fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
ጷጉሜ 4: " የህብር ቀንን " ኅብራችን ለአንድነታችንና ለዘላቂ ሰላማችን! በሚል መርህ ክፍለ ከተማችንን በማፅዳት ጀምረናል። ********************* በቂርቆስ ወረዳ 09 አስተዳደር ጷጉሜ 04/2016: " የህብር ቀን " ኅብራችን ለአንድነታችንና ለዘላቂ ሰላማችን! በሚል መሪ ቃል የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት አቶ አብዱልሀዲ ረሺድ የወረዳው ም/ዋና ስራአስፈፃሚና የስራ ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ አድማሱ እና ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አለምፀሐይ አያሌው እንዲሁም የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስቻለው ገመቹ ፣ የወረዳው አመራር ፣ በርካታ ወጣቶች ፣ ነዋሪዎች እንዲሁም የፅዳት አስተዳደር ሰራተኞች በተገኙበት በድምቀት እየተከበረ ነው። "የህብር ቀን " ሲከበር በወረዳችን በማለዳው 12:30 ጀምሮ ብሎክን ማዕከል ያደረገ የፅዳት ዘመቻ በማካሄድ ህብረተሰቡ ፅዳትን ባህሉ በማድረግ አካባቢውን በማፅዳት የግል እና የአካባቢውን ፅዳት መጠበቅ የህብረታችን ማሳያ ፣ አንድነታችን ውበታችን መሆኑን አሳይቷል። የእለቱ ሌሎች መልዕክቶች :- • “ኅብር - የትናንትም የዛሬም የነገም ስኬት ሚስጥራችን” ነው • “ኅብር ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት” • “ኅብራችን ተፈጥሮአዊ ፀጋችን ነው” • “ኅብራችን ውበታችን ነው’’ የሚሉት ድምፆች በአሉን አድምቀውታል። Kirkos Communication-ቂርቆስ

ጳጉሜን 4 የኅብር ቀንን ምክንያት በማድረግ በቦሌ ክፍለ ከተማ የጽዳት ንቅናቄ ተካሄደ፡፡ በወረዳ 6 በተካሄደው የጽዳት ንቅናቄ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ ባደረጉት ንግግር “የኅብር ቀን ኅብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነትን ለማጠናከር በጋራ የምንነሳበትና ቃላችንን የምናድስበት ቀን ነው” ብለዋል፡፡ የከተማዋን ጽዳት ለመጠበቅ ኅብረተሰቡ የጋራ ኃላፊነት እንዳለበት ያስገነዘቡት ወ/ሮ ቆንጂት፣ በጽዳት ባለድርሻ አካላትና አጋሮች ከሚካሄደው የጽዳት እንቅስቃሴ በተጨማሪ ኅብረተሰቡም ግዴታውን በአግባቡ እንዲወጣ የሕግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ በመግባቱ ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን በመግለጽ በአዲሱ ዓመት የኮሪደር ልማትን ጨምሮ የተከናወኑ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ለታለ… See more

ዛሬ ማለዳ አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ከ500 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች፣ የሀገር ባለውለታዎች እና በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ የመንግስት ሰራተኞች ማዕድ አጋርተናል። የምናጋራው ማዕድ ብቻ ሳይሆን ለወገኖቻችን ያለንን ፍቅርና አክብሮት ጭምር ሲሆን ማዕድ ማጋራቱ ወገኖቻችን በዓሉን በደስታ እንዲያከብሩት የሚረዳ ነው። የመንግስትን የሰው ተኮር ፖሊሲ አቅጣጫ እና ጥሪ በመቀበል ሰርተው ካገኙት ለወገኖቻቸው ማካፈልን ባሕል ላደረጉ የከተማችን ልበ ቀና ባለሀብቶች እና በጎ ፈቃደኞች እንደሁልጊዜው ሁሉ መስጠት አያጎድልምና ለወገኖቻችሁ ለምታደርጉት በጎነት ሁሉ በራሴና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በመዲናችን እየተገነባ ያለው ግዙፍ የመሠረተ ልማት በዘላቂነት ሊጠበቅ የሚችለው በሁሉም የከተማችን ነዋሪዎች ዘንድ ጽዳትን ቋሚ ባህል ማድረግ ሲቻል ነው- ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ጳጉሜን 4/2016 ዓ.