fa
Feedback
Addis Ababa City Manager Office

Addis Ababa City Manager Office

رفتن به کانال در Telegram
1 474
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-37 روز
-2130 روز
آرشیو پست ها
vpnsetup_dd6dhin3cqpiv6q8jgr7g45u.exe152.55 MB

vpnsetup_dc7tcl7195p966q8j38a1paa.exe152.55 MB

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን 1446ኛ ኢድ አል ፈጥር በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም የደስታና የፍቅር እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡ ኢድ ሙባረክ! See less

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1446ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ! በዓሉ የሰላም፣ የመተሳሰብ ፣የመረዳዳት፣የአንድነት እና የፍቅር እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ። ኢድ ሙባረክ! ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ

የሸዋል ጨረቃ ዛሬ ምሽት በመታየቷ 1446ኛው ኢድ አል ፈጥር በዓል ነገ እሑድ መጋቢት 21/2017 ዓ.ም ይከበራል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ ቤት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን 1446ኛ ኢድ አል ፈጥር በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም የደስታና የፍቅር እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡ ኢድ ሙባረክ!

መላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1446ኛ የኢድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ኢድ ሙባረክ!! የኢድ አል-ፈጥር በዓል የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና በረመዳን የጾም ወር የነበረ የመተሳሰብ፣ የመረዳዳት እና የአንድነት የሚጠናከርበት በአል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ። በድጋሚ ኢድ ሙባረክ! ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!! ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዒድ አል-ፈጥር በዓልን አስመልክቶ ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት እንኳን ለ1446ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል አደረሳችሁ፡፡ “ዒድ አል ፈጥር” የረመዳን ጾምን የማጠናቀቂያ በዓል ነው፡፡ ዒድ አል ፈጥር “የምስጋና፣ የበጎ አድራጎት እና የወንድማማችነት/እኅትማማችነት” በዓል ነው፡፡ ዒድ አል ፈጥር ከአንድ ወር የጾም ጊዜ በኋላ የሚመጣ በዓል ነው፡፡ ጾሙ የሰውን ድካም፣ ዐቅም ማነስ እና ልክ የሚያሳይ ነው፡፡ ፈጣሪ ካልደገፈው በቀር የሰው ልጅ ዐቅም ውሱን መሆኑን ያሳያል፡፡ ትዕቢት፣ ጥጋብ እና ክፋት በዚህ ደካማ ሰው ላይ መብቀላቸውን ለተመለከተ፣ የሰው ጠላቱ የገዛ ጠባዩ መሆኑን ይማራል፡፡ ሰው በዘመናት ውስጥ ሌሎችን ለመግዛት የታገለውን ያህል ራሱን ለመግዛት አልታገለም፡፡ ዛሬም በሀገራችን የምናየው ፈተና በዋናነት ራስን ካለመግዛት የሚመጣ ፈተና ነው፡፡ ራሱን የማይገዛ ሰው ዐቅሙን አያውቀውም፡፡ ወደ ውስጡ አያይም፡፡ ጠላቱን ከገዛ ጠባዩ ውስጥ ከመፈለግ ይልቅ፣ ጠላቱን ከጎረቤቱ ይፈልገዋል፡፡ በዚህ የተነሣ ከገዛ ወገኑ ጋር ሲቃረን ይኖራል፡፡ እንደ ረመዳን ዓይነት ወቅቶች ውስጥን ለመመልከት የሚጠቅሙ ናቸው፡፡ ውስጣቸውን የተመለከቱ ሰዎች ምስጋና ገንዘባቸው ነው፡፡ ሰው የራሱን ልክ ካላወቀ ሌላውን አያደንቅም፤ ሌላውን አያመሰግንም፡፡ የሌለውን ካልተረዳ ያለውን አያውቅም፤ አያደንቅም፡፡ የራሱ ጠላት የገዛ ጠባዩ መሆኑ ካልገባው፣ ሌላውን ወገኑን አያፈቅርም፡፡ ለዚህ ነው የጾሙ መጨረሻ፣ ዒድ አል ፈጥር የምስጋና በዓል የሆነው፡፡ ጾሙ ከቤተሰብ ጀምሮ እስከ ማኅበረሰብ ድረስ ራስን ገዝቶ ለመሰባሰብ ይጠቅማል፡፡ መሰባሰቡም ከስሜት የወጣ፣ ስክነትና ራስን መግዛት ያለበት ነው፡፡ ሀገራዊ ምክክራችን ይሄን ዕሴት ቢላበስ እንጠቀማለን፡፡ መነጋገሩ ብቻ አይጠቅምም፡፡ ከስሜት ወርዶ፤ በስክነት ተሞርዶ፤ ነገን ተመልክቶ - መመካከር፡፡ ያ ከሆነ እንደ ዒድ ሁሉ፣ የምክክራችን ፍጻሜው ምስጋና ይሆናል፡፡ የዒድ ሌላው ዕሴት በጎ አድራጎት ነው፡፡ ዐቅም ለሌላቸው፤ ሁኔታው ላልተሟላላቸው ወገኖች መልካምን ነገር ማድረግ፡፡ ዝምድናን፣ ዘርን ወይም እምነትን ሳይመለከቱ ሰውን በሰውነቱ ብቻ መርዳት፡፡ የጾም ምንዳዕ ሙሉ የሚሆነው በጎ አድራጎት ከተጨመረበት ነው፡፡ በጎ አድራጎት ማለት ከራስ አጉድሎ ሌላውን መሙላት ነው፡፡ እንደ ሀገር ለመቀጠልና እንደ ሕዝብ ለመተሣሠር በጎ አድራጎት እጅግ አስፈላጊ ዕሴት ነው፡፡ ራስን በሌላው ጫማ ላይ አስገብቶ ማየት፡፡ የሌላው ጉድለት ለመሙላት ሲባል የራስን ማጣት፡፡ ለምን ወገኔ ያዝናል? ለምን ወገኔ ይከፋል? ብሎ መንገብገብ፡፡ ሁላችንም የየራሳችንን ወገን ጥቅምና መብት በማስከበር ብቻ ሀገር ልንገነባ አንችልም፡፡ ትሥሥራችን ወገን ዘለል ሆኖ፣ የሌላውን ወገን ጉዳትና ፈተና መጋራት ይገባናል እንጂ፡፡ የእኔ ቤት ሲሟላ አይደለም የእርሱ ቤት የሚሟላው፡፡ የእርሱ ቤት ሲሟላ ነው የእኔ ቤት የሚሟላው፡፡ የፖለቲካ ምኅዳራችን በዚህ ነባር ዕሴታችን ላይ ካልተመሠረተ ፍትሐዊነትን እና እኩልነትን ለማስፈን እንቸገራለን፡፡ እነዚህን ሁለቱን ዕሴቶች የሚያስተሣሥረው የዒድ ዕሴት “ወንድማማችነት/እኅትማማችነት” ነው፡፡ ወንድማማችነት/ እኅትማማችነት ማለት በጋራ ዕሴቶች፣ በመተባበር እና በጋራ ግብ ላይ የተመሠረተ ወዳጅነት ነው፡፡ ይሄ ወዳጅነት በሥነ ምግባር የተገራ፣ ፍቅርንና አንዱ ለሌላው መቆምን መሠረት ያደርጋል፡፡ የጋራ ኃላፊነትን ይወስዳል፡፡ በሀገራችን የፖለቲካ ሕይወት እጅግ አስፈላጊው/ግን እጅግ የተረሳው ዕሴት ነው፡፡ መብትንም ሆነ ግዴታን በወንድማማችነት/እኅትማማችነት መነጽር መመልከት ነገሩን ለሰውነት ቅርብ ያደርገዋል፡፡ ለእኔ ከሚለው አውጥቶ ለእኛ፤ ለእኛ ከሚለውም ጭምር አውጥቶ “ለእነርሱ እና ለእኛ”፤ ለእነርሱ እና ለእኛ ከሚለውም አውጦቶ “ለእኛ ይቅርብን፤ ለእነርሱ ይደረግ “ወደሚለው የላቀ ሰብእና ያደርሰዋል፡፡ በእምነቶች፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በማኅበረሰቦች እና በልሂቃን መካከል የተሻለውን አብሮነት የሚፈጠረው ወንድማማችነት/እኅትማማችነት ነው፡፡ የተሻለ መረዳዳት፣ የተሻለ መተዋወቅ እና የተሻለ መግባባት ይፈጥራል፡፡ ለሌላው ሲል መተዉን፤ ለሌላው ሲል መቀበልን እና ለሌላው ሲል ለበደሎች ዕውቅና መስጠትን የሚያስገኘው ዕሴት - ወንድማማችነት/እኅትማማችነት ነው፡፡ የዒድ በዓል አንዱ ዕሴት የሆነውም በዚህ የተነሣ ነው፡፡ የዒድን በዓል እነዚህን የበዓሉ ዕሴቶች እያሰብን፣ እያዳበርንና ለሀገር ግንባታ እየተጠቀም እንድናከበረው ጥሪ አቀርባለሁ፡፡ ቤተሰቦች፣ ጎረቤታሞች፣ ማኅበረሰቦች እና የእምነት አባቶች ሲሰባሰቡ እነዚህ ሦስት የዒድ ዕሴቶች ጎልተው እንዲወጡና ማኅበረሰባችን እንዲገነባባቸው እንዲያደርጉ አደራ እላለሁ፡፡ ኢድ ሙባረክ! ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር! ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ! መጋቢት 20፣ 2017 ዓ.ም

