሪካዊ ክፍፍሎች በላይ ልቀን መገኘት ይኖርብናል።
በሁሉም ሀገሮቻችን መካከል ኅብረትን በማሳደግ የጋራ እጣፈንታችንን በጋራ በመጨበጥ ኃብቶቻችንን እና ተስጥኦዎቻችንን በማስተባበር የአኅጉራችንን ሙሉ አቅም ልንጠቀም እንችላለን።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ
,የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ በየካ ክ/ከተማ የወረዳ 01 ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤትን የዘመናዊነት ሞዴል በማድረግ የቢሮ ማስመረቂያ መርኃ-ግብር ተካሂዷል።
በመርኃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ አስተዳደር ም/ቤት ማዘጋጃ ቤታዊና መሰረተ ልማት ቋሚ ኮሚቴ ም/ሰብሳቢ ዶ/ር አለማየሁ፣ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ሥራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ እና የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማን ጨምሮ ሌሎች የከተማና የክ/ከተማ እንዲሁም የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
የወረዳው የጽዳት አስተዳደር ላለፉት 4 ዓመታት ስኬታማ የስራ ውጤታማነት በማስመዝገቡ የከተማው የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ተቋሙን የማዘመንና ግብዓት የማሟላት ለተገልጋይና ለጽ/ቤቱ ባለሙያዎች ምቹ የማድረግ ተግባር ማከናወኑን በመርኃ-ግብሩ ላይ ተመላክቷል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ እንደገለፁት ተቋማትን ሪፎርም በማድረግ ቃል በተግባር የለወጥንበትና ባህል ያደረግንበት የብልጽግናችን ተምሣሌት የምናረጋግጥበት አንዱ ማሣያችን ነው ብለዋል።
የመሥሪያ ቦታዎችን ምቹ የማድረግ ለተገልጋዮችና ለሠራተኞች ምቹ የምናደርግበት ተሞክሮዎችን የምናሰፋበት ሙሉ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሣሌት የምናደርግበትም ነው ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ በበኩላቸው ከተማዋን ጽዱና ውብ ለማድረግ በርካታ ተግባራት መከናወኑን ገልጸዋል፡፡
ብሎክን ማዕከል ያደረገ የጽዳት ስራዎች መሰራቱን የገለጹት ኃላፊው ብሎክን መነሻ በማድረግ በሁሉም ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች በርካታ ሞዴል ቤተሰቦች መፈጠር መቻላቸውን ጠቁመዋል፡፡
የከተማው የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ጽ/ቤቱን የማዘመንና ግብዓት የማሟላት ተግባር በማከናወኑም የወረዳው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሳሙኤል ታዲዎስ የላቀ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ወረዳውን ሞዴል ከማድረግ አኳያ ለሰራው ተግባር ጽ/ቤቱን ሞዴል የማድረግ ለተገልጋዮችና ለሰራተኞች ምቹና ሳቢ የማድረግ ተግባር መስራታቸውን ገልጸዋል፡፡
በሁሉም ክ/ከተማ 12 ወረዳዎችን ለተግልጋይና ለሰራተኛ ምቹ የማድረግ ተግባር ማከናወናቸውንና ይህንንም ተግባር አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል፡፡
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በ38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ መክፈቻ ላይ ያስተላለፉት መልዕክት
የግሎባል ፈንድ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ፒተር ሳንድስ ወደ ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ። ግሎባል ፈንድ የኢትዮጵያን የጤና ዘርፍ በመደገፍ ቁልፍ አጋር ሆኖ ቀጥሏል። የዛሬው ውይይታችንም ይኽን ትብብር በማጠናከር ላይ ያተኮረ ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የግሎባል ፈንድ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ፒተር ሳንድስ ወደ ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ። ግሎባል ፈንድ የኢትዮጵያን የጤና ዘርፍ በመደገፍ ቁልፍ አጋር ሆኖ ቀጥሏል። የዛሬው ውይይታችንም ይኽን ትብብር በማጠናከር ላይ ያተኮረ ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ዛሬ የአልጄሪያ ፕሬዝዳንት አብድልመጂድ ቴቡኔን ለሁለትዮሽ ውይይት አግኝቻለሁ። ኢትዮጵያ እና አልጄሪያ በታሪካዊ ትስስር፣ በፓን አፍሪካኒዝም እና በጋራ ፍላጎት ላይ የተመሠረተ ጠንካራ የዲፕሎማሲ ቁርኝት ይጋራሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
