1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
ህዳር ሲፀዳ" በሚል መሪ ቃል የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ
በልደታ ክፍለ ከተማ በተካሄደው በዚሁ የጽዳት ንቅናቄ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳዲቅ ሽኩር የፅዳቱ ዓላማ ህዳር ሲታጠን የሚለውን ልማዳዊ ድርጊት ወደ ህዳር ሲፀዳ በመቀየር ማህበረሰቡ አካባቢውን ፅዱ ውብና ለኑሮ ተስማሚ እንዲያደርግ ለማስቻል ነው ብለዋል።
በልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ እጅግአየሁ አድማሱ እንደተናገሩት ህዳር ሲታጠን በሚል በማህበረሰቡ ዘንድ የነበረው ልማዳዊ አስተሳሰብ ተቀይሮ ቆሻሻን በማፅዳት በፅዳት ሞዴል የሆነች ክፍለ ከተማን መፍጠር አለብን ብለዋል።
የክ/ ከተማው ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ተረፈ እንደገለፁት ለማህበረሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር ፅዳትን ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ እየተፈጠረ ነው ብለው በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ገልፀዋል።
በዘመቻው የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተገኙ ሲሆን ለተከታታይ ቀናት እንደሚቆይም ተገልጿል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን እና በአዲስ አበባ ከተማ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለሥልጣን መካከል ይፋዊ የስራ ርክክብ ተካሄደ
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን አዲስ ከተቋቋመው አዲስ አበባ ከተማ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለሥልጣን ጋር ይፋዊ የስራ ርክክብ ስነ ስርዓት አከናወነ፡፡
በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፤ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የከተማዋን የመንገድ ዳር መብራት ተደራሽ ለማድረግ ባለፉት ዓመታት በርካታ ስራዎች ሲከናወን መቆየቱን ገልፀዋል፡፡
የመንገድ ዳር መብራት አገልግሎትን ማሻሻል የአንድ ከተማ የስልጣኔ መገለጫ መሆኑን የጠቆሙት ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የከተማዋ ነዋሪዎች በቀንም ሆነ በማታ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ምቹ እና ከአደጋ የፀዳ ለማድረግ በአዲስ የተደራጀው ተቋም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተቃኘ የመንገድ ዳር መብራት ከመዝርጋት ጀምሮ ነባር የመንገድ መብራቶችን ደረጃ የማሻሻል ሰፊ ስራ እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል፡፡
ኢንጂነር ወንድሙ አክለውም በከተማዋ የሚገነቡ የመንገድ ዳር መብራቶችን ከጉዳት መጠበቅና መንከባከብ የሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የጋራ ኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰብስብ ሁሴን በበኩላቸው፤ አዲስ አበባ ከተማን ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የከተማዋን የመንገድ ዳር መብራት በተደራጀ መልኩ ለመገንባትና ለማስተዳደር ተቋሙ በአዋጅ ቁጥር 166/2016 ሊቋቋም መቻሉን ገልፀው፤ተቋሙ የተሰጠውን ስልጣንና ኃላፊነት በትጋት ለመወጣት መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሙህዲን ረሻድ በበኩላቸው፤ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ቀደም ሲል ባለፈባቸው አደረጃጀቶች ውስጥ ሆኖ የመንገድ ዳር መብራት ዝርጋታና ጥገና በማከናወን የመንገድ ዳር መብራት ተደራሽነትን ለማሳደግ ሰፊ ስራ ሲያከናውን መቆየቱን አስታውሰዋል።
ኢንጅነር ሙህዲን አያይዘውም፤ ከተማዋ ከሚያስፈልጋት የመንገድ መሠረተ-ልማት ማስፋፋትና ማዘመን ፍላጎት አንፃር፤ የከተማዋን የመንገድ መብራት ራሱን አስችሎ ማስተዳደር በማስፈለጉ የአዲስ አበባ ከተማ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለሥልጣን ሊመሰረት መቻሉን ገልፀው፤ በቀጣይም ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ለተቋሙ ተልዕኮ ስኬት የሚያደረገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በማረጋገጥ መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆን ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም በሁለቱ ተቋማት መካከል የተሸከርካሪዎች፣ የሰንድ ርክክብ እና የፊርማ ሥነ - ሥርዓት ተካሂዷል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ካዛንቺስ አካባቢ ካሉ ባለሀብቶች ጋር አካባቢውን በትብብር መልሶ ማልማት በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል::
በውይይቱ ወቅት ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ የመኖሪያ አካባቢ ለማድረግ በተጀመረው የኮሪደር ልማት ስራ እንደ መጀመሪያው ሁሉ የሁለተኛውንም የኮሪደር ልማት ስራ ህብረተሰቡን እና ባለሀብቱን በማሳተፍ በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል::
በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የካዛንቺስ አካባቢ ባለሀብቶች በበኩላቸው በኮሪደር ልማት እና በመልሶ ማልማት ስራው እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን የከተማው ጽዳትና ውበት ለኢኮኖሚ መነቃቃት ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ በመሆኑ በሚችሉት ሁሉ ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመቆም አካባቢውን እንደሚያለሙ ቃል በመግባት እንዲሁም ያላቸውን የልማት ጥያቄዎች በማቅረብ ለመልሶ ማልማት ስራው በቀረበላቸው ጥሪ ደስተኛ መሆናቸውንም ገልጸዋል::
