fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
ለግንዛቤ.... የጋብቻ ምዝገባ አገልግሎት እና ማስረጃ ሲፈልጉ ማሟላት ያለብዎት ቅድመ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው:: 1. ተጋቢዎች ጋብቻ ለመፈፀም ማሰባቸውን እጅግ ቢዘገይ ጋብቻቸውን ለመፈፀም ከወሰኑበት ቀን ከአንድ ወር በፊት ለክብር መዝገብ ሹሙ ማስታወቅ አለባቸው፡፡ ሆኖም ይህ ድንጋጌ በሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ስርዓት የሚፈፀም ጋብቻን አይመለከትም፡፡ 2. የክብር መዝገብ ሹሙ ጥያቄው በቀረበለት ቀን ከተጋቢዎቹ ጋር በመነጋገር ከወሰነ በኃላ በማግስቱ ጋብቻው የሚፈፀምበትን ቀን በመግለጽ አመቺ በሆነው መንገድ ለ15 ተከታታይ ቀን የሚቆይ ማስታወቂያ ያወጣል፡፡ 3. ማስታወቂያ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ የጋብቻ መቃወሚያ በጽሁፍ መቅረብ አለበት፤ መቃወሚያ ሊያቀርቡ የሚችሉ ወላጆችና ተወላጆች፣ አቃቤ ሕግ፣ አሳዳሪ ወይም የቀደመ ጋብቻ አለኝ የሚል ሰው መሆን አለበት፡፡ 4. የክብር መዝገብ ሹሙ በቀረበው የጋብቻ መቃወሚያ ላይ በአምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውሳኔ በመስጠት ማሳወቅ አለበት፡፡ 5. ወንደም ሆነ ሴቷ 18 ዓመት ሳይሞላቸው ጋብቻ መፈፀም አይችለም፡፡ ደጋፊ ማስረጃዎች :- 1. ተጋቢዎች ጊዜው ያላለፈበት የነዋሪነት ወይም ብሔራዊ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም ስደተኛነቱን የሚገልጽ ማስረጃ ወይም የመኖሪያ ፈቃድ ወይም ከዝቅተኛው የአስተዳደር ጽህፈት ቤት የተሰጠ የነዋሪነት ማስረጃ ወይም የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ ዜግነት መታወቂያ መቅረብ አለበት፡፡ 2. ጋብቻው የሚፈፀመው በተጋቢ ወላጆች ወይም በቅርብ ዘመዶች መደበኛ መኖሪያ ቦታ ከሆነ የወላጆች ወይም የቅርብ ዘመዶች የነዋሪነት/ብሄራዊ መታወቂያ ወይም ከዝቅተኛው የአስተዳደር ጽህፈት ቤት የተሰጠ የነዋሪነት ማስረጃ መቅረብ አለበት፡፡ 3. ካምፕ/ፕሮጄክት በሚገኝበት አስተዳደር ጽ/ቤት መደበኛ ነዋሪነት መታወቂያ የሌላቸዉ ጋብቻ አስመዝጋቢዎች ጋብቻን ማስመዘገብ ሲፈልጉ ካምፑ/ ፕሮጄክቱ/ፋብሪካው የምዝገባ ጽ/ቤቱ በሚገኝበት አስተዳደር ጽ/ቤት አካባቢ መሆኑን በማረጋገጥና ተመዝጋቢዎቹ/አስመዝጋቢዎቹ የካምፑ/የፕሮጄክቱ/ የፋብሪካው ሰራተኛ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ሲያቀርቡ መመዝገብ ይችላሉ፡፡ 4. የተጋቢ ምስክሮች አገልግሎቱ ያላለፈበት የነዋሪነት/ብሄራዊ ወይም ፓስፖርት ወይም ማንነታቸውን የሚገልጽ ማስረጃ መቅረብ አለበት፡ 5. ሙሽራው/ዋ ከዚህ በፊት አግብቶ/ታ የፈታ/ች ከሆነ የፍቺ ምስክር ወረቀት ካለ መቅረብ አለበት፡፡ 6. ከ 6 ወር ወዲህ በተመሳሳይ ጊዜ የተነሱት ሁለት ሁለት 3 በ 4 የሆነ የተጋቢዎች ፎቶ-ግራፍ መቅረብ አለበት፡፡ 7. በሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ስርዓት የተፈፀመ ጋብቻ የተጋቢዎች ምስክሮች ወይም በጋብቻ ስርዓቱ ላይ የታደመ ሰው በክብር መዝገብ ሹሙ ፊት በአካል ቀርበው ፊርማቸውን ማኖር አለባቸው፡፡ 8. የተጋቢዎች የልደት ምስክር ወረቀት ካለ መቅረብ አለበት፡፡ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ቦታ:- በወረዳ የሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ ቅጽ/ቤት አገልግሎቱን ለማግኘት የተቀመጠው ጊዜ:- 20 ደቂቃ አገልግሎቱን ለማግኘት የሚጠይቀው ክፍያ:- 1.ለወቅታዊ ምዝገባ 120.00 ብር 2.ለዘገየ ምዝገባ 200.00 ብር 3.የጊዜ ገደቡ ያለፈ ምዝገባ 250.00 ብር 4.ለእርማት፣ ለእድሳት፣ ለማመሳከርና ለግልባጭ150.00 ብር ለምትክ ምስክር ወረቀት 120.00ብር በመክፈል አገልግሎቱን ማግኘት ይቻላል:: ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...

