fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید 👈

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
ከተማ አስተዳደሩ ባለፉት 6 ወራት ያሳካቸዉ የፕሮጀክቶች አፈፀፀም በተመለከተ፤- 👉ፕሮጀክቶች በፍጥነት ጀምሮ የመጨረስ ባህልን በማዳበር ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን መሰረተ-ልማቶች፤ዲዛይንና ግንባታን በማከናወን የህበረተሰቡን ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ባቀድነው መሰረት 217 ግንባታዎችን ማጠናቀቅ ተችሏል፡፡ 👉ለአብነት፡-ልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ህንጻ፣ ት/ቤቶች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ የአስተዳደር ህንፃዎች ፣የተለያዩ ስፖርት ማዘውተሪያዎች፣ አቃቂ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ምዕራፍ አንድ፣ የሼድ ግንባታዎችና የየካቲት 12ሆስፒታል እድሳት እና መሰል ፕሮጀክቶች ሙሉ ለሙሉ ተጠናቅቀዋል፡፡ 👉በተለያየ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ የሚገኙትም፤-ሃይሌ ጋርመንት የግብርና ምርቶች የገበያ ማዕከል ግንባታ 98% ፣የህፃናትና ወጣቶቸ ቴያትር ምዕራፍ ሶስት 81.25 %፤ራስ ደስታ ሆስፒታል B+ጂ+5 ህንፃ የእድሳት ስራ 87.5% ፣ኮልፌ አጠቃላይ ሆስፒታል 82%፣ ላፍቶ ሆስፒታል 80%፣ ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል 85%፣ ዘውዲቱ ሆስፒታል 71% ግንባታቸዉን ማድረስ ተችሏል፡፤ 👉ከሜጋ ፕሮጀክቶች አንፃር የአዲስ አለም አቀፍ ኤግዝብሽንና ኮንቬንሽን ማዕከል ግንባታዉን ማጠናቀቅ ተችሏል። 👉ይህ ግዙፍ ማዕከል ከተማችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮንፍረንስና ኤግዚቢሽን ተመራጭና ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችል ከመሆኑም ባሻገር የከተማዋን ብሎም የሀገራችንን ገፅታ በመቀየር ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው የጎላ ይሆናል። 👉እንዲሁም 13 ነባር ትላልቅ ሜጋ ፕሮጀክቶች በተለያየ የአፈፃፀም ደረጃ ላይ የሚገኙ ሲሆን ለአብነትም የትራንስፖርት ቢሮ ሕንፃ ግንባታ 67.88%፤ አዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ግንባታ 76.11%፤ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪያ ክላስተር ግንባታ ሎት 3 / 93.6%፤ ሎት 153 % የካ 2 G+5 መኪና ማቆሚያ ግንባታ 97.5% ተጠቃሽናቸዉ፡፡ 👉 ፕሮጀክቶቹ ግንባታቸው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በከፍተኛ ሁኔታ የከተማውንና የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች የሚያቃሉ በመሆናቸዉ ባልተጠናቀቁት ላይ በተያዘላቸው በጀትና ጊዜ ልዩ ትኩረት በመስጠት በፍጥነት እንዲጠናቀቁ ይደረጋል ተብሏል፡፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ከተማ አሰተዳደሩ በ6 ወራት ህዝቡን የሰላም ባለቤት ከማድረግ አኳያ 👉በበጀት አመቱ 6 ወራት ህዝብን የሰላም ባለቤት ከማድረግ አኳያ፣ በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ ህዝቡ በሰላም ሰራዊት ተደራጅቶ አካባቢውን መጠበቅና ህገወጥ ድርጊቶችን