1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
ኤጀንሲው በ11ኛው የኢትዮጵያ የጥራት ሽልማት ውድድር " የአድናቆት ደረጃ" ተሸላሚ ሆነ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ተወዳዳሪ አገልግሎት ሰጪ ተቋም መሆን እንዲችል በ11ኛው የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ውድድር ላይ የተሳተፈ ሲሆን በዚሁ መሰረት በታላቁ ቤተ-መንግስት በተዘጋጀው የእውቅና መድረክ የአድናቆት ደረጃ / Award of Honorbale Certificare / ተሸላሚ ሆኗል።
ተቋሙ ለህዝብ የሚሰጠውን አገልግሎት ለማሻሻል ከተለመደው አሰራር በመውጣት ተወዳዳሪ ሊያደርገው የሚችሉ አለም አቀፍ መስፈርትን መሰረት አደርጓ እንደሚሰራ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ በተቋሙ ላይ የሚነሱ ችግሮችን በመቅረፍ ደረጃውን ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ተነግሯል።
ኤጀንሲው በ11ኛው ሃገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ውድድር ላይ አመልክተው ከተወዳደሩ እና የደረጃውን እውቅና ካገኙ ጥቂት የፌደራል፣ የክልል እና የከተማ አስተዳደር የመንግስት ተቋማት አንዱ ሲሆን የማመልከት፣ መመዘኛዎችን የመሙላት እንዲሁም የተሰሩ ስራዎች የመስክ ምልከታ የተከናወነበት ሂደትን አልፏል።
ተቋሙ በህዝብ የተመሰከረለት ጥራት ያለው አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ሆኖ ማየት እስኪቻል የሃገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ውድድር ተሳታፊ ሆኖ እንደሚቀጥል በዕለቱ ሽልማቱን ተገኝተው የወሰዱት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ የተናገሩ ሲሆን ውድድሩን የመንግስት ተቋማት በስፋት እንዲሳተፉና እራሳቸውን እንዲፈትሹ እንዲሁም ለግል ተቋማት ብቻ የሚተው የውድድር ዓይነት ብቻ ተደርጓ ሊወሰድ የማይገባ እንደሆነ አሳስበዋል።
ታህሳስ 7/ 2017
ለበለጠ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 7533 ይደውሉ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ልብንም ጭንቅላትንም ለሰዎች ሀሳብ ክፍት ማድረግ እና የቡድን ስራን ማዳበር ለውጤታማነት ወሳኝ ነው!!"
: - ዶ/ር ፍፁም አሰፋ
አቃቂ ቃሊቲ የነገዋ የሴቶች የልህቀትና የተሀድሶ ማዕከል ፣ የአይነስውራን አዳሪ ት/ቤት እና ሌሎች ግዙፍ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ያሉበት ክ /ከተማ ነው።
ሰፋፊ የመንገድ ግንባታን ጨምሮ መሰረተ ልማቶችም በፍጥነት እየተገነቡበት የሚገኝ ክ/ከተማ ሲሆን 60 በመቶ የሚሆነው የከተማችን ኢንዱስትሪዎችም ያሉት ከዚሁ ክ/ከተማ ነው፡፡
በፕላን ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ እና በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የተመራው የፌዴራል የሱፐርቪዥን ቡድን በከተማችን የሚገኙ ግዙፍ ሰው ተኮር ስራዎችንና የአገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ የሚያደርገውን ምልከታ ዛሬም በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የቀጠለ ሲሆን የክ/ ከተማው ያለፉት ወራት አፈፃፀምም በዋና ስራ አስፈፃሚው በአቶ አለማየሁ ሚጀና አጠር ብሎ ቀርቦላቸዋል።