"ውድ ተገልጋዮቻችን በዋና የከተማችን መረጃ ማዕከል ላይ በገጠመ የቴክኒካል ብልሽት የዲጂታል አገልግሎታችን ከዛሬ መጋቢት 10/2016ዓ.ም ከስዓት 9:00 ጀምሮ ተቋርጧል። ከከተማው የኢኖቬሽን እና
"ውድ ተገልጋዮቻችን በዋና የከተማችን መረጃ ማዕከል ላይ በገጠመ የቴክኒካል ብልሽት የዲጂታል አገልግሎታችን ከዛሬ መጋቢት 10/2016ዓ.ም ከስዓት 9:00 ጀምሮ ተቋርጧል። ከከተማው የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እንዲሁም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ ጥገና በማድረግ ለመፍታት ጥረት እያደረግን ያለን ሲሆን የከተማችን ነዋሪዎች በትዕግስት እንድትጠባበቁን በአክብሮት እንጠይቃለን። " የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ C R R S A ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...

የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ስርቆት ላይ የተሰማሩና ከተማዋን በሚያቆሽሹ አካላትና ተቋማት ላይ በአፋጣኝ የተጠያቂነት ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ማሳሳቢያ ተሰጠ። በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የከተማ ም/ዋ/ስራ አስኪያጅና የአገልግሎት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ተፈራ ሞላ እና በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የፅ/ ቤቱ ም/ ዋ/ ስራ አስኪያጅና የጥናትና ትግበራ ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ በመሩት መድረክ በዛሬው እለት በከተማ ኤሌክትረክ አገልግሎት ጋር ተያይዞ የሚታይ የኃይል መቆራረጥ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት እንዲሁም በከተማው ጽዳት ህገወጥነትን በመከላከል ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል:: በዚሁ መድረክ ላይ ከአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በከተማው በኤሌክትሪክ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የኃይል መቆራረጥ መንስኤና መፍትሄ የባለድርሻ አካላት ሚና በሚል የተዘጋጀ ሰነድ ለውይይት ቀርቧል:: በጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ በኩል የኤጀንሲው ም/ ዋ/ ዳይሬክተር አቶ ሙላት ተገኝ በፅዳት ዙሪያ ህገ ወጥነትን ለመከላከልና እርምጃ ለመውሰድ የተዘጋጀ የውይይት መነሻ ሰነድ አቅርበዋል:: በሰነዱ ላይ በቅንጅታዊ አሰራር ፎረም የተካተቱ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት ተካሂዷል:: በማጠቃለያም የፅ/ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮቾ በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ስርቆት ላይ የተሰማሩና ከተማዋን በሚያቆሽሹ ህገወጦች ላይ የተጠያቂነት እርምጃ መውሰድ እንደሚገባ አሳስበዋል። የኤሌክትሪክ ሃይል መቆራረጥ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች የሚመለከታቸው ተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር በአፋጣኝ ለችግሩ መፍትሄ መስጠት እንደሚገባም በአፅንኦት አሳስበዋል:: ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...

በአዲስ አበባ ከተማ ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ከኤሌክትሪክ አገልግሎትና በፅዳት ዙሪያ እየተከናወኑ ባሉ ተግባራትና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በቅንጅት ለመፍታት ያለመ የባለድርሻ አካላት መድ
+5
በአዲስ አበባ ከተማ ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ከኤሌክትሪክ አገልግሎትና በፅዳት ዙሪያ እየተከናወኑ ባሉ ተግባራትና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በቅንጅት ለመፍታት ያለመ የባለድርሻ አካላት መድረክ በመካሄድ ላይ ነው:: በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ ዋ/ ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ መድረኩን በመክፈቻ ንግግር አስጀምረዋል:: በመድረኩ ላይ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን:ከአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን: ከንግድ ቢሮ: አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን :ከከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ: ከህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሸን:ከግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን እንዲሁም ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ዘርፍ የሚመለከታቸው ተቋማትና የክ/ከተማ ስራ አስኪያጆች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ:: ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...

