1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
ዛሬ በስምንት የኮሪደር አቅጣጫዎች እና 2879 ሄክታር በሚሸፍን ስፋት ላይ እየተሰራ ያለውን የሁለተኛውን ምዕራፍ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ሥራ ሪፖርት ገምግመናል።
ከተማዎቻችንን ለእድገት እና ለኑሮ ይበልጥ ምቹ ለማድረግ ከመጀመሪያው ምዕራፍ ልምዶችን በመቀመር ትርጉም ያለው ርምጃ ለመራመድ ተችሏል።
አሁን በሶስት መሠረታዊ ኃላፊነቶች ላይ ማተኮር ይገባናል። በመጀመሪያ ለቀጣዩ ትውልድ ፍላጎት የተስማሙ ከተሞችን መገንባት፤ ሁለተኛ በመለወጥ ላይ ባሉት ከተሞች ከፍ ብሎ ማደግ የሚችል ትውልድ መቅረጽ፤ ሶስተኛም እነዚህን የዘመኑ ከተሞች በልህቀት ለመምራት የተዘጋጀ አመራር ኮትኩቶ ማብቃት ናቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸማችንን ድክመት እና ጥንካሬዎቻችንን ከነመንስዔዎቻቸው በመለየት ገምግመናል።
የስራ ባህላችን ወጪ ቆጣቢ ፣ጥራትና ባጠረ ጊዜ ውስጥ የሰራናቸው ስራዎች ከተማችንን ለነዋሪው ምቹ ከማድረግ አኳያ ትልቅ ትርጉም ያላቸው ሲሆን አዲስ አበባ የቱሪስት መዳረሻ፣ ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል ለማድረግ እና የሀገራችንን ገፅታ ለመገንባት የሰራናቸው የኮሪደር ልማትና ከተማዋን መልሶ የማደስ ስራዎቻችን ዉጤታማ ሆነዉ ከተማችን በሩብ አመቱ ብቻ 20 የተለያዩ አህጉርና አለምአቀፍ ኮንፍረንሶችን በብቃት ማስተናገድ ችላለች።
በዚህ ሩብ ዓመት በየተቋማቱ አቅደን ከፈፀምነዉ አንፃር 86 እጅ ዉጤታማ አፈፃፀም የታየበት ሲሆን ከህዝብ ጋር ተቀራርበን የሰራንበት፣ የአመራር ቅንጅት፣ የስራ ባህላችን መለወጥ እና ከተማችንን የሚመጥን የስማርት ከተማ ግንባታ ስራዎቻችን ስኬት ያገኘንባቸው ናቸው::
በኮሪደር ልማት ምክንያት ለኑሮ ከማይመች ጎስቋላ አካባቢ ያነሳናቸው ነዋሪዎቻችንን ለኑሮ ምቹ የሆነ ንጹህ የመኖሪያ ቤት እና አካባቢ እንዲያገኙ ማድረግ የቻልን ሲሆን ከተማ ብቻ ሳይሆን የሰው ህይወት አብሮ የታደሰበት አፈፃፀም መሆኑንም ገምግመናል::
ፈተናዎችን እየተሻገርን ባሳካናቸው ስኬቶች ሳንረካ የአገልግሎት አሰጣጣችንን ከህዝባችን ፍላጎትና ካስቀምጥነው ስታዳርድ አኳያ፣ ሌብነትና ብልሹ አሰራር ያልተሻገርናቸው መሆናቸውን
አምነን ለመከላከል የዘረጋነዉ አሰራር እንዲሁም ነዋሪው የሰጠንን ጥቆማና አስተያየትን መሰረት በማድረግ የሰራናቸው ስራዎች ፍሬ ማፍራት የጀመሩ ሲሆን አሁንም አፅእኖት ሰጥተን ችግሩን በሚመጥን ደረጃ በዘላቂነት ለማረም የሚያስችል የአመራር ቁመና ለመፍጠር፣ ግልፅነትን እየጨመርን እና ነዋሪውን እያሳተፍን መስራት የሚያስችል አቅጣጫም አስቀምጠናል::
በተጨማሪም በተቋም ግንባታ፣ የሰው ተኮር ስራዎችን ማጠናከር፣ የስራ እድል ፈጠራ፣ የኑሮ ውድነትን በመቀነስ፣ ገቢ አሰባሰብ ማሻሻል፣ የንግድ ስርአቱን ማጠናከር፣ ለነዋሪዎቿ የተመቸች ከተማ መገንባት እንዲሁም የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት በመጨረስ ወደ አገልግሎት ማስገባት እና የ2ተኛ ዙር ኮሪደር ስራን በጥራት እና በፍጥነት ማጠናቀቅ በቀጣይ በልዩ በትኩረት የምንሰራቸው ስራዎች ናቸው::
አገልግሎት አሰጣጣችንን ይበልጥ ቀልጣፋና ከሌብነትና ብልሹ አሰራር የጸዳ በማድረግ በትጋትና በታማኝነት በማሳተፍ መስራታችንን አሁንም አጠናክረን እንቀጥላለን::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ዛሬው 4ተኛ አመት 3ተኛ መደበኛ የካቢኔ ስብሰባች ሁለተኛ ኮሪደር ስራ ያለበትን በጥልቀት ገምግሟል ።
በግምገማው በዋናነት ትኩረት ያደረግነው የልማት ተነሺዎች የተስተናገዱበትን አግባብ፤ በመንግስት የሚኖሩ የነበሩ የተነሱበት አግባብ፤ መሰረተ ልማት የተሟሉላቸው መሆኑን፤ በተመሳሳይ ሁኔታ የግል ተነሺዎች ደግሞ የካሳ የ3 አመት የቤት ኪራይ እና ምትክ መሬት መውሰዳቸውን ፤የትራንስፖርት አቅርቦት እና የሞራል ካሳ በህጉ መሰረት የተከፈለ መሆኑን የተተነተነ ሪፖርት በየኮሪደሩ አስተባባሪዎች ቀርቦ ተገምግሟል።
