fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید 👈

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
ለ129ኛው የዐድዋ ድል በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ። ዐድዋ ለሰላም የተደረገ ዘመቻ ነው። ከዐድዋ ዘመቻ በፊት ኢትዮጵያውያን ለሰላም ያላቸውን የጸና አቋም ደጋግመው ገልጸዋል። ለሰላም ያላቸው አቋም የጠላት ፉከራዎችንና ትንኮሳዎችን በትዕግሥት እስከማለፍ የደረሰ ነበር። እንደሚታወሰው የወራሪው የኢጣልያ ጦር ባንዳ ይመለምል ነበር። ባንዳ ያስታጥቅ ነበር። የባንዳ ተላላኪዎችን በመንግሥት ውስጥ ለማሥረግ ይሞክር ነበር። ሽብር ይነዛ ነበር። የኢትዮጵያን መንግሥት ይከስ ነበር። አንዳንድ ቦታዎችን ለመያዝ ይሞክር ነበር። በዓለም አቀፍ መድረክ ኢትዮጵያን ለማሳጣት ይፍጨረጨር ነበር። ኢትዮጵያ ይሄንን ሁሉ በትዕግሥት እና በዝግጅት ትመለከተው ነበር። ኢትዮጵያውያን ከጥንት ጀምሮ በጦርነት ኖረዋል። በዚህ የተነሣ የጦርነትን አስከፊ ገጽታ ያውቁታል። ስለሚያውቁትም በቻሉት አማራጭ ሁሉ ይሸሹታል። ለሰላማዊ አማራጭ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋሉ። አንዳንድ ጊዜም ለሰላም ሲሉ ከአስፈላጊው በላይም ያደርጋሉ። ይሄንን ሁሉ ገፍቶ የሚመጣ ጠላት ሲገጥማቸው ግን ለሰላም ሲሉ ዘምተው፤ ለሰላም ሲሉ ያሸንፋሉ። የዐድዋ ዘመቻም እንደዚሁ ነው። የወራሪው የኢጣልያ ጦር ወደ ጦርነት እንዳይገባ ተለምኗል። የሰላም አማራጮች ቀርበውለታል። "ኩራትና ትዕቢት የሞሉት አናት፣ ሰይፍና ጎራዴ የመቱት አንገት" እንደሚሉት ሆነ። የኢትዮጵያን ትዕግሥት እንደ ፍርሃት፣ የኢትዮጵያን የሰላም መንገድ እንደ ሽንፈት ቆጠረው። ጠላቶቻችን ምንጊዜም የስሌት ስሕተት ይሠራሉ። ትኅትናችን፣ ትዕግሥታችንና ሰላም ወዳድነታችን ያሳስታቸዋል። ወራሪው የኢጣልያ ጦርም ተሳሳተ። ኢትዮጵያውያን ግን እየታገሡ ይዘጋጁ ነበሩ። በሁሉም ረገድ ሰላማቸውን ለመጠበቅ ዝግጁ ነበሩ። ነጻነት ፣ ሉዓላዊነት እና ክብር የሚገኙት የሀገር ሰላምን በመጠበቅ መሆኑን ያውቃሉ። ስለዚህ ሰላማቸውን በክንዳቸው ለመጠበቅ ተዘጋጁ። የዐድዋ ጦርነት ለሰላምና ለጦርነት በሚዋጉ ኃይሎች መካከል የተደረገ ጦርነት ነው። የአሸናፊነታችን አንዱ ምሥጢርም ይሄው ነው። ከጦርነቱ በኋላ ወደ በቀልና ጥላቻ እንዳናመራ ያደረገንም ይሄው ነው። ለሰላም ስንል እንጂ ለጦርነት ስንል አልተዋጋንምና። የዐድዋ ድል ለሰው ልጅ ሉላዊ ዕሴቶች ያለንን ዋጋ አሳይተንበታል። በምርኮኛ አያያዛችን፣ ከተዋጉን ጋር መልሰን ለሰላማዊ ውይይት በመቀመጣችን፣ ለዘላቂ ሰላም በመሥራታችን። እናቶቻችንንና አባቶቻችንን በድል አድራጊነታቸው ብቻ ሳይሆን ለሰው ልጅ ዕሴቶች በከፈሉት ዋጋ ጭምር እናመሰግናቸዋለን። የተዋጉት ለሰላም ሲሉ ነው። የተዋጉት ሰላምን እና ሰላማዊ መንገድን እምቢ ካለ ኃይል ጋር ነው። የዐድዋ ዘማቾች ልጆች ነን። ለሰላም ቅድሚያ እንሰጣለን። ዛሬም ጠላቶቻችን ከተሳሳተ ስሌት እንዳልወጡ እናውቃለን። በሰላማዊ መንገድ የሚመጡትን መቀበል ከዐድዋ ዘማቾች ተምረናል። በሰላም የማይመጡትንም መቅጣት ከዐድዋ ዘማቾች አይተናል። እኛም እንደቀደምቶቻችን የሰላሙን መንገድ እንመርጣለን። ነገር ግን እንደ ቀደምቶቻችን ሁሉ፣ ለሁለቱም ምንጊዜም ዝግጁዎች ነን። የዐድዋ ዘማቾች ልጆች ነንና። መልካም በዓል ይሁን። ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!! ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ! የካቲት 22፣ 2017 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

