fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ካቢኔ 4ተኛ ዓመት፤ 4ተኛ መደበኛ ስብሰባ ለከተማዋ ልማት ጉልህ ፍይዳ ያላቸውን አጀንዳዎች ተወያይቶ አፅድቋል፡፡ የፀደቁ አጀንዳዎች፤- 1ኛ. የወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ብክለት መከላከል ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ለከተማዋ ነዋሪዎቻ ጤና እና ፅዳትና ውበት ወሳኝ እና ጠቃሚ መሆኑን በማረጋገጥ ደንቡን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡ 2ኛ. በከተማ ፕላን ልማት ቢሮ የተዘጋጁና የሚዘጋጁ የአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጀት፤ አፈፃፀም ቁጥጥር፤ ደንብ ማሻሽያን መርምሮ በመወያየት፤ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡ 3ኛ. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች ማቅረብ በመጀመሩ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችአገልግሎት አስተዳደር ረቂቅ መነሻ ሀሳብ ላይ መርምሮ በጥልቅ በመወያየት በመንግስት እና የግል አጋርነት (PPP) እንዲተዳደሩ፣ ብሎም .በከተማዋ የመንግስት እና የግል ትራንስፖርት አገልግሎት እስከ ምሽቱ 4፡00 ድረስ አግልጋሎት እንዲሰጡ እና በሁሉም የኮሪደር ልማት በሚተገበርባቸው ቦታዎች የትራንስፖርት አገልግሎት እለታዊ የጊዜ ሰሌዳ እንዲጠቀሙ እንዲደረግ :: 4ተኛ -በሁሉም የከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ያሉ የንግድ እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3፡30 ለህብረተሰቡ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ 5ተኛ -ሁሉም ዋና መንገድ እና መጋቢ መንገድ ላይ ያሉ ተቋማት ህንፃዎች፣ የግልና የመንግስት ቢሮዎች የምሽት መብራት ማጥፋት እንዲከለከል እና ሙሉ የመብራት አገልግሎት እንዲኖር ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

በከተማዉ እያጋጠሙ ያሉ የአደጋ ስጋቶችን ለመቀነስ የብሎክ አመራሮች ሚና የላቀ እነደሆነ ተገለጸ። የጉለሌ ክፍለ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ለ10 ሩም የወረዳ ብሎክ ሰብሳቢዎች በአደጋ መከሌከልና መቆጣጠር ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ዛሬ ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም ሰጥቷል። በኮሚሽን መ/ቤቱ የጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ኒቆዲሞስ ቡቼ እንደተናገሩት በእሳት አደጋ ቅድመ መከላከል፣ በአደጋ ጊዜ እና ድህረ መከላከል ዙሪያ በክፍለ ከተማ ደረጃ በርካታ ተግባራት መከናወኑን ገልፀው የአደጋ ቅነሳው በመንግስት ብቻ የሚከናወን ሳይሆን በህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ በመሆኑ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መስጠት ከስጋት ነፃ የሆነች ከተማን መፍጠር ነው ብለዋል። የጉለሌ ክፍለ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የህብረተሰብ ተሳትፎ ስራዎች አስተባባሪ ወ/ሮ ቡዙዬ አለሙ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው በሁሉም ወረዳዎች የሚገኙ የብሎክ አመራሮች ግንዛቤውን በመጨበጥ በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን የአደጋ ስጋት የመቀነስ ተልዕኮአቸውን መወጣት አለባቸው ሲሉ ገልፀዋል። ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ! ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የአፍሪካ መዲና እና የፅናት ተምሳሌት የሆነችው አዲስ አበባ ዘመናዊነቷ ጎልቶ እየታየ ነው!! በደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ትምህርት ቤት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ቡሳኒ ንግካዌኒ ዴይሊ ማቭሪክ ለተሰኘ በደቡብ አፍሪካ ለሚዘጋጅ መጽሔት እንዳሉት የአፍሪካ መዲና እና የፅናት ተምሳሌት የሆነችው አዲስ አበባ ዘመናዊነቷ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጎልቶ እየታየ ነው። ቡሳኒ ንግካዌኒ አዲስ አበባ እንደ ደርባን፣ ሉዋንዳ፣ ሞምባሳ እና ኪንሻሳ ላሉ ከተሞች የልማት እና የዕድገት ምልክት እየሆነች መምጣቷን ባሰፈሩት ትንታኔ ገልጸዋል። በመዲናዋ እየተገነቡ ያሉ ሰማይ ጠቀስ ፎቆችን በአድናቆት እንደሚያዩ የገለጹት ምሁሩ፣ በፈተናዎች ውስጥ ማደግ፣ በተቃርኖዎች መካከል መታደስ የሚታይባት እንደነ ካይሮ እና ኬፕታውን ዕድገት እና ለውጥ ለማምጣት ከፍተኛ ጥረት እያደረገች ያለች ከተማ ናት ብለዋል። የአዲስ አበባ ለውጥ ጎልቶ የሚታይ መሆኑን እማኝነታቸውን ያስቀመጡት ቡሳኒ ንግካዌኒ፣ በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች ከቀያቸው መለወጥ ጋር በተያያዘ በዋጋ ንረት እና በትራንስፖርት እጥረት እንዳይቸገሩ በማድረግ ለውጡን በስኬት እየመራች መሆኑን መታዘባቸውን ነው የገለጹት። መዲናዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት እና በመሠረተ ልማት ግንባታው ከተማዋ ሌላ ማራኪ ገፅታ እንድትላበስ እየተደረገ መሆኑንም አመልክተዋል። ብልህ እና ታታሪ የሆነው የከተማዋ አስተዳደር በመዲናዋ ከሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ከንቲባ ጽ/ቤት ያለው መንገድ ፅዳቱን የጠበቀ እና በሥርዓት የተሰደረ እንዲሆን መደረጉን መታዘባቸውንም ጠቁመዋል። ከእያንዳንዱ አስፋልት ሥር አዳዲስ የውኃ ቱቦዎች እና የፋይበር ኦፕቲክ ኬብሎች መዘርጋታቸውን አመልክተው ይህም የከተማዋን ዕድገት ቀጣይነት ያመለክታል ብለዋል። የከተማዋን ነዋሪዎች፣ የባንኮች እንዲሁም የኤምባሲዎችን ድንበር እና ግድግዳ በመግፋትም ጭምር እየተገነባ ያለው የአስፋልት መንገድ የትራፊክ መብራቶች እና አደባባዮች የተካተቱበት፣ ከመኪና በተጨማሪ የሳይክል እና የእግረኛ መንገድ ያሉት መሆኑንም መመልከታቸውን ነው ሐሳባቸውን ያሰፈሩት። የአዲስ አበባ የዕድገት መሠረት የሆኑት ነዋሪዎቿ መሆናቸውን የሚገልጹት ምሁሩ፣ የመዲናዋ ጎዳናዎች የደከመ ጉልበትን የሚያበረቱ፣ ሕይወት የሚዘሩ መሆናቸውን መስክረዋል። እንደ ስሟ አዲስ የትውልድ ሀገር ልትሰኝ የምትችልም ሆናለች ሲሉ አስተያየታቸውን አጠቃለልዋል። ቡሳኒ ንግካዌኒ:- የደቡብ አፍሪካው ምሁር ናቸው። A love note to Addis Ababa — like a desert flower, our love endures dailymaverick.co.za A love note to Addis Ababa — like a desert flower, our love endures Addis Ababa stands as a defiant symbol of motion and progress. Unlike the stasis that has gripped cities like Durban, Luanda, Mombasa and Kinshasa, this mountainous city carves its identity as a hopeful antithesis — a space where despair melts into the promise of something greater.