የቻይና ጂያንግዙ ግዛት አስተዳዳሪ ከሆኑት ሹ ኩሊን በአድዋ መታሰቢያ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ተቀብለናል።
የትብብር አድማስ ማስፋት የሚያስችል እና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ስራዎች እና በጂያንግዙ ኩባኒያ በከተማችን በመገንባት ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት እና በጥራት ማጠናቀቅ በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ተነጋግረናል::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባን የኢትዮጵያ የብልጽግና ተምሳሌት በማድረግ ሂደት የአካባቢ ጽዳት የከተማችን አንዱ መገለጫ ባህል ሆኖ በዘላቂነት እንዲቀጥል የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ
"ህዳር ሲፀዳ" በሚል መሪ ሃሳብ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ከተማ አቀፍ የፅዳት ንቅናቄ በዛሬው እለት ይፋ ተደርጓል።
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ እና የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ የዘንድሮውን "የህዳር ሲጸዳ" የፅዳት ንቅናቄ የማእከል፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ ስራ አስኪያጅ እና የጽዳት ጽ/ ቤት አመራሮች እና የባለድርሻ አካላት በተገኙበት በይፋ አስጀምረዋል ።
የከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት እና የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ በጋራ ባካሄዱት የ"ህዳር ሲፀዳ" የከተማ አቀፍ የጽዳት ንቅናቄ የማስጀመሪያ መድረክ ላይ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ የአካባቢ ጽዳት የከተማችን መለያና ቋሚ የህብረተሰብ ባህል ሆኖ እንዲዘልቅ እና በዘርፋ የተመዘገቡ ዉጤቶችም ቀጣይነታቸው እንዲረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚያደርጉትን ጥረት ማጎልበት እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል።
አክለዉም አዲስ አበባን ደረጃዋን የጠበቀች፣ ለኑሮና ለስራ ተመራጭ እንዲሁም ተወዳዳሪ የማድረግ እቅዳችን እንዲሳካ ሁሉም ባለድርሻ አካላት፣ የመላው የከተማችን ነዋሪዎች በጽዳቱ ዘርፍ እያደረጉ ያለውን ተሳትፎ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል::
የአዲስ አበባ ከተማ የብልጽግና ፅ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ በበኩላቸው አዲስ አበባ ከተማን ጽዱና ዉብ የማድረግ ጉዳይ የአመራሩ፣ የፓርቲው አባላትና የህዝባችን ቀዳሚና ዋነኛ አጀንዳ መሆን አለበት ሲሉ ገልፀው በዚህ ረገድ ሁላችንም የምንናገረውን በተግባር የምንተረጉም ግንባር ቀደም ዜጎች መሆን ይኖርብናል ሲሉ ተናግረዋል ።
አያይዘውም የዘንድሮው የ"ህዳር ሲፀዳ" የጽዳት ንቅናቄ የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ አመት የምስረታ በአል አከባበር አንዱ አካል መሆኑን ጠቅሰው ተከታታይነት ባለው መልኩ መላ ህዝባችንን እያሳተፈ የሚካሄደው የጽዳት ስራችን በቀጣይ ጊዜያትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስገንዝበዋል።
በህዳር ሲጸዳ" የጽዳት ንቅናቄ በከተማችን ተማሪዎች፣ ሴቶች፣ወጣቶች እና የተለያዩ አደረጃጀቶችን ጨምሮ መላው የብልጽግና ፓርቲ አባላት አመራሮችና የከተማው ነዋሪዎች በየብሎኩ፣ ትምህርት ቤቶች፣ ተቋማትና በሁሉም የከተማዋ አካባቢዎች የሚካሄድ ይሆናል።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዳጉ በቀጥታ ስርጭት ፕሮግራሙ በኮሪደር ልማት ዙሪያ ከከፍተኛ አመራሮች ጋር ቆይታ አድርጓል። በዚሁ ፕሮግራም ላይ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ያነሷቸው አንኳር ነጥቦች እንደሚከተለው ቀርቧል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በመጸዳጃ ቤት ዉስጥ ተጥላ ህይወቷን ማትረፍ የተቻለችዉ ህጻን በከተማ አስተዳደሩ ስራ ኃላፊዎች ተጎበኘች ።
ህዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሶስት ጣፎ መጠለያ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በወላጅ እናቷ በመጸዳጃ ቤት ዉስጥ ተጥላ በአደጋ ጊዜ ባለሞያዎች ህይወቷ የተረፈችዉ ህጻን ዛሬ ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም በከተማ አስተዳደሩ ስራ ኃላፊዎች ተጎብኝታለች።
የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶችና ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወይንሸት ዘሪሁን በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት
በአበበች ጎበና እናቶችና ህጻናት ሆስፒታል ለህጻኗ እየተደረገ ስላለዉ እንክብካቤ እንደዚሁም የህጻኗን ህይወት ለታደጉት የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ የአመሰገኑ ሲሆን ቢሮአቸዉ ህጻኗን የሚከታተል ባለሞያ በመመደብ ክትትል እንደሚያደርግ በመጥቀስ አስተዳደጓን በተመለከተም ሙሉ ኃላፊነት ወስዶ እንደሚያመቻችም አስታዉቀዋል ።
በአበበች ጎበና የእናቶችና ህጻናት ሆስፒታል ሀኪሞች በቡኩላቸዉ እንደተናገሩት አሁን ላይ ለህጻኗ አስፈላጊዉ እንክብካቤ እየተደረገላት መሆኑን ጠቅሰዉ ህጻኑ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደምትገኝም አብራርተዋል።
በጉብኝት መርሀ ግብሩ ላይ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛዉና ም/ኮሚሽነር መስፍን አያሌዉ ተገኝተዋል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