ከሁሉ በማስቀደም የረዳን እና ያከናወነልን ፈጣሪ ይመስገን! ዛሬ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ያስመረቅነው የአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማእከል ለከተማችን ብሎም ለሀገራችን አዳዲስ እድሎችን የሚከፍት፣ የማያቋርጥ የሃብት ምንጭ መፍጠሪያ የሚሆን እንዲሁም ለገጽታ ግንባታ እና ለቱርስት ስበት ትልቅ ሚና የሚጫወት ማዕከል ነው:: ማዕከሉ አለምአቀፋዊ ኮንፍራንሶችን፣ የንግድ ውይይቶችንና ስምምነቶችን፣ ባህላዊ መድረኮችንና ልዩ ልዩ ኤግዚቢሽኖችን ለማስተናገድ እንዲሁም አዳዲስ ሃሳቦች የሚንሸራሸሩበት የንግድና የኢኮኖሚ ስምምነቶች የሚጎለብቱበት ነው:: 15ሺ ካሬ የውጪ ሁነት ማስተናገጃ ቦታ ያለው የአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማእከል ባለ 5 ኮከብ ዘመናዊ ሆቴል፣ ሪስቶራንቶች፣ የስፖርት፣ የጤና፣ የመዝናኛ እና የልዩ ልዩ አገልግሎት መስጫን ያከተተ ግዙፍ ማዕከል ነዉ። ከዚህም ባሻገር፣ በአንድ ጊዜ እስከ 2000 ተሽከርካሪዎችን ማቆም የሚችል ፓርኪንግ ያለዉ ሲሆን የለሚ ፓርክ እና በቀጥታ ከአየር መንገድ ጋር የሚያገናኝ ሰፊ የመንገድ መሰረተ ልማትም ከማዕከሉ ጋር ተያይዞ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል ፤ይህም ኢኮኖሚያችንን የሚያነቃቃ፣ ሰፊ የስራ እድል የሚፈጥር ከመሆኑ በላይ እንግዶች ሲመጡ ያለምንም እንግልት ሁሉንም አገልግሎቶች በአንድ ስፍራ እንዲያገኝ ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡ ይህ ስራ ከዳር እንዲደርስ የቅርብ ድጋፍና ክትትል ላደረጉልን ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ከፍ ያለ ምስጋናና አክብሮቴን በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ላቀርብ እወዳለሁ:: ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

''ዛሬ የምናስመርቀው የኮንቬንሽን ማዕከል ኢትዮጵያ ሰርታ የምታሳይ አርአያ መሆን የምትችል ሃገር መሆኗን ማሳያ ነው።'' - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ዛሬ የሚመረቀው አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል! - 40 ሄክታር መሬት ላይ አርፏል - እያንዳንዳቸው ከ3 ሺሕ እስከ 4 ሺሕ ሰዎችን የመያዝ አቅም ያላቸው 2 ትላልቅ አዳራሾች፣ 8 አነስተኛ እና መካከለኛ የመሰብሰቢያ አዳራሾች በጠቅላላ እስከ 10 ሺሕ ሰዎችን የሚያስተናግዱ - እስከ 1 ሺሕ ሰዎችን የሚያስተናግዱ አልጋዎችን የያዙ 2 ሆቴሎች - ከቤት ውጪ እስከ 50 ሺሕ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል የኤግዚቢሽን ስፍራ - አለምአቀፍ እና ሀገር አቀፍ ሁነቶችን የሚያስተናግድ

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በእሳት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸዉ ተጎጂዎች ድጋፍ አደረገ። የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በአዲስ ከተማ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 6 ሀብተጊዮርጊስ ድልድይ አካባቢ የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም በተከሰተዉ የእሳት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸዉ ተጎጂዎች ዛሬ የካቲት 22 ቀን 2017 ዓ.ም የአይነት ድጋፍ አድርጓል። ኮሚሽኑ መ/ቤቱ ተጎጂዎች በጊዚያዊነት በተጠለሉበት መጠለያ ተገኝቶ ፍራሽ ፣ ብርድልብስ ፣ የንጽህና መጠበቂያና የምግብ ማብሰያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል። በሌላ በኩልም በአደጋዉ ጉዳት ለደረሰባቸዉ ተጎጂዎች የስነ-ልቦና ድጋፍና የምክር አገልግሎት በኮሚሽኑ ባለሞያዎች ተሰጥቷቸዋል። ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በነፃ የስልክ መስመር በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ! ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ዛሬ በይፋ የሚመረቀው የአዲስ አለምአቀፍ የኮንቬንሽን ማዕከል:- - 40 ሄክታር መሬት ላይ አርፏል - እያንዳንዳቸው ከ3 ሺሕ እስከ 4 ሺሕ ሰዎችን የመያዝ አቅም ያላቸው 2 ትላልቅ አዳራሾች፣ 8 አነስተኛ እና መካከለኛ የመሰብሰቢያ አዳራሾች በጠቅላላ እስከ 10 ሺሕ ሰዎችን የሚያስተናግዱ - እስከ 1 ሺሕ ሰዎችን የሚያስተናግዱ አልጋዎችን የያዙ 2 ሆቴሎች - ከቤት ውጪ እስከ 50 ሺሕ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል የኤግዚቢሽን ስፍራ - ሁለት አንፊ ቴአትር - 2 ሄክታር የዉጪ ኤግዚቢሽ ቦታ - ሁለት ሞሎች - ሬስቶራንቶች፣ በርካታ የንግድ ሱቆች፣ ባንኮች እንዲሁም ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት - በሀገራችን ትልቁ የኮንፍራንስ ማዕከል - አለምአቀፍ እና ሀገር አቀፍ ሁነቶችን የሚያስተናግድ - በከተማችን ከመስቀል አደባባይ ቀጥሎ ሁለተኛው ግዙፍ አደባባይ ከሆነው የለሚ ፓርክ ጋር ተያይዞ የተሰራ በአጠቃላይ እስከ 2 ሺሕ መኪናዎችን የማቆም አቅም ያላው ግዙፍ ፕሮጀክት ነው::

በም /ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጀነር ወንድሙ ሴታ በእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸዉን ተጎጂዎች ጎበኙ። የካቲት 21 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ ከተማ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 6 ሀብተጊዮርጊስ ድልድይ አካባቢ በተከሰተዉ የእሳት አደጋ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸዉ ነዋሪዎች በጊዚያዊነት በተጠለሉበት ቦታ ተገኝቸዉ ጎብኝተዋል። ኢንጀነር ወንድሙ ከተጎጂዎች ጋር ባደረጉት ዉይይት በተፈጠረዉ አደጋ በደረሰዉ ጉዳት እጅግ ማዘናቸዉን ገልጸዉ ተጎጂዎችን ለማገዝ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በጉብኝት መርሀ -ግብሩ ላይ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ኮማንደር አህመድ መሀመድና የአዲስ ከተማ ክፍለ-ከተማ አመራሮች ተገኝተዋል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

ህብረተሰቡ የፅዳቱ ባለቤት እንዲሆን በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ነው። የካቲት22/2017 ዓ.ም ****************** ላለፉት ዓመታት የከተማዋን ፅዳት ለመጠበቅና ህብረተሰቡ የፅዳቱ ባለቤት እንዲሆን በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ ገልፀዋል። በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 02 በተካሄደው የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ዋና ዳሬክተሩ የከተማዋን ፅዳት በዘላቂነት ለመጠበቅ በመንግሰት አቅም ብቻ ሳይሆን የሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ንቁ ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ገልፀው እያንዳንዱ ነዋሪ አካባቢውን በ20 ሜትር ርቀት ፅዳቱን መጠበቅ እንዳለበት አብራርተዋል። በየሳምንቱ በሚካሄዱ የፅዳት ንቅናቄ ስራዎች ብቻ የአካባቢ ፅዳት አይጠበቅም ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ፅዳትን ባህል አድርጎ የአካባቢን ፅዳት ማስጠበቅ ላይ የህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ ነው ብለዋል። አካባቢያችንን ማፅዳት ብቻ ሳይሆን ዳግም የቆሻሻ መጣያ ቦታ እንዳይሆኑ ነዋሪው በባለቤትነት መጠበቅ ይኖርበታልም ብለዋል:: ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ብዙሀኑ ያፀዳውን ጥቂቶች ማቆሸሸ ስለማይገባቸው በህግ ተጠያቂ የማድረጉ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። የቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘሪሁን ዘለቀ በበኩላቸው በወረዳቸው ላይ በተሰሩ የፅዳት፣ የውበት እና አረንጓዴ ስራዎች ምክንያት በርካታ ሞዴል ብሎኮች መፍጠር መቻላቸውን ገልፀዋል። አቶ ዘሪሁን አክለውም የተፈጠሩ ሞዴል ብሎኮች ዳግም የአካባቢን ገፅታ እንዳያባላሹ ለነዋሪው ህብረተሰብ በባለቤትነት እንዲጠብቁ የማስተላለፍ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም አብራርተዋል። ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

የአዲስ ዓለምአቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ራዕይ መዲናችን አዲስ አበባ በአህጉራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ኩነቶች መስተንግዶ በአፍሪካ ቀዳሚ ሆና ማየት ሲሆን፣ ይህ ታላቅ ጉዞ መጀመሩ ለመላው ኢትዮጵያውን ከፍ ያለ ኩራት ነውና በድጋሚ እንኳን ደስ አለን! ከንቲባ አዳነች አቤቤ