በድርጅቱ ዉስጥ የሚከሰቱ የእሳት ቃጠሎና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎችን በአጭር ጊዜ ለመቆጣጠር፣ እንዲሁም በህይወትም ሆነ በንብረት ላይ ሊደርስ የሚችለዉን አደጋ ለማስቀረት፣ የጉዳቱን መጠን ለመቀነስ እንዲሁም ተገቢዉን ዕርዳታ በተቀላጠፈ ሁኔታ ለመስጠት ያመች ዘንድ መተላለፊያ መንገዶች ከማናቸዉም አደናቃፊ ነገሮች ነጻ ሆነዉ እና ከመዉጫ በሮች ጋር ትይዩ ሆነዉ ሊዘጋጁ ይገባል፡፡ 6. የማንቂያ ደወል / Fire Alarm/፡- • ከሥራ መግቢያና መዉጫ ሰዓት ከሚሰማዉ የደወል ድምጽ የተለየ ሆኖ የእሳት ቃጠሎ አደጋ መከሰቱን የሚያስገንዘብ ሲሆን እያንዳንዱ ሠራተኛ የሣይረኑን ድምጽ በሚስማበት ወቅት አደጋ መፈጠሩን ተገንዘቦ አደጋዉ ከተፈጠረበት አካባቢ እራሱን ነፃ በማድረግ በአደጋ ጊዜ መገናኛ ወይም መሰብሲቢያ ሥፍራ እንዲገኝና በአቅራቢያዉ የሚያገኘዉን የማጥፊያ መሣሪያ ይዞ በመሄድ እሳቱን ለማጥፋት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ለማድረግ ያስችላል፡፡ 7የአደጋ ማሳወቂያ መሳሪያዎች /Detectors/ • የእሳት ቃጠሎ አደጋን ሊያስከትሉ የሚችሉ ሁኔታዎችን የሚያሳዉቁ ማለትም ከሚቀጣጠልዉ ነገር በሚወጣዉ ጭስ፡- ሙቅትና ነበልባል በቀላሉ ሊቀጣጠሉ የሚችሉ ጋሶች ከመያዣ ዕቃዎች ዉስጥ አምልጠዉ በመዉጣት ከፍተኛ ቃጠሎን በመፍጠር ሕይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከመፈጠሩ አስቀድሞ ለመቆጣጠር እንዲቻልና በተለይም በሰዉ ላይ ጉዳት ለያደርሱ የሚችሉ ሁኔታዎችን ጭምር የሚጠቁሙ መሣሪያዎች ሰለሆኑ እንደየሥራ ባህሪዉ በተገቢዉ ቦታ ላይ መዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡ 8.የዕቃዎች አደራደር፡- በማናቸዉም ድርጅቶች ዉስጥ በተለያዩ መጋዘኖች ዉስጥ ንብረቶች ሲቀመጡ በዓይነታቸዉና እንደየመቀጣጠል ባህሪያቸዉ ተለይተዉ በየድርድሩ መካከል በቂ መተላለፊያ በማስቀረት ከግድግዳዉ የተወሰነ ክፍተት በመተዉና በመጋዘኑ ዉስጥ በቂ የአየር ምልልስ እንዲኖር በማድረግ የንብረት አያያዝ ወይም የእቃዎች አደራደርን ከቃጠሎ አደጋ ሊጠበቁ በሚችሉበት ሁኔታ ማከማቸት ይገባል፡፡ ይህም በእሳት ቃጠሎ አደጋ ወቅት ንብረትን ከአደጋ ሥፍራ ለማዳን፣ ቃጠሎዉን በቀላሉ ለመቆጣጠርና እሳቱ እንዳይስፋፋ ይረዳል፡፡ ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

በተለያዩ ተቋማት ውስጥ መፈጸም እና መሟላት የሚገባቸው የቅድመ አደጋ መከላከል የደህንነት ተግባሮች:- 1.በቂ የማምለጫ በሮች፣ /Emergency Exit/ በአንድ ድርጅት ዉስጥ የበሮች ብዛት ከሁለት በላይ ሆነዉ መዘጋጀት የሚኖርባቸዉ ሲሆን የበሮች ብዛት ሊወሰን የሚችለዉ የሚከተሉትን ነጥቦች መሠረት በማድረግ ሊሆን ይችላል፡፡  የድርጅቱን ስፋት፣  የጥሬ ዕቃዎችና የምርት ዉጤት ብዛትና ዓይነት፣  የማምረቻ መሣሪያዎች ብዛት፣  በድርጅቱ ተቀጥረዉ ያሉና ለወደፊት ሊቀጠሩ የታሰቡ ሠራተኞች ብዛት፣  የተገልጋዮች /የጎብኝዎች/ ብዛትን ታሣቢ በማድረግ ነዉ፡፡ የማምለጫ በሮች አላማ፡- • የተወሰኑ በሮች በአደጋ ወይም በቃጠሎ አደጋ ቢያዙ ቀሪዎቹ ፡- 1. ሰዎች ከአደጋዉ ስፍራ በቀላሉ ማምለጥ እንዲችሉ /ሕይወትን ለመታደግ/ 2. ንብረትን ከአደጋ ለማዳን፣ 3. አደጋዉን በተለያዩ አቅጣጫዎች በመግባት በአፋጣኝ በቁጥጥር ሥር ለማዋል እንዲቻል ነዉ፡፡ 2.