fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید 👈

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
የአዲስ አበባ ከተማ ሰራ አሰኪያጅ ጽ/ቤት የሰርአተ ፆታ ማስረፅ ለተቋሙ ሴት ሰራተኞች እና ለተጠሪ ተቋማት የሴት ተወካዮች በማይንድ ሴት እና በውጤታማ የሰራና የህይወት ሚዛን ክህሎት ላይ ሰልጠና ሰጠ። በዚህ የሰራ ላይ ስልጠና የተገኙት በቢሮ ሀላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ሰራ አስኪያጅ እና የጥናት እና ትግበራ ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ እንደተናገሩት ሴቶች በተፈጥሮ የተሰጠንን ጥበብ በስልጠና አዳብረን እርስ በርስ ተጋግዘን እና ተደጋግፈን የሰራም የህይዎትም ተልዕኳች ን በብቃት መወጣት ይገባናል ሲሉ አስገንዝበዋል። የምንኖርባት አዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ ተልእኮ የተሰጣቸው ሴቶች እየመሩ አስደናቂ ውጤት እየተመዘገበባት ያለች ከተማ መሆኗን አውስተው እኛም ከተማችን ለሴቶች በሰጠችው እድል እና እየተመዘገባ ባለው ውጤት ትልቅ ትምህርት የምንወስድበት እና በስራችን የምንተረጉመው ነው ብለው በተቋማችን የተጀመሩ እንዲህ አይነት ሴቶችን የሚያበቁ ሰልጠናዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆናቸዉን ገልጸዋል። በሰርአተ ፆታ ሰርፀት አመቻችነት የተሰጠው ሰልጠና የሴቶችን አእምሯዊ ልህቀት በማሳደግ ውጤታማ የሰራና የህይወት ሚዛን ክህሎት እንዲኖራቸው እርስ በርስ በመደጋገፍ እንደ ተቋም የተሰጠን ተልእኮ ለመወጣት እንዲቻል አቅም የሚጨምር መሆኑ ተመልክቷል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

አዲስ ድል፤ ሌላ ስኬት! የአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል የምረቃ ስነ ስርዓት እና የምሽት ገፅታ በምስል:-

ከሰሞኑ በአዲስ አበባ የእሳት አደጋ ተደጋግሟል። ለምን ? ለእሳት አደጋ መከሰትና መባባስ ነፋሻማና ፀሀያማ አየር ንብረት እንዴት ምክንያት ሊሆን ይችላል ? እሳት ከተነሳ በኋላ የሚፈጠር ወይም የተፈጠረ ንፋስ የኦክስጂን አቅርቦትን በመጨመር ለቃጠሎ መባባስን ይፈጥራል፡፡ በነፋስ አማካኝነት ከፍተኛ ሙቀትን በመሸከም እና ፍም በመያዝ በአቅራቢያው ላሉና ቀድመው ላልተቀጣጠሉ ተቀጣጣይ ነገሮችን በተጨማሪ ወደ እሳትነት የመቀየር ሰፊ እድል አለው፡፡ ይህም ማለት ንፋስ ከእሳት ጋር ሲገናኝ የኦክስጅን መጠኑንን ስለሚጨምረው እሳቱ እያደገ ይሄዳል ፡፡ የንፋስ መኖር በማንኛውም ሰዓት እሳት አደጋ ከማስከተሉም በላይ የመቀጣጠል ሂደትን ከማፋጠን በተጨማሪም የእሳትን አቅጣጫ ሊያስቀይርና የደረሰው አደጋ ከቁጥጥር ውጭ ሊያደርግ ይችላል ፡፡ የእሳት አደጋ ተከላካዮች ላይም ስራቸውን በማክበድ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል፡፡ ብዙውን ጊዜ በአነስተኛ ብልጭታ በነፋስ የሚነድ እሳት ደን በተከማቸበት ወይም ቁጥቋጦ ባለበት አካባቢ ይፈጠራል ፡፡ በከተማ አካባቢም በእንጨትና ቆርቆሮ የተሰሩ እንዲሁም ያረጁ መኖሪያ ቤቶች ከመኖራቸው በተጨማሪ አንዳንድ ቦታዎች ደግሞ አደጋ በሚደርስበት ጊዜ አደጋውን ለመቆጣጠር የሚሆን የመንገድ መሠረተ ልማት ውስንነት በመኖሩ ጭምር አሁን ላይ ያለው የነፋሻማና ፀሀያማ አየር ንብረት ተጨምሮበት ከፍተኛ እሳት አደጋ እየተፈጠረ ቀላል የማይባል ጉዳት እያደረሰ ይገኛል፡፡ ኮሚሽን መ/ቤቱ እያጋጠሙ ያሉ አደጋዎችን አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራትን በሙሉ አቅሙ እያከናወነ ቢሆንም ስራዉ ለኰሚሽን መስሪያ ቤቱ ብቻ የሚተዉ ባለመሆኑ የከተማችን ነዋሪዎች የወቅቱን የአየር ንብረት ታሳቢ ያደረገ ጥንቃቄዎችን ማድረግ እንደሚገባ እያሳሰብን በተለያዩ አማራጮች እየተላለፉ ያሉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን በመተግበር ህይወትና ንብረትን ከአደጋ እንዲጠብቅ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል። ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ! ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

አዲስ ድል፤ ሌላ ስኬት! ትላንት በድምቀት የተመረቀው የአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል የምረቃ ስነ ስርዓት በምስል:-

አዲስ ድል፤ ሌላ ስኬት!! ከጅማሮው አንስቶ እስከሚጠናቀቅ ድረስ አብራችሁን የለፋችሁትን እና ያሳካችሁትን ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ።

የአፍሪካውያን የነጻነት ብስራት የመላ ኢትዮጵያውያን ደማቅ ታሪክ ለሆነው ለ129ኛው የአድዋ ድል በአል እንኳን አደረሳችሁ ! …

129ኛው የዓድዋ የድል በዓል በዓድዋ ድል መታሰቢያ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው "ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ በሚገኘው በዓል ላይ ድሉን በሚዘክሩ የፖናል ውይይት እና ሌሎች ዝግጅቶች ይቀርባሉ ተብሎም ይጠበቃል። በበዓሉ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታየ አፅቀስላሴን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፤ አባት አርበኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ AMN-Addis Media Network የካቲት 23/2017 ዓ.ም

እንኳን ለ129ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ አደረሰን የአድዋ ድል የኢትዮጵያዊያን ሕብረ ብሔራዊነት መገለጫ፣ የይቻላል መንፈስ ምንጭ፣ ያለፉ እና የቀጣይ ትውልዶች የወል ትርክት ነው። የአድዋ ድል በዓልን ስናከብር ድሉ በፈጠረልን የአንድነት እና የይቻላል መንፈስ የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ ያለንን ቁርጠኝነት በመግለፅ እንዲሆን ጥሪዬን አስተላልፋለሁ። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በዚህ ማዕከል ንግድ እንነግድበታለን፤ ሃሳብ እንለዋወጥበታለን።