የመከላከል ስራ አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ 👉ከፌዴራልና ከአጎራባች ሸገር ከተሞች ጋር ጠንካራ ቅንጅታዊ አሰራር በመፍጠር የወንጀልና ህገ-ወጥ ድርጊቶችን በመከላከልና በመቆጣጠር የወንጀል ምጣኔ ከመቀነስ አኳያ ከህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር፤ከህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ከኢኮኖሚ አሻጥር ከዝርፊያ ከሽብርና ደረቅ ወንጀሎች ጋር የተያያዙ ከ4687 በላይ የወንጀል ድርጊቶች ላይ የመከላከልና ህጋዊ እርምጃ የመውሰድ ስራ የተሰራ ሲሆን በት/ቤት ዙሪያና ከት/ት ተቋማት ውጭ የሚገኙና ለጸጥታ ስጋት በሆኑ 2919 አዋኪ ድርጊቶች ላይ እርምጃ በመውሰድ ተችሏል፡፡ 👉በአጠቃላይ የአደባባይ ፕሮገራሞችና ኩነቶች በሰላም እንዲከበሩ ከማድረግ በተጨማሪ የከባድ ወንጀል ምጣኔ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ33 በመቶ እንዲቀንስ ተደርጓል፡፡ የደንብ መተላለፍና ተያያዥ ህገ-ወጥ ተግባራትን በመከታተል፣ በመቆጣጠርና እርምጃ ከመውሰድ አንፃር 2464 ህገወጥ ግንባታዎች ላይ፣ 108 ህገ-ወጥ ንግድን፣ ህገ-ወጥ ደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድን መቆጣጠርና ደንብ ማስከበር ተችሏል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከተማ ሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት በተመለከተ 👉የሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማትን በተመለከተ፦ በቂ ዝግጅት የተደረገበትና የመጀመሪያውን ኮሪደር ልማት አፈፃፀም ልምዶችንና የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮዎች ከነባራዊ ሁኔታችን ጋር በመቀመር/ በማስተሳሰር በፍጥነትና በጥራት 24/7 እየተተገበረ ይገኛል። 👉 ከልማት ተነሽዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር ወይይቶችና በመፍጠር እንዲሁም ክፍተቶችና ቅሬታዎችን ገለልተኛነት መፍትሄ የሚሰጥ አደረጃጀት በመፍጠር የተመራ ስራ ነው። ለመኖር ምቹ ካልሆነ ጎስቋላ መኖሪያ ቤቶችና አካባቢዎች ለተነሱ ነዋሪዎች 9ሺህ የሚደርሱ የመኖሪያ ቤቶችን፣ 1,402የመስሪያ ሼዶችን፣200የንግድ ሱቆችን ፤2124የመስሪያ ቦታዎች እና ወደ 3000 የሚደርሱት ደግሞ በኢንዱስትሪ ቋሚ ስራ እድል እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ እንዲሁም አረንጓዴና መጫዎቻ ቦታዎችን፣የጤናና የትምህርት ተቋማትን ጨምሮ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ማሟላት እንዲሁም የንግድ ሱቆችን ለነዋሪዎቻችን አስተላልፈናል። 👉የኮሪደር ልማቱ አዲስ አበባ በተሟላ የከተሜነት ፅንሰ ሃሳብና የመሰረተ ልማት ስርአት እንድትመራ የሚያደርግ ሲሆን በአጠቃላይ ስፋቱ 3515 ሄክታር የሚሸፍንና እና 136 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን፤በልማት ስራዎች ውስጥም የመንገድ ግንባታ፣ የአረንጓዴ ቦታዎች ግንባታ፣ የብስክሌት መንገድ፣ የእግረኛ መንገድ፣ የህፃናት መጫወቻዎች፣ የታክሲና አውቶቢስ መጫኛና ማውረጃ ተርሚናሎች፣ የመኪና ማቆሚያዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች፣የህፃናት መጫወቻ ቦታዎች፣ የህዝብ መጸዳጃ ቦታዎች፣ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮች፣ ደረጃውን የጠበቀ የከተማ መብራት፣ የቴሌኮም መሰረተ ልማት፣ የደህንነት መጠበቂያ ቴክኖሎጂዎች ዝርጋታ ስራዎችን በተቀናጀና በተናበበ መልኩ አየገነባን እንገኛለን።