fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን በሰጡን ኃላፊነት መሰረት ዛሬ በጎንደር ከተማ ተገኝተን በፍጥነት ያስጀመርነው የኮሪደር ልማት ስራ ያለበትን ደረጃ ጎብኝተናል። የኮሪደር ልማት ስራው 12 ኪ.ሜ ርዝመት አለው። በዋነኛነት ከኤርፖርት እስከ መሃል ከተማ ፒያሳ፣ ፋሲል ግንብ ዙሪያን እንዲሁም ፒያሳ አካባቢ የማደስ ስራን ያካተተ ሲሆን የህዝቡ ተባባሪነት ከፍተኛ በመሆኑ በፍጥነት እየተሰራ ይገኛል። የጎንደር ከተማ ጥንታዊ እና ታሪካዊ ከተማ እንደመሆኗ በኮሪደር ልማት ስራችን ህንፃዎችን እና ታሪካዊ ቦታዎችን በማደስ የቱሪስት መስህብነቷ ይበልጥ እንዲጨምር የምንሰራ ይሆናል። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን በሰጡን ኃላፊነት መሰረት ዛሬ በጎንደር ከተማ ተገኝተን በፍጥነት ያስጀመርነው የኮሪደር ልማት ስራ ያለበትን ደረጃ ጎብኝተናል። የኮሪደር ልማት ስራው 12 ኪ.ሜ ርዝመት አለው። በዋነኛነት ከኤርፖርት እስከ መሃል ከተማ ፒያሳ፣ ፋሲል ግንብ ዙሪያን እንዲሁም ፒያሳ አካባቢ የማደስ ስራን ያካተተ ሲሆን የህዝቡ ተባባሪነት ከፍተኛ በመሆኑ በፍጥነት እየተሰራ ይገኛል። የጎንደር ከተማ ጥንታዊ እና ታሪካዊ ከተማ እንደመሆኗ በኮሪደር ልማት ስራችን ህንፃዎችን እና ታሪካዊ ቦታዎችን በማደስ የቱሪስት መስህብነቷ ይበልጥ እንዲጨምር የምንሰራ ይሆናል። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በህብር የፀናች ሀገር በህብረተሰብ ተሳትፎ የምትፀዳ ከተማ አዲስ አበባ" በሚል መሪ ሀሳብ በየካ ክፍለ ከተማ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት የፅዳት ንቅናቄ ተካሄደ ጳጉሜ 4/2016 ዓ.ም የየካ ክ/ከተማ ዋና ስራ አሰፈፃሚ አቶ ብርሀኑ ረታ፣የአዲስ አበባ ስራ አስኪያጅ አማካሪ አቶ ይብሬ ኢስማኤል እንዲሁም የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሙሉ ገዳሙ በየካ ወረዳ 05 በየካ ክ/ከተማ ቅጥር ግቢ ጀርባ ተገኝተው ፅዳቱን አስጀምረዋል። በመርሃግብሩ ላይ የክፍለ ከተማና የ12ቱም ወረዳ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል። የፅዳት ንቅናቄ መርሀ ግብሩ “በህብር የፀናች ሀገር በህብረተሰብ ተሳትፎ የምትፀዳ ከተማ አዲስ አበባ" በሚል መሪ ሀሳብ በየካ ወረዳ 05 ከያከ ክ/ከተማ ቅጥር ግቢ ጀርባ ጀምሮ ከመገናኛ እስከ እንግሊዝ ኢምባሲ በላይ እና በታች የኮሪደር ልማቱ ፅዳት ተከናውኖል። ፅዳት እና ውበት የስልጣኔ ምልክት መሆኑን እና ባለፉት ጊዜያት አዲስ አበባን ውብ እና ፅዱ የማድረግ ስራ በማህበሩ ተሳትፎ እውን ማድረግ መቻሉን አቶ ብርሀኑ ገልፀዋል። አቶብርሀኑ አክለውም በህብር ቀን አከባቢያችንን ከማፅዳት ባለፈ በጋራ አንድነታችንን በማረጋገጥ ጥላቻን እና ዘረኝነትን ጠርገን እያስወጣን አዲሱ አመትን በአንድነት እና በፍቅር እንቀበል በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል። የአዲስ አበባ ስራ አስኪያጅ አማካሪ አቶ ይብሬ ኢስማኤል በበኩላቸው የካ ክ/ከተማ በቅርብ ግዜያት በኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ከተከናወነባቸው ክ/ከተማዎች አንዱ እደመሆኑ መጠን አከባቢውን ፅዱ እና ውብ አድርጎ የማስቀጠል ስራ በፅዳት አስተዳደር ሰራተኞች እና በክ/ከተማው ነዋሪዎች እየተከናወነ ስለሆነ ለሁሉም ተሳታፊ አካላት ታላቅ ምስጋና ይገባል ብለዋል፡፡ የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሙሉ ገዳሙ በፅዳት መርሀ ግብሩ የተገኙ እግዶችን እንኳን ደህና መጣችሁ መልእት ያስተላለፉ ሲሆን በህብር ቀን በጋራ ተሰባስበን አከባቢያችንን በጋራ በማፅዳት መጪው ዘመንን ከተማችንን ብሎም አከባቢችንን ውብ እና ፅዱ አድርገን እንቀበላለን ብለዋል፡፡ Yeka Communication-የካ ኮሙኒኬሽን ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