በቂ የእሳት ማጥፊያ መሣሪያዎች፡- • እንደ ድርጅቱ የሥራ ባሕሪይና ባሉት የሥራ ክፍሎች ብዛት አኳያ በቂና ተገቢ የሆኑ የእሳት ማጥፊያ መሣሪያዎ ሊዘጋጁ ይገባል፡፡ እነሱም፡- • በቋሚነት /Fixed Installation/ • በተንቀሳቃሽ /Mobile/ • በቀላሉ በእጅ የሚያዙ /Portable/ የእሳት ማጥፊያ መሳሪያዎችን እንዲሟሉ በማድረግ እይታን ከሚከለከሉና መሰናክል ከሚሆኑ ነገሮች ነፃ ሆነዉ በስድስት ወር አንድ ጊዜ ፍተሻ እየተደረገላቸዉ ደህንነታቸዉን በማረጋገጥ ከመሬት በ1.50 ሜትር ከፍታ በግድግዳ ላይ ማዘጋጅት ያስፈልጋል፡፡ 3.በእሳት አደጋ መከላከልና መቆጣጠር ሙያ የሰለጠነ የሠው ሀይል ማዘጋጀት 4. ዓለም አቀፍ የድህንነት ምልክቶችን ማዘጋጀት • በድርጅቱ ውስጥ ባለው የጥሬ ዕቃ፣ የምርት ውጤት ዓይነት፣ እንደተቁዋሙ አይነትና የአገልግሎት አሰጣጥ፣ እንዲሁም የአንድን የሥራ አካባቢ ምንነት የሚገልፁ ምልክቶችን በቅድሚያ ማዘጋጀት ተገቢ ሲሆን ይህም በሰውም ሆነ በንብረት ላይ አደጋን ሊያስከትሉ የሚችሉ ሁኔታዎችን በቅድሚያ በማስገንዘብ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ያስቀራሉ /ይከላከላሉ/፡፡ 5. በቂ መተላለፊያዎች፡- በድርጅቱ ዉስጥ የሚከሰቱ የእሳት ቃጠሎና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎችን በአጭር ጊዜ ለመቆጣጠር፣ እንዲሁም በህይወትም ሆነ በንብረት ላይ ሊደርስ የሚችለዉን አደጋ ለማስቀረት፣ የጉዳቱን መጠን ለመቀነስ እንዲሁም ተገቢዉን ዕርዳታ በተቀላጠፈ ሁኔታ ለመስጠት ያመች ዘንድ መተላለፊያ መንገዶች ከማናቸዉም አደናቃፊ ነገሮች ነጻ ሆነዉ እና ከመዉጫ በሮች ጋር ትይዩ ሆነዉ ሊዘጋጁ ይገባል፡፡ 6. የማንቂያ ደወል / Fire Alarm/፡- • ከሥራ መግቢያና መዉጫ ሰዓት ከሚሰማዉ የደወል ድምጽ የተለየ ሆኖ የእሳት ቃጠሎ አደጋ መከሰቱን የሚያስገንዘብ ሲሆን እያንዳንዱ ሠራተኛ የሣይረኑን ድምጽ በሚስማበት ወቅት አደጋ መፈጠሩን ተገንዘቦ አደጋዉ ከተፈጠረበት አካባቢ እራሱን ነፃ በማድረግ በአደጋ ጊዜ መገናኛ ወይም መሰብሲቢያ ሥፍራ እንዲገኝና በአቅራቢያዉ የሚያገኘዉን የማጥፊያ መሣሪያ ይዞ በመሄድ እሳቱን ለማጥፋት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ለማድረግ ያስችላል፡፡ 7የአደጋ ማሳወቂያ መሳሪያዎች /Detectors/ • የእሳት ቃጠሎ አደጋን ሊያስከትሉ የሚችሉ ሁኔታዎችን የሚያሳዉቁ ማለትም ከሚቀጣጠልዉ ነገር በሚወጣዉ ጭስ፡- ሙቅትና ነበልባል በቀላሉ ሊቀጣጠሉ የሚችሉ ጋሶች ከመያዣ ዕቃዎች ዉስጥ አምልጠዉ በመዉጣት ከፍተኛ ቃጠሎን በመፍጠር ሕይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከመፈጠሩ አስቀድሞ ለመቆጣጠር እንዲቻልና በተለይም በሰዉ ላይ ጉዳት ለያደርሱ የሚችሉ ሁኔታዎችን ጭምር የሚጠቁሙ መሣሪያዎች ሰለሆኑ እንደየሥራ ባህሪዉ በተገቢዉ ቦታ ላይ መዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡ 8.የዕቃዎች አደራደር፡- በማናቸዉም ድርጅቶች ዉስጥ በተለያዩ መጋዘኖች ዉስጥ ንብረቶች ሲቀመጡ በዓይነታቸዉና እንደየመቀጣጠል ባህሪያቸዉ ተለይተዉ በየድርድሩ መካከል በቂ መተላለፊያ በማስቀረት ከግድግዳዉ የተወሰነ ክፍተት በመተዉና በመጋዘኑ ዉስጥ በቂ የአየር ምልልስ እንዲኖር በማድረግ የንብረት አያያዝ ወይም የእቃዎች አደራደርን ከቃጠሎ አደጋ ሊጠበቁ በሚችሉበት ሁኔታ ማከማቸት ይገባል፡፡ ይህም በእሳት ቃጠሎ አደጋ ወቅት ንብረትን ከአደጋ ሥፍራ ለማዳን፣ ቃጠሎዉን በቀላሉ ለመቆጣጠርና እሳቱ እንዳይስፋፋ ይረዳል፡፡ ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et በተለያዩ ተቋማት ውስጥ መፈጸም እና መሟላት የሚገባቸው የቅድመ አደጋ መከላከል የደህንነት ተግባሮች:- 1.