fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
መዲናችን አዲስ አበባን ሳይታክቱና ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ዘወትር በማፅዳት ከተማችንን ፅዱ ፣ ንፁህና ማራኪ በማድረግ ላይ ያሉ ወደ 12 ሺህ የሚጠጉ የመንገድ ፅዳት ባለሙያዎች ከተማችን አሏት። ከእነዚህ የመንገድ ፅዳት ባለሙያዎቻችን ከ75 በመቶው በላይ ሴቶችና እናቶች ሲሆኑ የከተማችንን ፅዳት ቀን ከሌሊት ፣ከእሁድ እስከ እሁድ ያለ መታከት፣ ብርድ ፣ ዝናብ ፣ ጠራራ ፀሃይና ሌሎችም ተግዳሮቶች ሳይበግራቸው ሙያቸውን በታማኝነትና በቅንነት እየተወጡ ያሉ ናቸው። ይሁን እንጅ የፅዳት ባለሙያዎቻችን በሌሊት ተነስተው ያፀዱትን የከተማዋ መንገዶች አንዳንድ ሰዎች በግዴየለሽነት ቆሻሻ ከቤታቸው አውጥተው የፀዱ መንገዶችና አካባቢዎች ላይ በመጣል ሲያቆሽሹ እንታዘባለን:: ይህ ተገቢ ያልሆነና ሊታረም የሚገባው የፅዳት ባለሙያዎቻችንም ሆነ ለከተማችን ፅዳት በዘላቂነት ለመጠበቅ የሚደክሙትን አካላት ጥረትና ልፋት ሁሉ መና የሚያስቀር በመሆኑ ከእንዲህ አይነቱ ድርጊት መቆጠብ ይገባል::እንዲህ አይነት ያልተገባ ድርጊት የሚፈፅሙ አካላትንም ከጥፋታቸው እንዲታረሙ ማድረግ ከሁላችንም የሚጠበቅ ሃላፊነት ነው! አዲስ አበባን በተባበረ ጥረታችን ፅዱና ማራኪ እናድርጋት! ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲን ጎብኙ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በከተማው የተቋም ግንባታ በዋናነትም የዲጂታላይዜሽን ስራ ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ እንዲሁም ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዮዳሄ ዘሚካኤል በዋና መስርያ ቤት ተገኝተው ጎብኝተዋል። ዋና ዳይሬክተሯ ኤጀንሲው እያደረገ ያለውን የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የዲጂታላይዜሽን ስራ የተመራበትን መንገድ ያደነቁ ሲሆን በሃገራዊ የዲጂታል ሃገር ግንባታ ላይ ተቀራርቦ በመስራት ውጤት ማምጣት እንደሚገባ ገልፀዋል። ወ/ሮ ትዕግስት ከተማው ለሴክተሩ የሰጠው ትኩረት የሚበረታታና ለሌሎች አርዕያ እንደሆነ ያነሱ ሲሆን ተቋማቸው በቴክኖሎጂ ስልጠና፣ በመረጃ ድህንነት ፍተሻ ፣ የቴክኖሎጂ ዘርፍን በማጠናከር በተለይም የሳይበር ደህንነት የስራ ክፍልን በማቋቋም ሂደት እና መስል ጉዳዮች ላይ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። በዕለቱ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እየሰራ ያለውን ስራ ያብራሩ ሲሆን ዋና መስርያ ቤት ላይ የተሰሩ ስራዎች እና ተቋሙ በቀጣይ ግብ አስቀምጦ በትኩረት እየሰራ ያለውን በዋናነትም ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ያሉ እቅዶች ገለፃ ተደርጓል። ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...