በተያዘለት ጊዜ፣በጀት/ ወጪና ጥራት የምናጠናቅቀው ይሆናል። 👉ስራው በዋናነት በከተማው አቅም እና በጀት እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን ፤ ኢትዮ ቴሌኮም፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፤ የመብራት አገልግሎት እና የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን መሰረተ ልማታቸውን በመዘርጋትና ከተማዋን ስማርት ሲቲ በማድረግ በኩል ትልቅ እገዛ እያደረጉ ይገኛሉ። 👉በኮሪደር ልማት ስራችን ፦ከልማቱ ማንም ወደ ኋላ ሳይቀር ሁሉም ተጠቃሚ እንዲሆን ያስቻልንበት፣የከተማችንን ደረጃ መሻሻል እና የተወዳዳሪነት አቅም የፈጠርንበት፣የሥራ ባህል መሻሻል 24/7፣ የይቻላል አስተሳሰብን ያዳበርንበት፣ የከተማችንን ገጽታ መቀየር/ ለሀገር ክብር አስተዋፅኦ ያደረግንበት የቻልንበት፣ የፕሮጀክት አመራርና የኮንትራት አስተዳደር አቅም ያሳደግንበት፣ የባለድርሻ አካላት አቅም እየጎለበተ የመጣበት ፣ የመሰረተ ልማት ተቋማት የቅንጀት እና ትብብር ደረጃ በዕጅጉ የተሻሻለበት፣ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል የተፈጠረበት ፣በቀጥታና በተዘዋዋሪ ሰፊ የገበያ ትስስር በመፍጠር ኢኮኖሚውን በማነቃቃት ለበርካታ ዜጎችን ፍትሐዊነት፣ተጠቃሚነት ያረጋገጥንበት ፣ የጥቃቅንና አነስተኛ ማኅበራት አቅም መጠናከር ሽግግር የፈጠርንበት እና የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ማሳደግ የቻልንባቸው ውጤታማ ስራዎች ናቸው፡፡ 👉በኮሪደር ልማቱ ሥራ ውስጥ የከፍተኛ አመራሩ ሀሳብ ከማመንጨት ጀምሮ ለተግባራዊነቱ በትጋት፣ በቁርጠኝነት፣ በጥብቅ ዲስፕሊን እና መሰጠት ክትትልና ድጋፍ የደረገበት አግባብ፤ ወደ ታች ወርዶ በፕሮጀክት ሳይት ፈጣን ዉሳኔ አየሰጠ መሄድ፣ ሰዉ ተኮር የሆኑ የልማት ተነሺዎች አያያዝና መስተንግዶ፣ የተሻለ የመረጃ አያያዝ እና መረጃ መር ውሳኔ መስጠት የተጠናከረ እና ሀገር በጋራ በመገንባት መንፈስ፤ ኮንትራክተሮችና አማካሪዎች በፍጥነት ወደ ስራ መግባት እና የተቋማት ቅንጅት እና ትምምን በጥንካሬ የሚታዩና ባህል ማድረግ ታይቷል። 👉እንዲሁም በጎ ፈቃዳቸውን አሳይተው ለተባበሩ የልማት ተነሽዎች፣ ህዝባችን፣ለሀይማኖት ተቋማት፣ ባለሃብቶች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ኮንትራክተሮችና አማካሪ ድርጅቶች፣ሌት ተቀን እየተረባረቡ ለሚገኙ የከተማችን ሰራተኞችና አመራሮች፣ ማህበራት፣ የጸጥታ አካላትና ሌሎችም ምስጋና አቀርባለሁ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ያለፉት 6ወራት የሴቶችና ህጻናት ዘርፍ ጥቅል የሥራ አፈጻጸም *አዲስ አበባ በአፍሪካ ሕጻናት ዕድገት ምቹ እንድትሆን ለማስቻል በቀዳማይ የልጅነት ፕሮግራም በ 3 ዓመት ለ1000 ህፃናት ማቆያ ለማቋቋም በዕቅድ ተይዞ የግሉን ዘርፍ ጨምሮ 822 የተዘጋጀ ሲሆነ በዚሕም ከ10,000 በላይ ህፃናት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል *ከ 11,900 ነፍሰ-ጡር ሴቶች፣ አጥቢ እናቶችና ሕፃናት የቀጥታ አልሚ ምግብ ድጋፍ እንዲያገኙ ተደርጓል። * ለሰንበት ዝግ በሚደረጉ መንገዶች በርካታ ሕጻናት የመጫወቻ ስፍራ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል *በተመሳሳይ ለ7,591 አረጋውያን እና ለ1,605 