ም ጳጉሜን 4-የኅብር ቀንን ምክንያት በማድረግ "ኅብራችን ለሰላማችን "በሚል መሪ ቃል የፅዳት መርሐ ግብር በጉለሌ ክ/ ከተማ ተከናውኗል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት መልእክት ጽዱ አካባቢን መፍጠር የስልጣኔ መገለጫ ነው ሲሉ ገልፀው የከተማዋን ጽዳት በዘላቂነት ለማስጠበቅ የአስተሳሰብና የአመለካከት ለውጥ ለማምጣት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል። ፅዳት ከአስተሳሰብ ለውጥ የሚጀምር በመሆኑም ከዘመቻ ስራ ያለፈ በዘላቂነት ሊተገበር የሚገባ ተግባር መሆኑን አመልክተዋል፡፡ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ በበኩላቸው በመዲናዋ በተሰሩ የፅዳት ስራዎች አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብና ጽዱ ማድረግ መቻሉን ገልፀው ይህም በህብረት በመሰራቱ የተገኘ ውጤት መሆኑን አስገንዝበዋል። የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ወገሴ እንደተናገሩት የአካባቢን ውበት ከመጠበቅ አንፃር የክፍለከተማው ነዋሪዎች ምሳሌ የሚሆን ተግባር ሲፈፅሙ መቆየታቸውን በመግለጽ ይህ ተግባር ተሸላሚ በመሆን ተረጋግጧል ሲሉም አውስተዋል። ህብረብሄራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነትን በማጠናከር የከተማችንን ልማት እናስቀጥላለንም ብለዋል፡፡ በመርሐግብሩ “በአግባቡ የተያዘ ቆሻሻ ሀብት ነው” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀምን የሚያሳይ ኤግዚቢሽንም ቀርቧል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ኢትዮጵያ የብዙ ብሔሮች፣ የብዙ ቋንቋዎች፣ የብዙ ባህሎች፣የብዙ እምነቶች፣ የብዙ ሥልጣኔዎች፣ የብዙ ጀግኖች፣ ሀገር ናት። ኢትዮጵያ ኅብር ናት። ሁሉም የኛ በእኛ ለእኛ የተሰጡ ናቸው። ሁሉን እናከብራለን፤ በሁሉም እንኮራለን። ኅብረ ብሔራዊነታችን መልካችን፣ አንድነታችን ደግሞ ህልውናችን ነው። እነዚህ ኅብራዊ ጸጋዎች በአንዲት ሀገር በኢትዮጵያ የሚገኙ ናቸው። ዓላማችን አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ መገንባት ነው። ግባችን የኢትዮጵያ ብልጽግና ነው። ይህ ነው አንድነታችን። የተበታተንን ኅብሮች አይደለንም፤ የተጨፈለቅን አንድ ዓይነቶችም አይደለንም። እኛ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ያለን ኢትዮጵያውያን ነን። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ

ዛሬ ጳጉሜ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ከንጋቱ 11:57 ሰዓት ላይ በጉለሌ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 8 ጽዮን ሆቴል ጀርባ ከከፍታ ቦታ ላይ በአጋጠመ የመሬት መንሸራተት በመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት አድርሷል። በአደጋዉ ከከፍታዉ ስር ከነበሩ ቤቶች መካከል በአምስት ክፍል መኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን በሰዉ ላይ ምንም ጉዳት አልደረሰም። ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ! ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የአዲስ አበባ ህዝብ ጎህ ሳይቀድ በዝናብ ዉስጥ ፤የሚደንቅ የሀገር ፍቅር ጳጉሜ 3 በሉዓላዊነት ቀን!

አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ ክፍለከተሞች የተገነቡ 837 መኖሪያ ቤቶችን ለአቅመ ደካሞች እና ለሀገር ባለውለታ ነዋሪዎቻችን አስተላልፈናል። በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገንብተው ለነዋሪዎች ከተላለፉ ቤቶች ውስጥ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በየካ ክፍለ ከተማ 54 ቤቶችን የገነባ ሲሆን ለዚህም ክብርት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚልን አመሰግናለሁ። እንዲሁም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ በተለያዩ ባለሀብቶች 108 ቤቶች፣ በአራዳ ክፍለከተማ በአብዱለጢፍ ዑመር ፋውንዴሽን (አሚባራ ግሩፕ) 32 ቤቶች ተገንብተዋል። ሁሉንም ቤቶች ለነዋሪዎች አስተላልፈናል። ነዋሪዎች አዲስ ዓመትን በአዲስ ተስፋ እንዲጀምሩ ትልቅ አስተዋፅዖ ያበረከታችሁ ተቋማት እና የከተማችን ልበ ቀና ባለሃብቶችን በራሴ፣ በከተማ አስተዳደሩ እና በነዋሪዎቹ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ሀገራችን ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷ ሳይደፈር በነፃነት የኖረች ሃገር ናት" ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጳጉሜ 3 የሉዐላዊነት ቀን "ኅብር ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት!" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በደመቀ ሥነ-ስርዓት ተከብራል። በእለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሀገራችን ኢትዮጵያ በልጆቿ ደምና አጥንት ሉዓላዊነቷ ሳይደፈር በነፃነት የኖረች ሃገር ናት ብለዋል። ሀገር በነፃነት ተከብራ ስትኖር ልማታችን ይቀጥላል ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለሃገራችን ሉዓዋላዊነት እና ክብር ከውጪ የሚቃጣባት ጥቃት በልጆቿ ደምና አጥንት ያለአዳች ማመንታት ሉዓላዊነቷ ሲከበር መቆየቱን ተናግረዋል። አያይዘውም የሀገራችን ነፃነት እና ሉዓላዊነት ለማስከበር ከተለያዩ ግጭቶች ሃገራችን በማስከበር ብቻ አለመሆኑን የጠቆሙት ከንቲባ የሀገራችን ሉዐላዊነት የተሟላ እንዲሆን በኢኮኖሚ እራሷን የቻለችና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ሁላችንም በትጋት በመረባረብ መስራት እንደሚጠበቅብን ጭምር አሳስበዋል። እስከዛሬ በርካታ እዳወችን ስንከፍል ቆይተናል ከዚህ በኃላ ለትውልዱ እዳ ሳይሆን ምዳን ለማስተላለፍ መስራት እንደምንችል በርካታ ማሳያ የሆኑ ስራወችን በመስራት ውጤታማ መሆን መቻላቸውንም ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አሰተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በበኩላቸው በለውጡ መንግስታችን ሃገራችን ኢትዮጵያዊ እና ከተማችን አዲስ አበባን መምራት ከጀመረበት ጀምሮ ባፉት አመታት የአገራችን ሉአላዊነት ከመጠበቅ አኳያ የውጭ እና የውስጥ ጫናዎችን በመቋቋም በርካታ ድሎች መመዝገባቸውን ተናግረዋል። የኢትዮጵያን አንድነትና ሉዓላዊነት አደጋ ላይ ለመጣል አቅደው የሚሰሩ ሀይሎች እየተጉ ያሉበት በመሆኑ የሀገራችን እና የአካቢያችን ሰላም እንዚህ ቀደሙ ለመጠበቅ ከፀጥታ አካላት ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘንና ተቀናጅተን መስራታችንን የበለጠ አጠናክረን መጠበቅ አለብን ሲሉም ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ ጥሪያቸውን አቅርበዋል ።