በቂ የማምለጫ በሮች፣ /Emergency Exit/ በአንድ ድርጅት ዉስጥ የበሮች ብዛት ከሁለት በላይ ሆነዉ መዘጋጀት የሚኖርባቸዉ ሲሆን የበሮች ብዛት ሊወሰን የሚችለዉ የሚከተሉትን ነጥቦች መሠረት በማድረግ ሊሆን ይችላል፡፡  የድርጅቱን ስፋት፣  የጥሬ ዕቃዎችና የምርት ዉጤት ብዛትና ዓይነት፣  የማምረቻ መሣሪያዎች ብዛት፣  በድርጅቱ ተቀጥረዉ ያሉና ለወደፊት ሊቀጠሩ የታሰቡ ሠራተኞች ብዛት፣  የተገልጋዮች /የጎብኝዎች/ ብዛትን ታሣቢ በማድረግ ነዉ፡፡ የማምለጫ በሮች አላማ፡- • የተወሰኑ በሮች በአደጋ ወይም በቃጠሎ አደጋ ቢያዙ ቀሪዎቹ ፡- 1. ሰዎች ከአደጋዉ ስፍራ በቀላሉ ማምለጥ እንዲችሉ /ሕይወትን ለመታደግ/ 2. ንብረትን ከአደጋ ለማዳን፣ 3. አደጋዉን በተለያዩ አቅጣጫዎች በመግባት በአፋጣኝ በቁጥጥር ሥር ለማዋል እንዲቻል ነዉ፡፡ 2.በቂ የእሳት ማጥፊያ መሣሪያዎች፡- • እንደ ድርጅቱ የሥራ ባሕሪይና ባሉት የሥራ ክፍሎች ብዛት አኳያ በቂና ተገቢ የሆኑ የእሳት ማጥፊያ መሣሪያዎ ሊዘጋጁ ይገባል፡፡ እነሱም፡- • በቋሚነት /Fixed Installation/ • በተንቀሳቃሽ /Mobile/ • በቀላሉ በእጅ የሚያዙ /Portable/ የእሳት ማጥፊያ መሳሪያዎችን እንዲሟሉ በማድረግ እይታን ከሚከለከሉና መሰናክል ከሚሆኑ ነገሮች ነፃ ሆነዉ በስድስት ወር አንድ ጊዜ ፍተሻ እየተደረገላቸዉ ደህንነታቸዉን በማረጋገጥ ከመሬት በ1.50 ሜትር ከፍታ በግድግዳ ላይ ማዘጋጅት ያስፈልጋል፡፡ 3.በእሳት አደጋ መከላከልና መቆጣጠር ሙያ የሰለጠነ የሠው ሀይል ማዘጋጀት 4. ዓለም አቀፍ የድህንነት ምልክቶችን ማዘጋጀት • በድርጅቱ ውስጥ ባለው የጥሬ ዕቃ፣ የምርት ውጤት ዓይነት፣ እንደተቁዋሙ አይነትና የአገልግሎት አሰጣጥ፣ እንዲሁም የአንድን የሥራ አካባቢ ምንነት የሚገልፁ ምልክቶችን በቅድሚያ ማዘጋጀት ተገቢ ሲሆን ይህም በሰውም ሆነ በንብረት ላይ አደጋን ሊያስከትሉ የሚችሉ ሁኔታዎችን በቅድሚያ በማስገንዘብ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ያስቀራሉ /ይከላከላሉ/፡፡ 5. በቂ መተላለፊያዎች፡-

መዲናችን አዲስ አበባን እንደ ስሟ ፅዱ ንፁህና ማራኪ ለማድረግ ነዋሪዎቿ የሚያደርጉትን የየእለት ጥረት ከምንም ባለመቁጠር በግዴለሽነት አካባቢን ማቆሽሽና የከተማዋን ገጽታ ማበላሸት ተጠያቂነትን ያስከትላል:: በዚህም መሠረት 1 ማንኛውም ሰው ያመነጨውን ደረቅ ቆሻሻ በግቢው ውስጥ በአግባቡ አለመያዝ፤ በዓይነት አለመለየት፤ ማዝረክረክ፤ ለጤናና የአካባቢ ገጽታ በሚጎዳ መልኩ ማከማቸት፤ ከዚህ ቀጥሎ የተጠቀሱትን የገንዘብ ቅጣት ያስቀጣል:: ያከማቸውን ደረቅ ቆሻሻም እንዲያነሳ ይደረጋል:: 1.1 ከመኖሪያ ቤት ከሆነ ብር 500 1.2 ከድርጅት ከሆነ ብር 3,000. ማንኛውም የጽዳት ድርጅት/ማህበር አገልግሎት ሰጭ ከሆነ 2.1 ደረቅ ቆሻሻ ሲሰበስብ በአካባቢው ላይ ካንጠባጠበ ወይም የአካባቢውን ገጽታ ካበላሸ 300 ብር 2.2 በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት ለደንበኛው ተገቢውን አገልግሎት ካልሰጠ 1,000.