1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የመጋቢት 2017 ዜና መጽሔት፦ https://bit.ly/4jbBJD9
PMO April 2025 Newsletter:- http://bit.ly/4jcxhny
የሰላም ሰራዊቱ የክፍለ ከተማውን ሰላም ከመጠበቅ ባሻገር በእሳትና አደጋ ስጋት ቅነሳ ሒደት ላይ የላቀ ሚናውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የካ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ከየካ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ፅህፈት ቤት ጋር በመተባበር በአደጋ ስጋት ቅነሳ ዙሪያ ከ12ቱም ወረዳ ለተወጣጡ የሰላም ሰራዊት አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል።
የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩን ያስጀመሩት የየካ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምርክነህ ያዕቆብ እንደገለፁት ስልጠናው የሰላም ሰራዊቱ የአካባቢውን ሰላምና ጸጥታ ከማስጠበቅ ባለፈ በየአካባቢው የሚደርሱ ድንገተኛ አደጋዎች ምንነት በበቂ ሁኔታ በመጨበጥና በመገንዘብ መከላከሉ ላይ የላቀ ሚናቸውን እንዲወጡ ለማስቻል መዘጋጀቱን ገልፀዋል።
የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ደበሌ በበኩላቸው የሰላም ዘብ የሆነው የሰላም ሰራዊት ሰላምን ከማስጠበቅ በዘለለ የአደጋ ስጋቶችን የመቀነስ ተልእኮውን ከክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ጋር በቅርበት በመስራት ከአደጋ የፀዳች ሰላማዊ ከተማን በመገንባት ረገድ ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ኒቆዲሞስ ቡቼ በበኩላቸው ኮሚሽኑ በአራት ዋና ዋና ተግባሮች ላይ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ አንስተው የከተማዋን የአደጋ ስጋት መቀነስ በመንግስት ብቻ የሚከናወን ሳይሆን የሁሉንም የነቃ ተሳትፎ የሚጠይቅ መሆኑን ገልፀው የሰላም ሰራዊት አባላት ግንዛቤውን በመጨበጥ በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን የአደጋ ስጋት የመቀነስ ተልዕኮአቸውን በአግባቡ በመወጣት ከስጋት ነፃ የሆነች ከተማን በመፍጠር ሒደት ላይ የድርሻየውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
ስልጠናውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደጋ ስጋት ዳይረክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደሲሳ ጦና የሰጡ ሲሆን ስልጠናውን ተከትሎ ከተሳታፊዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል።
Yeka Communication-የካ ኮሙኒኬሽን
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/aacitymanager
"በተቻለ መጠን የዚህ አመራር ዋነኛ ዓላማ መሆን ያለበት የተሸፈኑ ነገሮችን ገለጥ ገለጥ አድርጌ ይቺን ሀገር እንደ ስሟ ትልቅ አድርጌ ኢትዮጵያውያን እንዳይለምኑ፣ እንዳይሰደዱ ማድረግ እችላለሁ። መሬት አለን፣ ውኃ አለን፤ ሰብሰብ አድርገን ብንሠራ ቢያንስ “ስንዴ ብርቅ አይሆንብንም” ብሎ የቆረጠ፤ የወሰነ፤ ሊመራ የተዘጋጀ ኃይል እንዲሆን ነው የሚፈለገው። ይሄን ማሳካት ከቻላችሁ አዲሱ ትውልድ ደግሞ ላቅ ያለ ራእይ ስለሚሰንቅ በዚያው ጉዞ ውስጥ ይገባ እና ይበልጥ ያማረ ከምናስበውም በብዙ የላቀ ነገር ሊፈጠር ይችላል። ጫናዎች፣ መከራዎች፣ ግፊቶች ብታምኑም ባታምኑም፣ የኢትዮጵያ ብልጽግና የተዘጋውን መስኮት የሚከፍቱ እንጂ የሚያዳፍኑ ሊሆኑ አይችሉም፡፡"
