1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
በመዲናዋ የወንዝ ዳርቻሞችን በማልማት የጎርፍ አደጋ ተጋላጭነትን መቀነስ መቻሉን በምክትል ከንቲባ ማዕርግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ተናገሩ ።
የወንዝ ዳርቻሞችን በማልማትና በማጽዳት በወንዝ ዳርቻ ዙርያ የሚኖሩ ከ13 ሺህ በላይ ዜጎችን ከጎርፍ አደጋ ተጋላጭነት መታደግ መቻሉን በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ተናገሩ፡፡
በ3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በሰጡት ማብራሪያ ከ247 በላይ ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች መለየታቸውን ሙሉ ለሙሉ አደጋውን ለማስቀረት በትኩረት እየተሰራ እንደሆነም ኢንጂነር ወንድሙ ሲታ አስረድተዋል፡፡
እንዲሁም በያዝነው ክረምት በደረቅ ቆሻሻዎች፣በፕላስቲክ እና በኮንስትርክሽን ተረፈ ምርቶች ሊደርስ የሚችልን አደጋ ለመቀነስም ከተቋማት ጋር በቅንጅት የማጽዳት ስራ እየተሰራ እንደሆነም ተናግረዋል::
ክቡር ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ለምክርቤት አባላት የሰጡትን ማብራሪያ በቀጣዩ ቪዲዮ ይመልከቱ:-
በበጀት ዓመቱ የኮሙኒኬሽን ስራዎች በተመለከተ፤
👉በበጀት አመቱ ከተማ አስተዳደሩ በማህበራዊ፤ በኢኮኖሚያዊ፤ በፖለቲካዊ እና የልማት ስራዎች ያከናውናቸውን ተግባራት አስመልክቶ የመረጃ ተደራሽነትን በማስፋት ውጤታማ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ስራዎችን ማከናወን ተችሏል፡፡
👉ዋና ዋና ከተማ አቀፍ የልማት፣ የመልካም አስተዳደር እና ሀገራዊ ፋይዳ ያለቸው ፕሮጀክቶች ዙሪያ መልዕክቶችን በማዘጋጀት በዜና፣ በአጫጭር ፕሮግራሞች፣ በዶክመንተሪ፣ በተከታታይ የቴሌቪዥን ፕሮግራም፣ በኅትመቶች፣ በፕሬስ ሪሊዞችና ፓናል ውይይቶች ተደራሽ በማድረግ በከተማዋ የልማት አጀንዳዎች ሕዝባችን የላቀ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን ተደርጓል።
👉ከተማችንን አስመልክቶ የሚሰራጩ ሚዛን የሳቱና የተዛቡ 172ዐ መረጃዎች በመለየት የመመከትና ሚዛን የማስያዝ ሥራዎችን በመስራት መረጃዎቹ እንዲታረሙ ማድረግ ተችሏል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
የሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማትን በተመለከተ፦
👉የመንገድ መሠረተ ልማት፡- 135 ኪ.ሜ የተሽከርካሪ መንገድ፣ 246 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ፣141 ኪ.ሜ የብስክሌት መንገድ፣ 43 ኪ.ሜ የመሮጫ ትራክ፣ 53 የተሽከርካሪ እና እግረኛ መሻገሪያ ድልድዮች፤190 ኪ.ሜ የጎርፍ ማስወገጃ ሥርዓት ዝርጋታና፣ 83 ኪ.ሜ የድጋፍ ግንብ ሥራ ተሰርቷል።
👉 የትራንስፖርት ሥርዓት ለማሳደግ ፦ 153 ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያዎች፣ በአንድ ጊዜ 35,000 ተሸከርካሪዎችን የማስተናገድ አቅም ያላቸውና 33 የባስ እና ታክሲ ዘመናዊ ተርሚናሎች፣
👉 የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ፦ 1,122 ስማርት እና 1708 ኖርማል በአጠቃላይ 2830 የመብራት ምሰሶዎች ተተክሏል፤ 179.6 ኪ.ሜ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ፤ 5,048 የኤሌክትሪክ ምሰሶ ማዛወር፤ 22.41 የመሬት ውስጥ መካከለኛ የኤሌክትሪክ መስመር መቅበር፤ 324 የዲስትሪቢዩሽን ትራንስፎርመሮችና 7.9 ኪ.ሜትር ፒቪሲ ዝርጋታ ሥራ ተሰርቷል።