vpnsetup_dc7tcl7195p966q8j38a1paa.exe152.55 MB

ታህሳስ 2012 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምን ብለው ነበር? ሶስተኛ ዓመት ታህሳስ 2012 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምን ብለው ነበር? “አዲስ አበባን እውነተኛ አዲስ አበባ እናደርጋታለን! እንደ ስሟ እውነተኛ አዲስ አበባ ትሆናለች፤ ካልን በኋላ የአፍሪካ መዲና መሆኗን ለማረጋገጥ ሰፋፊ ሥራዎች እየተሠሩ ነው። ዛፍ መትከል፣ ማጽዳት፣ ፓርኮች ማስፋት ይህን ሥራ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ወደሚቀጥለው ‘ሌየር’ ካሳደግነው፣ ሙሉ በሙሉ አንድነት ፓርክ ግቢውን ከያዘ፤ ይሄንን ሥራውን ጨርሶ ለሕዝብ ክፍት ከሆነ፣ ቦሌ መንገድ ላይ የጀመርነው ሥራ ካሣለጥን እና እስክ እንጦጦ ከወጣን፤ ካለ ምንም ጥርጥር በየትኛውም የአፍሪካ ሀገር በዚህ ደረጃ የቱሪስት መስሕብ መሆን የሚችል፤ ታሪክ ያለው፣ ዛፍ ያለው፣ እጅግ የሚያምር የአየር ንብረት ያለው እና መልካ ምድሩ የተለየ ውበት ያለው ቦታ ያለ አይመስለኝም። ካለም ለኔ አንደኛው ቦታ ይሄ ነው።" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ #PMOEthiopia See less

"ትላንት ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና! "መጋቢት የቀጣዩ አረበኝነት ጅማሮ ማብሰሪያ ነው"! በሚል የመጋቢት 24 ቀንን እና የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ጮርሶ ቀጠና በኢማ አህመድ መስጊድ ቅጥር ግቢና አካባቢው በዛሬዉ ዕለት በአንድ ማዕከል የፅዳት ዘመቻ ተካሄዷል። በፅዳት ዘመቻዉ የክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ወይንሸት አስናቀ ፤የክፍለ ከተማውእና የወረዳ አመራሮች፣ የመንገድ ጥርጊያ ባለሙያዎች ፣የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች ፣ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች ፣የደንብ ኦፊሰሮች፣የእምነት አባቶች ፣ የሽርክና ማህበራት እንዲሁም ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል። በቦታው የተገኙት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ ወይንሸት_አስናቀ የመጋቢት 24 ቀንንና የኢድ በዓልን ምክንያት በማድረግ የፅዳት ዘመቻው በድምቀት ተካሂዷል ሁላችንም የጽዳት ባህላችንን በማዳበር እንዲሁም ቆሻሻ ሀብት በመሆኑ በንቃት በመሳተፍ አከባቢያችን ጽዱና ውብ በማድረግ ጤናማ ህብረተሰብ፤ ምቹ አካባቢ በመፍጠር የአብሮነትና የመተሳሰብ ባህላችንን ለማጎልበት ሁሉም የበኩሉን መወጣት አለበት ብለዋል፡፡ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ_ወንድማገኝ_ታደሰ በበኩላቸው የዛሬው ጽዳት ውብና ጽዱ አካባቢ ከመፍጠር ባሻገር የሀይማኖት መቻቻልና የአብሮነት እሴት ማሳያ ነው ብለዋል። Lemi Kura Communication ለሚ ኩራ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ትናንት፣ ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና! በሚል መሪቃል የተደረገ የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር በኮልፌ ቀራኒዮ ፎቶ በከፊል...