#የኅብር ቀን #ኅብራችን ለሰላማችን በአብሮነት የኮልፌ ክፍለ ከተማን ውብና ማራኪ ከማድረግ ጎን ለጎን ለሀገር ሰላምና ብልፅግና በጋራ መቆም እንደሚያስፈልግ ተገለፀ፡፡ ጳጉሜ 4/2016 ዓ.ም በዛሬው ዕለት የጳጉሜ 4 የኅብር ቀንን ምክንያት በማድረግ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ፅዳት አስተዳደር በአየር ጤና ሁለተኛና የመሰናዶ ትምህርት ቤት ቅጥር ዙሪያ የፅዳት ንቅናቄ ዘመቻ መርሀ-ግብር ተካሂዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ አቶ አለማየሁ ፍቃዱ የኮልፌ ክፍለ ከተማ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ለአንድ ከተማ ውበትና ፅዳት ወሳኝ በመሆኑ የክፍለ ከተማ አስተዳደሩ ለጽዳት ተግባር ልዩ ትኩረት በመስጠት ስራዎችን እየሰራ ይገኛል በተሰሩትም የጽዳት ተግባራት የተለያዩ ለውጦች መተዋል ያሉ ሲሆን እነዚንህም አጠናክሮ መቀጠል ተገቢ ነው ብለዋል። አቶ አለማየሁ አክለውም በአብሮነት የክፍለ ከተማውን ውብና ማራኪ ከማድረግ ጎን ለጎን ለሀገር ሰላምና ብልፅግና በጋራ መቆም እንደሚያስፈል አስታውቀው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ደረጀ ደበበ እንዳሉት የዛሬው የፅዳት ንቅናቄ እኛ ኢትዮጵያውያን የመተባበራችንና የመደመራችን አንዱ ማሳያ ነው ያሉ ሲሆን ሁላችንም ለነዋሪዎቻችንና ለተማሪዎቻችን ውብና ማራኪ የሆኑ አካባቢዎችን መፍጠር አለብን ብለዋል። የፅዳት መርሀ-ግብሩ ላይ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች፣የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች፣የደንብ ማስከበር አባላት ፣የመንገድ ጥርጊያ ባለሙያዎችና የሽርክና ማህበራት በተገኙበት ተካሂዷል። Kolfe Keranio Communication /ኮልፌ ቀራኒዮ ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

በህብር የፀናች ሀገር በህብረተሰብ ተሳትፎ የምትፀዳ ከተማ አዲስ አበባ በሚል መሪ ቃል የፅዳት ንቅናቄ መረሃ-ግብር ተካሄደ!" ጳጉሜ 04/2016 ዓ.ም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት አስተባባሪነት "በህብር የፀናች ሀገር በህብረተሰብ ተሳትፎ የምትፀዳ ከተማ አዲስ አበባ!!" በሚል መልዕክት በዛሬው ዕለት በወረዳ 8 አስተዳደር የፅዳት ንቅናቄ መርሀ-ግብር ተካሄዷል። በፅዳት የንቅናቄ መርሀ-ግብሩ ላይ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ዮሀንስ ለገሰ ጨምሮ የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮች፤የክ/ከተማው ነዋሪዎች እንዲሁም የፅዳት አባሳደሮች ተሳትፈዋል። የክ/ከተማው ፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በየነ ቱሉ በበኩላቸው የጳጉሜ ቀናትን በተለያዩ ስያሜና መርሀ-ግብር ሲከበር እንደቆየ ገልፀው፤ በዛሬው ዕለትም የህብር ቀንን በማስመልከት የፅዳት ዘመቻ መካሄዱን ገልፀዋል። በጋራ ሆነን ክ/ከተማችንን ብሎም አዲስ አበባ ከተማን እናፀዳለን፤ ቆሻሻን በተገቢው መንገድ ካስወገድና ካስተዳደርነው ሀብት መሆኑን በመገንዘብ ህብረተሰቡም የመልሶ መጠቀም ኡደትን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ አስታውቀዋል። የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ዮሀንስ ለገሰ በንቅናቄ መረሃ-ግብሩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ጳጉሜ 4 የህብር ቀንን በማስመልከት በከተማ ብሎም በክፍለ ከተማ ደረጃ ዘርፈ ብዙ ስራዎች የሚከናወኑ መሆኑን ጠቁመው የዛሬው የፅዳት ዘመቻ መረሃ-ግብርም የዚሁ አንዱ አካል ነው ብለዋል። ኃላፊው አያይዘውም በህብር ከተባበርንና ከተጋገዝን የማንሻገር ፈተና የማናስመዘግበው ስኬቶች አለመኖራቸውን ጠቁመው ቆሻሻን በጋራ በማፅዳት አደስ አበባን እንደስሟ ፅዱ ውብ ለነዋሪዎቿ ምቹ ከተማ ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል። Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ማዕድ ማጋራት የሀገር ወዳድነት ምልክት፤ የወዳጅነት ውብ ማስታወሻ ነው። ማዕድ ማጋራት አንጡራ ባህላችን ነው። ካለን ላይ እናጋራ፤ ደስታን እንጋራ፣ እርስ በርሳችን እንደጋገፍ፤ በዓሉን በኀብረት ካለችን ለሌለው እያካፈልን ልባችንን እና ነፍሳችንን የሚመግቡ ትውስታዎችን በመፍጠር እናሳልፍ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አሕመድ

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳደር የጳጉሜ 4 የህብር ቀንን ምክንያት በማድረግ የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ፡፡ ጳጉሜ 4-2016ዓም የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጳጉሜ 4 የህብር ቀን ‘’ኅብራችን ለሰላማችን’’ በሚል መሪ ቃል የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል የተወጣጡ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ፅዳት ዘመቻ በወረዳ 3 ተካሂዷል። የአካባቢ ፅዳት ስራ የሁሉም ሰው የእለት ተለት ተግባር መሆን አለበት ያሉት የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ትኩ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ዉብና ማራኪ፤ ለስራና ለኑሮ ምቹ ለማድረግ እየተሰራ ላለው ስራ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡ አቶ ሙስጠፋ አክለው አካባቢን ከማፅዳት ጎን ለጎን የቆሸሹ አስተሳሰቦችን በማፅዳት መጪውን አዲስ አመት በንፁህ አካባቢ እና አስተሳሰብ ልንቀበል ይገባል ብለዋል፡፡ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ገመቹ ደፋሩ በበኩላቸው መጪው አዲስ አመት በህብረት የአካባቢያችን ፅዳትና ውበት መጠበቅ ከሁሉም ህብረተሰብ ክፍል የሚጠበቅ ኃላፊነት በመሆኑ ህብረተሰቡ አካባቢውን በቋሚነት እንዲያፀዳ አሳስበዋል፡፡ Addis Ketema Communication-አዲስ ከተማ ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ኅብራችን ለሰላማችን በሚል መሪ ሀሳብ ጳጉሜ 4 የህብር ቀንን ምክንያት በማድረግ የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ኅብራችን ለሰላማችን ጳጉሜ 4 የህብር ቀንን ምክንያት በማድረግ የክፍለ ከተማ አጠቃላይ አመራሮችና ፣የወረዳ 8 አመራሮች እና የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ወረዳ 8 ሎው ኮስት ቤቶች ግንባታ አካባቢ ፅዳት ዘመቻ ተካሂዷል ። በእለቱ በክብር እንግድነት ተገኙት የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ እና ስራና ክህሎት ፅ/ኃላፊ አቶ ልመንህ ምህረቱ ኅብራችን ለሰላማችን በሚል መልዕክት እየተከበረ የሚገኘው ጳጉሜ 4 ህብር ቀንን በህብረት ለአካባቢያችን ፅዳት እና ውበት በጋራ በመቆም ለመኖር ምቹ፣ መተሳሰብ እና አብሮነት የሰፈነበት ለማድረግ ህብረታችን ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል። የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ወንድማገኝ ታደሰ በበኩላቸው መጪው አዲስ አመት በህብረት የአካባቢያችን ፅዳትና ውበት መጠበቅ ከሁሉም ህብረተሰብ ክፍል የሚጠበቅ ኃላፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል ። Lemi Kura Communication ለሚ ኩራ ጳጉሜ 4/2016ዓ.ም ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et