fa
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን በተመለከተ 👉በደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ረገድ ከተማዋ ከ983,944.9 ቶን በላይ ደረቅ ቆሻሻን በመሰብሰብና በማስወገድ፣ ከ11 በመቶ ወደ 12.2 በመቶ በማሳደግ በመልሶ መጠቀም ወደ ሀብትነት መለወጥ ተችሏል። 👉በሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት በኩል ከተማዋ 377,624 የወሳኝ ኩነት ምዝገባዎች ተከናውኗል። 👉በ2017 የበጀት አመት ወደ ዲጂታል ምዝገባ ያልተቀላቀሉ 671,019 ነዋሪዎች በዲጂታል አገልግሎት አግኝተዋል ። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

በበጀት አመቱ የኑሮ ውድነት ቅነሳን በተመለከተ 👉በከተማዋ አምራቾች ምርታቸውን በቀጥታ በገበያ በማዕከላት እንዲያቀርቡ በተፈጠረው እደል 3.5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንዲቀርብ ተደርጓል። 👉የቅዳሜና እሁድ የገበያ ቦታዎችን በማስፋት ከ193 ወደ 219 በማሳደግ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ ይገኛል፡፡ 👉በድጎማ ከሚቀርቡ ምርቶች የስኳር ምርት 305,295 ኩንታል፤ የምግብ ዘይት 4,382,179 ሊትር በትስስር ማሰራጨት ተችሏል። 👉በትራንስፖርት፣በጤና መድን፣ በዳቦ አቅርቦት፣ በምገባና በምርት አቅርቦት ከ14 ቢሊዬን ብር በላይ በመደጐም የነዋሪዎቻችን የኑሮ ጫናን የማቅለል ስራ ተሰርቷል፡፡ 👉የዳቦ አቅርቦትን ለመጨመር በመንግስትና በግል ባለሀብቶች የጋራ ጥምረት በተሰራው ሥራ የሸገር ዳቦና ብረሃን ዳቦ ፋብሪካ ውደ ስራ በማስገባት፤በአጠቃላይ በ26 ዳቦ ፋብሪካዎች በሚሊዮኖች ዳቦ በማምረት የነዋሪውን ኑሮ ለመደገፍ ጥረት ተደርጓል። 👉በ26 የምገባ ማእከልላት በቀን አንድ ጊዜ ምግብ ማግኘት ችግር ላለባቸው 36ሺ ሰዎችን በምገባ ፕሮግራም ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የአዲስ አበባ ምክር ቤት የ2017 ሰራ አፈጻጸም ግምገማ ማካሄድ ጀምረናል። Gamaaggama raawwii hojii bara 2017 Mana maree magaalaa Finfinnee gaggeessuu eegaleerra.

በበጀት ዓመቱ የተጠናቀቁ የፕሮጀክቶችን አስመልክቶ የሕዝባችንን የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎችን ከመመለስ አንጻር በመንግስትና በህብረተሰብ ተሣትፎ 15‚69ዐ ግንባታዎችን ማጠናቀቅ የተቻለ ሲሆን፤ ካቀድነው በላይ ማከናወን ተችሏል፡፡ 👉 205 በህብረተሰብ ተሳትፎ የተሰሩ የተለያዩ ኘሮጀክቶች 👉 8,786 በበጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር ለአቅመ ደካሞች የተገነቡ ቤቶች 👉 5,176 በከተማ አስተዳደር የተገነቡ ቤቶች 👉 1064 የመስሪያ ሼዶች 👉 5,563 ሱቆች / ካዛንቺስ፣ ቦሌ፣ ላፍቶ፣ ልደታ፣ አራዳ እና አራት ኪሎ ሽሮሜዳ/ የተገነቡ 👉 1,155 የህፃናት መጫወቻ ቦታዎች 👉 122 የእስፖርት ማዘወተሪያ ሜዳዎች 👉 245 የአረንጓዴ ልማት ስራ 👉 153 የመኪና ፓርኪንጎችና ተርሚናሎች 👉ከዚህ ውስጥ 16 ቱ ሜጋ ኘሮጀክቶች ሲሆኑ ወደ 9ሺ ኘሮጀክቶች በህብረተሰብ ተሳትፎና በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተሰሩ ናቸው፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የድህነት ቅነሳና ስራ እድል ፈጠራን በተመለከተ 👉በከተማችን ለሚገኙ ለ366,044 ስራ ፈላጊዎች ቋሚ የስራ እድል መፍጠር ተችሏል፡፡ 👉በከተማ ግብርና ዘርፍ 40,230 በኢንዱስትሪ ዘርፍ 91,737 እና በአገልግሎት ዘርፍ 234,077 👉ለሴቶች የስራ እድል ፈጠራ 201,309 👉ለወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ 290,360 ምሩቃን 52,866 የስራ እድል ተጠቃሚ ሆነዋል። 👉ተረጂነትን በማስቀረት ምርታማነት ለማሳደግ የልማታዊ ሴፍትኔት ሦስት ዓመት የሆናቸው የሁለተኛ ምእራፍ ተጠቃሚዎች የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግና ስልጠና በመስጠት 31,002 የቤተሰብ ተወካዮች በማስመረቅ የራሳቸውን ገቢ የሚፈጥሩበት ቌሚ የስራ መስክ ማስገባት ችለናል፡፡ 👉በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ምክንያት የሚጎዳ የህብረተሰብ ክፍል እንዳይኖር 130,135 በላይ በዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የከተማችን ነዋሪዎችን ለቀጣይ ሶስት ዓመት የሚደግፍ ስራ በበጀት ዓመቱ አስጀምረናል፡፡ 👉የቁጠባ ባህልን ለማሳደግ በተሰሩ ስራዎች 27,293 ኢንተርፕራይዞች 5,132,495,487 ብር ቁጠባ እንዲቆጥቡ ተደርጓል፡፡ 👉 ለኢንተርፕራይዞች ብድር በማመቻቸት 3,559,287,049 ብር ማበደር ተችሏል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

