1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ኤፍኤም 97.1 ሬድዮ ጋር በመተባበር የሚቀርበው ሳምንታዊ የሬድዮ ፕሮግራም እነሆ 11ኛ ክፍል ደርሷል።በዚህ ፕሮግራም በከተማችን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የገላን የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩ የቅድመ አደጋ መከላከል ስልጠና ከወሰዱ ነዋሪዎች ጋር ቆይታ አድርጓል። እንድትከታተሉት ተጋብዛችሁዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የሁለት ተጠሪ ተቋማትን የ11 ወራት የስራ አፈፃፀም ገመገመ::
ጽ/ቤቱ ዛሬ ሰኔ 04 ቀን 2016 የፅዳት አስተዳደር እና የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲን ያለፉት 11 ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ከተቋማቱ አመራሮች ጋር በጋራ ገምግሟል።
በምክንትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ክብርት ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን በመሩት በዚህ የግምገማ መድረክ ላይ ባለፉት 11 ወራት በሁለቱም ተቋማት ግንዛቤ ከመፍጠር ፣የማህበረሰብን ተሳትፎ ከማሳደግ እና በስታንዳርዱ መሠረት አገልግሎት ከመስጠት አንጻር በጥንካሬና በክፍተት የታዩ አፈፃፀሞች በሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።
በተጨማሪም ቅንጅታዊ አሰራርን እና የሪፎርም ስራዎችን ከማጠናከር ፣የንቅናቄ ስራዎች እንዲሁም የኘሮጀክት አፈፃፀሞችና ሌሎች ተግባራት አፈጻጸምም ተገምግሟል::
በመድረኩ ላይ ክብርት ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን እንደገለፁት ሁለቱም ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጣቸውን ለማዘመን እና በእቅዳቸው መሠረት ስራዎችን ለማከናወን የተደረጉ ጥረቶችና የመጡ ውጤቶች መልካም የሚባል በመሆኑ በቀሪው አንድ ወር ይኸው ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል::
አክለውም ከፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ አንጻር በቀሪ አንድ ወር ጊዜ እና ለ2017 በጀት አመት የከተማው ሁሉንም አካባቢዎች በጽዳታቸው ተቀራራቢ ወደሆነ ደረጃ ማምጣት፣ ዘርፉን በቴክኖሎጅ ማዘመን እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ማስፋት በልዩ ትኩረት እንዲፈፀም አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ክብርት ወ/ሮ ሂክማ ከሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልገሎት አንፃርም የሁነት ምዝገባን ከትምህርት ቤቶች የአዲስ አመት የምዝገባ ወቅት ጋር በማያያዝ እና ከጤና ተቋማት ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር ሰፊ ስራ መሰራት እንደሚገባ ገልጸዋል።
በተያያዘም ከፍትህ አካላት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር የተጀመሩ ቅንጅታዊ አሰራሮች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ሲሉ ተናግረው በ2017 ለነዋሪዎች የተሻለና የዘመነ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የእቅድ ዝግጅት ከወዲሁ ተዘጋጅቶ እንዲቀርብ ሲሉም አሳስበዋል:።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ለፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ለቡድን መሪዎች ያዘጋጀው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና መስጠት ተጀመረ ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ለፅዳት አስተዳደር ፅ/ቤት የክፍለ ከተሞች የግንዛቤና ህብረተሰብ ተሳትፎ ቡድን መሪዎች ለ3 ቀናት የሚቆይ ስልጠና ዛሬ ሰኔ 4 ቀን 2016 ዓ.ም መስጠት ተጀምሯል።
በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ በስልጠናው መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት የከተማዉ የጽዳት ጉዳይ ከጊዜ ወደጊዜ ከፍተኛ የሆነ መሻሻል እየታዬበት መሆኑን ጠቅሰው ይህንኑ በተጠናከረ ሁኔታ ለማስቀጠል እና ጽዳት የሁሉም ነዋሪዎች ባህል እንዲሆን ለማድረግ ይህን መሰል የአቅም ግንባታ ስልጠና በልዩ ትኩረት ተዘጋጅቷል ብለዋል።
የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ እንደገለፁት በስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ለግንዛቤና ለህብረተሰብ ተሳትፎ ቡድን መሪዎች የተዘጋጀው ይኸው ስልጠና ከከተማው ነዋሪዎች ጋር በየእለቱ ከጽዳት ጋር ተያይዞ የአመለካከት ለውጥ እንዲመጣና እና ግንዛቤን ለማሳደግ የሚሰሩ እንደመሆናቸው በዚህ ረገድ እገዛው ከፍተኛ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል።