ብር 2.3 . ከጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ እውቅና ውጭ የአገልግሎት ክፍያ ከደንበኛው ከተቀበለ ብር 3,000. 2.4 ጊዚያዊ የደረቅ ቆሻሻ ማስቀመጫቦታዎችን እሰከ 5 ሜትር ዙሪያ ድረስ ጽዱ ካላደረገ ብር 1,000 ለመልሶ መጠቀምና ኡደት አገልግሎት የሚውል ደረቅ ቆሻሻ ከጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ህጋዊ እውቅና ሳይኖረው በግል፤ በማህበርም ይሁን በድርጅት ስም በግቢ ውስጥ ወይም በክፍት ቦታ ላይ ያከማቸ፤ ብር 2,000 ያስቀጣል:: ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok 👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager... Website 👇👇👇👇 https://www.aacitymanger.gov.et

"እናገልግለዎ" በሚል የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ኤፍ ኤም 97 .1 ጋር በየሳምንቱ ማክሰኞ ማለዳ ከ2 ሰዓት 30 እስከ 3 ሰዓት የሚተላለፈውን ፕሮግራም ይከታተሉ:: ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:-… See mor"እናገልግለዎ" በሚል የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ኤፍ ኤም 97 .1 ጋር በየሳምንቱ ማክሰኞ ማለዳ ከ2 ሰዓት 30 እስከ 3 ሰዓት የሚተላለፈውን ፕሮግራም ይከታተሉ:: ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:-… See mor

በአዲስ አበባ ከተማ ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ከኤሌክትሪክ አገልግሎት አሰጣጥና በፅዳት ዙሪያ እየተከናወኑ ባሉ ተግባራትና ባጋጠሙ ተግዳሮቶችን በቅንጅት ለመፍታት ያለመ የባለድርሻ አካ
+7
በአዲስ አበባ ከተማ ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ከኤሌክትሪክ አገልግሎት አሰጣጥና በፅዳት ዙሪያ እየተከናወኑ ባሉ ተግባራትና ባጋጠሙ ተግዳሮቶችን በቅንጅት ለመፍታት ያለመ የባለድርሻ አካላት መድረክ በመካሄድ ላይ ነው:: በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ ዋ/ ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ መድረኩን በመክፈቻ ንግግር አስጀምረዋል:: በመድረኩ ላይ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን:ከአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን: ከንግድ ቢሮ: አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን :ከከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ: ከህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሸን:ከግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን እንዲሁም ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ዘርፍ የሚመለከታቸው ተቋማትና የክ/ከተማ ስራ አስኪያጆች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ:: ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...