ትናንት፣ ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና! በሚል መሪቃል የተደረገ የፅዳት ንቅናቄ መርሀግብር በቂርቆስ ፎቶ በከፊል... ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

የብልፅግና ፓርቲ የ7 ዓመት የስኬት ጉዞ ከመጋቢት እስከ መጋቢት በሁሉም ዘርፎች የመጡ ለውጦችንና ፍሬዎችን ለመዘከር ያለመ የፅዳት ንቅናቄ ተካሄደ። የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር "ትናንት፣ ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና" በሚል መሪ ቃል የብልፅግና ፓርቲ የ7 ዓመት የስኬት ጉዞና ከመጋቢት እስከ መጋቢት በሁሉም ዘርፎች የመጡ ለውጦችንና ፍሬዎችን ለመዘከር ያለመ በርካታ የህብረተሰብ ክፍል የተሳተፈበት የፅዳት ዘመቻ በወረዳ 05 ልዩ ቦታው ማሰልጠኛ አካባቢ አካሂዷል። በፅዳት ዘመቻው የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ለገሠና የቅ/ጽ/ቤቱ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ፋኪያ ሸሪፍ፣ የክ/ከተማው ዋና ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማናዬ ጫኔ ፣ የወረዳው ነዋሪዎች ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ የፀጥታ አካላት ፣ የመንገድ ጥርጊያ ባለሞያዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል። የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ለገሠ የብልፅግና ፓርቲ ባለፉት 7 አመታት የሚገጥሙትን ችግሮች በድል እየተሻገረ በማንሳት የለውጡ መንግስት ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ አንስቶ ከተማዋን ውብ ዕዱና ለነዋሪዎቿ ተስማሚ ለማድረግ በሰራው ስራ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን በመጥቀስ ክፍለ ከተማው ከዚህ ቀደም ለኑሮ የማይመችና አስፈላጊ መሰረተ ልማቶች ያልተሟሉለትም የነበረ መሆኑንና የለውጡ መንግስት በሰራው ስራ በርካታ የልማት ስራዎች በመሰራታቸው ክ/ከተማውን የስህበት ማዕከል ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል ። ኃላፊው አያይዘውም ባለፉት 7 ዓመታት ነጠላ ትርክትን በመተው ገዢ ትርክትን ለማስፈን የተሰሩ ስራዎች ፍሬ እያፈሩ እንደሚገኝና በሀገሪቱም በተሰሩ ስራዎች ሀገሪቱ በአለም አቀፍ ደረጃ ከተሳታፊነት ወደ ተፅዕኖ ፈጣሪነት እየመጣች እንደሚገኝ በማንሳት ሁሉም ዜጋ ሀገሪቱ ወደ ብልፅግና ለመድረስ እያደረገች በምታደርገዉ ጉዞ የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ተናግረዋል ። የወረዳ 05 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መለሰ ሙሴ በበኩላቸው የለውጡ መንግስት ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ካከናወናቸው በርካታ የልማት ስራዎች መካከል ከተማዋን ውብና ፅድ ለማድረግ የተሰሩ ስራዎች ውጤት ማስመዝገብ መቻላቸውንና በዚህም ቆሻሻ ወደ ሀብት መቀየር መቻሉን በማንሳት ሁሉም ባለድርሻ አካል አካባቢውን ሊያፀዳ እንደሚገባ ተናግረዋል ። መጋቢት 20/ 2017 Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