ማህበረሰቡ እያሳየ የሚገኘው ሁለንተናዊ ድጋፍ በክፍለ ከተማው እየተሰራ ለሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ ትልቅ አቅም እየሆነ ነው ተባለ ዛሬ አመሻሹን ከሳርቤት - መካኒሳ - ፉሪ አደባባይ የኮሪደር ልማት ሰራተኞች፣ አስተባባሪዎችና የፀጥታ ሀይሎች በአካባቢ ባለሀብት የእራት ግብዣ ተደርጎላቸዋል:: የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ በእራት ፕሮግራሙ ላይ እንደተናገሩት የባለሀብቱና የአካባቢው ነዋሪ ተሳትፎ ስራው ከታሰበበት ቀን ጀምሮ በልዩ ሁኔታ ተጠናክሮ ቀጥሏል:: ይህ ደግሞ ለስራው ቅልጥፍና እና ለሚሰራው ሰው ትልቅ የሞራል ስንቅ ከመሆን አንፃር የጎላ ሚና እየተጫወተ ነው ብለዋል:: ሁሉም የተሰጠውን ሀላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ በተያዘው አግባብ ማመስገንና ማበረታታት ይቀጥላልም ብለዋል:: እራት ለጋበዙት ፍቅሬ ኮንስፖኛ ድርጅትም ምስጋና አቅርበዋል:: የአዲስ አበባ ከተማ ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ገዛኸኝ ዴሲሳ በበኩላቸው ይህ ትብብር ከቀጠለ በቦሌ በፒያሳና አራት ኪሎ የታየው ውብና ምቹ የከተማ ገፅታ እዚህም በቅርቡ ይደገማል:: የሚሰራውን ስራ ለማበረታታት እየተደረገ ያለው የእራት ግብዣና ሌሎችም ማበረታቻዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥሉና በሀላፊነት ስሜት ስራውን ከዳር ማድረስ እንደሚገባም አሳስበዋል:: በተያያዘ ዜና እለታዊ የስራ ግምገማም የኮሪደር ስራው አስተባባሪና በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በተገኙበት ተካሂዷል:: መስተካከል የሚገባቸውና ተጠናክሮ መቀጠል የሚገባቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል:: #laftocommunication ታህሳስ 3/2017አ.ም ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

በተሰራው የኮሪደር ልማት የትራፊክ አደጋዎችን መቀነስ ተችሏል ተባለ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ በተሰራው የኮሪደር ልማት ባለፉት አምስት ወራት የትራፊክ አደጋዎችን መቀነስ መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ ባለስልጣኑ ይህን ያለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮርደር መሰረት ልማት ጥምር ግብረ ሀይል የ5 ወራት የኮርደር መሰረት ልማት እቅድ አፈፃፀም ስራዎችን በግምገማ መድረክ ላይ ነው። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ክበበው ሚደቅሳ እንደገለጹት፡- በኮሪደር ልማት ስራ ለትራፊክ ፍሰት ምቹ ያልሆኑ መንገዶች እንዲስተካከሉ በማድረግ እና በተሰሩ አዳዲስ መንገዶችን ባለፉት አምስት ወራት የትራፊክ አደጋዎችን መቀነስ መቻሉን ተናግረዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በበኩላቸው አዲስ አበባን ውብ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ እና እንደስሟ አበባ ለማድረግ በኮሪደር ልማቱ የተጣለባቸውን አደራ ለመወጣት ቀን ከለሊት እጅ ለእጅ በመያያዝ በርካታ ስራውች መሰራታቸውን ተናግረዋል፡፡ በዚህም ባለፉት በ5 ወራት ጥምር ግብረ ሃይሉ በቅንጅት በሰራው ስራ 266 ድርጅትን እና 19 ሽህ በሚሆኑ ግለሰቦችን ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ በመውሰድ ከ103 ሚሊዮን ብር በላይ የማስተማሪያ ቅጣት በመቅጣት ወደ መንግስት ካዝና ገቢ መድረጉን ጠቅሰዋል፡፡ በግምገማ መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን፣የፅዳትና አስተዳደር ኤጀንሲ፣ የትራፊክ መኔጅመንት ባለስልጣን እና የግንባታ እና ፈቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን በቅንጅት የተሰሩ ስራዎችን በጋራ ገምግመዋል፡፡