በስራ ዕድል ፈጠራ ፣ በግብርናውም በኢንዱስትሪውም ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የኑሮ ውድነቱን በማቃለል ፣ ህግና አሰራርን በማስጠበቅ ፣ ህዝብን የሰላም ባለቤት በማድረግ በተከናወኑ የሰላምና ፀጥታ ስራዎች እና በመሳሰሉት ክ /ከተማው አበረታች ስኬቶችን ማስመዝገቡን አቶ አለማየሁ ሚጀና አስረድተዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ አስተባባሪነት እየተካሄደ የሚገኘው የሱፐርቪዥን ቡድኑ ጉብኝት በከተማ አስተዳደሩና በ ክ/ከተማው አቅም የተገነቡ ፕሮጀክቶችን በአካል የሚጎበኝ ሲሆን የስራና ክህሎት ፅ/ቤትንም ተመልክተዋል።
የፕላን ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ የስራ ዕድል ፈጠራ እንደ ሀገርም የማክሮ ኢኮኖሚው የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ጠቅሰው የፅ/ቤቱ አገልግሎት አሰጣ ለተገልጋዮች እና ለአገልጋዮች ምቹ መሆኑን የሚበረታታ ነው ብለዋል።
ልብንም ጭንቅላትንም ለሰዎች ሀሳብ ክፍት ማድረግ እና የቡድን ስራን ማዳበር ለውጤታማነት ወሳኝ ነው ሲሉም ዶ/ር ፍፁም አሰፋ ምክራቸውን ለግሰዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ማለዳ የኡጋንዳ ህዝብ መከላከያ ሃይል ጠቅላይ አዛዥ ከሆኑት ጀነራል ሙሆዚ ካይኔሩጋባ ጋር ተገናኝተዋል።
በከተማችን ያለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በመንግስትና የግል ዘርፍ አጋርነት ከምናካሂዳቸው የቤት ግንባታ መርሃ ግብር ትልቁ የሆነው የኦቪድ ገላን ጉራ ሳይት 60 ሺሕ ቤቶች ግንባታ፣ በለገሀር ጊፍት ሪልስቴት የሚገነባቸው 4,370 ቤቶች የግንባታ ሂደትን እንዲሁም በቦሌ ሩዋንዳ በግሉ ዘርፍ እየለሙ የሚገኙ ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታን ጎብኝተናል::
በምናካሂዳቸው የልማት ስራዎች ቅድሚያ ለልማት ተነሺዎች በማለት በጀመርነው አሰራር መሰረት የኦቪድ ገላን ጉራ ሳይት ለልማት ተነሺ አርሶአደሮች የሚሆኑ 770 ደረጃቸውን የጠበቁ ምትክ ቤቶችን ቅድሚያ ሰጥተን ግንባታቸውን በማፋጠን ላይ እንገኛለን::
በዚህ የገላን ጉራ ፕሮጀክት ከሚገነቡ ቤቶች ውስጥ ኮንዶሚኒየም በመቆጠብ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ በማመቻቸት ላይ የምንገኝ ሲሆን በከተማችን ያለውን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመቅረፍ ከግሉ ዘርፍ ጋር በመተባበር የጀመርናቸው ስራዎችን ከመሰረተልማትና ከፋይናንስ ጋር ተያይዞ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመቅረፍ በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ትኩረት ሰጥተን የምንሰራ ይሆናል::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ለሁሉአቀፍ የማህበረሰብ ጤንነት!” በሚል መሪ ቃል የጤና ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች ከከተማችን ነዋሪዎች ጋር በመሆን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አከናውነዋል።
የከተማችን ነዋሪ በአካልና በአዕምሮ የዳበረ እንዲሁም ጤናው የተጠበቀ እንዲሆን ማህበረሰብ አቀፍ ስፖርትን ባህል በማድረግ ሁሉም በየአካባቢው እና በየመስሪያ ቤቱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን እንዲያደርግ መስራት ይኖርብናል።