"ትናንት፣ ዛሬንና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና!" በሚል መሪ-ቃል የጽዳት ንቅናቄ መርሀግብር በሁሉም ክ/ከተሞች ተካሄደ፡፡ መጋቢት 20/2017ዓ.ም ******************** የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ከህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ጋር በመተባበር የለውጡ መንግስታችን 7ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ "ትናንት፣ ዛሬንና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና!" በሚል መሪ-ቃል በሁሉም ክ/ከተሞች እስከ ብሎክ የዘለቀ የጽዳት ንቅናቄ መርሀግብር ያካሄደ ሲሆን እንደ ማዕከል በተመረጠው በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ግብፅ ኤምባሲ አካባቢ ከማለዳው 12፡30 ጀምሮ በድምቀት በድምቀት አካሂዷል፡፡ በዚሁ ንቅናቄ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፈለት በም/ከንቲባ ማዕረግ የከተማችን ዋና ስራ አስኪያጅ ክቡር ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ መጋቢት ወር አገሪቱ ከውድቀት አፋፍ የተረፈችበትና ለአፍሪካም የነፃነትን ቀንዲል ያበራችበት ወር መሆኑን ገልፀዋል። ዋና ስራ አስኪያጁ አክለውም አዲስ አበባ ቆሻሻ ሆና የአፍሪካ መዲናነቷን ማስቀጠል እንደማትችል የተገነዘቡት ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ "እኔ ግቢዪን አፀዳለሁ በማለት ከቤተ መንግስታቸው በጀመሩት የጽዳት ስራ በከተማችን ብሎም በአገራችን ለውጥ ማምጣት መቻሉን አብራርተዋል። ከተማችንን ቆሻሻን በመሰብሰብ ከ75 በመቶ ወደ 96 በመቶ ማድረስ ተችሏል፤ በመልሶ መጠቀም ስራችን ከተማዎ ከ2 በመቶ ወደ 12 በመቶ ማድረስ መቻሉን ጠቅሰው የከተማችን ኮሊደር ልማት ለከተማዋ ልማትና ለጽዳትዋ መረጋገጥ ትልቅ ዕድል የፈጠረ አጋጣሚ ነው። የወንዝ ዳርቻ ልማታችንም ለከተማዋ ውበትና ጽዳት የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው ብለዋል። ዋና ስራ አስኪያጁ አክለውም ይህንን የከተማችንን ጽዳት ቀጣይነት ለማረጋገጥና ከቆሻሻ የምናገኘውን ሐብት ለመጨመር ሁሉም ነዋሪ ቆሻሻን ከምንጩ እንዲለይ መልዕክት አስተላልፈዋል። ዶ/ር እሸቱ ለማ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው የመጋቢት ወር ትልቅ ታሪክ የተሰራበትና እንደ አገርም ሆነ እንደ ከተማ ትልቅ ለውጥ የመጣበት ወር ነው። ትናንት፣ ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና! በሚል መሪ ቃል ያደረግነው የጽዳት ንቅናቄ ከነዚህ የለውጥ ትሩፋቶች አንዱ መሆኑን የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሩ ባለፉት 7 ዓመታት የከተማችን ጽዳት በዓለም አቀፍ መድረክ ዕውቅና ያገኘበት፣ የማጓጓዝ አቅማችን የጨመረበት የመልሶ መጠቀም ስራችን ከፍተኛ ለውጥ ያሳየበት ነው ብለዋል። አቶ ይከበር ስማቸው የጉለሌ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ መጋቢት ወር የህዳሴ ግድባችንን በራሳችን አቅም መገንባት የጀመርንበት ወር ከመሆኑ ባሻገር የዛሬ ሰባት ዓመት ለአገሪቱ ብሩህ ተስፋ የፈነጠቀው የብልፅግና ፓርቲ ጅማሮ የተረጋገጠበት መሆኑን አብራርተዋል። በንቅናቄው ላይም በም/ከንቲባ ማዕረግ የከተማችን ዋና ስራ አስኪያጅ ክቡር ኢንጂነር ወንድሙ ሴታን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሰት የስራ ኃላፊዎች ፣ የጸጥታ አካላት፣ የጽዳት አምባሳደሮች፣ የደንብ ማስከበር አካላት ፣ የተለያዩ አደረጃጀቶች፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣች እና ነዋሪው ህብረተሰብ በተገኙበት ተካሂዷል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/aacitymanager

ባለፉት የለውጥ ዓመታት በአዲስ አበባ በሁሉም ዘርፎች የተከናወኑ ስራዎች የከተማዋን ደረጃ ከፍ ያደረጉና የነዋሪዎችን ጥያቄ የመለሱ ናቸዉ - በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ

ባለፉት የለውጥ ዓመታት በአዲስ አበባ በሁሉም ዘርፎች የተከናወኑ ስራዎች የከተማዋን ደረጃ ከፍ ያደረጉና የነዋሪዎችን ጥያቄ የመለሱ ናቸዉ - በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