በግምገማውም ሁሉም ህጋዊ ውል ወይም ሰነድ ኑሯቸው እንዲሁም በመጠለያ በተገኙበት ተጠልለው የሚኖሩ ነዋሪዎችን ሁሉ የቤት መስተንግዶ እና የቤት መሰረተ ልማቶች በተሟላላቸው እጅግ የተሻለ ፣ ንፁህ ፣ መሠረታዊ መገልገያዎች የተሟሉላቸው ቤቶች የተስተናገድ ሲሆን፤ ለመኖር ምቹ አካባቢ ያገኙ ስለመሆኑ እና አንዳንድ ሳይቶች ላይ የመንገድ ደረጃውን ለማሻሻል ግንባታ እየተካሄደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦ ካቢኔው በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ውሳኔ አስተላልፏል።
ሌሎች ሳይት ላይ አስፈልጊው መሰረተ ልማት ተጠናቆ ነዋሪዎች የየእለት ኑሯቸውን እንዲቀጥሉ ተደርጓል ፤የማህበራዊ ኑሯቸው ሳይበታተን እድር ፤ ማህበር እና አብሮነታቸው የመሰረቱት ማህበራዊ መስተጋብር እንደተጠበቀ መስተናገዳቸው ን አቃቂ ፤ገላን ጉራ ፤ፉሪ ሃና ፤አራብሳ አምስት እና ስድስት አያት ሶስት፤ ላፍቶ ሃይሌ ጋርመንት እና ለሚኩራ አጠገብ የተሰሩት ሎኮስት ፤አየርጤና ቂርቆስ ለገሃር አካባቢ ፤አራዳ ሰባ ደረጃ አካባቢ በማሃል ከተማ የተገነቡ ቤቶች ላይም የተስተናገዳቸውን እና አፈፃፀሙም ጥሩ መሆኑን ካቢኔው ገምግሟል።
የመሠረተ ልማት ቅንጅት አካላት ከከተማ እስከ ፌደራል ተቋማት የነበራቸው ተሳትፎ በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ካቢኔው በጥንካሬ ገምግሟል ።
በተጨማሪም መሬት እና ካሳ ምትክ እስካሁን ድረስ ብቻ ከ4.6ቢሊየን በላይ መከፈሉን የሁለት አመት የቤት ኪራይ መከፈሉን እና ቀሪ ተነሺዎችም ቅድመ ዝግጅት ሂደት ካቢኔው በጥንካሬ ገምግሟል ። በሌላ በኩል የኰሙኒኬሽን ሥራዎችን በደንብ ደጋግሞ ለሕዝብ መረጃን ማድረስ ላይ ከዚህ በላይ ማድረስ እና ተደጋጋሚ የሚዲያ ሽፋን ያላቸው የመረጃ ስርጭት ለህብረተሰቡ መድረስ እንዳለበት ካቢኔው አሳስቧል። መረጃን የሚያዛቡ እና ሀገር እንዳትለማ ውዝንብር በሚፈጥሩ የተለያዩ ዝንባሌዎች የሚያሳዩ የመረጃ ምንጮችን እና አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ በመወሰድ እንዳለበት በአፅንኦት ኣንስተዋል ::
በ2ኛው ዙር ኮሪደር ልማት ስራ 2879 ሄክታር ስፋት ፤ 135ኪሎ ሜትር የኮሪደር ርዝመት ያለው ሲሆን ፤ 240ኪሎ ሜ የአስፋልት መንገድ፣ 237 የእግረኛ መንገድ ፣ 32 የህፃናት መጫዎች ቦታዎች ፣ 79 የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች ፣ 114የታክሲ እና አውቶቡስ መጫኛ እና ማውረጃ ፣ 58 የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ ቦታዎች፣ 368 ሄክታር አረንጋዴ ልማት ሽፋን ያላቸው ቦታዎች፣ የ 111 ኪ.ሜ ሳይክል መንገድ ፣ 17 የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች፣ 106 የህዝብ መረዳጃ ቤቶች፣ 121 ኪ.ሜ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ፣ 182 ኪ.ሜ ድሬኔጅ መውረጃ መስመር ፣ 50 የተሸርካሪና እግረኛ መተላለፊያ ፣ 75 ኪ .ሜ ሪቴይኒንግ (የድጋፍ ግንብ) ስራዎችን የሚያካትት ነው ::
ይህንኑ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ክትትል ማሳደግ፤ ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ የተተገበሩ የ አንደኛ ዙር ኮርድር ልማት ልምዶች ተቀምረው ለ2ተኛው ዙር በተሻለ ብቃት መስራት እንደሚያስፈልግ ፤ ቅንጅታዊ አሰራርም በተጠናከረ መልኩት አሳድጎ በጥንካሬ አሁን ካለው በላይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ካቢኔው አሳስቧል።