ጎዳናዎቻችን ጽዱ እና ለጤና ተስማሚ እንዲሆኑ ተደርገው የተገነቡ ሲሆን፣ ሁላችንም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እያደረግን እንንከባከባቸው።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በአዲስ አበባ ከተማ የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የአለም የነጭ ሪቫን ቀንና የኤች አይቪ ኤድስ ቀን ተከበረ።
በጽ/ቤቱ የነጭ ሪባን እና የኤችአይቪ ኤድስ ቀን አመራሮችና ሁሉም ባለሙያዎች በተገኙበት በዛሬው እለት ታህሳስ 5ቀን 2017 አ.ም በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።
በዚሁ ወቅት በአለም ለ33ኛ ጊዜ በአገራችን ደግሞ ለ19ኛ ጊዜ በመከበር ላይ ያለውን የነጭ ሪባን ቀን አስመልክቶ "የሴቷ ጥቃት የእኔም ነው! ዝም አልልም!" በሚል መሪ ቃል ታሪካዊ አመጣጡን፣የሚከበርበት አላማ፣ መርሆዎችና ጽንሰ ሃሳቦች እንዲሁም ለሴቶች እኩል ተጠቃሚነት እንደ ሃገር እና በከተማም ደረጃ ምን ምን ስራዎች እንደተከናወኑ የሚገልፅ ሰነድ በፅ/ቤቱ የኮሙኒኬሽን ዘርፍ ሀላፊ በወ/ሮ ሀይማኖት ዘለቀ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።
ስልጠናውን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት ሀላፊ አቶ ወሰን መግራ የነጭ ሪቫንንና የኤች አይቪ ቀንን ለተቋሙ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይቶች በዚህ መልክ መካሄዱ የባለሙያውን ግንዛቤ በማስፋትና የአመለካከት ለዉጦችን ለማምጣት ወሳኝ ነው ብለዋል።
የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የሜይንስትሪሚንግ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ወንድሙ ደንቡ በበኩላቸው እንደገለፁት የኤችአይቪ ኤድስ መስፋፋትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንደ አገርም እንደከተማም አበረታች ጥረቶች እየተደረጉ እንዳለ ጠቁመው ይሁን እንጅ ጥረቱ ሙሉ በሙሉ ውጤታማ የሚሆነው ዜጎች በሽታውን በመከላከል ረገድ በሚያመጡት የባህሪ ለውጥ ሲታገዝ ነው ብለዋል።
አቶ ወንድሙ በውይይቱ ላይ ስለ ማህጸን ጫፍ ካንሰር መንስኤ፣ሊደረግ ስለሚገባው ጥንቃቄ እና የመከላከያ መንገድ ለሠራተኛው ግንዛቤ ሰጭ ሙያዊ ሰነድ አቅርበው ውይይት ተካሂዶበታል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ዛሬ ማለዳ በልደታ ክፍለከተማ በመሰረትነው የበጎነት መንደር ውስጥ በመገንባት ላይ ያሉ ተጨማሪ ሁለት ባለ 9 ወለል የመኖሪያ ቤት ህንጻዎች ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተመልክተናል።
በበጎነት የመኖሪያ መንደር እስካሁን ሰባት የመኖሪያ ህንጻዎች ተጠናቅቀው ለልማት ተነሺዎች እና የኑሮ ጫና ላለባቸው የከተማችን ነዋሪዎች የተላለፉ ሲሆን፣ በመኖሪያ መንደሩ ለሚገኙ ነዋሪዎቻችን የእንጀራ ፋብሪካን ጨምሮ ልዩ ልዩ የስራ እድል ፈጥረንላቸዋል።
በከተማ አስተዳደሩ እና ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ትብብር እየተገነቡ የሚገኙትን ሁለት ባለ 9 ወለል የመኖሪያ ቤት ህንጻዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ለነዋሪዎች የምናስተላልፍ ይሆናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የእድገት ምልክት፣ የአፍሪካ የልብ ምት እና የአንድነት መቀመጫ:- አዲስ አበባ
አዲስ አበባ ለፈተናዎች አልበገርም ብላ የለውጥ እና የሽግግር ምልክት ሆናለች ይላሉ የደቡብ አፍሪካው ብሔራዊ የትምህርት አገልግሎት ተቋም ዳይሬክተር ጀነራል ቡሳኒ ንካዌኒ።
See less