በበጀት ዓመቱ ቱሪዝምን በተመለከተ 👉1ሚሊዮን የውጪ ሀገር ቱሪስቶች ከተማችንን እንዲጎበኙ በማድረግ፣ከ15ዐ በላይ ኮንፍረንሶች፣ እግዚቢሽኖችና ኤክስፖዎች በማካሄድ ከ143 ቢሊየን በላይ ገቢ ተሰብስቧል፡፡ 👉ከ9 ነጥብ 3 ሚሊዮን የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች ከ56 ነጥብ 6 ቢሊዮን በላይ የሚሆን ገቢ ወደ መዲናችን ኢኮኖሚ ፈሰስ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

በበጀት ዓመቱ ጤናን በተመለከተ 👉በሰለጠነ ባለሙያ የሚሰጥ የወሊድ አገልግሎት ለ170,155 እናቶች በመስጠት ከእቅዳችን 94% ማሳካት ተችሏል:: 👉የተመላላሽ ህክምና ተጠቃሚነት ቁጥርን በድግግሞሽ 16.6 ሚሊየን ጊዜ መስጠት ተችሏል፡፡ o ለ246,056 አስተኝቶ ህክምና ተገልጋዮች ተደራሽ በማድረግ ከእቅዳችን 117% ማከናወን ችለናል፡፡ 👉የከተማ አስተዳደሩ ለማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ድጎማ በማድረግ አምና ከነበረው 2.45 ሚሊየን አጠቃላይ የፕሮግራሙ የታቀፉ አባላት ቁጥር ዘንድሮ በእቅዳችን መሰረት 2.5 ሚሊየን ለማድረስ ተችሏል፡፡ በኮልፌና በንፋስ ስልክ ክ/ከተማ ሁለት አጠቃላይ የሪፈራል ሆስፒታሎች ግንባታቸው በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡: 👉የጥሩነሽ ቤጅንግ፣ የራስ ደስታ፣ የዘውዲቱ ሆስፒታል እና ሚኒሊክ ሆስፒታል እየተሰራ ያለው ግዙፍ ማስፋፊያ በማጠናቀቅ ላይ እንገኛለን፡፡ 👉ስምንት አዲስ ጤና ጣቢያዎች ግንባታቸው የተጠናቀቀና በቅርቡ ስራ የሚጀምሩ ሲሆን በአራት ነባር ሆስፒታሎች እና ሌሎች ተጨማሪ ጤና ጣቢያዎች የተቋማቱን አቅም በሚያሳድግ መልኩ ሰፊ እድሳቶች ተሰርተዋል፡፡ 👉የጤና መረጃ ስርዓታቸውን ሙሉ ለሙሉ ወረቀት አልባ ያደረጉ የጤና ተቋማት አምና ከነበሩት 40 ጤና ተቋማት ወደ 57 የጤና ጣቢያ ተቋማት በማሳደግ ችለናል፡፡