ኮምፖስት ለማምረት በሚደረገው ሂደት ላይ በሚስተዋሉ ተግዳሮቶችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ከከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ እንዲሁም ቴክኖ ሰርቭ ኢትዮጵያ ከተባለ መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር በኮምፖስት ማምረት ዘርፍ የተደራጁ ማህበራት በስራቸው ላይ በሚያጋጥሙ ዋና ዋና ችግሮች እና መፍትሄዎቻቻው ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በካፒታል ሆቴል ውይይት አካሂዷል::
የውይይቱ ዓላማም በኮምፖስት ዝግጅትና የገበያ ትስስር ዙሪያ ለሚታዩ ተግዳሮቶች ዙሪያ የጋራ መፍትሄ ለማስቀመጥ እንደሆነ ተመላክቷል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ለማ ከዛሬ ሶስት ዓመታት በፊት ከደረቅ ቆሻሻ ኮምፖስ የማምረት ግንዛቤ አነዳልነበር ገልፀው አሁን ላይ ግን በዘርፉ ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል የተፈጠረበት ዘርፍ ሆኗል ብለዋል።
አክለውም ዋና ዳይሬክተሩ በመዲናዋ ከሚመነጨው ሊበሰብስ የሚችል ደረቅ ቆሻሻ መጠን አንፃር በዘርፉ የተሰማሩ ማህበራት ገቢያቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ የመጣ ቢሆንም ከቆሻሻ የሚጠበቀውን ገቢ ግን እየተገኝ እንዳልሆነ ገልፀዋል።
በርካታ የውጭ ሀገር ዜጎች ጨምር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ተሞክሮ ለመቅሰም እየመጡ እንደሆነ አክለው ገልፀዋል።
የኤጀንሲው ም/ዳይሬክተር አቶ ሙላት ተገኝ በበኩላቸው በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 90 ሺህ 175 ቶን ደረቅ ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል በዘርፉ የተሰማሩ አካላት ከ1.4 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማገኝት መቻላቸውን ተናግረዋል።
የኮምፖስት ፍላጎት አለ እያልን በተቃራኒው ደግሞ የገበያ ትስስር ችግር አለ ማለታችን ትክክል አለመሆኑን አብራርተዋል። ይህን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የቅንጅት ስራዎቻችን ላይ ትኩረት ሰጥተን መስራት አለብን ብለዋል።
የውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ዋና አማካሪ አቶ ነጋሽ አረጋ በበኩላቸው ከአረንጓዴ ልማቱ ጋር ተያይዞ ሰፊ የኮምፖስት ፍላጎት እንዳለና በዘርፉ ላይ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ቅንጅታዊ አሰራር ተጠናክሮ መሠራት እንዳለበት አብራርተዋል።
የመወያያ መነሻ የሚሆን ሰነዶችን የኤጀንሲው የመልሶ መጠቀምና ኡደት ማዕከላት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ወ/ሮ ባዩሽ ታደሰ የቀረበ ሲሆን በኮምፖስት ማምረት ሂደት ላይ የሚስተዋሉ ጥንካሬዎችንንና ተግዳሮቶችን በዝርዝር አቅርበዋል።
ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራር ስርዓቱ ቢኖርም ክፍተቶች መኖራቸው : የገበያ ትስስር በቂ አለመሆን : የሚመረተው የኮምፖስት ጥራት : ኮምፖስት የሚመረትበት ምቹ የስራ ቦታና ሼድ : በዘርፉ ለተደራጁ ማህበራት የሚደረገው ድጋፍና ክትትል አናሳ መሆን: ኮምፖስትን ለማምረት የሚፈጀው የጊዜ ርዝመት : ህብረተሰቡ ለዘርፉ ያለው ግንዛቤ አናሳ መሆን እና የመሳሰሉት ኮምፖስትን ለማምረት በሚደረገው ጥረት እንደ ተግዳሮት ተነስቷል::