በቦሌ ክ/ከተማ የሚገኘው የቦሌ ቡልቡላ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሳይት እየተከናወነ የሚገኘው የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ግንባታ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለፀ:: በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሞላ የቦሌ ቡልቡላ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሳይት በዛሬው እለት ከከተማ አስተዳደሩ እና የአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አመራሮች ጋር በጋራ ጉብኝት አካሂደዋል፡፡ በጉብኝቱም 26 የተለያዩ አቅም ያላቸው ትራንስፎርመሮች ተተክለው በበጀት ዓመቱ አብዛኛዎቹ ትራንስፎርመሮች አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸው የከተማው ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገልጿል፡፡ በዚህም የ36 ብሎኮች ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎቱ ተጠቃሚ ሲሆኑ ለቀሪዎቹ 16 ብሎኮች መደበኛው የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ተገንብቶ ባለመጠናቀቁ ለቤቶች ግንባታ ከተዘረጋ መስመር በጊዜያዊነት አገልግሎቱን እያገኙ መሆኑንም ጠቁሟል፡፡ ከጉብኝቱ በሁዋላ አቶ ተፈራ ሞላ በሰጡት ገለፃ ነዋሪዎችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተከናወነ የሚገኘው የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ግንባታ ስራ በተያዘለት የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ አሉ የተባሉ ተግዳሮቶችን በፍጥነት በመፍታት በተያዘለት የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ በፍጥነት ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል:: ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...

በኤሌክትሪክ #መሰረተ-ልማቶች ላይ የሚፈፀም ስርቆትና ውድመት በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ አሉታዊ ተፅኖ ከማሳደሩም በላይ በቴሌ ኮሙዩኒኬሽንና የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት አውታሮች ጥበቃ አዋጅ ቁጥ
+1
በኤሌክትሪክ #መሰረተ-ልማቶች ላይ የሚፈፀም ስርቆትና ውድመት በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ አሉታዊ ተፅኖ ከማሳደሩም በላይ በቴሌ ኮሙዩኒኬሽንና የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት አውታሮች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 464/97 መሰረት በህግ ያስጠይቃል፡፡ አዋጁን ተላልፎ ድርጊቱን የፈፀመ ማንኛውም አካል ከ5 ዓመት እስከ 20 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት የሚቀጣ ይሆናል፡፡ ስለሆነም ህብረተሰቡ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶችን እንደራሱ ንብረት አድረጎ ሊጠብቅና በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ ጉዳት የሚያደርሱና ስርቆት የሚፈፅሙ ግለሰቦችን ሲመለከት በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት በማሳወቅ ሃገራዊ ሃላፊነትን ሊወጣ ይገባል! ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...

የሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ በኩነት ዘርፍ ከሚሰጡ አገልግሎቶች አንዱ የልደት ምዝገባ እና ማስረጃ የመስጠት አገልግሎት ነው:: ይህ አገልግሎት በወረዳ የሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ ቅ ጽ/ቤት ሲሰጥ መሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ምንድናቸው የሚሉት ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል:: ቅድመ ሁኔታዎች • የህፃኑ ወላጆች በህይወት ካሉ አባት እና እናት ሁለቱም ተገኝተው ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል:: ሁለቱም ወላጆች ልደትን ለማስመዝገብ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ተገኝቶ ልደቱን ማስመዝገብ ያልቻለው ወላጅ አባት ከሆነ ለህፃኑ ወላጅ እናት ልዩ የልደት ውክልና በመስጠት እንዲሁም ተገኝታ ማስመዝገብ ያልቻለችው ወላጅ እናት ከሆነች ለህፃኑ ወላጅ አባት ልዩ የልደት ውክልና በመሰጠት ልደትን ማስመዝገብ ይችላሉ፡፡ • ከወላጆቹ አንዱ በህይወት የሌለ እንደሆነ በህይወት ያለው ወላጅ የሟች ወላጅን ህጋዊ የሞት ማስረጃ ሲያቀርብ ልደቱ ይመዘገባል፡፡ • ዕድሜው 18 ዓመትና በላይ የሆነ ልደት ምዝገባ አገልግሎት ፈላጊ ልደቱን ራሱ ማስመዝገብ አለበት፡፡ • 18 ዓመት ሳይሞላቸው ልጅ የወለዱ ወላጆች የልጃቸውን ልደት ለማስመዝገብ ሲቀርቡ ከሚኖሩበት መደበኛ መኖሪያ ቦታ ካለው ዝቅተኛ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ማንነታቸውን የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ በማቅረብ ልደቱን ማስመዝገብ ይችላሉ፡፡ • ልደት ተመዝጋቢው የውጭ ዜጋ ከሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ የተወለደ መሆን አለበት፡፡ • ዕድሜው 18 ዓመትና በላይ የሆነ ልደት ተመዝጋቢ ወላጆቹን በሚመለከት ቦታ ላይ መረጃውን ካስሞላ በኋላ የወላጅ ፊርማ ቦታ ላይ ሰረዝ (-) ምልክት በማድረግ ይታለፋል፡፡ ደጋፊ ማስረጃዎች • ህፃኑ የተወለደው በጤና ተቋም ከሆነ አስመዝጋቢው ከጤና ተቋም የተሰጠውን የልደት ማሳወቂያ ቅጽ ማቅረብ አለበት፡፡ • የህጻኑ አስተዳዳሪ ወይም ተንከባካቢ ልደቱን ለማስመዝገብ ሲቀርብ ከፍርድ ቤት የተሰጠ የአሳዳሪነት ወይም የተንከባካቢነት ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡ • ተጥሎ የተገኘ ህፃንን ለማስመዝገብ የሚመጣ ፖሊስ ወይም አግባብ ያለው የመንግስት አካል ማንነቱን የሚገልጽ ሕጋዊ መታወቂያ ወይም ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡ • የልደት ተመዝጋቢው የውጭ ዜጋ ከሆነ ከጤና ተቋም የተሰጠ ማስረጃ መቅረብ አለበት፡፡ አገልግሎቱን ለመስጠት የተቀመጠው የጊዜ ስታንደደርድ -ማስረጃው በሙሉ ተሟልቶ የመጣ ከሆነ -በ20 ደቂቃውስጥ አገልግሎቱ ይሰጣል አገልግሎቱ የሚጠይቀው ክፍያ 1.ለወቅታዊ ምዝገባ 60.00 ብር 2. ለዘገየ ምዝገባ 150.00 ብር 3. የጊዜ ገደቡ ያለፈ ምዝገባ 200.00 ብር 4. ለእርማት፣ ለእድሳት፣ ለማመሳከርና ለግልባጭ 100.00 ብር ለምትክ ምስክር ወረቀት 60.00 ብር ብቻ በመክፈፈል አገልግሎቱን ማግኘት ይቻላል:: ለበለጠ መረጃ ወይም ማብራሪያ 7533 በነፃ የስልክ መስመር ይደውሉ:: ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s Tiktok https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...

በአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋትን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ በአደጋ ምላሽ ዘርፍ ባለፉት አምስት አመታት በከተማዋና በአካባቢዉ የደረሱ የእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎችን በመከላከልና በመቆጣጠር 70 ቢሊየን 101 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ከዉድመት ማዳን ተችሏል። በደረሱት አደጋዎች ምክንያት ህይወታቸዉ አደጋ ዉስጥ የነበሩ 165 ሰዎችንም መታደግ ተችሏል። በኮሚሽኑ በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ባለው ሁሉን አቀፍ ሪፎርም ተቋሙን በአስፈላጊው ግብአትና የቴክኖሎጅ አቅም በማጠናከር የቅድመ አደጋ መከላከል ስራዎችን በማጎልበት ከተማዋን ደህንነቷ የተጠበቀችና ለኑሮ ምቹ የማድረግ ተልእኮውን በብቃት እንዲወጣ ስራዎች በልዩ ትኩረት እየተከናወኑ ይገኛል::

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የየካቲት ወር ስራዎች በምስል

በአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነው የረጲ ከደረቅ ቆሻሻ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት (Waste to Energy facility) ፋይዳ ከብዙ በጥቂቱ፡- በከተማችን አዲስ አበባ ኮልፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 የሚገኘው የረጲ የደረቅ ቆሻሻ ኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በአፍሪካ ቀደምት የደረቅ ቆሻሻ የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ነው፡፡ የሃይል ማመንጫው በአዲስ አበባ ከተማ የሚመነጨውን ደረቅ ቆሻሻ በግብዓትነት በመጠቀም ደረቅ ቆሻሻን ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል ምንጭነት ይቀይራል:: የረጲ ከደረቅ ቆሻሻ የኤሌትሪክ ኃይል ጣቢያ ማመንጫ ጣቢያ ከከተማው የተሰበሰበው ደረቅ ቆሻሻ ተጓጉዞ ወደ ቆሻሻ ማቃጠያ ክፍል በመግባት በከፍተኛ ሙቀት ቆሻሻዉ እንዲቃጠል በማድረግ ከከፍተኛው ሙቀት ውኃውን እንዲፈላ በማስቻል የፈላው ውሃ ወደ እንፋሎት ተቀይሮ በተዘጋጀው ቱቦ ወደ ኤልክትሪክ ማመንጫ ክፍል በከፍተኛ ግፊት እንዲወረወር ያደርገዋል፡፡ ደረቅ ቆሻሻው በሚቃጠልበት ወቅት የሚወጡ መርዛማ ጋዞችና እንጥፍጣፊ ፈሳሽ ወደ ማከሚያ ክፍል በማሰባሰብ ታክመው እንዲወጡ ይደረጋል፡፡ ይህም የሚሆነው ከችግር አምጪ ነገሮች ነፃ የሚሆነው ከፍተኛ ቴክኖሎጂ ሲስተም የተገጠመለት ፕላንት በላብራቶሪም ጭምር በመጠቀም ነው፡፡ ከበካይ ነገሮች ነፃ ከሆነ በኃላ ኤሌትሪክ ማመንጫው ክፍል ውስጥ ሁለት ጀነሬተሮች ሲኖሩ ከማቃጠያው ክፍል በከፍተኛ ሙቀት ፈልቶ በግፊቱ ተወርውሮ የሚመጣው የዉኃ እንፋሎት ተርባይኖችን እንዲያንቀሳቅስ በማድረግ ኤሌትሪክ እንዲያመንጭ ያደርገዋል፡፡ ኤሌክትሪኩ ከመነጨ በኃላ በተለያዩ ኤሌትሪክ መሳሪያዎች አማካኝነት በማጓጓዝ ወደ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ እንደቀላቀል በማድረግ ለአዲስ አበባ ነዋሪ ተመልሶ የኤሌትሪክ ኃይል አገልግሎት እንዲሰጥ ያደርገዋል፡፡ በመጨረሻም ማስወገጃ ክፍል ቆሻሻው ከተቃጠለ በኋላ የሚወጣው ብናኝና ዝቃጭ አመድ (bottom and fly ash) እና ለኃይል ማመንጫው የዋለው ዉኃ የሚወጣበት ክፍል ይደርሳል፡፡ በተለይም Bottom ash የሚባለው አመድ እምብዛም ጉዳት የማያመጣና ለመልሶ መጠቀም ከፍተኛ ጥቅም ያለው ተረፈ ምርት በመሆኑ ለብሎኬት ማምረቻነት አልፎ አልፎም እንደ ማዳበሪያም ያገለግላል::አመዱን በመጠቀም ትንሽ ፈጠራን በመጨመር ወደ ወለል ንጣፍ ቴራዞ እንደ ጥሬ እቃ የሚያገለግል ስለሆነ ለስራ እድል ፈጠራም ጠቀሜታ አለው፡፡ የረጲ ደረቅ ቆሻሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፋሲሊቲ ( Waste to energy facility) በከተማችን የቴክኖሎጂ፣ የዕውቀት፣ የልምድና የክህሎት ሽግግር ከማምጣት ባሻገር የአካባቢ ብክለትን በመቀነስና በተለይ የከተማችንን ፅዳት ረገድ የማይናቅ ድርሻ አለው:: የረጲ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ በአሁኑ ወቅት ከከተማዋ ከሚመረተው ቆሻሻ በቀን እስከ 1000 ቶን ያህል ቆሻሻን በመቀበልና በማቃጠል ለኤሌክትሪክ ሃይል ምንጭነት እያዋለ ይገኛል:: ፈጣን እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን አድራሻዎች ይከተሉ፤ ቤተሰብ ይሁኑ! Facebook:- 👇👇👇👇 https://www.facebook.com/CITYMANAGER1 Telgram:- 👇👇👇👇 https://t.me/aacitymanager Twitter:- 👇👇👇👇 https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r YouTube:- 👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዛሬ በአድዋ ድል መታሰቢያ በተካሄደ ደማቅ ስነስርዓት ለአምስት ተቋማት ‘የኢትዮጵያ ተቋማት ስኬት ሽልማትን’ አበርክተዋል። በሽልማቱ የከበሩት ተቋማት የግብርና
+8
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዛሬ በአድዋ ድል መታሰቢያ በተካሄደ ደማቅ ስነስርዓት ለአምስት ተቋማት ‘የኢትዮጵያ ተቋማት ስኬት ሽልማትን’ አበርክተዋል። በሽልማቱ የከበሩት ተቋማት የግብርና ሚኒስቴር/በስንዴ ልማት ፕሮግራም/፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት፣ ኢትዮ ቴሌኮም እና ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ናቸው። ተቋማቱ የኢትዮጵያ የእድገት እና የፈጠራ ልክ ማሳያ የሆኑ ምልክቶች ናቸው።

የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በየካ ክፍለ ከተማ የጎርፍ ተጋላጭ ቦታዎች ቅኝት ሪፓርት ለክፍለ ከተማው አስተዳደር አቀረበ ኮሚሽኑ በየካ ክፍለ ከተማ የጎርፍ ተጋላጭ ና
+5
የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በየካ ክፍለ ከተማ የጎርፍ ተጋላጭ ቦታዎች ቅኝት ሪፓርት ለክፍለ ከተማው አስተዳደር አቀረበ ኮሚሽኑ በየካ ክፍለ ከተማ የጎርፍ ተጋላጭ ናቸው ያላቸውን ቦታዎች ለይቶ ለየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አቅርቧል። በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በየካ ክፍለ ከተማ የጎርፍ ተጋላጭ ናቸው ብሎ የለያቸውን ቦታዎች ሪፓርት ያቀረበ ሲሆን በሪፓርቱ በወረዳ አስር በጎርፍ አደጋ የሼድ ሰፈር ፣መገርሳ እርሻ፣ሳላይሽ ወንዝ ፣ ዳንሳ ጨለለንቆ ወረዳ 11 ራማ መስጊድ ፣ ወረዳ 6 አናጢ ሰፈር በጎርፍ አደጋ እንዲሁም ወረዳ 9 መናሃሪያ አከባቢ ጀሊሳ ወንዝ በከፍተኛ ደረጃ ለአደጋ ተጋላጭ በሚል መለየታቸውን ተገልጿል። ውይይቱን የመሩት የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሀኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በየካ ክፍለ ከተማ የጎርፍ ተጋላጭ ናቸው ያላቸው ቦታዎች አስተዳደሩ እንደሚያምንባቸው ገልፀው በቀጣይ በከተማ የተለዩትን ክፍለ ከተማው በራሱ ስጋት ናቸው ብሎ ከለያቸው ጋር በማጣመር መረጃውን በማጥራት ደረጃ በደረጃ ለመፍታት እንደሚሰራ ገልፀው የነዋሪዎቻችንን ደህንነት ለመጠበቅ ቅድሚያ ሰጥተን እንሰራለን ብለዋል። የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መላኪ አለማየሁ በበኩላቸው ኮሚሽኑ ችግሮች ከመድረሳቸው በፊት የመለየት ስራ እንደሚሰራ አንስተው ኮሚሽኑ ለየካ ክፍለ ከተማ ስጋት ናቸው ብሎ ያቀረባቸው ቦታዎች ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል ብለው እንደሚያምኑ እና ክፍለ ከተማው በራሱ የለያቸውን በጋራ በመሆን እንደሚያዩ ገልፀው ክረምት ከመግባቱ እና ችግሮች ከመፈጠራቸው በፊት ሁሉም አካል ርብርብ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።