አካል ጉዳተኞች መሰረታዊ ማህበራዊ አገልግሎት፣ የስነልቦና፣ የማህበራዊ እና የተሃድሶ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ተደርጓል። *ለ582 አካል ጉዳተኞች የሰው ሰራሽ አካልና የአካል ድጋፍም እንዲያገኙ ሆኗል *በነገዋ የሴቶች ተሃድሶና የልቀት ማዕከል ለከፍተኛ ማህበራዊ ችግር የተጋለጡ 302 እህቶቻችን በመጀመሪያ ዙር አሰልጥነን ለእያንዳንዳቸው ስራ በመፍጠር ስምሪት ሰጥተናቸዋል። * በተመሳሳይ በሁለተኛ ዙር 400 ሴቶች ተቀብለን በመረጡት ሙያ እያሰለጠንን ነው፡፡ *በተማሪዎች እና በማህበረሰብ ምገባ ስራ 20 ሺህ የሚደርሱ ምንም ገቢ ያልነበራቸው እናቶችም የቋሚ የስራ እድል ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ *ወጣቶች በጥቃቅንና አነስተኛ የዕድገት ተኮር የስራ ዘርፎች በሚፈጠሩ የስራ ዕድሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ለሀገር ግንባታ ያላቸው ሚና እንዲጎለብትና ዘውትር ለስራ ዝግጁ እንዲሆኑ ለማስቻል ግንዛቤ የመፍጠር እንቅስቃሴ በክረምትና በበጋ የበጎ ፍቃድ አገልገሎት ማከናወን ተችሏል። *1314የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን በማልማትና ማስፋት ለ10,957,268 የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል። * በየደረጃው የማህበረሰብ አቀፍ ስፖርትን በማስፋፋት 4,509,,896/129.7%/ የህብረተሰብ ክፍሎቸን እንዲሳተፍ ማድረግ ተችሏል፡፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ከተማ አሰተዳደሩ ባለፉት 6 ወራት በጤናዉ ዘርፍ ያስመዘገባቸዉ ዉጤቶች ማሳያ፤- 👉ከእናቶችና ህጻናት ጤና አገልግሎት አኳያ የቅድመ ወሊድ ክትትል አገልግሎት 94,812 እቅድ ተያዞ 94,548 ለሚሆኑ እናቶች አገልግሎት በመስጠት የእቅዳችንን (99.7% ) ማሳካት ተችሏል፡፡ 👉 የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ፕሮግራም አምና ከነበረው 2.3 ሚሊየን አጠቃላይ በፕሮግራሙ የታቀፉ አባላት ቁጥር ዘንድሮ 2.5 ሚሊየን ማድረስ የተቻለ ሲሆን የጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚነትንም ለ1,330,562 በማድረስ ተደራሽና ፍትሃዊ የጤና አገልግሎትን መስጠት ተችሏል:: 👉የጤና መረጃ ስርዓትን ከማዘመንና ዲጂታል ከማድረግ ረገድም የጤና መረጃ ስርዓታቸውን በሙሉ ወረቀት አልባ ያደረጉ (EMR implement)ካደረጉ 40 ጤና ተቋማት ወደ 91ጤና ተቋማት በማሳደግ እቅዱን ማሳካት ተችሏል፡፡ 👉የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት አመላካች መለኪያዎችን ስንመለከት የአስተኝቶ ህክምና ታካሚዎች ሞት ምጣኔ በእቅድ የተያዘው 1.4% እና ከዛ በታች ማድረስ ሲሆን 1.2% በማከናወን እቅዱን ማሳካት ተችሏል፡፡ 👉የድንገተኛ ታካሚዎች ሞት ምጣኔን ከታቀደው 0.5% እና ከዛ በታች 0.4% ማከናወን የተቻለ ሲሆን የፅኑ ህሙማን የሞት ምጣኔን ከመቀነስ ረገድም ውጤታማ ስራ ተሰርቷል፡፡ 👉በተሰጠዉ የህክምና አገልግሎት ጥራት አመላካቾችም የአለም የጤና ድርጅት በማደግ ላይ ላሉ ሃገራት ያወጣውን ስታንዳርድም ሆነ ሃገራዊ ኢላማ በሚገባ ማሳካት የተቻለ ሆኗል፡፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ከተማ አስተዳደሩ ባለ6 ወራት በጎ ፍቃድ ስራ ያስመዘገባቸዉ ዉጤቶች በተመለከተ፤- 👉የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለዘላቂ ልማት ያለውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ በተከናወኑ የሰው ተኮርና የበጎ ፈቃድ ተግባራት 1,197,413 (ከ100% በላይ) የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ 👉በዚሁ መሰረት 24 የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል በመክፈት በየቀኑ በአማካይ እስከ 36,000 ለሚደርሱ በቀን አንድ ጊዜ እንኳን ምግብ ለማግኘት የሚቸገሩ ነዋሪ ወገኖቻችንን መመገብ ተችሏል፡፡ 👉ለአቅመ ደካሞች፣ ለአረጋውያን፣ ለሀገር ባለውለታዎችና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች 3,737(74%) ቤቶችን በመገንባት 20,484 (77%) ቤተሰቦችን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ 👉 በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ከ917,829 (ከ100% በላይ) የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ ማጋራት ተችሏል። 👉በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚሰሩ መሰረተ ልማት ስራዎች ብር 479,361,717.8 እንዲሁም በበጎ ፈቃድ 8,714,683,077 በድምሩ ብር 9,194,044,794.80 ጥቅም ላይ እንዲውል ተደርጓል። 👉ማህበራዊ ሀላፊነትን በመወጣት ረገድ የመጡ ለዉጦች ተግባሩ እለት ከእለት እየተጠናከረ መሄዱን የሚያሳይና የበርካቶች ገመናን የሸፈነ የበጎነት ተግባር በመሆኑ ይበልጥ ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል፡፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ባለፉት 6 ወራት ገቢን በተመለከተ 👉ባለፉት 6 ወራት 125.5 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 111.5 (90%) ተሰብስቧል። የገቢ አሰባሰባችን አምና በተመሳሳይ ወቅት ከተሰበሰበው 74.3 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነፃፀር በ37.2 ቢሊዮን ብር (በ50%) ምርታዊ እድገት አሳይቷል። ባለፉት 6 ወራት የከተማ አስተዳደሩን ሀብት አመዳደብና አጠቃቀም ውጤታማነትን ለማሳደግ የበጀት ድልድል የከተማ አስተዳዳሩን የትኩረት አቅጣጫዎች በመለየት ለዘላቂ ልማት ዘርፎች እንዲደለደል ተደርጓል። በዚሁ መሰረት ለዘላቂ ልማት የሚመደበውን የመንግስት በጀት በ2016 ከነበረበት 60% ወደ 71% ታቅዶ አፈፃፀሙ 71% መድረስ ተችሏል። 👉ይህም ለመደበኛ ብር 29,049,654,788.14 እንዲሁም ለካፒታል ብር ብር 64,188,241,080.10 በድምሩ ብር 93,237,895,868.24 (98.34%) ክፍያ መፈፀም የተቻለ ሲሆን አፈፃፀሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከነበረዉ ጠቅላላ ብር 66,065,700,754.16 ጋር ሲነፃፀር የብር 27,172,195,114.10 (41.1%) ብልጫ አሳይቷል። የተጨማሪ እሴት ታክስ ስርአት ውስጥ መግባት እየተገባቸው ያልገቡትን 8,450 የንግድ ተቋማትን ወደ ቫት ስርአት እንዲገቡ በመደረጉና የታክስ ኦዲትና ሽፋንና ውጤታማነት ለማሻሻልና ለማስፋት በተሰራው ስራ፣ ባሻገር በመርካቶና በከተማችን በሚገኙ ትልልቅ የንግድ ቦታዎች የተሰራው የቁጥጥርና ህግ የማስከበር ስራ ገቢ ከማሳደግ ባሻገር ፍትሃዊነት እንዲሰፍን አስተዋፅኦ ተደርጓል፡፡ 👉የገቢና ወጪ መጣጣምና እድገቱ ከተማችን ምን ያህል በፈጣን ለውጥ ውስጥ እንደሆነች አንዱ ተጨባጭ ማሳያ ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር የበጀታችን 71 እጁ ለዘላቂ ልማት፣ ደህነት ለመቅረፍና የህዝቡን የኑሮ ጫና ለማቃለል መዋሉ ምን ያክል ለከተማችን ነዋሪዎች ትኩረት እንደሰጠንና በታማኝነት እያገለገልን መሆኑን የሚያሳይ ነው ፡፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ባለፉት 6 ወራት በስራ ዕድል ፈጠራ የተመዘገቡ ዉጤታማ አፈፃፀሞች ማሳያ፤- 👉150,000 የስራ እድል ለመፍጠር እቅድ ተይዞ ለ142,908 ቋሚ የስራ ዕድል መፍጠር ተችሏል። 👉በዘርፍ ከፋፍለን ስንመለከት 97,126 (68%) የስራ ዕድል የተፈጠረዉ በአገልግሎት ዘርፍ ሲሆን በኢንዱስትሪ ዘርፍ 30,606(21%) የስራ ዕድል ተፈጥሯል፡፡ 👉በከተማ ግብርና ዘርፍ 15 ሺ112(11%) የስራ ዕድል ተፈጥሯል፤በዚህም የሴቶች ድርሻ 76,107 (53.3%) ነዉ፡፡ 👉በኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ዋናው የትኩረት ነጥብ የአምራች ኢንዱሰትሪዎችን አቅም ማጎልበትና አምራች ኢንዱስትሪው የሚያነሱትን የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን የመፍታት ስራ ተሰርቷል፡፡ 👉 ከዚህም አኳያ የመብራት፤የውሀ እና የመንገድ ችግር የነበረባቸውን ኢንዱስትሪዎች በመለየት መብራት 231 ኢንዱስትሪዎች ችግራቸውን መፍታት ተችሏል፡፡ 👉በተመሳሳይ የካታል ሊዝ አቅርቦት ለ276 ኢንዱስትሪዎች በማቅረብ እቅዱን ማሳካት ተችሏል፡ 👉184 ኢንዱስትሪዎች ምርታቸውን ወደ ውጪ እንዲልኩ በማድረግ 1,671 አምራች ኢንዱስትሪዎች 725,480,810 ቶን ተኪ ምርት በማምረት 490,630,180 ዶላር የውጪ ምንዛሪ ማዳን ችለዋል፡፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ከተማ አስተዳደሩ ባለፉት 6 ወራት በንግዱ ዘርፍ ያስመዘገባቸዉ ስኬቶች ማሳያዎች፤- 👉የንግድ ምዝገባና ዕድሳት በተመለከተ 23,064 አዲስ የንግድ ምዝገባ አገልግሎት ለመስጠት እቅድ ተይዞ 31,267 መሰጠት መቻሉ እንዲሁም 46,002 አዲስ የንግድ ሥራ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት እቅድ ተይዞ 53,576 መስጠት የተቻለ ሲሆን ለ411,548 የንግድ ሥራ ፈቃድ እድሳት አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ 285,622 መፈፀም ተችሏል፡፡ 👉ከንግድ ቁጥጥርና ክትትል አኳያም በህገ-ወጥ የንግድ ሥራ ተሰማርተው ከተገኙ 14,129 ድርጅቶች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ በመውሰድ ወደ ህጋዊነት መመለስ ተችሏል፡፡ 👉በተጨማሪም በኮንትሮባንድ እና በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተያዘ መሰረታዊ ሸቀጥ እና ነዳጅ ምርት 18,985 ሊትር ቤንዚን፣ 9,434.5 ሊትር ናፍጣ፣ 189 ሊትር ኬሮሲን፣ 964,324 ሊትር ዘይት እና ቡና 48 ኬሻና 100 ኪሎ ግራም በመያዝ በአጠቃላይ 29,305,804.6 (ሃያ ዘጠኝ ሚሊዮን ሶስት መቶ አምስት ሺ ስምንት መቶ አራት ብር) ብር ለመንግስት ገቢ ተደርጓል፡፡ 👉የእሁድ ገበያ መዳረሻዎችን በማድረስ፤እንዲሁም ስታንዳርዳቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ በማድረግ በተሰራዉ ስራ የግብዓት አቅርቦት ሰንሰለቱን እንዲያጥር በማድረግ እና አቅርቦትን በማሳለጥ የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበት ለመቀነስ ተችሏል፡፡ 👉በሌላ በኩል በመንግስት በድጎማ ከሚቀርቡ ምርቶች አኳያ 149,532 ኩ/ል የስኳር ምርት፤ 2,195,569 ሊትር የምግብ ዘይት በተፈጠረዉ ትስስር ለንግድ ኮርፖሬሽና ለህብረት ሥራ ኤጀንሲ ማሰራጨት ተችሏል፡፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ባለፉት 6 ወራት በከተማ አስተዳደሩ በተቋም ግንባታና አገልግሎት አሰጣጥ ረገድ የተመዘገቡ አበረታች ዉጤት ማሳያዎች፤- 👉የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የሚያስችል የሪፎርም ስራ እየተከናወነ የሚገኝ በመሆኑ በተቋማት የስራ አፈጻጸም ላይ የአገልግሎት መሻሻሎችን መታየት ጀምረዋል፡፡ 👉በ19 ሴክተር ተቋማት 87 ተግባራትን በቴክኖሎጅ በማስደገፍ ቀልጣፋ እና ጥራት ያለው አልግሎት መስጠት የሚያስችል ስራ ተሰርቷል። 👉የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ ከ720,000 በላይ ዶክመንቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመለወጥ የተገልጋይ መረጃና ዶክመንት ደህንነቱ እንዲጠበቅ ከማስቻል ባለፈ ሃብትን ለማወቅ የሚያስችል ስራ በተጨባጭ ተሰርቷል። 👉አሽርካሪና ተሸርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ካሉት 45 አገልግሎቶች መካከል 35ቱን እንግልትን በሚያስቀር አኳሀን በዲጂታል ሲስተም አገልግሎት ሰጥቷል፡፡ 👉በተመሳሳይም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የ1.8 ሚሊዮን ተገልጋዮችን ፋይል በቴክኖሎጂ በመታገዝ በአዲስ መልክ ማደራጀት ችሏል። 👉በከተማ አስተዳደሩ የተቀናጀ የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ መረጃ አያያዝ ስርዓት (ኢስሚስ) ተግባራዊ በማድረግ የ168 ሺ ሠራተኞች ፋይል ስካን ተደርጎ ወደ ሲስተም እንዲገባ ተደርጓል፡፡ 👉በዚህም የሰራተኞችን አሃዝ ከማወቅ ባለፈ ከ100 በላይ የሚሆኑ ሠራተኞች ያላአግባብ በ2 እና 3 ቦታ ተቀጥረው ደሞዝ ሲበሉ የነበሩ መሆናቸዉ ተረጋግጦ ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ 👉የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን ዲጂታል በማድረግ በከተማችን የመታወቂያ፣ የልደት፣ የሞት፣ የጋብቻ፣ የፍቺ እና ተያያዥ መረጃዎችን ያለእንግልት በላቀ ፍጥነት መስጠት ተችሏል፡፡ 👉በዚህም የከተማ ነዋሪነት መታወቂያ 99.84 በመቶ ዲጂታል የተደረገ ሲሆን ቀሪው በቤት ለቤት አገልግሎት በማንዋል ተሰጥቷል፡፡ 👉ይህ በእንዲህ እንዳለ በከተማ አስተዳደሩ የጤና፣ የንግድ ፍቃድ፣ የግንባታ ፍቃድ፣ የግብር ማሳወቅና መሰብሰብ አገልግሎቶች ወደ ዲጂታል ስርዓት ተሸጋግረዋል፡፡ 👉ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በተጀመረው የኮደርስ ቴክኖሎጂ ኢንሼቲቭ በከተማ ደረጃ ከ20,000 በላይ ስልጠና ወስደዉ ያጠናቀቁ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ደግሞ 110,000 የሚሆኑ ወጣቶች ስልጠናዉን በመከታተል ላይ ይገኛሉ። 👉የተቋም ግንባታ ስራዎችችን ለማሳለጥ ብሎም አሰራሮች ግልፅ፣ የተነበቡ እና የተቀላጠፈ ፈጣን ሂደት እንዲኖራቸው በተቋማት አካታች የሪፎርም ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ 👉ምቹ የስራ ሁኔታን ለመፍጠር በተቋሞቻችን 153 የህጻናት ማቆያ ፣ 171 የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት የሰራተኞች ካፍቴሪያ እና ከ148 በላይ የሸማች ሱቆችን ወደ ስራ ማስገባት ተችሏል።