ከደረቅ ቆሻሻ ኮምፖስት በማምረት ሂደት ላይ የሚስተዋሉትን ተግዳሮቶች እና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከተሳታፊዎቹ ተነስተው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።
በውይይቱ ላይም የኤጀንሲው አመራሮችን ጨምሮ የክ/ከተማ ፅዳት አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊዎች፣ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ፣ በኮምፖስት ማምረት እና በውበትና አረንጓዴ ልማት ዘርፍ የተደራጁ ማህበራት ተወካዮች ፣ የመልሶ መጠቀምና ዑደት ማድረግ ቡድን መሪዎች እና ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል።
ህዳር 2 ቀን 2017 አ.ም
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
በአዲስ አበባ ከተማ የብዙሃን የአካል እንቅስቃሴዎች የነዋሪዎችን አንድነት እና መስተጋብር የሚያጠናክሩ በመሆናቸው ነዋሪው ተሳትፎውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀረበ።
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ "የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለሁለንተናዊ ብልፅግና" በሚል መሪ ሐሳብ የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ አመት የምስረታ በዓልን አስመልክቶ በልደታ ክ/ ከተማ በተካሄደው የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት የኮሪደር ልማቱ ለከተማው ነዋሪዎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች አመቺ ሁኔታዎችን የፈጠረ መሆኑን ገልፀዋል ።
አክለውም በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት የለውጥ አመታት በሺዎች የሚቆጠሩ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ተገንብተው በአካል ብቃት የዳበረ፣ ጤናማና ምርታማ ማህበረሰብ እንዲፈጠር ውጤታማ ተግባራት እየተከናወኑ መቆየቱን ተናግረው በዚህም ከዚህ በፊት ከነበረው በተሻለ የእግር ጉዞ፣ ስኬቲንግ እና ለብስክሌት እንቅስቃሴ አመቺ ሁኔታዎች መፈጠሩን አመልክተዋል። አያይዘውም በዚህም በአሁኑ ወቅት በርካቶች ስፖርትን እያዘወተሩ እንደሚገኙም አስገንዝበዋል።
የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በበኩላቸው እንደተናገሩት ባለፍት 5 የለውጥ ዓመታት ስፖርት በማህበረሰቡ ዘንድ ባህል እንዲሆንና ማህበረሰቡ ጤናውን እንዲጠብቅ የሚያስችሉ ስራዎች ተከናውነዋል ብለው በዚህም ሁሉም የልማት ስራዎች ስፖርትን አካተው እንዲሰሩ ተደርጓል ሲሉ ገልፀዋል።
ባለፍት የለውጥ ዓመታት መንግስት ሰው ተኮር መርህን በመከተል ኢንቨስት ካደረገባቸው አንዱ የስፖርት ዘርፍ ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ለአብነትም በክፍለ ከተማችን በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ የተሰሩ ደረጃቸውን የጠበቁ ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ማየት ይቻላል ሲሉ ተናግረዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለሁለንተናዊ ብልፅግና " በሚል መሪ ሐሳብ ከተማ አቀፍ የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራም እየተካሄደ ይገኛል።
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በልደታ ክ/ ከተማ በሜክሲኮ ወደ ሳር ቤት በሚወስደው መንገድ እየተካሄደ ባለው የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በመሳተፍ ላይ ናቸው።
የጽዳት የመንገድ ጥርጊያ ፅዳት ሰራተኞች ለከተማ ብሎም ለክ/ከተማዉ መንገድ ፅዳትና ዉበት የላቀ ሚና እንዳላቸዉ ተገለፀ ።
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት በክፍለ ከተማው ለሚገኙ የመንገድ ጥርጊያ ጽዳት ሰራተኞች ፤ለጽ/ቤት መዋቅር ሀላፊዎችና ባለሙያዎች በጽዳት ህብረት ሽርክና ማህበራት የአሰራር መመሪያ ቁጥር 6/2012 ዙሪያ የገንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
የክ/ከተማው ዋና ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማናዬ ጫኔ በመድረኩ ተገኝተው ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር በክ/ከተማው የሚገኙ የመንገድ ጥርጊያ የጽዳት ሰራተኞች ፀሃይና ብርድ ሳይበግራቸው የክ/ከተማውን መንገዶች ፅዳትና ውበት ለመጠበቅ የሚያደርጉት ጥረት የሚበረታታ መሆኑን ተናግረው በቀጣይም የአሰራር መመሪያን መሰረት በማድረግ የበለጠ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል።
የክ/ከተማው የፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በየነ ቱሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጽዳት ህብረት ሽርክና ማህበራት የአሰራር መመሪያ ቁጥር 6/2012 በሰፊ ገለፃና ማብራሪያ በዝርዝር አቅርበዋል ።
ሁሉም በስራ ዘርፉ የተሰማሩ ሰራተኞችና አመራሮች የአሰራር መመሪያው ተረድቶ በተቀመጠው ስታንዳራድ መሠረት አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ግንዛቤ ለማስጨበጥ አላማ ያደረገ ስልጠና እንደሆነም ኃላፊው አክለው ተናግረዋል።
በመድረኩ የመንገድ ጥርጊያ ደረጃዎች በመመሪያው ለፅዳት ስራ የተቀመጡ የሰው ኃይል ስታንዳርድ እንዲሁም በክ/ከተማው ደረጃ በዘርፉ ያሉ ጠንካራ ጎኖችና ሊቀረፉ የሚገባቸው ተግዳሮቶችን በዝርዝር አቅርቧል ።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ለስራ ወሳኝና አቅም የሚገነባ በመሆኑ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ጠቁመው ለስራ አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶች ከማሟላት እና ለስራውና በስራ ዘርፉ ለተሰማሩ ሰራተኞች ጥቅማጥቅምና ምቹ የስራ ሁኔታ ከመፍጠር ጋር የተያያዙ በቀጣይ ልዩ ትኩረት የሚሹ ያልተቀረፉ በርካታ ችግሮች መኖራቸውም ተናግረዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በየነ ቱሉ እና የጽ/ቤቱ የዘርፉ ቡድን መሪ ወ/ሮ ዘይነባ ዮሱፍ በመድረኩ ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ለስራ አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን እና የሰራተኞች ጥቅማጥቅም ከማሟላት እና ለስራው የበለጠ ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር ጋር የተያያዙ ችግሮችን በእኛ አቅም መፈታት የሚችሉትን እንፈታለን፤ ከጽ/ቤቱ አቅም በላይ የሆኑት ደግሞ ከኤጀንሲውና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር ለመፍታት ጥረት እንደሚደረግ ተናግረዋል።
የዘርፉ ሰራተኞች መብታችሁን እንዲከበር ከምታደርጉት ጥረት ጎን ለጎን ግዴታችሁን በአግባቡ በመወጣት መንገዶች ፣የመንገድ ጦርዞች፣ ዳርቻዎች፣የመንገድ አካፋዮችና ድልድይዎችን በመመሪያው በተቀመጠላቸው የፅዳት ስታንዳርድ መሰረት በሰዓቱ በማፅዳት የክ/ከተማው ብሎም የከተማችን መንገዶች ለነዋሪዎች፣ለዲፕሎማቶችና ለእንግዶች ፅዱ ፣ውብና ምቹ ለማድረግ በትጋት መስራት ይጠበቅባችኋል ሲሉ ሀላፊው አሳስበዋል ።