በዛሬው እለት የተጀመረው ስልጠና የመጀመሪያ ዙር ሲሆን በአራት ዙር ዙር ለ144 ለሰልጣኞች እንደሚሰጥም በዚሁ ወቅት ተገልጿል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ኤፍኤም 97.1 ሬድዮ ጋር በመተባበር የሚቀርበው ሳምንታዊ የሬድዮ ፕሮግራም እነሆ 11ኛ ክፍል ደርሷል።በዚህ ፕሮግራም በከተማችን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የገላን የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩ የቅድመ አደጋ መከላከል ስልጠና ከወሰዱ ነዋሪዎች ጋር ቆይታ አድርጓል። እንድትከታተሉት ተጋብዛችሁዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
+9
ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ ቦታዎች ላይ እየተሰሩ ያሉ የአደጋ ቅድመ መከላከል ስራዎች ሊፉጠኑ እንደሚገባ ተገለፀ።
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የእሳት አደጋ ፎረም ቋሚ ኮሚቴ በወረዳ ዐ1 ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች ላይ ዘላቂና ጊዜያዊ መፍትሔ በሚሰጥበት ሁኔታ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይትና የመስክ ምልከታ አካሄዷል።
በውይይቱ በመጪው የክረምት ወቅት ከባድ ዝናብ እንደሚኖርና ወረዳው ለጎርፍ ተጋላጭ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን ለጎርፍ ተጋላጭ ተብለው በተለዩ ቦታዎች ላይ ያሉ ነዋሪዎችን መመሪያው በሚፈቅደው መልኩ ከቦታው በማንሳት የምትክ ቤትና በመስጠት ዘላቂ መፍትሔ መስጠት እንዲሚገባ ተመላክቷል።
በመስክ ምልከታው ተጋላጭ ተብለው የተለዩ ቦታዎች በአብዛኛው ከፍተኛ የጎርፍ ስጋት ያለባቸው በመሆኑ አፋጣኝ ዘላቂ መፍትሄ የሚፈልጉ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን ስራው የተሳካ እንዲሆን ከነዋሪዎች ጋር በመወያየት መግባባት መፍጠር እንደሚገባ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የእሳት አደጋ ፎረም ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጠቁመዋል።
የፎረሙ አባላት ጨምረውም መንግስት የዜጎችን ህይወት የመጠበቅ ሀላፊነት ያለበት በመሆኑ የአንድም ዜጋ ህይወት ላይ አደጋ እንዳይደርስ ሲል በክ/ከተማና በወረዳው የሚቀመጡ አቅጣጫዎችን በማይቀበሉ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ገልፀዋል ።
Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች ላይ የመስክ ምልከታ ተካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ በሆኑ ወረዳዎች ቦታዉ ድረስ በመገኘት የጎርፍ አደጋ ስጋት እንዲሁም የእሳትና የአፈር መንሸራተት ያለባቸው ቦታዎችን የመስክ ምልከታ አከናውኗል።
የመስክ ምልከታዉ በክፍለ ከተማዉ ላይ የሚስተዋሉ የጎርፍ አደጋ፣የአፈር መንሸራተት ፣የእሳት አደጋ ስጋቶችን በመለየት እና የክረምት ወቅቱን ታሳቢ በማድረግ የቅድመ አደጋ መከላከልና ስራዎችን ተግባራዊ ለማድረግና አደጋውን ለመቀነስ የታለመ ነዉ።
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ስሙ "ፓይለት ሰፈር" ተብሎ በሚጠራው ከ35-40 የሚጠጉ አባወራና እማወራዎች የሚኖሩ ሲሆን በቦታዉ ከፍተኛ የአፈር መንሸራተት እንዲሁም የመፋሰሻ ቱቦዎች በደረቅ ቆሻሻ በመዘጋታቸው ከፍተኛ የሆነ የጎርፍ አደጋ የሚያስከትል በመሆኑ የፅዳት ስራዎች ተጠናክረው ቀጠል እንዳለበት የአካባቢዉ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በክፍለ ከተማው ወረዳ 6 እና 9 ስላሴ ቤተክርስቲያን ጀርባ በቦታዉ ከፍተኛ የአፈር መንሸራተት እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ የጎርፍ አደጋ የሚያስከትል ቦታ በመሆኑ የአደጋ ጥንቃቄ ስራው ተጠናክሮ ክረምት ከመግባቱ በፊት መጠናቀቅ እንደሚገባው የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በዚሁ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ልዩ ስሙ "ወይራ ሰፈር" እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ከ150 እስከ 200 በላይ የሚሆኑ ሰዎች የሚኖሩ ሲሆን ቦታው ከፍተኛ ለሆነ የአፈር መንሸራተት ተጋላጭ እንደሆነ ነዋሪዎቹ ገልፀው የሚመለከተዉ አካል አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።
በክረምት ወቅት አደጋዉ ከፍተኛ እንደመሆኑ ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን ቀድሞ በመለየትና ሊደርስ የሚችለዉን አደጋ ለመቀነስ በተጨማሪም የግንዛቤ መልዕክት መስጠት እንደሚያስፈልግ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት የግንቦት ወር ዜና መጽሄት በፊት ገጿ የከተማችን የጽዳት ጉዳይ ዋና ርእሰ ጉዳይ አድርጋለች።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
+7
ቃል በተግባር !