የፍትህ ሥርዓትና የሕግ የበላይነትን ማስከበር በተመለከተ 👉በፍትህ ሥርዓታችን የሕግ የበላይነትን በማስከበር የሰብዓዊ መብት አያያዝ እንዲጎለብት ለማድረግ በፍትሐብሔር ጉዳዮች የከተማ አስተዳደሩንና የነዋሪውን መብትና ጥቅም ከማስጠበቅ አንፃር ክርክር በፍ/ቤት የመርታት አቅም 96.05 % ማድረስ ታቅዶ በፍርድ ቤት ክርክር የቀረቡ 6,379 መዝገቦች፣ በፍ/ቤት ውሳኔ ካገኙ 3,963 መዝገቦች 3,683 ለአስተዳደሩ ማስወሰን በመቻሉ አፈፃፀሙ 96.8% ደርሷል፡፡ 👉የመንግስት እና ሕዝብ መብትና ጥቅም በማስከበርም በገንዘብ 5,608,175,281.16 ብር ሆኖ በአይነት ደግሞ 272 ቤቶች፣ 64 ሼዶች እንዲሁም 260.32 ሄክታር መሬት ማስከበር መቻሉ፤ምርመራ ከተጠናቀቀ 12,828 የግል አቤቱታ የወንጀል ምርመራ መዝገቦች ውስጥ 88% በእርቅ ለመጨረስ ታቅዶ 9,822 መዛግብት በፖሊስና በዐቃብያን ሕግ፣ 1,048 መዛግብት በፍርድ ቤት በአጠቃላይ 10,870 ክንውኑ 84.7% ሲሆን አፈፃፀሙ 96.2% ነው፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ቀዳማይ ልጅነትን ልማት ፕሮግራምን በተመለከተ 👉ፐሮግራሙ የከተማችንን 1.3 ሚሊዮን ህጻናትን በተለይ ደግሞ 330‚000 አነስተኛ ገቢ ካላቸው ቤተሰብ የተገኙ ህጻናት ለመድረስ ያለሙ አምስት አንኳር ኢኒሼቲቮሽን አቅደን ስንተገብር ቆይተናል። 👉ከተቀመጡት ግቦች አንጻር የወላጆችን እና አሳዳጊዎች የምክር እና የሙያ አገልግሎት የሚሰጡ 5‚000 ሰራተኞችን በማሰማራት በ 4‚979 የመኖሪያ ብሎኮች ለሚገኙ ለ 487,544 ወላጆች/አሳዳጊዎች በየአስራ አምስት ቀኑ የቤት ለቤት የምክር አገልግሎት ተሰጥቷል። 👉ለ11,900 አነስተኛ ገቢ ላላቸው እና ለድገት ውስኑነት ተጋላጭ የሆኑ ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች እንዲሁም ከ 3 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት የቀጥታ አልሚ ምግብ ድጋፍ በየወሩ ተሰጥቷል። 👉ስራውን አጠናክሮ ለመቀጠል በዚህ በጀት አመትም ከ 5ዐዐ ሚሊየን በላይ በጀት ለአልሚ ምግብ በጅተናል፡፡ 👉እድሜያቸው ከ 0 እስከ 3 ዓመት የሆኑ እና በኢኮኖሚ ሁኔታቸው ለዕድገት ውሱንነት ተጋላጭ የሆኑ ህጻናት የዕድገት ሁኔታ ፕሮግራሙ በተጀመረበት ወቅት ከነበረበት 66.9% ወደ 73.1% በማደግ የ 6.2 በመቶ መሻሻል አሳይቷል። 👉በጨዋታ መልክ በማስተማር በቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ይታይ የነበረው የትምህርት ዝግጁነት ምጣኔም ከነበረበት ዝቅተኛ ደረጃ ወደ 89.03% ከፍ በማለት የልጆች ሁለንተናዊ ዕድገት ማረጋገጥ ችለናል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የተቋም ግንባታና አገልግሎነት አሰጣጥ በተመለከተ 👉በተቋማት ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር ከ2 ሽህ 147 በላይ የመንግስት ሰራተኞች በህጻናት ማቆያ ልጆቻቸውን እንዲከባከቡ በማድረግ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል። 👉በተቋማት ከ185 በላይ የመንግስት ሰራተኞች ካፍቴሪያዎችን በመገንባት እና አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ እንዲሁም ከ150 የሸማች ሱቆችን ወደ ስራ በማስገባት ሰራተኞ የኑሮ ውድነቱን እንዲቋቋም የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል። 👉ከ21 ሽህ 046 የተገልጋይ ማረፊያ በማዘጋጀት ምቹ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ተገንብተዋል። 👉በተቋማት 347 አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ በማድረግ ብልሹ አሰራር፣የተገልጋይ እንግልትና ምልልስ በማስቀረት የሚቀርቡ ቅሬታዎች እንዲቀንሱ አድርጓል። 👉በሌብነትና ብልሹ አሰራር ተግባር ውስጥ የገቡ 4 ሽህ 965 አመራሮች፣ ፈጻሚዎች እና ተገልጋዩችን ተጠያቂ በማድረግ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃዎች ተወስዷል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/addisababacommunication