ዛሬ በኢትዮዽያ የቻይና አምባሳደር የሆኑት ቼይ ሃይ እና የሲጂሲኦሲ ግሩፕ (CGCOC group) በተገኙበት የገርቢ የመጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክት ግንባታን በፍጥነት ማስጀመር በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ ጋር ተወያይተናል:: የገርቢ የመጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክት በ2008 ዓ.ም ከኤግዚም ባንክ በተገኘ ድጋፍ ይገነባል ተብሎ የታቀደ ቢሆንም ብድሩ እስከ ዛሬ ባለመለቀቁ ምክንያት ሳይጀመር በመዘግየቱ ከተማው አስተዳደር በራሱ በጀት ለመገንባት ወስኗል ። በከተማዋ ያለውን የውሃ ፍላጎትና አቅርቦትን ለማጣጣም የከተማ አስተዳደሩ በራሱ በጀት ለመገንባት ዛሬ ከቻይና ኤምባሲ እና ከ‍ኮንትራክተሩ ሲጂሲኦሲ ግሩፕ ጋር መግባባት ላይ ደርሰናል:: የከተማችንን የውሃ አቅርቦት እጥረትን ለመቅረፍ ከፍተኛ በጀት መድበን በመስራት ላይ የምንገኝ ሲሆን የገርቢ መጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክት ግንባታም ሲጠናቀቅ ይህንን ጥረታችንን ይበልጥ ውጤታማ እንደ ሚያደርግ እና ያለብንን የውሃ ፍላጎትና አቅርቦት አለመጣጣም ይበልጥ እንደሚፈታ እናምናለን:: ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ የተመራ የፌደራል ሱፐርቪዥን ቡድን የኤጀንሲውን የሪፎርም ስራ አፈፃፀም ጎበኘ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ የተመራና የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር በለጠ ሞላን ያካተተው የፌደራል ሱፐርቪዥን ቡድን በሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና መስርያ ቤት በመገኘት የሪፎርም ስራ አፈፃፀም ጉብኝት አድርጓል። በዕለቱ ኤጀንሲው እያከወነ ያለውን የተቋም ግንባታ ስራ ያለበትን ደረጃ ለሱፐርቪዥን ቡድኑ በኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ገለፃ ተደርጎላቸዋል። ዋና ዳይሬክተሩ በተቋም ግንባታው የከተማዋን የዲጂታል አገልግሎት የላቀ በማድረግ ስማርት ሲቲን ለመገንባት እየተሰሩ ያሉ የቴክኖሎጂ ማሻሻያ ስራዎችን እንዲሁም የሲቪል ምዝገባ ስርዓት ላይ ከጤና እና ፍርድ ቤቶች ጋር ያለውን ቅንጅት እንዲሁም የየዲጂታል አገልግሎት መቆራረጥን በአዲስ ስርዓት ተክቶ በመፍታት የተገልጋይ እርካታን ለማሻሻል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በተጨማሪነትም በከተማው ያለውን የፋይዳ ምዝገባ አሁናዊ ሁኔታ አቅርበዋል። ዶ/ር ፍፁም በተቋሙ የመጣው ለውጥ ለሌሎች ተቋማት ልምድ የሚሆን መሆኑን ገልፀው የሲቪል ምዝገባ ስርዓት በተሻለ ቴክኖሎጂ መሰረት ላይ እንዲገነባ አዲስ አበባ የወሰደችውን ቆራጥ እርምጃ አድንቀው የዘርፉ መጠናከር ለሃገሪቱ የልማት እቅድ የሚኖሩው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል። ሚኒስትሯ ተቋሙ ያሳየው ለውጥ ተገልጋይ ጋር ሊመነዘር የሚችል የአገልግሎት እርካታ ማምጣት እንዲችል የተጀመሩ የቴክኖሎጂ ስራዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁና የተሟላ ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት ጥረት ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ላይ የተሰራውን ስራ አበረታች መሆኑን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር በለጠ ሞላ ያነሱ ሲሆን አክለውም ሪፎርሙ የተመራበትን መንገድ እንዲሁም ቴክኖሎጂን ለመተግበር በከተማው የተወሰደው ቁርጠኝነት የሚበረታታ መሆኑን ገልፀዋል። አምስት ሚልዮን ኮደርድን ለማፍራት በተጀመረው ፕሮግራም በቅርቡ ኤጀንሲው የወሰደውን ቁርጠኝነት ተምሳሌት አድርጓ መስርያ ቤታቸው የወሰደ መሆኑን ያስታወሱት ዶ/ር በለጠ በዘርፉ አስፈላጊውን ድጋፍ ሚኒስትር መስርያ ቤታቸው የሚያደርግ መሆኑን ቃል ገብተዋል። ክቡር አቶ አብርሃም ታደሰ የከተማው ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ በከተማው እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለቡድኑ እያስጎበኙ ያለ ሲሆን ተቋማትን ለመቀየር በከተማው እየተደረገ ያለውን ጥረት በኤጀንሲው ተገኝተው ከዋና ዳይሬክተሩ ጋር አስጎብኝተዋል። ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ በነፃ የስልክ መስመር 7533 ይደውሉ ታህሳስ 3/2017 ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቱርክ የነበራቸውን ስብሰባዎች አገባደው ዛሬ ጠዋት አትዮጵያ ገብተዋል:: Prime Minister Abiy Ahmed having concluded his meetings in Türkiye, has arrived in Ethiopia this morning. #PMOEthiopia

የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ድርድር በስምምነት ተጠናቀቀ በቱርክ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን አደራዳሪነት በአንካራ ለሶስተኛ ጊዜ የተካሄደው የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ድርድር ሁለቱንም አገራት በሚያግባባ ስምምነት ተጠናቅቋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ግብዣ ትናንት ምሽት በአንካራ ውይይት አድርገዋል፡፡ ሁለቱ መሪዎች ውይይቱን ካደረጉ በኋላም በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል። መሪዎቹ በመግለጫቸውም፤ ኢትዮጵያ በሶማሊያ የባሕር ዳርቻ በኩል ዘላቂ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ የወደብ አማራጭ በምታገኝበት አማራጭ ላይ የቴክኒክ ውይይቶችን ለመጀመር መስማማታቸውን ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመግለጫቸው፤ ቱርክ በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እንዲሰፍን ለምታደርገው ከፍተኛ አስታዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የኢትዮጵያና የሶማሊያ ህዝቦች በቋንቋ፣ በባህል እና በደም የተሳሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ኢትዮጵያ ለጋራ ሰላምና ልማት ከሶማሊያ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗንም ተናግረዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በበኩላቸው፤ የሶማሊያ መንግስት የኢትዮጵያ ወታደሮች ለሶማሊያ ሰላም የከፈሉትን መስዋዕትነት አይዘነጋም ሲሉ ገልፀዋል፡፡ ሁለቱ ሀገራት በቀጣይም ሰላምን ለማፅናት በሚያደረጉት ጥረት መንግስታቸው ቁርጠኛ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን በበኩላቸው፤ ሁለቱ ሃገራት የፈረሙት ሰነድ ትብብርን፣ የኢኮኖሚ እድገትን እና ብልጽግናን የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ AMN-Addis Media Network ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ለህዝባችን የገባነውን ቃል ወደ ተግባር በመቀየር የከተማችንን ልማት ለማፋጠን ቀን ከሌሊት መስራት ይገባል"!!-ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ፥ከከተማ፣ ከልደታ እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ አመራሮች፣ ከመሠረተ ልማት አስተግባሪ ተቋማት ተወካዮችና አማካሪዎች ጋር ከካርል አቦ ማዞሪያ ፤ከመከኒሳ ወንዝ እስከ ፋሪ አደባባይ እንድውም ከሳር ቤት አረቄ ፋብሪካ የሚዘልቀው እየተፋጠነ የሚገኘውን ሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ስራ የደረሰበትን ደረጃ በመገምገም በቀጣይ በሚሰሩ ተግባራት ዙሪያ አቅጣጫ አስቀመጡ። በውይይቱ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታን ጨምሮ የከተማ ከፍተኛ አመራሮች፣ የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ፥የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ካባ መብራቱ ና የሁለቱም ክ/ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም አማካሪዎች ተገኝተዋል። Lideta sub-city communication office ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ለህዝባችን የገባነውን ቃል ወደ ተግባር በመቀየር የከተማችንን ልማት ለማፋጠን ቀን ከሌሊት መስራት ይገባል"!!-ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ፥ከከተማ፣ ከልደታ እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ አመራሮች፣ ከመሠረተ ልማት አስተግባሪ ተቋማት ተወካዮችና አማካሪዎች ጋር ከካርል አቦ ማዞሪያ ፤ከመከኒሳ ወንዝ እስከ ፋሪ አደባባይ እንድውም ከሳር ቤት አረቄ ፋብሪካ የሚዘልቀው እየተፋጠነ የሚገኘውን ሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ስራ የደረሰበትን ደረጃ በመገምገም በቀጣይ በሚሰሩ ተግባራት ዙሪያ አቅጣጫ አስቀመጡ። በውይይቱ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታን ጨምሮ የከተማ ከፍተኛ አመራሮች፣ የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ፥የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ካባ መብራቱ ና የሁለቱም ክ/ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም አማካሪዎች ተገኝተዋል። Lideta sub-city communication office ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et