ከሁሉም በፊት የረዳን ፈጣሪን እናመሰግናለን !
በተያዘላቸው የሶስት ወር ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቁትን ፒያሳ የአድዋ ድል መታሰቢያ ዙሪያ እና የአራት ኪሎ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትርችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ፣ ከክብርት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ከሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጋር ገምግመናል።
አዲስ አበባን ከከተማው ነዋሪ ስንረከባት ልናስውባት፣ ልናለማት ቃል ገብተን ነው የጀመርነው። ለትውልድ የምትተርፍ፣ ቆሻሻ እና ስንፍና የሌለባት ከተማ ልናድርጋት ቃል ገብተን ነበር። እነሆ ቃላችንን ጠብቀናል !!
እንካችሁ የፀዳች አራዳን፤ እንካችሁ 24 / 7 የምትተጋ አራት ኪሎን፤ አሁን ለናንተ ምቹ አድርገናታል። ከውበቷና ከፅዳቷ ሳትጎድል ለትውልድ አኑሯት።
የኮሪደር ልማት ስራዎች ስንጀምር አብራችሁን ለተነሳችሁ፣ ለተባበራችሁ፣ ላሳመራችሁ ባለቤቶች፣ ለተባበራችሁ ባለ ሀብቶች፣ ተቋራጮች፣ በሙያችሁ ለተጋችሁ ሰራተኞች እና አመራሮች እንዲሁም የፌደራል ተቋማት ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።
ከሁሉ በላይ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለነበራቸው ድጋፍና ክትትል ምስጋናዬ ትልቅ ነው።
በአጠቃላይም ትናንት ምሽት ስንጎበኝ በጎዳናዎች ላይ ስራዎቹን እያደነቃችሁ ፍቅራችሁን ለገለፃችሁልን ሁሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናችን ይድረሳችሁ።
ያስቀመጥንላችሁ ፎቶዎች ከፊል ገፅታዎች ናቸው። ሙሉውን ገፅታ መጥታችሁ ትመለከቱ ዘንድ እጋብዛችኋለሁ ።
ቀሪ የኮሪደር ስራዎቻችንን ፍጥነትን እና የፈጠራ መርህን ተከትለን አጠናቅቀን ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን።
ጥራትን ማስጠበቅ እና ለዜጎቻችን ሁሉ የተመቸ ከባቢን መፍጠር ቅድሚያ የምንሰጣቸው ተግባራት ናቸው።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስክ ስራ የሚንቀሳቀሱ ሰራተኞቹ ህብረተሰቡ በቀላሉ እንዲያውቃቸውና ትብብርና እገዛ እንዲያደርግላቸው ለማስቻል የተቋሙ አርማ ያለበት የደንብ ልብስ፣ ባጅና መታወቂያ እንዲሁም ተሽከርካሪ እንዲጠቀሙ ማድረጉን ገልጿል።ይህን ሳያሟሉ ከተቋሙ እንደተላኩ በማስመሰል ከሚያጭበርበሩ ግለሰቦች ህብረተሰቡ ራሱን እንዲጠብቅም አሳስቧል ፡፡
ተቋሙ ባወጣው መግለጫ አንዳንድ ግለሰቦች የተቋማችን የስራ ባልደረቦች እንደሆኑ በማስመሰል የማጭበርበር ሙከራ እንደሚያደርጉ እንዳንድ ደንበኞች ጥቆማውን አድርሰውናል ሲል አመልክቶ አንዳንድ ጊዜ አጣራጣሪ ሁኔታ ሲያጋጥም ህብረተሰቡ መታወቂያ ወይም ባጅ በመጠየቅ ማረጋገጥ እንደሚገባው በመግለጽ የተቋሙ ሰራተኞችም ለሂደቱ ተባባሪ መሆን እንዳለባቸው ሲያሳስብ ቆይቷል ብሏል፡፡
በመሆኑም የተቋማችን የስራ ባልደረቦች በመምሰል የሚያጭበረብሩ ግለሰቦችን በ905 ነፃ የጥሪ ማዕከል፣ በአቅራቢያ ለሚገኝ ቢሮዎቻችን ወይም ለሚመለከታቸው የህግ አስከባሪ አካል ጥቆማ በመስጠት ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው እንድታደርጉ ሲል ተቋሙ አሳስቧል።
የስልጤ ልማት ማህበር እያከናወነ ያለውን ለትውልድ የሚሻገሩ ስራዎችን የበለጠ በማጠናከር መንቀሳቀስ አለበት-ክብርት ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን
የስልጤ ልማት ማህበር እያከናወነ ያለውን ለትውልድ የሚሻገሩ ስራዎችን የበለጠ በማጠናከር ተልዕኮውንም ከዚህ በተሻለ መልኩ ለማድረግ መንቀሳቀስ አለበት ሲሉ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጂ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን ጥሪ አቀረቡ፡፡
ማህበሩ የማጠቃለያ ኮንፍረንሱን በአዲስ አበባ በዓድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጂ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን፤ ማህበሩ ለትውልድ የሚሻገሩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን በመግለፅ በቀጣይ ተልዕኮውን ከዚህ በተሻለ መልኩ በማድረግ መንቀሳቀስ አለበት ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የብልጽግና ጉዞ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች እንዲረጋገጥ የልማት ማህበሩ ትላልቅ የልማት ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ያሉት የስልጤ ልማት ማህበር የቦርድ ሰብሳቢና የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢሊ ከድር፤ በተለይ በጤናና በትምህርት ዘርፍ ለትውልድ የሚሸጋገሩ ተግባራትን አከናውኗል ብለዋል፡፡
በቀጣይ የ10 ዓመት የልማት ፍኖተ ካርታ ቀርጾ ወደተግባር ገብቷልም ብለዋል፡፡
ለዚህም ትብብርና አጋርነትን ለማጠናከር፣ የህዝብ ለህዝብ ትስስርን የበለጠ ለማጎልበትና የጋራ እሴቶችን ለማጠናከር ከዞኑ አጎራባች ህዝቦችና የልማት ማህበራት ጋር የጋራ አብሮነትን ለማሳደግ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት መፈረሙን አብራርተዋል፡፡
የስልጤ ልማት ማህበር ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አደም ኑሪ፤ ማህበሩ እስካሁን የሄደበትን ርቀት በመገምገም ለቀጣይ ልማት ስራው ውጤታማነት እንደ አዲስ የቦርድ አባላትን መርጦ ወደ ተግባር ገብቷል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ስልማ የጋራ አብሮነትና ልማትን ለማሳደግ የኦሮሚያ ልማት ማህበርን ጨምሮ ከጉራጌ ልማት ማህበርና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር የመግባቢያ ሰነድ መፈራረሙ ተመላክቷል፡፡
AMN-Addis Media Network
+4
ከተረጂነት ወደ ምርታማነት፣ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነትና ክብር " በሚል መሪ ከተረጂነት አስተሳሰብ መላቀቅን ትኩረት ያደረገ ህዝባዊ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በምክክር መድረኩ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ፣ እንዲሁም የግብርና ሚንስትር ዶ/ር ግርማ አመንቴን ጨምሮ ሌሎችም የፌዴራል እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተው ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ።
+4
ዛሬ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ብፁዕ አቡነ ማትያስ ጋር በመሆን በኮሪደር ልማት ምክንያት በፈረሱ ቤቶች ምትክ በቤተክርስቲያኒቱ የሚገነባ ህንፃ የመሠረተ ድንጋይ አስቀምጠናል።
ቤተ ክህነት የከተማውን ልማት ሥራ በላቀ ሁኔታ በመደገፍ እና ለኮሪደር ልማት ስራዎች መጀመር፤ በማፍረስ ሂደትም ሆነ መልሶ በመገንባት ሂደት እንዲሁም ህንፃዎችን በማደስ ላደረገችው ተሳትፎ እና ተግባራዊ የሆነ ምላሽ ከልቤ ለማመስገን እወዳለሁ።
በዚህ አጋጣሚ ከቤተክርስቲያንቱ ለቀረበልኝ ምስጋናም እጅግ በጣም አድርጌ አመሰግናለሁ ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