በመጨረሻም ሁሉም የተቋሙ ሰራተኞች የፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ በወቅቱ እንዲያወጡ መልእክት ተላልፏል ።
Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
የስራ አስኪያጅ ልዩ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ የፓርቲዉን 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በዛሬው እለት አክብሯል።
የልዩ ወረዳው አመራሮችና አባላት የብልፅግና ፓርቲ 5ተኛ አመት የምስረታ በአልን "የሃሳብ ልዕልና ለሁለተናዊ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል በዛሬው እለት በልዩ ድምቀት አክብረዋል፡፡ በልዩ ወረዳው ከትናንትው እለት ጥቅምት 28 ጀምሮ ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የአባላት ስልጠናም በዛሬው እለት ተጠናቋል።
የምስረታ በአሉን አስመልክተው በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ ባስተላለፉት መልእክት መዲናችን አዲስ አበባን በፓርቲያችን ብልጽግና እሳቤ የኢትዮጵያና የአፍሪካ ብልፅግናና ተምሳሌት የማድረግ ተልእኳችን በፓርቲው አመራሮችና አባላት ግንባር ቀደም ጥረት ስኬታማ እየሆነ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል።
አክለዉም ባለፉት አምስት አመታት አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብና አበባ ለማድረግ የተቀረጹና ተግባራዊ የሆኑ በርካታ ፕሮጀክቶች እና የተካሄዱ የተቋማት ሪፎርሞች የመላ አመራሩና የፓርቲው መዋቅር ያለ እረፍት ሌት ተቀን በትጋት ባከናወናቸው ስራዎች የተመዘገቡ ውጤቶች ናቸው ብለዋል።
ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ አያይዘውም በማዘጋጃ ቤታዊ የአገልግሎት አሰጣጥ ረገድ ከብልሹ አሰራር የጸዳ፣ ተጠያቂነት ያለበትና ግልጽነት የሰፈነበት የአሰራር ስርአትን በማጠናከር፣ በተሟላ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግልት የህብረተሰቡን እርካታ በማረጋገጥ ረገድ የፓርቲው አመራሮችና አባላት በስነምግባር እና በስራ ትጋት የአገልጋይ መሪነትና የግንባር ቀደም ምሳሌነትን በመላበስ ሚናን መወጣት እንደሚገባ ከአደራ ጭምር አሳስበዋል።
በአባላት ስልጠና መድረክ ሰልጣኞች በየቡድኑ ባካሄዱት ውይይት በፓርቲው እሳቤዎች እና መርሆዎች ግንዛቤ ላይ ያተኮረ የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሂዶ የውጤት ብልጫ ላመጡ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በመድረኩ የስራ አስኪያጅ ልዩ ወረዳ ሰብሳቢና አመራሮች እንዲሁም የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ተቋማት አመራሮች እና መላው አባላት ተሳታፊ ሆነዋል።
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ እነዚህን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከተሉ። ቤተሰብ ይሁኑ!
Facebook:-
👇👇👇👇
https://www.facebook.com/CITYMANAGER1
Telgram:-
👇👇👇👇
https://t.me/aacitymanager
Twitter:-
👇👇👇👇
https://twitter.com/VxllwvOeB0tBe5r
YouTube:-
👇👇👇👇https://www.youtube.com/watch?v=h9xb_POJdxo&t=106s
Tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@addisababacitymanager...
Website
👇👇👇👇
https://www.aacitymanger.gov.et