ለግንዛቤዎ ... ደረቅ ቆሻሻ ምን ማለት ነዉ ? በምድር ላይ የቆሻሻ እድሜ ከሰው ልጅ እድሜ ጋር ይወዳደራል፡፡ የሰው ልጅ አንድ ብሎ በምድር ላይ ከተፈጠረበት ጊዜ አንስቶ መሰረታዊ ፍላጎቶቹን ለማሟላት በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ቆሻሻን ሲፈጥር ኖሯል፡፡ ይህ ሀቅ የሰው ልጅ በምድር ከተፈጠረበት ጊዜ አንስቶ የነበረ አሁንም ያለ ወደፊትም የሚቀጥል ነው፡፡ ይህ ከሰው ልጅ መፈጠር ጋር አብሮ የተፈጠረ ቆሻሻን የማምረት ጉዳይ የህዝብ ቁጥር ሲጨምር የሚመረተው የቆሻሻ መጠን አብሮ መጠኑ እየጨመረ መሄዱ እሙን ነው::የሰው ልጅ በፈጠራ ተራቆ በቴክኖሎጂ ውጤቶች ሲመጥቅ በአይነቱና በይዘቱ ይበልጥ እየተወሳሰበና አደገኛነቱ እየጨመረ አሁን ያለንበት ዘመን ላይ ደርሷል፡፡ ደረቅ ቆሻሻ ማለት ከመኖሪያ ቤት፣ ከንግድ ተቋማት ፣ ከኢንዱስትሪ ፣ ከልዩ ልዩ ተቋማት ፣ ከጋራዥ ፣ ከመንገዶች፣ ከግብርና በአጠቃላይ በሰዎችና በእንስሳት እንቅስቃሴ ምክንያት የሚፈጠር ጥቅም የማይሰጥ (የማይፈለግ ) ተብሎ የሚጣል ጠጣርና ከፊል ጠጣር ቆሻሻ ነዉ፡፡ ይሁን እንጅ ደረቅ ቆሻሻ የ ‹‹መ›› ህጎች አሉት ፡፡ የደረቅ ቆሻሻ የ‹‹መ›› ህጎች የሚባሉት መቀነስ ፣ መልሶ መጠቀም ፣ መለወጥ (መልሶ ዑደት ማድረግና) መቅበር ናቸዉ ፡፡ መቀነስ ፡- የሚለዉ ህግ ቆሻሻን ከምንጩ መቀነስ ማለት ነዉ ፡፡ለምሳሌ አንድ ሰዉ በቀን ሊያመነጭ ይችላል ተብሎ የሚታሰበዉን 1 ኪሎ ግራም የደረቅ ቆሻሻ መጠን የሚያመነጭ ቢሆን ይህንኑ ዝቅ እንዲል በማድረግ (ማሳነስ ) ማለት ነዉ ፡፡ መልሶ መጠቀም ፡- ደረቅ ቆሻሻን መልሶ መጠቀም ማለት ቆሻሻዉን ከማስወገድ ወይም በጊዜያዊ ማጠራቀሚያ ዉስጥ ከመጣል ይልቅ ይዘቱን ሳይቀይር ለሌላ አገልግሎት ( ተግባር ) እንዲዉል ማድረግ ማለት ነዉ፡፡ ለምሳሌ አንድ አገልግሎቱን የጨረሰ ጋዜጣ ወደ እንቁላል መያዣ ሳጥን ቢቀየር መልሶ መጠቀም ይባላል፡፡ ወይም አንድ የዉሃ መያዣ ፕላስቲክ ጠርሙስ የነበረ እቃ ለቅመማ - ቅመም ፣ ለቡና ፣ ለጨዉ ለመሳሰሉት መያዣነት እንዲያገለግል ማድረግ ማለት ነው፡፡ መለወጥ (መልሶ ዑደት ማድረግ)፡- ደረቅ ቆሻሻን ከማስወገድ ይልቅ ይዘቱን እና ቅርጹን በመቀየር መጀመሪያ ከተሰራበት አገልግሎት ዉጭ ለሌላ ጥቅም እንዲዉል ማድረግ ማለት ነዉ፡፡ ለምሳሌ ለዉሃ መያዣ ያገለግሉ የነበሩ ፕላስቲኮችን መልሶ ዑደት በማድረግ ከሌሎች ጥሬ እቃዎች ጋር ቀላቅሎ ለምሳሌ ከጥጥ ጋር ሊሆን ይችላል ልብስ ሊሰራበት ቢችል መለወጥ ( መልሶ ዑደት ማድረግ ) ይባላል፡፡ መቅበር ፡- የመጨረሻዉ አማራጭ ሲሆን ምንም አይነት ጥቅም የማይሰጥ ደረቅ ቆሻሻን የማስወገድ ወይም የመቅበር ሂደት ነዉ፡፡ ቆሻሻን ከምንጩ መለየት አሁን ባለንበት ዘመን ከተለያዩ ፋብሪካዎችና ድርጅቶችም ሆነ ከእያንዳንዱ ግለሰብ ቤት የሚወጡ ደረቅ ቆሻሻዎች የተለያየ ተዋፅኦ ያላቸው በተለያዩ የኬሚካልና ሌሎች ውህዶች ተመርተው ጥቅም ላይ የዋሉ እንደየባህሪያቸው ለይተን ልንይዛቸውና ልናስወግዳቸው ግድ የሚሉ የቆሻሻ አይነቶች ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ በርካቶቹም ደረቅ ቆሻሻዎች ተመልሰው ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ከፊሎቹ እንደገና ወደ ፋብሪካ ገብተው ለተለያዩ ምርቶች ጥሬ ዕቃ መሆን የሚችሉና የተፈጥሮ ሀብት ብክነትን የሚቀንሱ ናቸው፡፡ ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok

የከተማችን የፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮች የውሃ መውረጃ እንጅ የቆሻሻ መጣያ አይደሉም::" በዚህ ቪዲዮ ላይ የምትመለከቱት ግለሰብ በአራዳ ክ/ ከተማ ወረዳ 2 ቆሻሻ ተጥሎ የተደፈነን የፍሳሽ መስመር ወይም ቱቦ እያፀዳ ይታያል:: ምክንያቱም የፍሳሽ መስመር መውረጃው አላግባብ በውስጡ በተጣለ ቆሻሻ ተደፍኖ አካባቢው ላይ ከፍተኛ ብክለትና ጉዳት ፈጥሮ ቆይቷል:: በመሆኑም ይህ ብርቱ ዜጋ ለከተማችን ፅዳትና ለብዙሃኑ ደህንነት በመቆርቆርና ይመለከተኛል በሚል እራሱን ሰጥቶ ጉድጓዱን እየጠረገ በማፅዳት ላይ ይታያል:: በአንጻሩ ደግሞ አንዳንዶች በግዴለሽነትና በንዝህላልነት በፍሳሽ መስመር መውረጃ ቱቦዎች ላይ የተለያዩ ቆሻሻና ተረፈ ምርቶችን ከቤታቸው ጭምር አውጥተው በመጣል አካባቢን የሚበክሉና :- የሰውን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥሉ አሉ:: አልፎ ተርፎም የህዝብና የአገር ሃብት የፈሰሰበትን የመሠረተ ልማት የሚያወድሙ ስላሉ እነዚህን መሠል ህገወጦች በጋራ እንከላከል! የከተማችን ፅዳት ሁላችንንም ይመለከተናል!

በአዲስ አበባ ከተማ "ቆሻሻ ሃብት ነው" በሚል ቆሻሻን በአግባቡ በማስተዳደር ባለፉት አምስት አመታት ብቻ 2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ያህል ገቢ ማግኘት ተችሏል:: በመዲናችን ይህን ገቢ ማግኘት የተቻለው በከተማዋ የሚመረተውን ቆሻሻ መልሶ በመጠቀምና ኡደት በማድረግ የተለያዩ መገልገያ ቁሳቁሶችን በማምረትና ኮሞፖስት በማምረት ነው:: በከተማዋ ለበርካታ ዜጎቻችን በዚህ ዘርፉ የስራ እድል መፍጠር የተቻለ ሲሆን አዲስ አበባ ከተማችን ቆሻሻን መልሶ በመጠቀም ዘርፍ ( Recycling) ከበርካታ የአለም አገራት ጋር ተወዳድራም በማሸነፏ ከተማዋ በ2015 አ.ም የአለምአቀፍ ሽልማት አሸናፊ መሆኗም የሚታወስ ነው:::: ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...

ሽልማቱ የጋራ ትጋት ዉጤት ነው። ዛሬ ምሽት መቀመጫውን በእንግሊዝ ያደረገው እና በየዓመቱ በአፍሪካ ምርጥ ብቃት ያሳዩ አፍሪካዊያን መሪዎችን የሚሸልመው የአፍሪካ ሊደርሺፕ መጽሄት የሚያዘጋጀው የአፍሪ
+6
ሽልማቱ የጋራ ትጋት ዉጤት ነው። ዛሬ ምሽት መቀመጫውን በእንግሊዝ ያደረገው እና በየዓመቱ በአፍሪካ ምርጥ ብቃት ያሳዩ አፍሪካዊያን መሪዎችን የሚሸልመው የአፍሪካ ሊደርሺፕ መጽሄት የሚያዘጋጀው የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ መሪ (African leadership magazine person of the year) ሽልማትን አሸናፊ በመሆኔ ክብር እና ደስታ ተሰምቶኛል። ለዚህ ስኬት አብራችሁን ለሰራችሁ እና ለደገፋችሁን ሁሉ ልባዊ ምስጋናዬ ይደስረሳችሁ ! ከሁሉ በላይ ለረዳን ፈጣሪ ክብርና ምስጋና ይሁን። ከንቲባ አዳነች አቤቤ