👉የሕዝብ መዝናኛዎችና ማረፊያዎችን ማስፋፋት፦ የአረንጓዴ ልማት ፤ የህዝብ መዝናኛ ፕላዛዎች ፤ ዘመናዊ የመንገድ ዳር የሕዝብ መፀዳጃ ቤቶች (Public toilets)፣ ስፍራዎች ተገንብተዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በበጀት ዓመቱ ኢንቨስትመንት በተመለከተ
👉 ለ3,207 ባለሀብቶች አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጥቷል
👉 በተመሳሳይ ለ2,025 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ዕድሳት ተሰጥቷል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በበጀት ዓመት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በተመለከተ፤-
👉ለግድቡ በተደረገዉ የድጋፍ ሃብት አሰባሰብ በበጀት ዓመቱ ውስጥ ብር 506,000,000 ለማሰባሰብ ታቅዶ ክንውን 802,578,211 (ስምንት መቶ ሁለት ሚሊየን አምስት መቶ ሰባ ስምንት ሺ ሁለት መቶ አስራ አንድ ብር) ከዕቅድ በላይ የድጋፍ ሃብት ማሰባሰብ መቻሉ፤በዚህም በድምሩ ከ2ዐዐ3 ጀምሮ እስከ 2017 ዓ.ም ከ6.1 ቢሊየን ብር ድጋፍ በመሰብሰብ እንደ ሐገር መዲናችንን ከቀዳሚዎች ደረጃ ላይ እንድትጠቀስ አስችሏታል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
በበጀት ዓመቱ የቤት ልማትና ማስተላለፍን በተመለከት
👉በግለሰብ አልሚ 11,260 ቤቶች ::
👉በሪል እስቴት አልሚዎች 30,507 ቤቶች፣
👉በህብረተሰብ ተሳትፎ የታደሱ 8,786 ቤቶች፣
👉 በመንግስት ለልማት ተነሺ የተሰሩ 5,176 ቤቶች፣
👉በአጠቃላይ በ2017 በጀት አመት 55,729 ቤቶች ተገንብተዋል ማስተላለፍ ተችሏል::
👉በህገ -ወጦች የተያዙ 453 የመንግስት ቤቶች እና 212 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በድምሩ 665 ቤቶችን በማስለቀቅ ለሚገባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ማስተላለፍ ተችሏል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
በበጀት ዓመቱ በመንገድ ልማት ዘርፍ
የከተማውን የመንገድ መረብ ሽፋን የሚያሳድጉ፣ የትራፊክ ፍሰቱን የሚያሳልጡ፣ የመንገድ ድህንነቱን የሚያረጋግጡ፣ለኢንቨስመንት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩ፣ የጉዞ ጊዜንና ገንዘብን የሚቀንሱ የመንገድ ግንባታና ጥገና ስራዎችን በማከናወን በዚህም፤-
👉371 ኪ.ሜ. የሚሸፍን አስፓልት
👉 95.2 ኪ.ሜ የኮብል
👉 16.1 ኪ.ሜ ጠጠር ግንባታ
👉107 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገድ ግንባታ
👉3.7 ኪ.ሜ የድጋፍ ግንብ እና የድሬንጅ ግንባዎች
👉 1‚180 ኪ.ሜ የሚሸፍን የመንገድ ጥገና ስራዎች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል፡፡
በበጀት ዓመቱ ገቢን በተመለከተ
👉በመዲናዋ ከ241.46 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ ከ233 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 96.5% በመቶ መፈፀም የተቻለ ሲሆን ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 83.3 ቢሊዮን ብር ወይም 57% እድገት አሳይቷል::… See more
በበጀት ዓመቱ አምራች ኢንዱስትሪውን በተመለከተ
👉የምርት ጥራት፣ ምርትና ምርታማነታቸውን ከማሳደግ አንፃር ለ566 አምራች ኢንዱስትሪዎች 4,235 ማሽነሪ መሳሪያ እና በብር ደግሞ 1,860,822,877 በማቅረብ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
